Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 44—የእርማት ተግሳጽ እንዴት መተግበር እንዳለበት

    ጌታ እንዲገባ እና እንዲገዛ ይጠይቁ — በቤተሰብ ውስጥ ታዛዥነት እንደ መስፈርት አድርጉ፤ ነገር ግን ይህንን በምታደርጉበት ጊዜ ከልጆቻችሁ ጋር ጌታን በመሻት እንዲገባ እና እንዲገዛ ጠይቁት፡፡ ልጆቻችሁ ቅጣትን የሚያስከትል አንድ ነገር ሠርተው ይሆናል፤ ነገር ግን በክርስቶስ መንፈስ ብትይዟቸው እጆቻቸውን አንገታችሁ ላይ ይጠመጥማሉ፤ በጌታ ፊት ራሳቸውን ዝቅ ያደርጉ እና ስህተታቸውን ይቀበላሉ፡፡ ያ በቂ ነው። ከዚያ በኋላ ቅጣት አያስፈልጋቸውም፡፡ ሁሉንም ነፍስ የምንደርስበትን መንገድ ስለከፈተልን ጌታን እናመሰግን፡፡ 467Manuscript Releases 21, 1909.CGAmh 231.1

    ልጆቻችሁ የማይታዘዙ ከሆነ መታረም አለባቸው…፡፡ እነርሱን ከማረማችሁ በፊት ብቻችሁን ሂዱ እና የልጆቻችሁን ልብ እንዲያለሰልስ እና እንዲያሸንፍ እና ስለ እነርሱ አያያዝ ጥበብ እንዲሰጣችሁ ጌታን ጠይቁ፡፡ መቼም ቢሆን ይህ ዘዴ ሳይሰካ መቅረቱን በጭራሽ አላውቅም፡፡ አንድ ልጅ በስሜት እየታመሰ ሳለ መንፈሳዊ ነገሮችን እንዲረዳ ማድረግ አይቻልም፡፡ 468Manuscript Releases 27, 1911.CGAmh 231.2

    ልጆችን በትዕግስት አስተምሯቸው— ጌታ የእነዚህን ልጆች ልብ ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ አገልግሎቱ እንዲሰጥ ይፈልጋል፡፡ ከእነርሱ ጋር ለመመካከር ገና ልጆች ሳሉ፣ በተቻላችሁ መጠን አእምሯቸውን ቀይሩ፤ እያደጉ ሲሄዱም፣ የተሳሳተ ምኞታቸውን እንዳያረኩ በመመሪያ እና በምሳሌ አስተምሯቸው።CGAmh 231.3

    በትዕግሥት አስተምሯቸው። አንዳንድ ጊዜ መቀጣት አለባቸው፣ ነገር ግን በጭራሽ በቁጣ ሲቀጡ እንደነበር ሆኖ እንዲሰማቸው አታድርጉ፡፡ በእንደዚህ ዓይነት መንገድ የባሰ ክፉ ነገር ብቻ ነው የምትሰሩት፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን በማሰልጠን ረገድ የጌታን ምክር ቢታዘዙ ኖሮ በቤተሰብ ውስጥ ብዙ አስደሳች ያልሆኑ ልዩነቶች መወገድ ይችሉ ነበር። 469 Manuscript Releases 93, 1909.CGAmh 231.4

    ወላጆች ለአምላክ መገዛት አለባቸው— እናቶች፣ ምንም እንኳ ልጆቻችሁ ባለማወቅ የሚያናድዷችሁ ቢሆንም፣ ነገር ግን ለትዕግስት ማጣት ሥፍራ አትስጡ። በትዕግሥትና በፍቅር አስተምሯቸው። ለእነርሱ ጽኑዎች ሁኑ። ሰይጣን እንዲቆጣጠራቸው አታድርጉ። በአምላክ ተግሣጽ ሥር ስትሆኑ ብቻ እነርሱን ገስጿቸው። የዋህ እና ራሱን ያዋረደ፣ ንፁህ እና ያልረከሰ ከሆነው ከእርሱ የምትማሩ ከሆነ ክርስቶስ በልጆቻችሁ ሕይወት ውስጥ ድል ይነሳል፡፡ 470Letter 272, 1903.CGAmh 232.1

    ነገር ግን ራስን መግዛትን ሳትለማመዱ፣ ያለ ስርዓት፣ ያለ ሀሳብ እና ያለ ጸሎት ለመቆጣጠር ብትሞክሩ፣ በእርግጠኝነት መራራውን ውጤት ታጭዳላችሁ፡፡ 471The Signs of the Times, February 9, 1882CGAmh 232.2

    በጭራሽ በንዴት አታርሟቸው— ልጆቻችሁን በፍቅር ማረም አለባችሁ። እስክትናደዱና እስክትቀጧቸው ድረስ የራሳቸውን መንገድ እንዲከተሉ አታድርጓቸው። እንዲህ ዓይነቱ እርማት ከማስተካከል ይልቅ በክፋት እንዲቀጥሉ ያደርጋል፡፡ 472The Review and Herald, September 19, 1854CGAmh 232.3

    ለተሳሳተ ልጅ ስሜታዊነትን ማሳየቱ ክፋትን መጨመር ነው። ይህ የልጁን ክፉ ስሜቶች በማነሳሳት እና ለእርሱ እንደማታስቡ እንዲሰማው ያደርገዋል፡፡ ለእርሱ የምትጠነቀቁ ቢሆን ኖሮ በዚህ አይነት መንገድ አያያዝ እንደማትይዙት በውስጡ ያስባል፡፡ CGAmh 232.4

    ደግሞስ እነዚህ ልጆች የሚታረሙበትን መንገድ እግዚአብሔር አያውቅም ብላችሁ ታስባላችሁ? እርሱ ያውቃል፣ እናም የእርማቱ ተግባር ከመግፋት ይልቅ ለመማረክ በሆነ መልኩ የተሰራ ቢሆን ኖሮ የተባረከው ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል ያውቃል…።CGAmh 232.5

    እለምናችኋለሁ ልጆቻችሁን በቁጣ አታርሙ። ከሁሉ ጊዜ ይልቅ በትህትና፣ በትዕግስት እና በጸሎት እርምጃ መውሰድ ያለባችሁ ጊዜ ይህ ነው። እንግዲያው ከልጆች ጋር ተንበርክኮ ጌታን ይቅርታ መጠየቅ ያኔ ነው፡፡ ርህራሄ እና ፍቅርን በማሳየት እነርሱን ወደ ክርስቶስ ለመሳብ እሹ እና ከምድር ኃይል የላቀ ኃይል ከጥረቶቻችሁ ጋር እየሰራ መሆኑን ታያላሁ። 473Manuscript Releases 53, 1912.CGAmh 232.6

    ልጅን ለማረም ግዴታ ሲሆንባችሁ ድምጻችሁን ወደ ከፍተኛ የጩኸት ጥግ ከፍ አታድርጉ…፡፡ ራሳችሁን ከመቆጣጠር ውጭ አትሁኑ፡፡ ልጅን ሲያርም ለቁጣ ሥፍራን የሚሰጥ ወላጅ ከልጁ የባሰ የተሳሳተ ነው፡፡474The Signs of the Times, February 17, 1904. CGAmh 233.1

    ስድብ እና ብስጭት በጭራሽ ጠቃሚ አይደሉም— ሻካራ፣ የቁጣ ቃላት ከሰማይ የመነጩ አይደሉም። ስድብና ብስጭት በጭራሽ ጠቃሚ አይደሉም። ይልቁን የሰውን ልብ ክፉ ስሜቶችን የሚያነሳሱ ናቸው። ልጆቻችሁ ስህተት ሲሰሩ እና በአመፅ ሲሞሉ፣ እና ሻካራ ቃላትን ለመናገር እና ለመተግበር በምትፈተኑበት ጊዜ፣ እነርሱን ከማረማችሁ በፊት ቆየት በሉ፡፡ ለማሰብ እድል ስጧቸው፣ ቁጣችሁም እንዲቀዘቅዝ አድርጉ፡፡CGAmh 233.2

    ልጆቻችሁን በርህራሄ እና በእርጋታ በምትይዙበት ጊዜ፣ እነርሱ እና እናንተም የጌታን በረከቶች ትቀበላላችሁ። በእግዚአብሔር የፍርድ ቀን ለልጆቹ ታጋሽ እና ሩህሩህ ስለ መሆኑ የሚጸጸት ሰው እንዳለ ታስባላችሁን? 475 Manuscript Releases 114, 1903.CGAmh 233.3

    ብስጭት ትዕግሥት ለማጣት ሰበብ አይሆንም— ወላጆች አንዳንድ ጊዜ የተሳሳተ አካሄዳቸውን ጥሩ ስሜት ስላልነበራቸው እንዳደረጉ ሰበብ ያቀርባሉ፡፡ ብስጩዎች ስለሆኑ መታገስ እና መረጋጋት እና ደስተኛም ሆነው መናገር እንደማይችሉ ያስባሉ፡፡ በዚህ ረገድ ራሳቸውን በማታለል እናም የእግዚአብሔር ጸጋ በተፈጥሮ ድክመቶችን ለማሸነፍ በቂ እንዳልሆነ በሚቆጥሩ ሰዎች የሚደሰተውን ሰይጣንን ያስደስቱታል፡፡ በማንኛውም ጊዜ ራሳቸውን መቆጣጠር ይችላሉ፣ ራሳቸውን መቆጣጠርም አለባቸው። እግዚአብሔር ከእነርሱ ይህን ይፈልጋል፡፡ 476Testimonies For The Church 1:385.CGAmh 233.4

    ወላጆች አንዳንድ ጊዜ በሥራ ሲደክሙ ወይም በችግር ጊዜ ሲጨቆኑ የተረጋጋ መንፈስን ጠብቆ ከማቆየት ይልቅ እግዚአብሔርን የሚያሳዝንና በቤተሰብ ላይ ደመናን የሚያመጣ ትዕግሥት ማጣትን ያንጸባርቃሉ፡፡ ወላጆች፣ የመረበሽ ስሜት ሲሰማችሁ በዚህ አደገኛ ቁጣ መላውን ቤተሰብ በመመረዝ ታላቅ ኃጢአት መሥራት የለባችሁም፡፡ በእንደነዚህ ጊዜያት ራሳችሁ ላይ ሁለት ጊዜ ጥበቃ አኑሩ እና አስደሳች ከሆኑ ቃላት በስተቀር ከከንፈሮቻችሁ ምንም እንዳያመልጥ ወስኑ። በዚህ መንገድ ራስን በመግዛትን በመለማመድ ብርቱ በመሆን ታድጋላችሁ። የነርቭ ስርዓታችሁም እጅግ በቀላሉ የሚጎዳ አይሆንም…፡፡ የሱስ ድክመቶቻችንን ያውቃል፣ ከኃጢአት በስተቀር ራሱም በሁሉም ነገር ልምዳችንን ላይ ተካፍሏል፤ ስለዚህ ለችሎታችንና ለአቅማችን የሚመጥን መንገድ አዘጋጅቶልናል፡፡CGAmh 233.5

    አንዳንድ ጊዜ በቤተሰብ ክልል ውስጥ ሁሉም ነገር በተሳሳተ መንገድ የሄደ ይመስላል፡፡ ሁሉ ሥፍራ ብስጭት ያለ እና ሁሉም እጅግ የተረበሸ እና ደስተኛ ያልሆኑ ይመስላል። ወላጆች የሁከቱ መንስኤ ራሳቸው ሆነው ሳሉ ምስኪን ልጆቻቸው ላይ ወቀሳ ይሰነዝሩ እና እጅግ የማይታዘዙ እና አዋኪ፣ በዓለም ላይ እጅግ ክፉ ልጆች እንደሆኑ ያስባሉ፡፡ አምላክ ራሳቸውን እንዲገዙ ይፈልጋል። ለትዕግስት ማጣት እና ብስጭት ሲሸነፉ ሌሎች ላይ ችግር እንዲመጣ ምክንያት እንደሚሆኑ መገንዘብ አለባቸው፡፡ በዙሪያቸው ያሉት ሰዎች እነርሱ በሚያንጸባርቁት መንፈስ ተጽዕኖ ሥር ይወድቃሉ፣ እናም እነርሱ በተራቸው ተመሳሳይ መንፈስ ካሳዩ፣ ክፋቱ እየጨመረ ይሄዳል። 477 The Signs of the Times, April 17, 1884. CGAmh 234.1

    አንዳንድ ጊዜ በፀጥታ ውስጥ ሀይል አለ— ሌሎችን ለመቆጣጠር የሚሹ ሰዎች መጀመሪያ እራሳቸውን መቆጣጠር አለባቸው…፡፡ ወላጅ ወይም አስተማሪ ትዕግሥት የሌለው እና ጥበብ የጎደለው ንግግርን የመናገር አደጋ ላይ ሲሆን ዝም ይበል። በዝምታ ውስጥ አስደናቂ ኃይል አለ። 478Education, 292.CGAmh 234.2

    ጥቂት ትዕዛዞችን ይስጡ; ከዚያ ታዛዥነትን እንደ መስፈርት ይፈልጉ—እናቶች በሌሎች ፊት የራሳቸውን ስልጣን ለማሳየት ሲሉ አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን ከማድረግ ይጠንቀቁ፡፡ ጥቂት ትዕዛዞችን ይስጡ፣ ነገር ግን እነዚህ ትዕዛዞች ተቀባይነት ማግኘታቸውን ይመልከቱ፡፡ 479The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 234.3

    በልጆች የእርማት ሂደት ውስጥ እንዲያደርጉ ከጠየቃችኋቸው ግዴታዎች ነጻ አታድርጓቸው፡፡ በግዴለሽነት እንዲያድግ ምክንያት የሚሆኑ አእምሮዎቻችሁን የያዙ ሌሎች ነገሮች እንዲኖሩ አትፍቀዱ፡፡ እናም ልጆቻችሁ እንዳያደርጉ የከለከላችኋቸውን ነገር ስለሚረሱ እና ስለሚያደርጉ የጥበቃ ሥራችሁን ከመስራት አትዛሉ፡፡ 480Manuscript Releases 32, 1899.CGAmh 234.4

    በትዕዛዛችሁ ሁሉ ውስጥ የልጆቻችሁን ከፍተኛ ጥቅም ለማስጠበቅ የታለመ ይሁን፣ ከዚያም እነዚህ ትዕዛዛት መታዘዛቸውን ተመልከቱ። ኃይላችሁ እና ውሳኔአችሁ የማይለዋወጥ ነገር ግን ሁል ጊዜ ለክርስቶስ መንፈስ የተገዛ አለበት። 481 The Signs of the Times, September 13, 1910. CGAmh 235.1

    የቸልተኛ ልጅን አያያዝ— ልጃችሁ አንድ ነገር እንዲሰራ ስትጠይቁት እና “አዎን፣ አደርገዋለሁ” ብሎ ሲመልስላችሁ፣ እና ከዚያ ቃሉን ከመፈጸም ቸል ካለ፣ ጉዳዩን እዚያው ላይ መተው የለባችሁም። ለዚህ ቸልተኝነት ልጃችሁን ተጠያቂ ማድረግ አለባችሁ። ይህንን ልብ ሳትሉ ብታልፉ፣ የችላ ባይነትን እና የታማኝነት ማጣት ልማድን ልጅቻሁን እያስተማራችኋቸው ነው። እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ ልጅ መጋቢነትን ሰጥቷል፡፡ ልጆች ወላጆቻቸውን መታዘዝ አለባቸው፡፡ የቤቱን ሸክም እና ሀላፊነቶችን በመሸከም ረገድ ረዳት መሆን አለባቸው፤ የተሰጣቸውን ሥራ ለመስራት ችላ ሲሉ ተጠያቂ እና ሥራውን እንዲያከናውኑ የሚፈለግባቸው መሆን አለበት፡፡16Manuscript Releases 127, 1899.CGAmh 235.2

    የችኮላ እና አልፎ አልፎ የሚሆን እርማት ውጤቶች— ልጆች ስህተት ሲሠሩ፣ እነርሱ ራሳቸው በኃጢአታቸው ጥፋተኛነት፣ ውርደት እና ጭንቀት ይሰማቸዋል፡፡ እነርሱ ለሚፈጽሟቸው ስህተቶች ቁጣ ብዙውን ጊዜ ግትር እና ምስጢራዊ ያደርጋቸዋል፡፡ እንደማይታዘዙ የፈረስ ግልገሎች፣ ችግርን ለመፍጠር የወሰኑ ይመስላሉ፣ ቁጣም የተሻለ ነገር አያደርግላቸውም፡፡ ወላጆች አእምሯቸውን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለማዞር መሻት አለባቸው። CGAmh 235.3

    ችግሩ ግን ወላጆች በአስተዳደራቸው ወጥ አይደሉም፣ ከመርኾም ይልቅ በስሜት ይንቀሳቀሳሉ፡፡ በስሜት ይከንፋሉ፣ ለልጆቻቸው ምሳሌ የመሆንን ክርስቲያን ወላጆች ሊያደርጉ የሚገባቸውን ነገር አያደርጉም፡፡ አንድ ቀን የልጆቻቸውን ስህተት ዝም ብለው ያልፋሉ፣ በሚቀጥለው ቀን ደግሞ ትዕግስት የለሽ ወይም ራሳቸውን የማይቆጣጠሩ መሆናቸው ያሳዩአቸዋል፡፡ ፍትሕ እና ፍርድን ለማድረግ የጌታን መንገድ አይጠብቁም፡፡ ብዙውን ጊዜ ከልጆቻቸው ይልቅ የባሰ ጥፋተኞች ናቸው፡፡ CGAmh 235.4

    አንዳንድ ልጆች በአባታቸው እና በእናታቸው የተፈጸመባቸውን በደል ይረሳሉ፣ ነገር ግን የተለየ ባህሪይ ያላቸው ሌሎች ልጆች ደግሞ አደገኛ፣ የማይገባቸውን ምክንያታዊ ያልሆነ ቅጣትን መርሳት አይችሉም። በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ነፍሳቸው ይጎዳል፣ አዕምሯቸውም ግራ መጋባት ውስጥ ይገባል፡፡ እናት ራሷን መቆጣጠር ባለመቻሏ እና በአእምሮዋ ሚዛናዊነት ያለው በህሪይ እና ቃላትን ስለማታንጸባርቅ ትክክለኛ መርሆዎችን በልጁ አእምሮ ውስጥ ለማሳደግ ያላትን አጋጣሚዋን ታጣለች፡፡ 482 Manuscript Releases 38, 1895. CGAmh 235.5

    ብትቀጧቸውም እንኳን እንደምትወዷቸው እርግጠኛ እንዲሆኑ እጅግ የተረጋጋችሁ ከንዴት ነፃ የሆናችሁ ሁኑ፡፡18Manuscript Releases 2, 1903.CGAmh 236.1

    ማበረታቻዎች አንዳንድ ጊዜ ከቅጣት የተሻሉ ናቸው— በዚህ የሥራ መስክ ላይ ጥልቅ ፍላጎት ስለተሰማኝ ልጆች በትክክለኛው መንገድ እንዲሰለጥኑ ለማድረግ ማደጎ ልጆችን አሳድጋለሁ፡፡ ስህተት በሚሰሩበት ጊዜ እነርሱን ከመቅጣት ይልቅ ቀና ነገር እንዲሰሩ የሚያስችላቸውን ማበረታቻ እሰጣቸው ነበር፡፡ አንደኛዋ እንዳስፈለጋት መሆን ካልቻለች እራሷን መሬት ላይ የመጣል ልማድ ነበራት፡፡ እንዲህ አልኳት፡- “ዛሬ ለመጀመሪያ ጊዜ ንዴትሽን የምትቆጣጠሪ ከሆነ አጎትሽ ኋይት እና እኔ በሠረገላ እንወስድሻለን፣ ገጠር ላይም አስደሳች ቀን ይኖረናል፡፡ ነገር ግን ራስሽን ወላሉ ላይ የምትጥይ ከሆነ፣ ለመደሰት ያለሽን መብት በቅጣት መልክ ታጭያለሽ፡፡” ለእነዚህ ልጆች በዚህ መንገድ የሰራሁ ሲሆን ይህንን ሥራ ለመስራት አጋጣሚ በማግኘቴ አሁን አመስጋኝ ነኝ። 483Manuscript Releases 95, 1909. CGAmh 236.2

    ስህተት ላይ በፍጥነት፣ በጥበብ፣ በጽናት እርምጃ ይውሰዱ— አለመታዘዝ መቀጣት አለበት። ስህተት መታረም አለበት። በልጅ ልብ ውስጥ የበዛው በደልን ወላጆችና አስተማሪዎች መጋፈጥና ድል መንሳት አለባቸው፡፡ ስህተት ላይ በፍጥነት እና በጥበብ፣ በጽናት እና ውሳኔ እርምጃ መወሰድ አለበት። የክልከላ ጥላቻ፣ አግባብነት የሌላቸውን ፍላጎቶችን የማርካት ፍቅር፣ ለዘላለማዊ ነገሮች ግድየለሽ መሆን በጥንቃቄ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል። ክፋት ካልተወገደ በቀር ነፍስ ትጠፋለች፡፡ ከዚህም በላይ: በሰይጣን መሪነት እርሱን ለመከተል ራሱን የሰጠ ሰው ዘወትር ሌሎችን ማታለል ይፈልጋል። ከልጆቻችን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ በውስጣቸው ያለውን የዓለምን መንፈስ ለመቆጣጠር መሻት አለብን። 484 Letter 166, 1901.CGAmh 236.3

    ዱላ አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ነው— እናት “ልጄን በጭራሽ አልቅጣው?” ብላ ትጠይቅ ይሆናል፡፡CGAmh 237.1

    ሌሎች ይረዳሉ የተባሉ ዘዴዎች ያልሰሩ ከሆነ መግረፍ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ይህን ማስቀረት ሲቻል በትር መጠቀም የለባትም፡፡ ግን ቀለል ያሉ እርምጃዎች በቂ አለመሆናቸው ከተረጋገጠ ልጁን ወደ ልቦናው የሚያመጣ ቅጣት በፍቅር ተግባራዊ መሆን አለበት። የመቆጣጠሪያ መስመሮችን በእጁ እንዳያስገባ ለልጁ ለማሳየት አብዛኛውን ጊዜ አንድ እንዲህ ዓይነቱ እርማት ለሕይወት ዘመኑ በሙሉ በቂ ይሆናል።CGAmh 237.2

    እናም ይህ እርምጃ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ይህ የሚደረገው ወላጅን ለማርካት ወይም የአምባገነናዊ ስልጣናቸውን ለማርካት ሳይሆን፣ ነገር ግን ለልጁ ጥቅም እንደሆነ በውል እንዲገነዘብ መደረግ አለበት። እያንዳንዱ ያልታረመ ስህተት በራሱ ላይ ሐዘንን የሚያመጣበት እና እግዚአብሔርን እንደማያስደስት መማር አለበት፡፡ በእንደዚህ አይነቱ ተግሣጽ ውስጥ ልጆች ፈቃዳቸውን ለሰማያዊው አባት ፈቃድ በማስገዛት ከፍተኛ ደስታቸውን ያገኛሉ፡፡ 485 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 116, 117. CGAmh 237.3

    እንደ የመጨረሻው ሙከራ— አብዛኛውን ጊዜ በርህራሄ ከእነርሱ ጋር የምትመካከሩ ከሆነ መገረፍ እንደማያስፈልጋቸው ታያላችሁ፡፡ እንዲህም ዓይነቱ የአያያዝ ዘዴ በእናንተ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል፡፡ ምስጢረኛቸው ያደርጋቸዋል፡፡ እነርሱም ወደ እናንተ ይመጡ እና እንዲህ ይላሉ፣ ዛሬ በእንደዚህ ዓይነት ጊዜ ስህተት ሰርቼ ነበር፣ እናም ይቅር እንድትሉኝ እና እግዚአብሔር ይቅር እንዲለኝ እንድትለምኑልኝ እፈልጋለሁ፡፡ እንዲህ ያሉ ትዕይንቶችን አልፌያለሁ፣ እናም አውቃቸዋለሁ…፡፡ ስህተት ሲሠሩ፣ በጽናት እነሱን ለማነጋገር፣ ከእነርሱ ጋር ለመፀለይ እና የእግዚአብሔር ቃል መመዘኛዎችን ከፊታቸው ለማድረግ ድፍረት ስለነበረኝ አመስጋኝ ነኝ፡፡ ለአሸናፊው የተገቡትን ቃል ኪደኖች እና ታማኝ ለሆኑት የሚሰጡ ሽልማቶችን ለእነርሱ በማቅረቤ ደስ ብሎኛል፡፡ 486Manuscript Releases 27, 1911.CGAmh 237.4

    በጭራሽ በቁጣ የተሞላ ምት አትማቱ— ድብድብ እና ጭቅጭቅ እንዲማር እስካልፈለጉ ድረስ ልጃችሁን በቁጣ የተሞላ ምት በጭራሽ አትምቱት፡፡ ወላጆች እንደመሆናችሁ መጠን ለልጆቻችሁ የእግዚአብሔርን ቦታ ትይዛላችሁ፣ እናም ጥንቃቄ ማድረግ አለባችሁ፡፡ 487Manuscript Releases 3:2, 1899CGAmh 237.5

    በበትር መቅጣት ሊኖርባችሁ ይችላል፤ ይህ አንዳንድ ጊዜ አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን እስክትረጋጉ ድረስ ለማንኛውም ችግር መፍትሄ መስጠትን አዘግዩ፡፡ መንገዴን እና ፈቃዴን ለእግዚአብሔር አስረክቤአለሁ? ብላችሁ ራሰችሁን ጠይቁ፡፡ በቤት ውስጥ ለመቆጠጣር እምብተኛ የሆኑትን ለማስተካከል ጥበብ፣ ትዕግሥት፣ ርህራሄ እና ፍቅር ይኖረኝ ዘንድ እግዚአብሔር እኔን የሚቆጣጠርበት ሥፍራ ላይ ራሴን አድርጌአለሁ? 488Manuscript Releases 7:9, 1901CGAmh 238.1

    ቁጡ ለሆነ አባት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ— ወንድም ኤል፣ ልጅ ምን እንደ ሆነ እና የት እንደሚሄድ አስበው ያውቃሉ? ልጆችዎ ትናንሽ የጌታ ቤተሰብ አባላት ናቸው—ለሰማይ እንድታሰለጥኗቸው እና እንድታስተምሯቸው በሰማያዊ አባታችሁ በአደራ የተሰጣችሁ ወንድሞች እና እህቶች ናቸው። ብዙ ጊዜ እንደሚያደርጉት ርህራሄ በጎደለው አያያዝ ሲይዟቸው፣ በዚህ አያያዝዎ እግዚአብሔር እርሶን ተጠያቂ እንደሚያደርገዎ አስበው ያውቃሉ? በዚህ መንገድ ልጅዎን ርህራሄ በጎደለው መልኩ መያዝ የለብዎትም። ልጅ በአምባገነናዊነት እንዲታዘዝልዎ፣ በሁኔታዎች ሁሉ በዱላ ወይም በጅራፍ ወይም በእጅ ምት ወይም ቁጥጥር ሥር እንዲውል የሚደረግ ፈረስ ወይም ውሻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ልጆች በስሜታቸው እጅግ ግልፍተኞች ስለሆኑ ህመም እንዲሰማቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው፣ ነገር ግን በጣም ብዙዎች በዚህ የስነ-ስርዓት እርምጃዎች ሁኔታዎች እንዲባባሱ ይደረጋሉ…፡፡CGAmh 238.2

    በንጹህ ህሊና በእግዚአብሔር ፊት መስገድ እና በምትሰጡት እርማት ላይ በረከቱን መጠየቅ ካልቻላችሁ በስተቀር እነርሱን ለመምታት በጭራሽ እጃችሁን አታንሱ፡፡ በልጆቻችሁ ልብ ውስጥ ፍቅርን አበረታቱ። ራስን ለመግዛት የሚጠቅመውን ከፍ ያለ እና ትክክለኛውን ምክንያት በፊታቸው አቅርቡ፡፡ አምባገነናዊ ፈቃዳችሁ ስለሆነ፣ እነርሱ ደካሞች ስለሆኑ፣ እና እናንተ ብርቱዎች ስለሆናችሁ፣ አባት ስለሆኑ እና እነርሱ ልጆች ስለሆኑ በቁጥጥራችሁ ሥር መገዛት እንዳለባቸው እንዲሰማቸው አታድርጉ፡፡ ቤተሰብዎን ለማጥፋት ከፈለጉ፣ በብሩህ ኃይል መግዛቱን ይቀጥሉ፣ በእርግጥም ይሳካልዎታል፡፡ 489Testimonies For The Church 2:259, 260.CGAmh 238.3

    የሚያስቆጣ ልጅን በጭራሽ ወዲያና ወዲህ አታናውጡት — ወላጆች ለልጆቻቸው ትክክለኛውን ትምህርት አልሰጡም። በተደጋጋሚ በልጆቻቸው ውስጥ የሚታዩ ተመሳሳይ ጉድለቶችን ያሳያሉ። እነርሱ ተገቢ ባልሆነ መንገድ ይመገባሉ፣ እናም ይህ የነርቭ ኃይላቸውን ወደ ጨጓራ ያመጣል፣ ወደ ሌሎች አቅጣጫዎች ለመስፋፋትም ኃይል አይኖራቸውም፡፡ ትዕግሥት ከማጣት የተነሳ ልጆቻቸውን በአግባቡ መቆጣጠር አይችሉም፤ ትክክለኛውንም መንገድ ሊያስተምሯቸው አይችሉም፡፡ ምናልባትም በኃይል ይይዟቸው እና ያለ ትዕግስት ይመቷቸዋል። አንድን ልጅ ወዲያና ወዲህ ማናወጥ ሁለት እርኩሳን መናፍስትን በውስጡ ሲያናውጥ፣ አንዱ ግን ወደ ውጭ ያወጣዋል ብዬ ተናግሬአለሁ፡፡ አንድ ልጅ ስህተት የሠራ እንደሆነ እርሱን ወዲያና ወዲህ ማናወጥ ነገሩን ከማባባስ የተሸለ ሌላ ውጤት የለውም። አያስተካክለውም።26estimonies For The Church 2:365.CGAmh 239.1

    በመጀመሪያ ምክርን እና ጸሎትን ይጠቀሙ— በመጀመሪያ ከልጆቻችሁ ጋር ስህተቶቻቸውን በግልጽ በማብራራት ተማከሩ፣ በእናንት ላይ ብቻ ሳይሆን በእግዚአብሔርም ላይ ኃጢአት እንደሠሩም አሳዩአቸው፡፡ ልጆቻችሁ ስሕተት በመስራታቸው በሀዘን በተሞላ ልብ፣ እነርሱን ከማረማችሁ በፊት አብራችሁ ጸልዩ። በዚያን ጊዜ የምትቀጧቸው ምቾት ስለ ነፈጓችሁ ወይም ቁጣችሁን በእነርሱ ላይ ለማፍሰስ ስለምትፈልጉ ሳይሆን ነገር ግን ከኃላፊት ስሜት የተነሳ ለጥቅማቸው መሆኑን ሲመለከቱ፤ ይወዷችኋል፣ እንዲሁም ያከብሯችኋል። 490 The Signs of the Times, April 10, 1884. CGAmh 239.2

    ምክንያታዊነት የጎደለው ሰው እንዳልሆናችሁ ይመለከቱ ዘንድ ያ ጸሎት በአእምሮአቸው ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ስሜት እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። ልጆቻችሁም ምክንያታዊነት የጎደለው ሰው እንዳልሆናችሁ ባዩ ጊዜ ትልቅ ድል አግኝታችኋል፡፡ በእነዚህ የመጨረሻ ዘመናት በቤተሰባችን ውስጥ ሊከናወን የሚገባው ሥራ ይህ ነው፡፡ 491Manuscript Releases 73, 1909.CGAmh 239.3

    በእርማት ቀውስ ውስጥ የጸሎት ውጤታማነት — ስህተት ቢሠሩ በእግዚአብሔር ቁጣ አታስፈራሯቸው፣ ነገር ግን በጸሎቶቻችሁ ወደ ክርስቶስ አቅርቧቸው፡፡ 492Manuscript Releases 27, 1893.CGAmh 240.1

    ልጆቻችሁ ላይ አካላዊ ጉዳት ከማድረሳችሁ በፊት፣ ክርስቲያን አባት ወይም እናት ከሆናችሁ ስህተት ለፈጸሙ ልጆቻችሁ ያላችሁን ፍቅር መግለፅ ትችላላችሁ፡፡ ከልጃችሁ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ስትሰግዱ፣ በሩህሩሁ ቤዛ ፊት “ሕጻናትን ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ ተው አትከልክሏቸው፣ የእግዚአብሔር መንግሥት እንደነዚህ ላሉት ናትና፡፡” ማርቆስ 10:14 የሚለውን የራሱን ቃል ታቀርባለችሁ፡፡ ያ ጸሎት መላእክትን ከጎናችሁ ያመጣል፡፡ ልጃችሁ እነዚህን ልምዶች አይረሳም እናም እርሱን ወደ ክርስቶስ በመምራት የእግዚአብሔር በረከት በእንደዚህ ዓይነት ትምህርት ላይ ያርፋል፡፡ ልጆች ወላጆቻቸው ሊረዷቸው እየሞከሩ መሆናቸውን ሲገነዘቡ ኃይላቸውን ወደ በትክክለኛው አቅጣጫ ያዞራሉ። 493Counsels to Parents, Teachers, and Students, 117, 118CGAmh 240.2

    ከእርማት ጋር በተያያዘ የግል ተሞክሮዎች— ልጆቼ በልጅነታቸው ችግር ሊፈጥሩብኝ እንደሚችሉ እንዲያስቡ በጭራሽ አልፈቀድኩላቸውም፡፡ በቤተሰቤ ውስጥ ከሌላ ቤተሰብ የሆኑ ሌሎች ልጆችን አሳድጌአለሁ፣ ነገር ግን እነዚያ ልጆች እናታቸውን ሊያቸግሩ እንደሚችሉ እንዲያስቡ በጭራሽ አልፈቀድኩላቸውም፡፡ ሻካራ ቃል ለመናገር ወይም ልጆች ላይ ትዕግሥት የለሽ ወይም ብስጩ መሆንንበጭራሽ ለራሴ አልፈቀድኩም፡፡ እኔን ለማስቆጣት በጭራሽ አንድም ጊዜ ምቹ ሁኔታ አላገኙም - አንድም ጊዜ ይህ አልሆነም፡፡ መንፈሴ በሚረበሽበት ጊዜ፣ ወይም የሚያስቆጣ ነገር በሚሰማኝ ጊዜ እንዲህ እላለሁ፣ “ልጆች፣ ይህን አሁን ለጊዜው እናቆየዋለን፣ ስለዚህ ነገር ከዚህ ይልቅ አሁን ምንም ነገር አንናገርም። ከመተኛታችን በፊት እንነጋገራለን፡፡” ለማሰብ ይህን ሁሉ ጊዜ ካገኙ በኋላ፣ አመሻሹ ላይ ይረጋጋሉ፣ እናም እኔ በጥሩ ሁኔታ እነርሱን መቆጣጠር እችል ነበር…፡፡CGAmh 240.3

    ትክክለኛ መንገድ አለ፣ የተሳሳተም መንገድ አለ። ከእነርሱ ጋር ከመናገሬ በፊት በጭራሽ ልጆቼ ላይ እጄን አላነሳሁም፤ እነርሱ ሲሰበሩ እና ስሕተታቸውን ሲያዩ (ጉዳዩን በፊታቸው ሳቀርብ እና አብሬአቸው ስጸልይ ሁልጊዜ ያን ያደርጉ ነበር)፣ እናም ሲሸነፉ (ይህንን በምሠራበት ጊዜ ይሸነፉ ነበሩ) ከዚያም በቁጥጥሬ ሥር አደርጋቸው ነበር። በጭራሽ ከዚህ ውጭ ሆነው አላገኘኋቸውም። ከእነርሱ ጋር ስጸልይ ሁላቸውም ስብርብር ብለው፣ በእጆቻቸው በአንገቴ ላይ ተጠማጥመው እና ያለቅሱ ነበር…፡፡CGAmh 240.4

    ልጆቼን በማረም ረገድ፣ በማንኛውም መንገድ ድምጼ እንኳ እንዲቀየር በጭራሽ አልፈቅድም፡፡ የሆነ ስህተት ስመለከት “ግለቱ” እስኪያበቃ ድረስ እጠብቅ ነበር፣ ከዚያም ለማሰላሰል እድል ካገኙ እና እፍረት ከተሰማቸው በኋላ እወስዳቸው ነበር፡፡ ስለ እነዚህ ነገሮች እንዲያስቡ አንድ ወይም ሁለት ሰዓት ስሰጣቸው ያፍሩ ነበር። ሁልጊዜ እሄድ እና እጸልይ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አልናገራቸውም፡፡CGAmh 241.1

    ለጥቂት ጊዜ ለራሳቸው ከተተዉ በኋላ ስለ ጉዳዩ ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ እኔም “መልካም እስከ ማታ ድረስ መቆየት አለብን” እላቸዋለሁ፡፡ በዚያን ጊዜ የጸሎት ጊዜ ይኖረን ነበር፣ ከዚያ በኋላ የእራሳቸውን ነፍሶች እንደጎዱ እና በተሳሳተ አካሄዳቸው የእግዚአብሔርን መንፈስ እንዳሳዘኑ እነግራቸዋለሁ፡፡ 494Manuscript Releases 82, 1901.CGAmh 241.2

    ለጸሎት ጊዜ ውሰዱ— ሐዘን ሲሰማኝ እና የማፍርበትን ቃላት ለመናገር ስፈተን ዝም ብዬ ከቤት ወደ ውጭ እወጣና እነዚህን ልጆች ለማስተማር እግዚአብሔር ትዕግስት እንዲሰጠኝ እለምነዋለሁ፡፡ ከዚያም ተመልሼ ሄጄ ከእነርሱ ጋር ማውራት እችልና ይህን ስህተት እንደገና እንዳያደርጉ መንገር እችላለሁ፡፡ ልጆች ለቁጣ እንዳይነሳሱ በዚህ ጉዳይ ላይ እንደዚህ ዓይነት አቋም መውሰድ እንችላለን፡፡ እኛ ምን ያህል አስቸጋሪዎች እንደ ነበርን እና በሰማዩ አባታችን እንዴት መያዝ እንደምንፈልግ በማስታወስ በርህራሄ እና በትዕግሥት መናገር አለብን። CGAmh 241.3

    አሁን እነዚህ ወላጆች መማር የለባቸው ትምህርቶች ናቸው፣ እነዚህንም ስትማሩ፣ በክርስቶስ ትምህርት ቤት ውስጥ ምርጥ ተማሪዎች ይሆናሉ፣ ልጆቻችሁም እንዲሁ ምርጥ ልጆች ይሆናሉ። በዚህ መንገድ ለእግዚአብሄር አክብሮት እንዲኖራቸው እና ህጉን እንዲጠብቁ ልታስተምሯቸው ትችላላችሁ፣ ምክንያቱም በእነርሱ እጅግ ጥሩ አስተዳደር ስለሚኖራችሁ እና ይህን በማድረጋችሁ ማህበረተሰቡ ውስጥ በዙሪያቸው ላሉ ሁሉ በረከት የሚሆኑ ልጆችን እያሳደጋችሁ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሠራተኞች እንዲሆኑ ብቁ እያደረጋችኋቸው ነው፡፡ 495Manuscript Releases 19, 1887CGAmh 241.4

    የእርማት የሕመም ስሜትን ደስታ ሊከተል ይችላል— እውነተኛው የፈተና አያያዝ መንገድ ማምለጥ ሳይሆን እሱን መለወጥ ነው፡፡ ይህ ለሁሉም እርማቶች፣ ለቀድሞውም ሆነ ለኋለኛውም ያገለግላል፡፡ የልጅ የልጅነት ሥልጠና ቸልተኛነት ቸልተኝነት ማሳየት፣ እና የተሳሳቱ ዝንባሌዎችን ዘወትር ማበርታት፣ የኋለኞቹን ትምህርት የበለጠ ከባድ ያደርገዋል፣ እናም የተግሣጽ ሂደቱንም ብዙውን ጊዜ ህመም ያለበት ያደርገዋል። ተፈጥሮአዊ ፍላጎቶችን እና ዝንባሌዎችን በሚጻረርበት ጊዜ፣ ለተዋረደ ተፈጥሮ ሕመም ያለው ይሆናል፤ ነገር ግን ህመሙ ከፍ ባለ ደስታ ሊረሳ ይችላል፡፡ CGAmh 242.1

    ድል የተነሳ እያንዳንዱ ስህተት፣ እያንዳንዱ ጥፋት፣ እያንዳንዱ ችግር፣ ለተሻለ እና ከፍ ወዳሉ ነገሮች የመራመጃ ድንጋይ እንደሚሆን ልጅ እና ወጣቱ ይማሩ። ሕይወት ለሕያዋን ዋጋ እንዲኖረው ያደረጉ ሰዎች ስኬትን ያገኙት በእነዚያ ተሞክሮዎች አማካይነት ነው፡፡33Education, 295, 296CGAmh 242.2

    መለኮታዊ መመሪያ መጽሃፍን ይከተሉ— ልጆቻቸውን በትክክል ማሰደግ የሚፈልጉ ወላጆች ከቤት ሥልጠና ጋር በተያያዘ ፍትሃዊነትን ያሳዩ ዘንድ ከሰማይ ጥበብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ 496Pacific Health Journal, January, 1890.CGAmh 242.3

    በልጆች አያያዝ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ነው፡፡ እዚህ ጋር፣ ወላጆች ከፈለጉ፣ ስህተት እንዳይሰሩ ለልጆቻቸው ትምህርት እና ስልጠና ተለይተው የተቀመጡ ትምህርቶችን ሊያገኙ ይችላሉ…፡፡ ወላጆች ይህን የመመሪያ መጽሐፍ ሲከተሉ፣ ከመጠን በላይ ፍላጎትን ማርካትን ከመስጠት ይልቅ፣ ብዙውን ጊዜ የተግሳጽን በትር ይጠቀማሉ፤ ስህተቶቻቸውን፣ ጠማማ ስሜቶቻቸውን ለማየት አይነ ስውር ከመሆን እና ለእነርሱ ባህሪይ ብቻ ከመኖር ይልቅ፣ ግልጽ ማስተዋል ይኖራቸዋል፣ እነዚህንም ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ብርሃን ይመለከታሉ። ልጆቻቸውን በትክክለኛው መንገድ ማዘዝ እንዳለባቸው ያውቃሉ። 497Manuscript Releases 57, 1897.CGAmh 242.4

    እግዚአብሔር ዓመፀኞችን ወደ መንግሥቱ ሊወስድ አይችልም፤ ስለዚህ ለሕግጋቱ መታዘዝን እንደ ልዩ መጠይቅ ያደርገዋል። ወላጆች ጌታ ምን እንደሚናገር ልጆቻቸውን በትጋት ማስተማር አለባቸው። ከዚያም እግዚአብሔር በሕዝቡ ዙሪያ ከላለን እንደሚገነባ ለመላእክት እና ለሰዎች ያሳያል፡፡ 498Manuscript Releases 64, 1899.CGAmh 242.5

    የእናንተ ድርሻ እና የእግዚአብሔር ድርሻ— ወላጆች፣ ሀላፊነታችሁን በተቻላችሁ መጠን በታማኝነት ስትወጡ፣ እንግዲያው እናንተ ማድረግ የማትችሏቸውን ጌታ ለልጆቻችሁ እንዲያደርግ በእምነት ልትጠይቁት ትችላላችሁ።499The Signs of the Times, February 9, 1882 CGAmh 243.1

    ለልጆቻችሁ በታማኝነት ሀላፊነታችሁን ከተወጣችሁ በኋላ እነርሱን ወደ እግዚአብሔር ይዛችሁ በመምጣት እንዲረዳችሁ ጠይቁት፡፡ የራሳችሁን ድርሻ እንደሰራችሁ ንገሩት፣ ከዚያም ማድረግ የማትችሏቸውን እግዚአብሔር እንዲሰራ በእምነት ጠይቁ፡፡ ባህሪያቸውን እንዲያለዝብ፣ በቅዱስ መንፈሱ ጨዋ እና ትሁት እንዲያደርጋቸው ጠይቁት። እርሱ ጸሎታችሁን ይሰማል፡፡ ለጸሎታችሁም መልስ መስጠትን ይወዳል፡፡ ልጆቻችሁን እንድታስተካከሉ፣ “በማልቀሳቸው እንዳትተውአቸው” በቃሉ በኩል አዝዞአል፣ በእነዚህ ነገሮችም ቃሉን ታዛዥነትን ማግኘት አለበት፡፡ 500The Review and Herald, September 19, 1854.CGAmh 243.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents