Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 76—ለቤተ ክርስቲያን አባልነት መዘጋጀት

    እጅግ ሚዛናዊ የሆነ ሥልጠና— እግዚአብሔር እንዳዘዘውም መመሪያ መሰጠት አለበት፡፡ ልጆች በትዕግስት፣ በጥንቃቄ፣ በትጋት፣ በምህረት መሰልጠን አለባቸው፡፡ ለልጆቻቸው አካላዊ፣ አዕምሮአዊ እና መንፈሳዊ መመሪያ የመስጠት ኃላፊነት በወላጆች ላይ ያርፋል፡፡ የእግዚአብሔርን መጠይቆች ዘወትር በልጆች ፊት ማቅረብ አስፈላጊ ነው፡፡CGAmh 471.1

    የአካል ብቃት ስልጠና፣ የአካል መጎልበት፣ ከመንፈሳዊ ስልጠና በላይ በጣም በቀላሉ መሰጠት ይችላል…፡፡ CGAmh 471.2

    ለአስተሳሰብ ንጽህና እና ክብርን እና ለቃል እና ለተግባር መልካም መዓዛን የሚሰጠው የነፍስ ሁኔታ የላቀ ልባዊ ጥረት ይጠይቃል፡፡ እያንዳንዱን ክፉ ዓለማ ከልብ ማሳ ማረም ትዕግስትን ይጠይቃል፡፡ CGAmh 471.3

    መንፈሳዊ ሥልጠና በየትኛውም አይነት ሁኔታ ችላ መባል የለበትም፡፡ በዚህ ሳቢያ የእርሱን እውቀት ያገኙ ዘንድ የእግዚአብሔርን ውብ ቃል ትምህርት ልጆቻችንን እናስተምራቸው፡፡ ቀና ያልሆነውን ምንም ነገር እንዳያደርጉ ይረዱ፡፡ ፍትህን እና ፍርድን እንዲያደርጉ አስተምሯቸው፡፡ የተሳሳተ መንገድ እንዲይዙ እንደማትፈቅዱላቸው ንገሯቸው፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በእግዚአብሔር የጸጋ ዙፋን ፊት አቅርቧቸው፡፡ ኢየሱስ ሕያው የሆነው ስለ እነርሱ ለማማለድ እንደሆነ ይወቁ፡፡ በመለኮት አምሳል አንጻር ባህሪያቸውን ይቀርጹ ዘንድ አደፋፍሯቸው፡፡ 993Testimonies For The Church, September 15, 1904..CGAmh 471.4

    የእግዚአብሔር እና የክርስቶስ ዕውቀት መሰረታዊ ነው— መንፈሳዊ ሥልጠና በማንኛውም አይነት ሁኔታ ችላ መባል የለበትም፣ ምክንያቱም “የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፡፡” መዝ. 111፡10፡፡ አንዳንዶች ትምህርት ከኃይማኖት በኋላ የሚመጣ ያደርጋሉ፣ ሆኖም ግን እውነተኛ ትምህርት ኃይማኖት ነው፡፡ 994Counsels to Parents, Teachers, and Students, 108.CGAmh 471.5

    ተግባራዊ የኃይማኖት ልምድን መግለጽ—በኃይመኖት ውስጥ ያለውን ተግባራዊ ልምድ የክርስቲያን ወላጆች ለልጆቻቸው ለመስጠት ዝግጁ መሆን ያለባቸው ነገር መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ከእናንተ ይፈልጋል፣ በመሆኑም ይህንን ስራ ማከናወን ካልቻላችሁ ግዴታችሁን መወጣት አልቻላችሁም ማለት ነው። እግዚአብሔር የመረጣቸውን የእርምት ዘዴዎች እና በክርስቲያን ሕይወት ውስጥ የስኬት ሁኔታዎችን በተመለከተ ልጆቻችሁን አስተምሯቸው፡፡ አዕምሮአቸው ለጊዜያዊ ሕይወት ከመጠን በላይ በመጨነቅ እግዚአብሔርን ማገልገል እንደማይችሉ አስምሯቸው፤ ነገር ግን ልፋት እንደማያስፈልጋቸው እና የእረፍት ጊዜያቸውን በሥራ ፈትነት ማሰለፍ እንዳለባቸው እንዲያስቡ አታድርጓቸው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በዚህ ጉዳይ ላይ ግልፅ ነው፡፡ 995Testimonies For The Church 5:42..CGAmh 472.1

    ስለ እግዚአብሔር እውቀት ማስተማር— እግዚአብሔርን ማወቅ የዘላለም ሕይወት ነው፡፡ ልጆቻችሁን ይህን እያስተማራችኋቸው ነው ወይ የዓለምን መስፈርት እንዲያሟሉ እያስተማራችኋቸው ነው? እግዚአብሔር እያዘጋጀላችሁ ስላለው ቤት እየተዘጋጃችሁ ነው? … ስለ አዳኙ ሕይወት፣ ሞት እና ትንሳኤ አስተምሯቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠኑ አስተምሯቸው…፡፡ ለዘላለም መኖር የሚችል ባህሪይ እንዲቀርጹ አስተምሯቸው፡፡ እግዚአብሔር ልጆቻችሁን እንዲጠብቅ እና እንዲባርካቸው ከዚህ በፊት ጸልያችሁ በማታውቁት አይነት ሁኔታ ጸልዩ፡፡4Manuscript Releases 16:1895.CGAmh 472.2

    በየዕለቱ ንስሃ ስለ መግባት እና ስለ ይቅርታ አስተምሯቸው— የእያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ይቅር የሚባልበትን ጊዜ በእርግጠኝነት ለይቶ ማስቀመጥ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ልጆች መማር ያለባቸው ትምህርት ከልጅታቸው ሕይወት ጀምሮ ጉድለቶቻቸው እና ስህተቶቻቸው ወደ ኢየሱስ እንደሚቀርቡ ነው፡፡ እርሱ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ወደ እርሱ ያመጧቸውን ልጆች እንደተቀበለ ሁሉ በየዕለቱ ለፈጸሟቸው በደሎች ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባቸው በጸጸት ልብ የሚቀርብ ቀላል ልመናን ኢየሱስ እንደሚሰማ፣ ይቅር እንደሚላቸው እና እንደሚቀበላቸው አስተምሯቸው፡፡ 996Manuscript Releases 5:1896.CGAmh 472.3

    ጤናማ አስተምህሮ አስተምሯቸው— እውነትን የተመለከቱ፣ አስፈላጊነቱ የተሰማቸው እና በነገረ እግዚአብሔር ልምድ የነበራቸው ሰዎች፣ ልጆቻቸውን ጤናማ አስተምህሮ ማስተማር አለባቸው፡፡ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲቶች ለምን እንደሆንን፣ ከእምነታችን ታላላቅ ምሶሶዎች ጋር ማስተዋወቅ አለባቸው— ማለትም ልክ እንደ እስራኤል ልጆች ለምን እንደተጠራን፣ ልዩ ወገን፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ በምድር ገጽ ላይ ካሉ ሌሎች ሕዝቦች ሁሉ ለምን የተለየን እና የተመረጥን እንደሆን ማወቅ አለባቸው፡፡ እነዚህ ነገሮች ለመረዳት ቀላል በሆነ ቋንቋ ለልጆች መብራራት አለበት፤ እናም በዕድሜ እያደጉ ሲመጡ፣ የእውነት መሰረት ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ሥር እስኪሰድድ ድረስ እየደገ ከመጣው አቅማቸው ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ 997Testimonies For The Church 5:330.CGAmh 473.1

    አጭር እና ተደጋጋሚ መመሪያ ስጧቸው— ለልጆች እና ለወጣቶች መመሪያ የሚሰጡ ሁሉ አሰልቺ የሆኑ አስተያየቶችን ማስወገድ አለባቸው፡፡ አጫጭር፣ ዋና ነጥብ ላይ የተኩሩ ንግግሮች ደስተን የመስጠት ተጽዕኖ ይኖራቸዋል፡፡ ብዙ የሚነገር ነገር ካለ፣ አጠር ያለ እና ድግግሞሽ ያለው አድርጉት፡፡ ተደጋግመው የሚቀርቡ ጥቂት አስደሳች አስተያየቶች፣ ሙሉውን መመሪያ በአንድ ጊዜ ከመስጠት የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ረዥም ንግግሮች የልጆችን አእምሮ ያሰለቻሉ፡፡ ከመጠን በላይ መመገብ ጨጓራን እንደሚያጨናንቅ እና የምግብ ፍላጎትን በመቀነስ ምግብን እንደሚያስጠላ ሁሉ ከመጠን በላይ ማውራትም እንዲሁ መንፈሳዊ መመሪያዎችን ወደ መጥላት ያመራል፡፡ 998Gospel Workers, 208, 209.CGAmh 473.2

    ምሽቶች ውድ ወቅቶች ናቸው— ቤት የአሰልቺ ልፋት ሥፍራ ከመሆን ይልቅ መመሪያ የሚሰጥበት ትምህርት ቤት መደረግ አለበት፡፡ ልጆችን በጽድቅ መንገድ በመምራት ለማዋል ምሽቶች እንደ ውድ ወቅቶች መታየት አለባቸው፡፡ 999Counsels on Sabbath School Work, 48.CGAmh 474.1

    የእግዚአብሔርን ተስፋዎች ደጋግሞ መናገር— መንፈስ ቅዱስ ብርሃን ሰጪያችን እንደሆነ ማወቅ አለብን፡፡ ያ መንፈስ ልጆችን ተደራሽ ማድረግ እና የቃሉን ሐብት እና ውበት ለእነርሱ መግለጥ ይወዳል፡፡ በታላቁ አስተማሪ የተነገሩት ተስፋዎች የስሜት ህዋሳትን ይማርካሉ፣ ደግሞም መለኮታዊ የሆነው መንፈሳዊ ኃይል የልጁን ነፍስ ያነቃቃል። ከጠላት ፈተናዎች መመከት የሚችል ከነገረ መለኮት ጋር መላመድ ተቀባይ በሆነ አእምሮ ውስጥ ያድጋል። 1000Counsels to Parents, Teachers, and Students, 172.CGAmh 474.2

    ኃይማኖታዊ መመሪያን ማራኪ አድርጉ— ኃይማኖታዊ መመሪያ ለልጆች ገና በልጅታቸው ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህ መሰጠት ያለበት በመኮነን መንፈስ ሳይሆን በደስተኝነት መንፈስ መሆን አለበት፡፡ ፈተና እነርሱ ማወቅ በማይችሉት አይነት መንገድ ወደ ልጆቻቸው እንዳይመጣ እናቶች ዘወትር መንቃት አለባቸው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን በጥበበኛ እና በአስደሳች መመሪያ መጠበቅ አለባቸው፡፡ ድል በመንሳት ሥራ ውስጥ እንደ መልካም ጓደኞቻቸው ልምድ የሌላቸውን ልጆች መርዳት አለባቸው፣ ምክንያቱም አሸናፊዎች ይሆኑ ዘንድ ይህ ሁሉ ነገራቸው ነው፡፡ መልካም ለመስራት የሚሹ ውድ ልጆቻቸው የጌታ ቤተሰብ ትናንሽ አባላት እንደሆኑ መቁጠር አለባቸው፣ ደግሞም የንጉሱ ሰፊ የታዛዥነት ጎዳናን የቀና በማድረግ እነርሱን ለመርዳት ጥልቅ ፍላጎት ሊሰማቸው ይገባል፡፡ በፍቅር ዓላማ በየዕለቱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን እና ፈቃድን ለእርሱ በመታዘዝ ማስገዛት ማለት ምን እንደሆነ ማስተማር አለባቸው፡፡ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ለቤተሰብ መታዘዝን እንደሚያካትት አስተምሯቸው፡፡ ይህ የየዕለቱ፣ የየሰዓቱ ተግባር መሆን አለበት፡፡ ወላጆች ሆይ ንቁ፣ ንቁ እና ጸልዩ፣ ልጆቻችሁንም ጓደኞቻችሁ አድርጓቸው፡፡10Testimonies For The Church 6:93, 94.CGAmh 474.3

    ከተለመዱ የቤተሰብ ተግባራት መንፈሳዊ ትምህርቶችን ማስተማር— እግዚአብሔር ልጆችን እና ወጣቶችን በእነዚህ መንገዶች የማስተማር ሥራን ለወላጆች እና ለአስተማሪዎች የሰጣቸው ሲሆን ከሕይወታቸውም እያንዳንዱ ተግባር ሁሉ መንፈሳዊ ትምህርቶችን መማር ይችላሉ፡፡ ስለ አካላዊ ንፅህና ልምዶች ስናሰለጥናቸው፣ እግዚአብሔር በልባቸውም ሆነ በአካል ንፁህ እንዲሆኑ እንደሚፈልግባቸው ልናስተምራቸው ይገባል፡፡ አንድን ክፍል ሲያጸዱ ጌታ ልብን እንዴት እንደሚያነጻ መማር ይችላሉ። በሮችን እና መስኮቶችን ዘግተው በክፍል ውስጥ የተወሰነ የማጣሪያ ንጥረ ነገር ማስቀመጥ ሳይሆን በሮቹን እና መስኮቶቹን በሰፊው ከፍተው በትጋት አቧራውን ሙሉ በሙሉ ያስወግዳሉ። እንዲሁ የሥጋዊ ግፊት እና የስሜት መስኮቶች ወደ ሰማይ ተከፍተው የራስ ወዳድነት እና የምድራዊነት አቧራ መወገድ አለበት። የእግዚአብሔር ጸጋ የአእምሮ ክፍሎችን ማጽዳት አለበት፣ እናም እያንዳንዱ የተፈጥሮ አካል በእግዚአብሔር መንፈስ መንጻት እና መጠንከር አለበት። በዕለት ተዕለት ሥራዎች ላይ የሚኖረው ዝርክርክነት እና ንጽህና ማጣት እግዚአብሔርን ወደ መዘንጋት እና በእምነት ውስጥ ገሃድ አልባ ወደ ሆነ የኃይማኖት መልክ ያመራል፡፡ መንቃት እና መጸለይ አለብን፣ አለበለዚያ ጥላውን ይዘን ዋናውን ነገር እናጣለን።CGAmh 475.1

    እንደ ወርቅ ክሮች ያለ ህያው እምነት በየዕለቱ ተሞክሮ የጥቃቅን ግዴታዎች አተገባበር ውስጥ መታየት አለበት፡፡ 1001Testimonies For The Church 6:170, 171.CGAmh 475.2

    የልብ ትምህርት እና የመጽሐፍ ትምህርት በንጽጽር— ወጣቶች የአእምሮ ኃይሎቻቸውን ወደ ከፍተኛ የእድገት ደረጃ መድረስ እንዳለባቸው እንዲሰማቸው መሆኑ ትክክል ነው፡፡ እግዚአብሔር ገደብ ያላደረገበት ትምህርት ላይ እኛ ገደብ ማድረግ የለብንም፡፡ ነገር ግን ግኝቶቻችን ለአምላክ ክብር እና ለሰው ልጅ ጥቅም የማይውሉ ከሆነ ምንም አይጠቅሙም፡፡ እውቀታችን የላቁ ዓላማዎችን ለማሳካት መወጣጫ ድንጋይ እስካልሆነ ድረስ ዋጋ ቢስ ነው ...፡፡CGAmh 475.3

    ከመጻሕፍት ከሚገኘው ትምህርት ይልቅ የልብ ትምህርት የበለጠ ጠቀሜታ አለው፡፡ ስለ ምንኖርበት ዓለም ዕውቀትን ማግኘቱ ጥሩ ነው፣ እንዲሁም በጣም አስፈላጊም ነው፤ ሆኖም ግን ዘለአለማዊነትን ከሐሳባችን ውጭ ካደረግን በጭራሽ ማገገም ወደማንችልበት ውድቀት ውስጥ እንገባለን።12Testimonies For The Church 8:311.CGAmh 476.1

    የጋራ ጥቅሞች— ልጆቻችን የጌታ ንብረት ናቸው፤ እነርሱ በዋጋ ተገዝተዋል፡፡ ይህ አስተሳሰብ ለእነርሱ የምንሰራበት ዋና ምንጭ መሆን አለበት፡፡ ዘወትር ስለ እግዚአብሔር ቃል እነርሱን ማስተማር ድነታቸውን ለማረጋገጥ እና ከፈተና መንገድ እነርሱን ለመሰወር እጅግ የተሳካ ዘዴ ነው፡፡ ወላጆችም ከልጆቻቸው ጋር ተማሪዎች በሚሆኑበት ጊዜ፣ ራሳቸውን በእውነት እውቀት ይበልጥ በፍጥነት እያደጉ መሆናቸውን ያገኛሉ። አለማመን ይጠፋል፤ እምነት እና ተግባር ይጨምራል፤ ጌታን ለማወቅ በሄዱ ቁጥር ዋስትና እና መተማመን ጥልቅ ይሆናል። 1002Testimonies For The Church 8:311.CGAmh 476.2

    ወላጆች የመሰናክል ድንጋይ ሊሆኑ የሚችሉት እንዴት ነው— ለልጆቻችሁ ምን አይነት ምሳሌ ትሆናላችሁ? በቤት ውስጥ ምን ቅደም ተከተል አለዎት? ልጆቻችሁ ደግ፣ ለሌሎች አሳቢ፣ ገር፣ በቀላሉ የሚለመኑ፣ እና ከምንም ነገር በላይ፣ ሃይማኖታዊ ነገሮችን ለማክበር እና የእግዚአብሔርን የይገባኛል ጥያቄዎች አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ መማር አለባቸው። 1003Testimonies For The Church 5:424.CGAmh 476.3

    እግዚአብሔር እያንዳንዱን ቤተሰብ እንዲመራ የወሰነባቸው መንገዶች እርሱን በመፍራት እና በመውደድ ቢከበሩ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ገና በልጅነታቸው ጥልቅ እና የተመጣጠነ ኃይማኖተኝነትን ማሳየት ይችላሉ፡፡ የትክክለኛ ሥልጠና እና የእርምት ዋጋን ያሳያሉ። ነገር ግን የእውነት አስተማሪ ቃላት በልጆች አእምሮ ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ ብዙውን ጊዜ በወላጆች ቃላት እና ድርጊቶች ተቃርኖ ይገጥማቸዋል፡፡ የልጆች ልብ ለአስቸጋሪነት በቀላሉ ተጋላጭ ቢሆንም እንኳ ብዙውን ጊዜ በእውነት ተጽዕኖ ሥር ይወድቃል፣ ዳሩ ግን ብዙውን ጊዜ ፈተናዎች በአባት ወይም በእናት በኩል ይመጡባቸዋል፣ ለሰይጣን ዘዴዎችም ሰለባዎች ይሆናሉ፡፡ ወላጆች በማይተባበሩበት ጊዜ የልጆችን እግሮች በአስተማማኝ ጎዳናዎች ላይ ማኖር ፈጽሞ የማይቻል ነው፡፡ ብልሃት ከጎደላቸው ወላጆች ከንፈሮች የሚወጡ ክፉ ንግግሮች በልጆች መካከል እውነተኛ ለውጥ እንዳይፈጠር ዋነኞቹ እንቅፋቶች ናቸው፡፡15Manuscript Releases 4:9, 1901.CGAmh 476.4

    ከጸሎቶቻችሁ ጋር በሚስማማ መንገድ ኑሩ— “በእኔ ብትኖሩ ፣ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።” በምትጸልዩበት ጊዜ ይህንን ተስፋ አቅርቡ፡፡ በቅዱስ ድፍረት ወደ እርሱ መምጣት ልዩ መብታችን ነው፡፡ በቅንነት ብርሃኑ በእኛ ላይ እንዲበራ በጠየቅንበት ቅጽበት፣ ሰምቶ ይመልስልናል። ነገር ግን ከጸሎታችን ጋር በሚስማማ መንገድ መኖር አለብን፡፡ ከእነርሱ ጋር በተቃራኒው የምንራመድ ከሆነ ምንም ፋይዳ አይኖረውም፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍትን ክፍል ካነበበ እና ጸሎት ካቀረበ በኋላ ብዙውን ጊዜ ከእንብርክኩ እንደተነሳ ወዲያውኑ ልጆቹን መሳደብ የሚጀምር አንድ አባት አይቻለሁ፡፡ እርሱ ያቀረበውን ጸሎት እግዚአብሔር እንዴት ምላሽ መስጠት ይችላል? ደግሞም አንድ አባት ልጆቹን ከሰደበ በኋላ ፀሎት ቢያቀርብ ያ ጸሎት ለልጆቹ ይጠቅማቸዋል ወይ? ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ የንስኃ ጸሎት ካልሆነ በስተቀር አይጠቅማቸውም። 1004Manuscript Releases 11:4, 1903.CGAmh 477.1

    ልጆች ለጥምቀት ዝግጁ በሚሆኑበት ጊዜ— ልጆቻችሁ ለመጠመቅ እስከሚደርሱ ድረስ የእግዚአብሔር ልጆች እንዳልሆኑ እንዲያስቡ በጭራሽ አትፍቀድ፡፡ ጥምቀት ልጆችን ክርስቲያኖች አያደርጋቸውም፤ አይለውጣቸውምም፤ ነገር ግን እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኛቸው በማመን እና ከአሁን ወዲያ ለእርሱ በመኖር የእግዚአብሔር ልጆች እንደሚሆኑ ማወቃቸውን የሚያሳዩበት ውጫዊ ምልክት ነው፡፡17Manuscript Releases 5:1896.CGAmh 477.2

    ልጆቻቸው እንዲጠመቁላቸው የሚፈልጉ ወላጆች ራሳቸውን በመመርመርም ሆነ ለልጆቻቸው በታማኝነት መመሪያ በመስጠት ረገድ መስራት ያለባቸው ሥራ አላቸው፡፡ ጥምቀት እጅግ ቅዱስ እና አስፈላጊ ሥነ ሥርዓት በመሆኑ ስለ ትርጉሙ ጥልቅ ግንዛቤ ሊኖር ይገባል። እርሱ ለኃጢአት ንስሓ መግባት እና በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ አዲስ ሕይወት መግቢያ መንገድ ማለት ነው፡፡ ስርዓቱን ለመቀበል ከመጠን በላይ ጥድፊያ መኖር የለበትም። ወላጆችም ሆኑ ልጆች የሚያስከፍለውን ዋጋ እንዲያስቡ አድርጓቸው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲጠመቁ በመስማማት፣ በእነዚህ ልጆች ላይ ታማኝ መጋቢዎች ለመሆን፣ በባህሪያቸው ግንባታ ምሪት ለመስጠት የተቀደሰ ቃል ኪዳን መግባታቸው ነው፡፡ እንደሚያምኑ የሚናገሩትን እምነት እንዳያዋርዱ እነዚህን የመንጋ ጠቦቶች በልዩ ዓላማ ለመጠበቅ ቃል ኪዳን መግባታቸው ነው...፡፡CGAmh 477.3

    በሕይወታቸው ውስጥ በጣም አስደሳች ጊዜ ሲመጣ እና በልባቸው ኢየሱስን ሲወዱ እና ለመጠመቅ ሲፈልጉ፣ በዚያን ጊዜ በታማኝነት ፍርድ ስጧቸው። ሥርዓቱን ከመቀበላቸው በፊት፣ ለእግዚአብሔር መሥራት በሕይወታቸው የመጀመሪያ ዓላማቸው መሆን አለመሆኑን ይጠይቋቸው፡፡ ከዚያም እንዴት መጀመር እንዳለባቸው ንገሯቸው፡፡ እነዚህ ብዙ ትርጉም ያላቸው የመጀመሪያዎቹ ትምህርቶች ናቸው፡፡ ቀላል ባለ አይነት ሁኔታ ለእግዚአብሔር የመጀመሪያ አገልግሎታቸውን እንዴት መስራት እንዳለባቸው አስተምሯቸው፡፡ ስራውን በተቻለ መጠን ለመረዳት እንዲቻል ቀላል አድርጉት። በክርስቲያን ወላጆች ምክር ሥር በመሆን ራስን ለጌታ አሳልፎ መስጠት፣ ቃሉ እንደሚመራው መሥራት ምን ማለት እንደሆነ አስረዷቸው። 1005Testimonies For The Church 6:93, 94.CGAmh 478.1

    ከጥምቀት በኋላ የወላጆች ግዴታ— በታማኝነት ከተሰራ ሥራ በኋላ፣ ልጆቻችሁ የመለዋወጥ እና የጥምቀትን ትርጉም ተረድተው በእውነት ስለመለወጣቸው ከረካችሁ እንዲጠመቁ አድርጓቸው። ነገር ግን፣ ደግሜ እላለሁ፣ በመጀመሪያ ልምድ የሌላቸውን እግራቸውን በጠበበው የታዛዥነት መንገድ ለመምራት ታማኝ እረኞች ለመሆን ራሳችሁን አዘጋጁ፡፡ ለልጆቻቸው በፍቅር፣ በመልካምነት እና በክርስቲያን ትህትና እንዲሁም ሙሉ በሙሉ ለክርስቶስ ራስን በመስጠት ለልጆቻቸው ትክክለኛ ምሳሌ እንዲሆኑ እግዚአብሔር በወላጆች ውስጥ መሥራት አለበት፡፡ በልጆቻችሁ መጠመቅ ከተስማማችሁ እና ከዚያ የፈለጉትን ነገር እንዲያደርጉ ከተዋችኋቸው፣ እግሮቻቸውን ቀና ጎዳና ላይ ለማቆየት አንድም ልዩ ግዴታ እንደሌለባችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ፣ እምነታቸውን እና ድፍረታቸውን እና ለእውነት ፍላጎትን ቢያጡ ተጠያቂዎቹ እራሳችሁ ናችሁ፡፡ 1006Testimonies For The Church 6:94, 95.CGAmh 478.2

    የሰማያዊው ንጉሥ ልጆች፣ የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት ለመሆን መዘጋጀት እንዲችሉ እንድታስተምሯቸው እግዚአብሔር ይጠራችኋል። ለእነርሱ መዳን በትጋት በመስራት ከእግዚአብሔር ጋር ተባበሩ፡፡ ከተሳሳቱ በምሬት አትውቀሷቸው፡፡ ተጠምቀው አሁንም ስህተት በመሥራታቸው በጭራሽ አታፌዙባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ ሥራን በተመለከተ የሚማሯቸው ብዙ ነገሮች እንዳሉ አትዘንጉ። 1007Manuscript Releases 8:0.1901.CGAmh 479.1

    ለልዩ ስብሰባዎች መዘጋጀት— ቤተሰቦች ወደ ቅዱስ ጉባኤዎቻችን ከመምጣታቸው በፊት መሥራት ያለባቸው ሥራ ይህ ነው፡፡ ለመብላት እና ለመልበስ መዘጋጀት ሁለተኛ ጉዳይ ይሁን፣ ነገር ግን ጥልቅ ልብን የመመርመር ሥራ ቤት ውስጥ ይጀመር፡፡ በቀን ሦስት ጊዜ ጸልዩ፣ እንደ ያዕቆብም አጥብቃችሁ ያዙት፡፡ ቤት ኢየሱስ የሚገኝበት ሥፍራ ነው፤ ከዚያም እርሱን ወደ ስብሰባው ይዛችሁት ሂዱ እና እዚያ የምታሳልፏቸው ሰዓታት እጅግ ውድ ይሆናሉ። ነገር ግን ለዚያ ጊዜ የመዘጋጀት የግለሰብ ሥራ ቸል ተብሎ የጌታ መገኘት እንዲሰማችሁ እና የኃይሉ መገለጥ እንዲታያችሁ እንዴት ትጠብቃላችሁ?CGAmh 479.2

    ስለ ነፍሳችሁ፣ ስለ ክርስቶስ፣ እና ስለ ለሌሎች ሰዎች ስትሉ ቤታችሁ ላይ ሥሩ፡፡ ከዚህ በፊት ባልተለመደ ሁኔታ ጸልዩ፡፡ ልብ በእግዚአብሔር ፊት ይሰበር፡፡ ቤታችሁን ሥርዓት አስይዙ፡፡ ልጆቻችሁን ለመጪ ለክስተቶች አዘጋጇቸው፡፡ በንጹህ እጆች እና በንጹህ ልቦች በእግዚአብሔር ፊት እንደሚታዩ በጥሩ ልብስ መታየታቸው ብዙም ውጤት የሌለው መሆኑን አስተምሯቸው፡፡ በመንገዳቸው ላይ ያሉትን መሰናክሎች ሁሉ አስወግዱ— በእነርሱ መካከል ወይም በእናንተ እና በእነርሱ መካከል ሊኖሩ የሚችሉ ልዩነቶች ሁሉ ማለት ነው። ይህን በማድረጋችሁ የጌታን መገኘት ወደ ቤቶቻችሁ ትጋብዛላችሁ፣ ደግሞም ለስብሰባ ስትወጡ ቅዱሳን መላእክት ከእናንተ ጋር ይሆናሉ፣ እናም ብርሃናቸው እና መገኘታቸው የክፉ መላእክትን ጨለማ ወደኋላ ይመልሳሉ። 1008Testimonies For The Church 5:164, 165.CGAmh 479.3

    የእውነትን ዘሮች በእምነት መዝራት— የዘሪው ሥራ የእምነት ሥራ ነው። እርሱ የዘር መብቀል እና የእድገት ምስጢርን መረዳት አይችልም፤ ሆኖም ግን እግዚአብሔር እፅዋት እንዲበለጽግ በሚያደርግበት ወኪሎች ላይ እምነት አለው፡፡ በተትረፈረፈ መከር ብዙ እጥፍ እንደሚሰበስብ በመጠበቅ ዘሩን ይዘራል፡፡ እንዲሁም ወላጆች እና አስተማሪዎች ከሚዘሩት ዘር መከርን በመጠበቅ ሊሰሩ ይገባል፡፡ 1009Education, 105.CGAmh 480.1

    በተዘራው ዘር ላይ የእግዚአብሔርን በረከት መጠየቅ አለብን፣ እናም የመንፈስ ቅዱስ የማሳመን ኃይል ትንንሾቹን ልጆች እንኳን ይይዛቸዋል። በእግዚአብሔር ካመንን የዓለምን ኃጢአት ወደሚያስወግድ ወደ እግዚአብሔር በግ እነርሱን መምራት እንችላለን፡፡ ይህ ትናንሽ ለሆኑ የጌታ ቤተሰብ አባላት ታላቅ ትሩፋት ያለው ሥራ ነው። 1010Testimonies For The Church 6:105.CGAmh 480.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents