Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 14—የአካል ብቃትን ጠብቆ መንከባከብ

    ምዕራፍ 61—የቤት አስተዳዳሪ በማዕድ ቤት ውስጥ*Note:Counsels on Diet and Foodspresents detailed counsels on the whole food question.

    የቤት አስተዳዳሪ ከፍተኛ ጥሪ— ከቤት ሥራ የበለጠ አስፈላጊ ሥራ ሊኖር አይችልም፡፡ በደንብ ማብሰል፣ በሚማርክ ሁኔታ የምግብ ጠረጴዛ ላይ ጤናማ ምግብ ማቅረብ ብልህነት እና ልምድን ይጠይቃል፡፡ ጨጓራችን ውስጥ የሚቀመጠውን፣ የአካል ስርዓትን ለመመገብ ወደ ደም የሚለወጠውን ምግብ የሚዘጋጅ ሰው እጅግ አስፈላጊ እና ከፍ ያለ ቦታ ይይዛል፡፡1Testimonies For The Church 3:158.CGAmh 351.1

    ከዕለት ተዕለት ሥራዎች ጋር በደንብ መተዋወቅ ለእያንዳንዱ ወጣት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ አንዲት ወጣት በፈረንሣይኛ እና በአልጄብራ ወይም በፒያኖ ዕውቀት እንኳ ልትታደል ትችላለች፤ ነገር ግን ጥሩ ዳቦ መሥራት፣ በጥሩ ሁኔታ ገጣሚ የሆኑ ልብሶችን ማዘጋጀት፣ እንዲሁም የቤት ሥራን የሚመለከቱ ብዙ ሥራዎችን በብቃት ለመወጣት መማሩ በጣም አስፈላጊ ነው።CGAmh 351.2

    ለመላው ቤተሰብ ጤና እና ደስታ በምግብ አበሳሰል በኩል ካለው ችሎታ እና ብልህነት የበለጠ አስፈላጊ ነገር የለም። በጥሩ ሁኔታ ያልተዘጋጀች፣ ጤናማ ያልሆነ ምግብ የጎልማሳውን ጠቃሚነትም ሆነ የልጅን እድገት ሊያደናቅፍ አልፎ ተርፎም ሊያጠፋ ይችላል፡፡ ወይም ከሰውነት ፍላጎቶች ጋር የተጣጣመ ምግብ በማቅረብ እና በተመሳሳይ ጊዜ የሚማርክ እና የሚጥም በማድረግ በተሳሳተ አቅጣጫ እንደምታደርገው ሁሉ በትክክለኛው አቅጣጫም ብዙ ማከናወን ትችላለች፡፡ ስለዚህ፣ በብዙ መንገዶች፣ የሕይወት ደስታ ከተራ ኃላፊነቶች ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ 2Education, 216.CGAmh 351.3

    የምግብ ዝግጅት ሳይንስ አስፈላጊ ሥነ-ጥበብ ነው፡፡—የምግብ ዝግጅት ሳይንስ አንድ ትንሽ ጉዳይ አይደለም…፡፡ ይህ ሥነ ጥበብ ከህይወት ጋር በጣም የተቆራኘ ስለሆነ ከሁሉም ስነ-ጥበባት እጅግ ዋጋ ያለው ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል፡፡ የበለጠ ትኩረት ማግኘት አለበት፤ ምክንያቱም የአካል ሥርዓት ጥሩ ደም ለመሥራት ጥሩ ምግብ ይፈልጋል፡፡ ሰዎች በጤንነት እንዲጠበቁ የሚያደርጋቸው መሠረቱ ጥሩ ምግብ የማብሰል የሕክምና የወንጌል አገልግሎት ሥራ ነው፡፡ CGAmh 352.1

    ብዙውን ጊዜ የጤና ተሃድሶ በማይጥም የምግብ አዘገጃጀት የጤና ጉድለት እንዲሆን ይደረጋል፡፡ የጤና ተሃድሶ ስኬታማ ከመሆኑ በፊት የጤናማ ምግብ አዘገጃጀትን በተመለከተ ያለው የእውቀት ማነስ መታረም አለበት፡፡CGAmh 352.2

    የጥሩ ምግብ አዘጋጆች ጥቂት ናቸው፡፡ ብዙ፣ እናቶች ለቤተሰብ በደንብ የተዘጋጀ እና በጥሩ ሁኔታ የተሰናዳ ምግብ ማቅረብ ይችሉ ዘንድ የምግብ አዘገጃጀት ትምህርት መውሰድ አለባቸው። 705Counsels on Diet and Foods, 263.CGAmh 352.3

    የኪነ-ጥበባት እመቤት መሆንን እሹ—እህቶቻችን ብዙውን ጊዜ የምግብ አዘገጃጀትን አያውቁም። ለእንደዚህ ዓይነቶቹ እንዲህ እላለሁ፣ በአገሪቱ ውስጥ ወደምትገኝ እጅግ ጥሩ የምግብ አዘጋጅ ጋር እሄድ እና የኪነ ጥበብ እመቤት— አስተዋይ፣ ችሎታ ያላት የምግብ አዘጋጅ እስከምሆን ድረስ ለሳምንታት እዚያው እቆያለሁ፡፡ አርባ ዓመት ቢሆነኝም እንኳ ይህንን መንገድ እከተላለሁ፡፡ የምግብ አዘገጃጀትን ማወቅ የእናንተ ግዴታ ነው፣ እንዲሁም ሴቶች ልጆቻችሁን ስለ ምግብ አዘገጃጀት ማስተማር የእናንተ ግዴታ ነው፡፡ 706Testimonies For The Church 2:370.CGAmh 352.4

    ጥናት እና ልምምድ — ምግብ ቀላል ባለ እና ጤናማ በሆነ ሁኔታ ሊዘጋጅ ይችላል፣ ነገር ግን የሚጣፍጥ እና ገንቢ እንዲሆን ለማድረግ ክህሎት ይጠይቃል። ሴቶች የምግብ አዘገጃጀትን ለመማር ማጥናት እና ከዚያም የተማሩትን በትዕግስት በተግባር ላይ ማዋል አለባቸው፡፡ ሰዎች ይህንን ለማድረግ መቸገር ስለማይወስዱ እየተሰቃዩ ነው፡፡ ለእንደነዚህ አይነቶቹ እንዲህ እላለሁ፣ ዋልጌ ኃይሎቻችሁን የምታንቀሳቅሱበት እና ለራሳችሁ የምትነግሩበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ ጤናማ፣ ጥሩ ጣዕም ያለው ምግብ ለማዘጋጀት የተሟላ እውቀትና ልምድ ለማግኘት ያዋለ ጊዜ እንደ ባከነ አትቁጠሩ፡፡ በምግብ አዘገጃጀት ላይ ምንም ያህል ልምድ ቢኖራችሁ፣ አሁንም የቤተሰብ ኃላፊነቶች ካለባችሁ፣ እነርሱን እንዴት በአግባቡ መንከባከብ እንደምትችሉ መማር የእናንተ ግዴታ ነው። 707Christian Temperance and Bible Hygiene, 49.CGAmh 352.5

    ልዩ ልዩ አይነት ማድረግ እና ቀለል ያለ ዘይቤን መከተል አስፈላጊ ናቸው—ምግቦቹ የተለያዩ መሆን አለባቸው፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የተዘጋጁ ተመሳሳይ ምግቦች ከምግብ ሰዓት ሁሉ እና በየቀኑ በምግብ ጠረጴዛው ላይ መታየት የለባቸውም፡፡ ምግብ ልዩ ልዩ አይነት ሲሆን ምግቦቹ በታላቅ ደስታ ይበላሉ፣ የአካልም ሥርዓት በተሻለ ሁኔታ ይመገባቸዋል።708The Ministry of Healing, 300. CGAmh 353.1

    ሰውነታችን የተገነባው ከምንበላው ነገር ነው፤ እና ህብረ ህዋሳት ጥሩ ጥራት ያላቸው ለማድረግ ትክክለኛውን አይነት ምግብ ሊኖረን ይገባል፣ እናም ከአካል ስርዓት ፍላጎቶች ጋር በተሻለ ሁኔታ እንዲስማማ በሚያስችል ችሎታ መዘጋጀት አለበት። ምግብ የሚጥም እና ጤናማ ይሆን ዘንድ ጤናማ ምግቦችን በልዩ ልዩ አይነት መንገድ እንዴት እንደሚዘጋጅመማር ሃይማኖታዊ ግዴታ ነው፡፡ 709Christian Temperance and Bible Hygiene, 48, 49.CGAmh 353.2

    በምግብ ገበታ መሳናዶ ላይ እንኳን፣ ፋሽን እና ታይታ አስቀያሚ ተጽዕኖአቸውን ያሳድራሉ፡፡ ጤናማ የሆነ የምግብ ዝግጅት ሁለተኛ ጉዳይ ሆኗል፡፡ እጅግ ብዙ የተለያዩ ምግቦችን ማቅረብ ምንም ጥሩ ውጤት ሳያመጣ ጊዜን፣ ገንዘብን እና ጉልበትን ያባክናል። በአንድ የምግብ ክፍል ጊዜ ግማሽ ደርዘን ምግብ መውሰዱ ፋሽን ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ባህሉ ለጤና ጎጂ ነው፡፡ አስተዋይ ወንዶች እና ሴቶች በተግባርና በምሳሌ ሊያወግዙት የሚገባ ፋሽን ነው ...፡፡ የምግብ ገበታ ዝግጅቶች የበለጠ ቀላል ያለ ቢሆን ለቤተሰብ ጤና ምን ያህል የተሻለ በሆነ ነበር!8Christian Temperance and Bible Hygiene, 73.CGAmh 353.3

    የደካማ የምግብ ዝግጅት ውጤቶች—ደካማ የምግብ ዝግጅት በሺዎች የሚቆጠሩትን የሕይወት ኃይላቸውን እየደከመ ነው፡፡ ብዙዎች ከሚያስተውሉት በላይ ብዙ ሰዎች ከዚህ ምክንያት ይጠፋሉ፡፡ ይህ የአካል ስርዓትን በማበላሸት በሽታን ያስከትላል፡፡ በዚህ መንገድ በተፈጠረው ሁኔታ ሰማያዊ ነገሮች በቀላሉ ተለይተው ሊታወቁ አይችሉም። 710Christian Temperance and Bible Hygiene, 49.CGAmh 353.4

    አነስተኛ እና በደንብ ያልበሰለ ምግብ ደም ሰጭ አካላትን በማዳከም ደምን ያረክሳል፡፡ ነርቮችን በማስቆጣት እና በመጥፎ አመሎች በመታጀብ የአካል ስርዓትን ያዛባ እና በሽታን ያመጣል፡፡ ለደካማ የምግብ አበሳሰል ሰለባዎች የሆኑ በሺዎች እና በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ ከብዙ መቃብሮች ላይ “በደካም የምግብ አበሳሰል ሳቢየ የሞተ” “በተበደለ ጨጓራ ሳቢያ የሞተ” ተብሎ ሊፃፍ ይችላል፡፡ 711The Ministry of Healing, 302.CGAmh 354.1

    ልጆቻችሁን ምግብን እንዴት ማብሰል እንዳለባቸው አስተምሯቸው— ልጆቻችሁን እንዴት ማብሰል እንደሚችሉ ከማስተማር ቸል አትበሉ፡፡ ይህን ሲታደርጉ በሃይማኖታዊ ትምህርታቸው ሊኖሯቸው የሚገቡ መርሆዎችን እየሰጣችኋቸው ነው፡፡ ለልጆቻችሁ የሥነ-አካል ትምህርቶችን በመስጠት እና ቀለል ባለ መንገድ ሆኖም ግን በክህሎት እንዴት ማብሰል እንደሚችሉ ሲታስተምሯቸው በጣም ጠቃሚ ለሆኑት የትምህርት ዘርፎች መሠረት እየጣላችሁ ነው፡፡ ጥሩ ቀለል ያለ ዳቦ ለማዘጋጀት ችሎታ ያስፈልጋል። በጥሩ ምግብ አበሳሰል ውስጥ ሃይማኖት አለ፣ እና ያ ምግብ ማብሰልን ለመማር በጣም ቸልተኛ እና ግድየለሽ የሚሆነው ክፍል ሃይማኖት ጥያቄ ውስጥ እንዳለ ይሰማኛል፡፡ 712Testimonies For The Church 2:537.CGAmh 354.2

    በትዕግስት እና በደስታ አስተምሯቸው— እናቶች ሴት ልጆቻቸው ገና በጣም ትናንሽ ሆነው ሳሉ ወደ ማእድ ቤት ይዘዋቸው መሄድ እና የማብሰል ጥበብን ማስተማር አለባቸው፡፡ እናት ሴት ልጇን ያለ ትምህርት የቤት አያያዝ ምስጢሮችን እንዲገነዘቡ መጠበቅ የለባትም፡፡ በትዕግስት፣ በፍቅር፣ እና በደስታ ገጽታ እና በአበረታች ቃሏ ስራውን የቻለችውን ያህል ምቹ ማድረግ አለባት። 713Testimonies For The Church 1:684.CGAmh 354.3

    አንድ ጊዜ፣ ሁለት ጊዜ ወይም ሦስት ጊዜ ቢያቅታቸው አታውግዙአቸው፡፡ ቀድሞውኑ ተስፋ መቁረጥ ሥራውን እየሰራ እና “ምንም ጥቅም የለውም፤ እኔ ይህን መስራት አልችልም” እንዲሉ ይፈትናቸዋል፡፡ ይህ የተግሳጽ ጊዜ አይደለም፡፡ ፍላጎት እየተዳከመ ነው፡፡ “ያደረጋችኋቸውን ስህተቶች በጭራሽ አታስቡ፡፡ እናንተ ገና ተማሪዎች ናችሁ፣ ስህተቶችን መስራትን የሚጠበቅ ነው፡፡ እንደገና ሞክሩ፡፡ አዕምሮአችሁን በስራችሁ ላይ አድርጉ፡፡ በጣም ተጠንቀቁ፣ በእርግጥም ይሳካላችኋል፡፡” የሚሉ የማበረታቻ፣ የደስታ እና የተስፋ ቃላትን ይፈልጋሉ። 714Testimonies For The Church 1:684, 685.CGAmh 355.1

    ፍላጎት እና ጉጉት እንዴት እንደሚቀዘቀዝ — ብዙ እናቶች የዚህን የእውቀት ዘርፍ አስፈላጊነት አይገነዘቡም፣ በመሆኑም ልጆቻቸውን ከማስተማር እና በሚማሩበት ጊዜ ስህተቶቻቸውን እና ጉድለቶቻቸውን በመታገስ ችግር እና ሐሳብ ውስጥ ከመግባት ይልቅ ሁሉንም ነገር እራሳቸው መስራትን ይመርጣሉ። እንዲሁም የሴት ልጆቻቸው ጥረቶች ሳይሳካላቸው ሲቀር “ምንም ጥቅም የለውም፣ ይህንን ወይም ያንን ማድረግ አችሉም፡፡ ከምትረዱኝ በላይ ግራ እያጋባችሁኝ እና ችግር እየፈጠራችሁብኝ ነው” በማለት ይሸኟቸዋል፡፡ CGAmh 355.2

    በዚህ መንገድ የተማሪዎቹ የመጀመሪያ ጥረቶች ውድቅ ይደረጋሉ፣ እናም የመጀመሪያው ውድቀት የመማር ፍላጎታቸውን እና ጉጉታቸውን ከማቀዘቅቀዙ የተነሳ ሌላ ሙከራ ማድረግን በመፍራት ስፌት፣ ሹራብ መስራት፣ ቤትን ማጽዳት እና ምግብን ከማብሰል ውጭ ሌለ ማንኛውንም ነገር ለመስራት ሀሳብ ያቀርባሉ። እዚህ ጋር እናት በጣም ጥፋተኛ ነች፡፡ በተግባር በመለማመድ ፍርሃትን የሚያስወግድ እና ልምድ የሌለውን ሰራተኛ ብልሃት የጎደለውን እንቅስቃሴ የሚያስተካክል ልምድ እንኪያገኙ ድረስ በትዕግስት መምከር ነበረባት፡፡14Testimonies For The Church 1:685.CGAmh 355.3

    ወጣት ሴቶች ለተግባራዊ ሕይወት ማድረግ የሚችሉት በጣም አስፈላጊው ዝግጅት— ወጣት ሴቶች በምግብ ማብሰል ረገድ በደንብ መማር ይገባቸዋል፡፡ በሕይወታቸው ውስጥ ያሉባቸው ሁኔታዎች ምንም ሊሆኑ ቢችሉም እንኳ ተግባራዊ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል እውቀት እዚህ አለ፡፡ ይህ በሰው ሕይወት ላይ በተለይም በጣም ተወዳጅ በሆኑት ሰዎች ሕይወት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ያለው የትምህርት ዘርፍ ነው፡፡ 715Testimonies For The Church 1:683, 684.CGAmh 355.4

    እኔ ለልብስ ሰፊዎቼ ዋጋ እሰጣለሁ፤ የቅጂ ሥራዬን ለሚሰሩት ዋጋ እሰጣለሁ፤ ነገር ግን እንዴት አድርጎ ሕይወትን ለማቆየት እና አንጎልን፣ አጥንትን እና ጡንቻን ለመመገብ የሚችለውን ምግብን ጠንቅቆ የሚያውቁ የምግብ አዘጋጆቼ ከቤተሰቤ ረዳቶች መካከል በጣም አስፈላጊውን ክፍተት የሚሸፍኑ ናቸው፡፡16Testimonies For The Church 2:370.CGAmh 356.1

    ወጣት ሴቶች ምግብ ማብሰል እና ሌሎች የቤት ውስጥ ሥራዎችን ማከናወን ዝቅተኛ ሥራ እንደሆነ ያስባሉ፤ እንዲሁም በዚህ ምክንያት፣ ያገቡ እና የቤተሰብ ኃላፊነት ያላቸው ብዙ ልጃገረዶች በሚስት እና በእናት ላይ ስለሚያርፉ ግዴታዎች ብዙም ግንዛቤ የላቸውም፡፡ 716The Ministry of Healing, 302.CGAmh 356.2

    በዚህ መንገድ በከንቱነት እና በመጥፎ ምግባር ላይ ምሽግን ይገንቡ— [ለሴት ልጆቻችሁን] የምግብ አበሳሰል ጥበብን ሲታስተምሯቸው ይህ ሳይሆን ቀርቶ በዚያ ላይ ለመሳተፍ ሊፈተኑበት ከሚችሉ ከከንቱነት እና መጥፎ ስነ ምግባር የሚጠብቃቸውን ምሽግ እየገነባችሁ ነው። 717Testimonies For The Church 2:370.CGAmh 356.3

    ወንዶችም ሆኑ ሴቶች የምግብ ዝግጅትን መማር አለባቸው— ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ቀላል እና ጤናማ የሆነውን የምግብ ዝግጅትን መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ሥራቸው ብዙውን ጊዜ ጤናማ ምግብ ማግኘት በማይችሉበት ቦታ ይጠራቸዋል፤ ከዚያም የምግብ ዝግጅት እውቀት ካላቸው ለመልካም ዓላማ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡ 718The Ministry of Healing, 323.CGAmh 356.4

    ወጣት ወንዶችም ሆኑ ወጣት ሴቶች በቁጠባ እንዴት ማብሰል እንደሚችሉ እና የስጋ ምግብ ጋር የተያያዘ እያንዳንዱን ነገር ማስወገድን መማር አለባቸው፡፡ 719Counsels to Parents, Teachers, and Students, 313. CGAmh 357.1

    ስለ ቁጠባ አጥኑ፤ ብክነትን አስወግዱ— በእያንዳንዱ የምግብ አዘገጃጀት ዘርፍ ውስጥ ሊጤን የሚገባው ጥያቄ “ምግብ በጣም ተፈጥሯዊ እና ውድ ባልሆነ መንገድ እንዴት ይዘጋጃል?” የሚል ነው፡፡ እንዲሁም ትራፊ የምግብ ቁርጥራጮች እንዳይባክኑ በጥንቃቄ ማጥናት አለበት፡፡ እነዚህ የምግብ ቁርጥራጮች የማይጠፉበትን መንገድ አጥኑ፡፡ ይህ ችሎታ፣ ቁጠባ እና ዘዴ ሀብት ነው፡፡ ሞቃታማ በሆኑ ወቅቶች ላይ አነስተኛ ምግብ አዘጋጁ፡፡ ይበልጥ ደረቅ ነገርን ተጠቀሙ። ብዙ ድሃ ቤተሰቦች አሉ፣ እነርሱ ምንም እንኳን ለመብላት በቂ ምግብ ቢኖራቸውም፣ ብዙውን ጊዜ ለምን ድሃ እንደሆኑ ሊብራራላቸው ይገባል፤ ይህም በጣም ብዙ ቁርጣራጮች እና ትርፍራፊዎች ስለሚባክኑ ነው፡፡21Counsels on Diet and Foods, 258.CGAmh 357.2

    ለውይይት የሚረዱ ከባባድ ጥያቄዎች— “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት፡፡” የምግብ ገበታ ስታዘጋጁ እና ቤተሰቦቻችሁ እንዲመገቡ ስትጠሯቸው ይህንን ታደርጋላችሁ? በጣም ጥሩውን ደም እንደሚፈጥር የምታወቁትን ምግብ ብቻ ለልጆቻችሁ ፊት ታኖራላችሁን? ያ ምግብ በአነስተኛ የትኩሳት ሁኔታ የአካል ስርዓቶቻቸውን የሚጠብቅ ነውን? እርሱ ከህይወት እና ከጤንነት ጋር በተያያዘ በጣም ጥሩ ሁኔታ ላይ እንዲኖሩ የሚያደርጋቸው ነውን? በልጆቻችሁ ፊት ለማቅረብ የምታጠኑት ምግብ ይህ ነውን? ወይስ መጻኢ ጠቀሜታቸው ምንም ይሁን ምን ጤናማ ያልሆነ፣ አነቃቂ፣ የሚያስቆጣ ምግብ ትሰጧቸዋላችሁን? 720Testimonies For The Church 2:359, 360.CGAmh 357.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents