Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 24—ምጣኔ ሀብትና ቁጠባ

    የብኩንነት ልማዶችን ያስወግዱ—በንብረቶቻቸው ሁሉ ላይ እግዚአብሔር የይገባኛል ጥያቄ እንዳለው እና ይህን የይገባኛል ጥያቄ ምንም ሊሰርዘው እንደማይችል፤ ንብረቶቻቸው በሙሉ ይታዘዙ እንደሆነ እነርሱን ለመፈተን በአደራ የተሰጣቸው እንደሆነ ልጆችዎን ያስተምሯቸው። ገንዘብ ተፈላጊ ሀብት ነው፤ ለማያስፈልጋቸው በብኩንነት አይሰጥ፡፡ አንድ ሰው የፈቃድ ስጦታዎን ይፈልጋል...፡፡ የብኩንነት ልምዶች ካለብዎት በተቻለ ፍጥነት ከህይወትዎ ቆርጠው ያውጡት፡፡ ይህንን ካላደረጉ በስተቀር ለዘለአለም ይከስራሉ፡፡ እንዲሁም የምጣኔ ሐብት፣ የታታሪነት እና የአሳቢት ልምዶች በዚህች ዓለም ቢሆን እንኳን ከብዙ ጥሎሽ ይልቅ ለእርስዎ እና ለልጆችዎ የተሻሉ ድርሻ ናቸው፡፡ 232Manuscript Releases 13:9, 1898. CGAmh 127.1

    ሕፃናትን ስለ ምጣኔ ሐብት ያስተምሯቸው—አሁን በጌታ የተሰጠኝ ብርሃን ውድ ጊዜአችንን እና ገንዘባችንን አላግባብ እንዳንጠቀም መጠንቀቅ እንዳለብን ነው። ብዙ የምንወዳቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፣ ነገር ግን እንጀራ ለማይሆን ነገር የገንዘብ ወጭ እንዳናደርግ ልንጠነቀቅ ይገባል፡፡ በከተሞቻችን ውስጥ ሥራውን በቆራጥነት ለማስፋፋት ብዙ ገንዘብ ያስፈልገናል፡፡ እያንዳንዱ ሰው በጌታ ሥራ ውስጥ የሚሳተፍት ድርሻ ሊኖረው ይገባል፡፡ ታናናሽ የመንጋው አባላት በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔርን ሥራ የመደገፍ ሀላፊነትን መጋራት ይማሩ ዘንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ምጣኔ ሐብት ትምህርት ማስተማር አለባቸው፡፡2Letter 4, 1911.CGAmh 127.2

    ፍቅር የሚገለጠው በብኩንነት አይደለም—በቤትዎ ውስጥ ምጣኔ ሐብትን ይለማመዱ፡፡ ጣኦታት በብዙዎች እጅግ ይወደዳሉ፣ ይመለኩማል፡፡ የራስ ወዳድነትዎን ደስታ ይተው፡፡ ገንዘብዎ የእግዚአብሔር ገንዘብ ስለሆነ እና እንደገናም ከእርሶም ስለሚፈለግ፤ እለምንዎታለሁ ቤትዎን ለማስጌጥ አይጨርሱት፡፡ ወላጆች፣ ስለ ጌታ ስትሉ የልጆቻችሁን የቅንጦት ፍላጎት ለማሟላት የጌታን ገንዘብ አትጠቀሙ። በዓለም ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ቅጥ እና ታይታን እንዲፈልጉ አታስተምሯቸው…፡፡ CGAmh 128.1

    ልጆቻችሁ ለእነርሱ ያላችሁ ፍቅር ኩራታቸውን፣ ብኩንነታቸውን እና ለታይታ ያላቸውን ፍቅር በማሞላቀቅ መገለጽ አለበት ብለው እንዲያስቡ አያስተምሯቸው፡፡ ገንዘብን በምን መንገዶች መጠቀም እንዳለብን ለመፈልሰፍ አሁን ጊዜ የለም፡፡ የፈጠራ ችሎታዎ መዘርጋት ያለበት እንዴት መቆጠብ እንዳለብዎት ለማየት መሆን አለበት፡፡ 233Manuscript Releases 13:9, 1898.CGAmh 128.2

    ስለ ቁጠባ የክርስቶስ ትምህርት—አምስቱን ሺህ ሰዎች በመመገብ ሂደት ውስጥ አንድ ትምህርት እናገኛለን፣ ይህም በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ስንሆን እና ጥብቅ ቁጠባን እንድንለማመድ በምንገደድባቸው ጊዜያቶች ውስጥ በተለየ ሁኔታ ተግባራዊ የሚሆን ትምህርት ነው፡፡ ተዓምራቱን ሠርቶ የብዙዎችን ረሃብ ካረካ በኋላ፣ የተቀረው ምግብ እንዳይባክን ክርስቶስ ጥንቁቅ ነበር፡፡234Manuscript Releases 3:1912. CGAmh 128.3

    ለደቀመዛሙርቱ “ምንም እንዳይጠፋ የቀረውን ትርፍራፊ ሰብስቡ” አላቸው፡፡ የሰማይ ሀብቶች ሁሉ በእርሱ ትዕዛዝ ሥር ቢሆኑም እንኳ፣ የዳቦ ቁራሽ እንኳን እንድትባክን አልፈቀደም፡፡5Letter 20a, 1893.CGAmh 128.4

    ጠቃሚ የሆነው ምንም ነገር አይጣል—ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ማንኛውም ነገር መጣል የለበትም፡፡ ይህ ጥበብን፣ ቀድሞ ማሰብን እና ዘላቂ እንክብካቤን ይጠይቃል። በትናንሽ ነገሮች መቆጠብ አለመቻል ብዙ ቤተሰቦች ለሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በማጣት ምክንያት የሚሠቃዩበት አንደኛው ምክንያት እንደሆነ ተገልጦልኛል፡፡ 235Manuscript Releases 3:1912.CGAmh 128.5

    ቁጠባን በጭራሽ አልተማሩም—ለጌታ መሠራት ያለበት ብዙ ሥራ አለ፣ እናም ዛሬ ከእግዚአብሄር ስራ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ማዕረግ ይዘው ያሉ ሰዎች ያልተሳካላቸው ቁጠባን በጭራሽ ስላልተማሩ ነው፡፡ ወደ ሥራው ሲገቡ ፍላጎታቸውን በገቢዎቻቸው መጠን አልገደቡም፣ የብኩንነት ልማዶቻቸው በሥራው ውስጥ ያላቸውን ጠቀሜታ ማውደሙን አረጋግጧል፡፡ 236 Letter 48, 1888.CGAmh 129.1

    አግባብነት ያለውን የገንዘብ አጠቃቀም እንዴት ማስተማር እንደሚቻል—እያንዳንዱ ወጣት እና እያንዳንዱ ልጅ ምናባዊ ችግሮችን ለመፍታት ብቻ ሳይሆን ስለ ገቢው እና ስላ ወጪው ትክክለኛ አመዘጋገብ እንዲኖረው ይስተማር። ይህን በመጠቀም አግባብነት ስላለው የገንዘብ አጠቃቀም ይማር፡፡ በወላጆቻቸው ሰጥቷቸውም ሆነ በራሳቸው ሠርተው ያገኙ ቢሆን፣ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች የራሳቸውን ልብስ ፣መፅሀፎቻቸውን እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን መምረጥ እና መግዛትን ይማሩ፤ እናም ወጪዎቻቸውን በመመዝገብ፣ በሌላ መንገድ መማር የማይችሉትን፣ የገንዘብን እሴት እና አጠቃቀም ይማራሉ። 237Counsels on Stewardship, 294.CGAmh 129.2

    የሂሳብ መዝገብ መያዝ ጠቀሜታ—ልጆች ገና በልጅነታቸው ማንበብን፣ መፃፍን፣ አሀዞችን መረዳትን፣ የራሳቸውን የወጪና ገቢ መመዝብ መማር አለባቸው፡፡ በዚህ እውቀት ደረጃ በደረጃ ወደፊት በማደግ ሊራመዱ ይችላሉ፡፡ 238 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 168, 169. CGAmh 129.3

    ልጆች ወጪና ገቢያቸውን መያዝን ይማሩ፡፡ ይህ ትክክለኛ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። ብኩን ወንድ ልጅ ብኩን ጎልማሳ ይሆናል፡፡ ከንቱ፣ ራስ ወዳድ፣ ለራስዋ ብቻ የምትጠነቀቅ ሴት ልጅ ተመሳሳይ ሴት ትሆናለች፡፡ እኛ ተጠያቂ የምንሆንባቸው ሌሎች ወጣቶች እንዳሉም መዘንጋት የለብንም፡፡ ልጆቻችን ትክክለኛ ልማዶች እንዲኖራቸው ካሠለጠንናቸው በእነርሱ አማካኝነት በሌሎች ላይ ተጽዕኖ ማሳደር እንችላለን፡፡10Letter 11, 1888.CGAmh 129.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents