Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 12—የአዕምሮ ችሎታዎች ዕድገት

    ምዕራፍ 50—እውነተኛ ትምህርት ምን ምን ያካትታል?

    የእውነተኛ ትምህርት ስፋቱ — እውነተኛ ትምህርት ማለት የተወሰኑ ትምህርቶችን ከመማር የላቀ ነው፡፡ ሰፋ ያለ ነው፡፡ የአካል ኃይሎች እና የአዕምሮ ችሎታዎች ሁሉ ቅንጅታዊ እድገትን ያካትታል። እግዚአብሔርን መውደድ እና መፍራትን ያስተምራል እንዲሁም የህይወት ግዴታዎች በታማኝነት ለመወጣት ዝግጁ የሚያደርግ ነው። 566Counsels to Parents, Teachers, and Students, 64.CGAmh 276.1

    እውነተኛ ትምህርት የአእምሮ ስርዓትን ብቻ ሳይሆን፣ መልካም ግብረ-ገብን እና ትክክለኛ ጸባይን የሚያስገኝ ስልጠናን የሚያካትት ነው፡፡ 567Counsels to Parents, Teachers, and Students, 331.CGAmh 276.2

    በሁሉም ትምህርት ውስጥ የመጀመሪያው ታላቅ ትምህርት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እና መረዳት ነው፡፡ ይህንን እውቀት ለማግኘት መደረግ ያለበትን ጥረት በየዕለቱ ሕይወት ውስጥ ማምጣጥ አለብን፡፡ ሳይንስን በሰዎች ትርጓሜ ብቻ መማር የሐሰትን ትምህርት ማግኝት ነው፣ ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር እና ስለ ክርስቶስ መማር የሰማይን ሳይንስ መማር ነው፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ እና እውቀት ከፍ ስላልተደረገ በትምህርት ውስጥ ግራ መጋባት ተፈጥሯል፡፡ 568 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 447.CGAmh 276.3

    የራስ ወዳድነት እና የስግብግብነት ተቃራኒ ተፅእኖ— እንዲህ ባለ ጊዜ የሚሰጠው የትምህርት አዝማሚያ ምን ይመስላል? ብዙውን ጊዜ ወደ የትኛው ዓለማ ነው ስበት የሚያደርገው? ወደ ራስ ወዳድነት ነው፡፡ ከሚሰጠው ትምህርት አብዛኛው ስሙን የሚጻረር ነው። በእውነተኛ ትምህርት ውስጥ የአለማችን እርግማን የሆነውን የራስ ወዳድነት ምኞት፣ ለሥልጣን መስገብገብ፣ ለሰብአዊ መብቶች እና ችግሮች ግድየለሽ መሆን፣ ተቃራኒ ተጽዕኖን ያገኛል፡፡ የእግዚአብሔር የሕይወት እቅድ ለሁሉም የሰው ልጆች ቦታ አለው፡፡ እያንዳንዱ ሰው መክሊቱን የተቻለውን ያህል ማሻሻል አለበት፤ ይህንንም በማድረግ ውስጥ ያለው ታማኝነት ስጦታዎቹ ይነስም ይብዛ አንድን ሰው እንዲከብር ብቁ የሚያደርጉ ናቸው። CGAmh 276.4

    በእግዚአብሔር ዕቅድ ውስጥ ለራስ ወዳድነት ጠብ ቦታ የለም፡፡ እራሳቸውን ከራሳቸው ጋር የሚያመዛዝኑ፣ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር የሚያስተያዩ ጥበበኞች አይደሉም፡፡ (2 ቆሮንቶስ 10: 12) የምናደርገው ነገር ሁሉ “እግዚአብሔር በሚሰጠን ኃይል” መሆን አለበት። 1ኛ ጴጥሮስ 4፡11፡፡ ይህ “ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ ሁሉ በትጋት አድርጉ፡፡ ከጌታ የርስቱን ብድራት እንድትቀበሉ ታውቃላችሁና፤ የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና፡፡” ቆላስይስ 3:23, 24፡፡ የሚደረገው አገልግሎት እና እነዚህን መርኾዎች በመፈፀም የሚገኘው ትምህርት የከበረ ነው። ነገር ግን አሁን የሚሰጠው ትምህርት ምንኛ ሰፊ ልዩነት ያለው ነው! ይህ ከልጁ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ የክፋት ሁሉ ሥር የሆነውን ማስመሰል እና ተቀናቃኝነት እንዲጎመጅ ያደርጋል፤ ራስ ወዳድነትን ያበረታታል። 569Education, 225, 226.CGAmh 277.1

    ምሳሌ በኤደን ውስጥ ተሰጥቷል — በዓለም መጀመሪያ ላይ የተቋቋመው የትምህርት ስርዓት ለዘላለም ለሰው ምሳሌ መሆን አለበት፡፡ የትምህርት ቤትን መርኾዎችን ለማሳየት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን መኖሪያ በኤደን ውስጥ እንደ ምሳሌ ተቋቁሟል። የኤደን የአትክልት ስፍራ የትምህርት ቤት ክፍል፣ ተፈጥሮ የመማሪያ መጽሐፍ፣ ፈጣሪ ራሱ አስተማሪ ነበር፡፡5Education, 20.CGAmh 277.2

    በዋናው መምህር ምሳሌው ተሰጠ — በደቀመዛሙርቱ ስልጠና አዳኙ በመጀመሪያ የተቋቋመውን የትምህርት ስርዓት ተከትሏል። መጀመሪያ የተመረጡ አሥራ ሁለቱ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍላጎታቸውን ሲያገለግል ስለነበር ከእርሱ ጋር የተቆራኙ ሌሎች ጥቂቶች ጋር፣ የኢየሱስ ቤተሰብ ሆነዋል። እነርሱ በቤት፣ በምግብ ገበታ፣ በእልፍኝ ውስጥ እና በሜዳ ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ በጉዞው ላይ አብረውት ይጓዙ ነበር፣ ፈተናውን እና መከራውን ተካፍሉ፣ እናም በመካከላቸውም በቆየበት ጊዜ ወደ እርሱ ሥራ ገበተዋል። CGAmh 277.3

    አንዳንድ ጊዜ ተራራ አጠገብ ሲቀመጡ፣ አንዳንድ ጊዜ በባህር ዳር፣ ወይም ከዓሳ አጥማጁ ጀልባ ላይ፣ አንዳንድ ጊዜ በመንገድ ላይ ሲጓዙ ያስተምሯቸው ነበር። ለሕዝቡ በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ ደቀመዛሙርቱ ይከቡት ነበር፡፡ ከትምህርቱ ምንም እንዳያመልጣቸው ወደ እርሱ እጅግ ይጠጉ ነበር፡፡ በሁሉም አገር ለዘመናት ሁሉ ሊያስተምሩ የሚገባቸውን እውነቶች ለመረዳት በመጓጓት ትጉ አድማጮች ነበሩ። 570 Education, 84, 85.CGAmh 278.1

    እውነተኛ ትምህርት ተግባራዊ እና ሥነጽሁፋዊ ነው— በልጅነት እና በወጣትነት ጊዜ ተግባራዊ እና ሥነ-ፅሁፍ ስልጠና አንድ ላይ የተጣመረ እና አዕምሮም በእውቀት የተሞላ መሆን አለበት…፡፡CGAmh 278.2

    ልጆች በቤት ውስጥ ተግባራት ውስጥ ድርሻ እንዳላቸው መማር አለባቸው፡፡ መስራት በሚችሉት ትናንሽ ነገሮች አባትና እናትን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ሊማሩ ይገባል፡፡ አእምሯቸው ማሰብ እንዲችል፣ ትውስታቸው የተሰጣቸውን ሥራ በማስታወስ የተጠመደ እንዲሆን መሰልጠን አለበት፤ እና ቤት ውስጥ ፋይዳ የመስጠት ልማዶች ስልጠና ውስጥ፣ ከእድሜያቸው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ተግባራዊ ስራዎችን በመማር ላይ ናቸው፡፡ 571Fundamentals of Christian Education, 368, 369.CGAmh 278.3

    ይህ የወጣት ተፈጥሮአዊ ምርጫ አይደለም — ወጣቱን ለተግባራዊ ህይወት ብቁ የሚያደርግ ዓይነት የትምህርት፣ እነርሱ በተፈጥሮ አይመርጡትም። ምኞቶቻቸውን፣ የሚወዷቸውን እና የሚጠሏቸውን፣ ምርጫዎቻቸውን እና ዝንባሌዎቻቸውን አጥብቀው ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን ወላጆች ስለ እግዚአብሔር ስለ እውነት እና በልጆቻቸው ዙሪያ ስላሉ ተጽዕኖዎች እና ጓደኞች ትክክለኛ እይታ ካላቸው፣ እግዚአብሔር የሰጣቸው ልምድ የሌላቸውን ወጣቶችን የመምራት ኃላፊነት በእነርሱ ላይ እንደሚያርፍ ይሰማቸዋል። 572Counsels to Parents, Teachers, and Students, 132.CGAmh 278.4

    የህይወት ሸክሞችን ከመሸከም የማምለጫ ዘዴ አይደለም—ትምህርት ዓላማው ለህይወት ደስ የማይሉ ሥራዎችን እና ከባድ ሸክሞችን እንዴት ማምለጥ እንደሚችሉ ማስተማር እንዳልሆነ፤ ዓላማው የተሻሉ ዘዴዎችን እና የላቀ ዓላማዎችን በማስተማር ስራቸውን ማቃለል እንደሆነ ወጣቶች ይገዘንዘቡ፡፡ የህይወት እውነተኛ ዓላማ ለእራሳቸው ትልቁን ጥቅም ማስገኛ ሳይሆን፣ በዓለም ውስጥ የሚሰራውን ሥራ ድርሻቸውን በመወጣት እና ለእነዚያ ደካማ ወይም እጅግ አላዋቂ ለሆኑ ሰዎች የእርዳታ እጃቸውን በመዘርጋት ፈጣሪያቸውን ያከብራሉ። 573Education, 221, 222.CGAmh 278.5

    ትምህርት የአገልግሎት መንፈስን መነሳት አለበት — ከየትኛውም ሁኔታ በላይ፣ በዕለት ተዕለት ጥቃቅን ተሞክሮዎች ለክርስቶስ ሲባል የሚደረግ አገልግሎት ባህሪይን ለመቅረጽ እና ህይወትን ከራስ ወዳድነት ወደ ጸዳ አገልግሎት ለመምራት ኃይል አለው፡፡ ይህን መንፈስ ለማነሳሳት፣ እርሱን ለማበረታታት እና በትክክለኛው መንገድ መምራት የወላጆች እና የአስተማሪዎች ስራ ነው። ከዚህ የለቃ ወሳኝ ሥራ ሊሰጣቸው አይችልም፡፡ የአገልግሎት መንፈስ የሰማይ መንፈስ ነው፣ እናም እርሱን ለማሳደግ እና ለማበረታታት በሚደረገው ጥረት ሁሉ መላእክት ይተባበራሉ።CGAmh 279.1

    እንዲህ ዓይነቱ ትምህርት በአምላክ ቃል ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። መርኾዎቹ በሙላት የተሰጡት እዚህ ጋር ብቻ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የጥናት እና የአስተምህሮ መሠረት መደረግ አለበት። ወሳኙ እውቀት እግዚአብሔር እና እርሱ የላከውን ማወቅ ነው። 574The Ministry of Healing, 401.CGAmh 279.2

    ከአእምሮአዊ ባህል በላይ የስነ-ምግባር ስልጠናን የላቀ ያደርጋል— ልጆች በዓለም ውስጥ ፋይዳ የሚሰጡ ይሆኑ ዘንድ ተገቢ ትምህርት እጅግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ነገር ግን ከግብረ-ገብ ሥልጠና በላይ የአእምሮ ባህልን ከፍ ከፍ የሚያደርግ ማንኛውም ጥረት በተሳሳተ መንገድ የተመራ ነው። ወጣቶች እና ልጆችን ማልማት፣ እና ማንጻት የወላጆች እና የአስተማሪዎች ዋና ሸክም መሆን አለበት። 575Counsels to Parents, Teachers, and Students, 84, 85.CGAmh 279.3

    ዓላማው የባህርይ ግንባታ ነው — ከፍተኛው የትምህርት ክፍል ወደ የተሻለ የባህሪይ ዕድገት የሚያመራ ዕውቀት እና ሥልጠናን የሚሰጥ እና ነፍስን ከእግዚአብሔር ሕይወት ጋር ለሚጣጣም አይነት ሕይወት ብቁ የሚያደርግ ነው፡፡ ዘለአለማዊነት ከግንዛቤ መጥፋት የለበትም። ከፍተኛው ትምህርት ልጆቻችንን እና ወጣቶቻችንን የክርስትናን ሳይንስ የሚያስተምር፣ ስለ እግዚአብሔር መንገዶች የተፈተሸ ዕውቀትን የሚሰጥ፣ እና ክርስቶስ የእግዚአብሔርን አባታዊ ባህርይ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸውን ትምህርት የሚሰጥ ነው። 576Counsels to Parents, Teachers, and Students, 45, 46.CGAmh 279.4

    እርሱ የሚመራ እና የሚያለማ ሥልጠና ነው — ልጆችን ለማሠልጠን ጊዜ አለው፣ ወጣቶችንም ለማስተማር ጊዜ አለው፣ እናም አነዚህ ሁለቱም በትምህርት ቤት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ አንድ ላይ ማዋሃዳቸው አስፈላጊ ነው፡፡ ልጆች ለኃጢኣት አገልግሎት ወይም ለጽድቅ አገልግሎት ሊሰለጥኑ ይችላሉ። የወጣት የመጀመሪያ ትምህርት በአለማዊውም ሆነ በሃይማኖታዊ ሕይወታቸው ባህሪያቸውን ይቀርፃል፡፡ ሰሎሞን “ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው፣ በሸመገለም ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም” ይላል፡፡ ይህ ቋንቋ አዎንታዊ ነው፡፡ ሰለሞን የዘዘው ሥልጠና መምራት፣ ማስተማር እና ማሳደግ ነው፡፡CGAmh 280.1

    ወላጆች እና አስተማሪዎች ይህንን ሥራ ይሰሩ ዘንድ፣ ልጅ የሚሄድበትን “መንገድ” እራሳቸው መረዳት አለባቸው፡፡ ይህ የመጽሐፎችን እውቀት ከማግኘት የላቁ ጉዳዮችን ያጠቃልላል። መልካም፣ ጨዋ፣ ጻድቅ፣ እና ቅዱስ የሆነውን ሁሉ ውስጥ ያጠቃልላል። ራስን መግዛትን፣ እግዚአብሔርን መምሰልን፣ የወንድማማችነት ርህራሄ እና ፍቅር ለእግዚአብሔር እና እርስ በእርስ መዋደድን መለማመድን ይይዛል። ይህንን ዓላማ ለማሳካት የልጆች አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ሥነ ምግባራዊና ሃይማኖታዊ ትምህርት ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡13Testimonies For The Church 3:131, 132.CGAmh 280.2

    እርሱ ሰራተኞችን ለእግዚአብሔር ያዘጋጃል — በአደራ የተሰጣቸውን ልጆች የክርስትና ትምህርትን የመስጠቱ ኃላፊነት አባቶች እና እናቶች ላይ ተጥሏል፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታ ቢሆን ልጆቻቸው ከእግዚአብሄር ርቀው እስኪለያዩ ድረስ እንዲንሸራተቱ ለመተው በየትኛውም ሥራ አእምሮ፣ ጊዜ እና ተሰጥኦዎች ተጠምደው እንዲይዙ መፍቀድ የለባቸውም፡፡ ልጆቻቸው ከእጃቸው አምልጠው ወደ የማያምኑ ሰዎች እጅ እንዲሆኑ መፍቀድ የለባቸውም፡፡CGAmh 280.3

    የዓለምን መንፈስ በአዕምሮአቸው እንዳይቀረጽ የተቻላቸውን ሁሉ ማድረግ አለባቸው። ከእግዚአብሔር ጋር ተባብረው እንዲሠሩ እነርሱነ ማሠልጠን አለባቸው፡፡ እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን ማለቂያ ለሌለው ሕይወት ብቁ በማድረግ እግዚአብሔር የሚጠቀምባቸው ሰብአዊ እጅ መሆን አለባቸው፡፡ 577Fundamentals of Christian Education, 545..CGAmh 281.1

    የእግዚአብሔርን ፍቅር እና ፍርሃትን ያስተምራል— ክርስቲያን ወላጆች፣ ለክርስቶስ ስትሉ ፍላጎቶቻችሁን፣ ለልጆቻችሁ ያላችሁን ዓላማ በመፈተሽ የእግዚአብሔርን ህግ መመዘኛ ማለፍ መቻሉን አትመለከቱምን? በጣም ወሳኙ ትምህርት እግዚአብሔርን መውደድ እና መፍራትን የሚያስተምራቸው ነው፡፡15The Review and Herald, June 24, 1890.CGAmh 281.2

    ብዙዎች ጊዜ እንዳለፈበት ይቆጥራሉ— ለዘላለም የሚዘልቅ ትምህርት እንደ ጊዜ እንዳለፈበት እና የማይመች ሆኖ ሙሉ በሙሉ ችላ ተብሏል። ከጊዜያዊ ጥቅማቸው ጋር፣ ጊዜያዊ ሰላምና ደስታ እና ለጌታ ለተቤዡት በተዘረጋው ጎዳና ላይ እንዲጓዙ እግሮቻቸውን ለመምራት የባህሪይ ግንባታ ሥራ ለመሥራት ልጆችን ማስተማር ጊዜ እንዳለፈበት እና በመሆኑም አላስፈላጊ እንደሆነ ይቆጠራል። ልጆቻችሁ እንደ ድል አድራጊዎች ወደ እግዚአብሔር ከተማ በሮች እንዲገቡ ለማድረግ፣ በአሁኑ ህይወት እግዚአብሔርን መፍራት እና ትእዛዛቱን እንዲጠብቁ የተማሩ መሆን አለባቸው፡፡ 578Fundamentals of Christian Education, 111.CGAmh 281.3

    ዘወትር የሚያድግ፣ ፈጽሞ የማያልቅ ነው — እዚህ ያለው የሕይወት ሥራችን ለዘለአለም ህይወት ዝግጅት ነው። እዚህ የተጀመረው ትምህርት በዚህ ህይወት የሚጠናቀቅ አይደለም፤ ዘወትር እያደገ፣ ፍጻሜ ሳይኖረው እስከ ለዘላለም የሚዘልቅ ነው። በድነት ዕቅድ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ እና ፍቅር ይበልጥ በሙላት ይገለጣል። አዳኙ ወደ ሕያው የውሃ ምንጮች ልጆቹን ሲመራ፣ ብዙ የእውቀት ክምችቶችን ይሰጣቸዋል። እናም በየዕለቱ የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራዎች፣ ጽንፈ ዓለምን የመፍጠር እና ጠብቆ የማፅቆየት የኃይሉ ማስረጃዎች አዳዲስ ውበቶችን ወደ አዕምሮ ያመጣሉ። ከዙፋኑ በሚወጣው ብርሃን፣ ምስጢሮች ይወገዳሉ፣ እናም ነፍስ ከዚህ በፊት ፈጽሞ ባልተረዳችው ቀለል ባለ ሁኔታ ትገረማለች። 579The Ministry of Healing, 466.CGAmh 281.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents