Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 8—የላቀ ጠቀሜታ ያለው ተግባር- ባህሪይን ማጎልበት

    ምዕራፍ 31—የባህሪይ አስፈላጊነት

    ከዚህ ዓለም የሚወሰድ ብቸኛው ሀብት—በመለኮታዊ አምሳያ መሠረት የተቀረጸ ባህሪይ ከዚህ ወደ ቀጣዩ ዓለም ይዘነው የምንሄድ ብቸኛው ሀብት ነው። በዚህ ዓለም በክርስቶስ መመሪያ ሥር ያሉት ሁሉ እያንዳንዱን መለኮታዊ ስኬት ከእነርሱ ጋር ወደ ሰማያዊ ቤት ይወስዳሉ፡፡ እናም በሰማይ ቤት ዘወትር እንሻሻላለን፡፡ ታዲያ በዚህ ሕይወት ውስጥ የባህሪይ እድገት ምን ያህል አስፈላጊ ነው! 280 Christ[U+0092]s Object Lessons, 332.CGAmh 152.1

    እውነተኛ ባህሪይ የነፍስ ውበት ነው—የአእምሮ ችሎታ እና ከፍተኛ ተሰጥኦ ባህሪይ አይደሉም፣ ምክንያቱም እነዚህ ብዙውን ጊዜ የመልካም ባህሪይ ተቃራኒ የሆኑ ሰዎች የሚኖራቸው ችሎታዎች ናቸው። ዝና ባህሪይ አይደለም። እውነተኛ ባህሪይ በስነ-ምግባር ራሱን የሚገልጥ የነፍስ ውበት ነው። 281The Youth’s Instructor, November 3, 1886.CGAmh 152.2

    መልካም ባሕርይ ከወርቅ ወይም ከብር የላቀ ዋጋ ያለው ሐብት ነው። እርሱም በጭንቀት ወይም በመታወክ የማይጎዳ፣ ምድራዊ ሐብቶችም ተጠራርገው ሲጠፉ፣ እርሱ ከፍተኛ ትርፍ ይዞ የሚመጣ ነው፡፡ ሐቀኝነት፣ ጽናት እና ትጋት ሁሉም በቅንነት እንዲያዳብራቸው የሚፈለግባቸው ባህሪዎች ናቸው፣ ምክንያቱም እነዚህ ባለቤቱን ማንም ሊቋቋማቸው የማይችለውን ኃይል ያላብሳሉ—ይህም ኃይል መልካም እንዲያደርግ፣ ክፉን እንዲቋቋም፣ ጠላትነትን እንዲቋቋም የሚያበረታው ኃይል ነው፡፡ 282The Youth’s Instructor, November 3, 1886.CGAmh 152.3

    ሁለቱ እጅግ አስፈላጊ መሠረታዊ ነገሮች—የባህሪይ ጥንካሬ ሁለት ነገሮችን ያካትታል— እነርሱም የፈቃድ ኃይል እና ራስን የመግዛት ኃይል ናቸው። ብዙ ወጣቶች ኃይለኛ እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ስሜትን በስህተት ጠንካራ ባህሪይ እንደሆነ ይቆጥራሉ፤ ነገር ግን እውነታው ለስሜቱ የሚገዛ ሰው ደካማ ሰው መሆኑ ነው፡፡ የሰው ታላቅነት እና ክቡርነት የሚለካው ስሜቶቹ እርሱን ለማሸነፍ ባላቸው ኃይል ሳይሆን፣ እርሱ ስሜቶቹን ለማሸነፍ ባለው ኃይል ነው፡፡ እጅግ ብርቱ ሰው ጥቃት ሲደርስበት ስሜቱን የሚገታ እና ጠላቶቹን ይቅር የሚል ሰው ነው፡፡ 283Counsels to Parents, Teachers, and Students, 222.CGAmh 152.4

    ከውጫዊ ታይታ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ነገር—ወጣቶች በአለባበስ እና በአካሄድ የዓለምን ፋሽን ለመምሰል እንደሚጥሩ የባህሪይ ውበት እና የተወዳጅ ፀባይ ባለቤት መሆን አስፈላጊ እንደሆነ ቢቆጠሩ ኖር ዛሬ በማህበረሰብ ላይ የከበረ ተጽዕኖን ለመጣል አንድ ሰው ወደ ትግበራ የሕይወት መድረክ በሚመጣ ፋንታ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ባየን ነበር፡፡284Fundamentals of Christian Education, 69. CGAmh 153.1

    እድገት የዕድሜ ልክ ተግባር ነው—የባህሪይ ግንባታ የዕድሜ ልክ ተግባር ነው፣ ዘላለማዊም ነው። ሁሉም ይህንን ቢገነዘቡ፣ በግለሰብ ደረጃ የዘለአለም ህይወትን ወይም የዘለአለም ጥፋት እዳላችንን እንደምንወስን ቢነቁ ኖሮ እንዴት ያለ ለውጥ በመጣ ነበር! ይህ የአመክሮ ጊዜ ምን ያህል የተለየ በሆነ፣ ዓለማችንንም እንዴት ያለ የተለየ ባህሪይ በሞላት ነበር! 285The Youth’s Instructor, February 19, 1903. CGAmh 153.2

    ልማት እና እድገት—የዘሩ መብቀል የመንፈሳዊ ሕይወት ጅምርን ይወክላል፣ እንዲሁም የእፅዋቱ እድገት የባህሪይ እድገት መገለጫ ነው። እድገት የሌለው ሕይወት ሊኖር አይችልም፡፡ ተክሉ ማደግ ወይም መሞት አለበት። እድገቱ ድምጽ አልባ እና በአይን ሊታይ የማይችል፣ ነገር ግን ቀጣይነት ያለው እንደሆነ ሁሉ፣ የባህሪይ እድገትም እንዲሁ ነው። በማንኛውም የእድገት ደረጃ ሕይወታችን ፍጹም ሊሆን ይችላል፤ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ዓላማ የተፈጸመ እንደሆነም የማያቋርጥ እድገት ይኖራል፡፡7Education, 105, 106.CGAmh 153.3

    እርሱ የሕይወት መከር ነው—የሕይወት መከር ባህሪይ ነው፣ ለዚህም ሆነ የሚመጣውን ሕይወት ዕጣ ፈንታ የሚወስነውም ይህ ነው። መከሩ የተዘራው ዘር መባዛት ነው፡፡ እያንዳንዱ ዘር እንደየወገኑ ፍሬ ያፈራል። የምንወዳቸውም ባህሪዎችም እንዲሁ ናቸው፡፡ የራስ ወዳድነት፣ ስስታምነት ፣ ልቅ ፍላጎቶችን ማርካት፣ እራሳቸውን ያባዛሉ፤ መጨረሻውም ጉስቁልና እና ጥፋት ነው፡፡ “በገዛ ሥጋው የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፣ በመንፈስ ግን የሚዘራ ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።” ገላትያ 6: 8፡፡ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ እና ደግነት የበረከት ፍሬ፣ የማይጠፋም መከር ናቸው፡፡ 286Pacific Health Journal, June, 1890.CGAmh 153.4

    ታላቁ የክርስትና ማስረጃ—ክርስቲያን እናቶች የባህሪይ ሐቀኝነት፣ ጽኑ መርኾዎች እና ጥሩ ግብረ-ገብ ያላቸውን ልጆች ለህብረተሰቡ ቢለግሱ ከሁሉም የሚስዮናዊነት ስራዎች የላቀ አስፈላጊነት ያለውን ሥራ ይሰራሉ፡፡ በኅብረተሰቡ ውስጥ ቦታቸውን እንዲይዙ በደንብ የተማሩ ልጆቻቸው ለዓለም ሊሰጥ ከሚችል የክርስትና እምነት ትልቁ ማስረጃ ናቸው፡፡ 287Pacific Health Journal, June, 1890.CGAmh 154.1

    በአግባቡ የሰለጠነ የአንድ ልጅ ተፅእኖ—ባህሪይን ከመቅረጽ በላይ ሟች ለሆኑ ሰብአዊ ሰዎች የተሰጠ ከፍተኛ ስራ የለም፡፡ ልጆች እንዲማሩ ብቻ ሳይሆን ስልጠናም ጭምር ያስፈልጋቸዋል፤ እንዲሁም በዕድገት ላይ ስላለ ልጅ ወይም ወጣት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ማን ሊናገር ይችላል? በልጆችዎ ባህሪይ ላይ ከፍተኛ እንክብካቤ ይደረግ፡፡ በእውነት መርሆዎች መሰረት በአግባቡ የሰለጠነ፣ እግዚአብሔርን መፍራትና መውደድ ከባህሪይው ጋር የተሸመነ አንድ ልጅ፣ በዓለም ውስጥ መልካም ለማድረግ ሊገመት የማይችል ኃይል ባለቤት ይሆናል።288The Signs of the Times, July 13, 1888CGAmh 154.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents