Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 4—መታዘዝ፣ እጅግ አስፈላጊው ትምህርት

    ምዕራፍ 10—የደስተኝነት እና የስኬት ምስጢር

    ደስተኝነት መታዘዝ ላይ የተመሰረተ ነው—አባቶች፣ እናቶች እና በትምህርት ቤቶቻችን የሚያስተምሩ መምህራን ልጆችን እንዲታዘዙ ማስተማር የትምህርት እጅግ ትልቁ ክፍል እንደሆነ ማስታወስ አለባቸው፡፡ ከዚህ የትምህርት ዘፍር ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ እጅግ ጥቂት አስፈላጊት እንዳለው ተስተውሏል፡፡ 114Manuscript Releases 9:2, 1899.CGAmh 75.1

    ልጆች የልሰለጠና ስሜቶቻቸው የሚመሯቸውን እንዲያደርጉ ከሚተው ይልቅ ተገቢ በሆነ ሥርዓት ሥር ሲሆኑ ይበልጥ ደስተኖች፣ ይልቅም ደስተኞች ይሆናሉ፡፡ 115Manuscript Releases 4:9, 1901.CGAmh 75.2

    ጥበበኛ ለሆነው የወላጆች ሕግ ቅጽበታዊና ዘላቂ ታዛዥነት የልጆችን ደስተኝነትን፣ እና የእግዚአብሔርን ክብር እና የማህበረሰቡን ጥቅም ከፍ ያደርጋል፡፡ ልጆች ፍጹም ነጻነታቸው የሚገኘው ለቤተሰብ ሕግጋት በመገዛት እንደሆነ ሊማሩ ይገባቸዋል፡፡ ክርስቲያኖችም ፍጹም ነጻነታቸው የሚገኘው ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ እንደሆነ ተመሳሳይ ትምህርት መማር አለባቸው፡፡ 116The Review and Herald, August 30, 1881.CGAmh 75.3

    የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰማይ ሕግ ነው፡፡ ያ ሕግ የሕይወት ሕግ እስከሆነበት ጊዜ ድረስ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሁሉ ቅዱስ እና ደስተኞች ነበሩ፡፡ ነገር ግን የመለኮት ሕግ በተጣሰ ጊዜ፣ ከዚያ በኋላ ቅናት፣ ምቀኝነት፣ እና ጠብ ተጀምረ፣ የተወሰኑ የሰማይ ነዋሪዎችም ወደቁ፡፡ በምድራዊ ቤታችን የእግዚአብሔር ሕግ እስከ ተከበረ ድረስ፣ ቤተሰብ ደስተኛ ይሆናል፡፡ 117Ibid.CGAmh 75.4

    አለመታዘዝ ኤደንን ማጣትን አስከተለ—ገና በመጀመሪያ የምድር ታሪክ ላይ የአዳምና ሔዋን አለመታዘዝ ታሪክ በሙላት ተሰጥቷል፡፡ በዚያች በአንድ ያለመታዘዝ ድርጊት የመጀመሪያ ወላጆቻችን ወብ የኤደን ቤታቸውን አጡ፡፡ ያን ያህል ትንሽ ነገር ነበር! ትልቅ ጉዳይ ባለመሆኑ አመስጋኝ የምንሆንበት ምክንያት አለ፣ ምክንያቱም ትልቅ ሆኖ ቢሆን ኖሮ፣ ትናንሽ አለመታዘዞች ላይ ችላ ማለት በተስፋፋ ነበር፡፡ እግዚአብሔር በኤደን ለነበሩ ጥንዶች አነስተኛ ፈተና መስጠት ነበረበት፡፡ CGAmh 75.5

    ምንጊዜም ቢሆን አለመታዘዝና መተላለፍ ለእግዚአብሔር ታላቅ ፀያፍ ነገር ነው፡፡ በጥቂት ነገር አለመታመን፣ ካልታረመ ወዲያው ትልቅ ወደ ሆነው መተላለፍ ያመራል፡፡ የአለመታዘዝ ትልቅነት ሳይሆን፣ ነገር ግን አለመታዘዝ በራሱ ወንጀል ነው፡፡ 118Manuscript Releases 9:2, 1899.CGAmh 76.1

    የምድራዊ እና መንፈሳዊ ብልጽግና መሠረት—ምድራዊና መንፈሳዊ ብልጽግና ለእግዚአብሔር ሕግ በመታዘዝ ላይ የተወሰነ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ስለማናነብብ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ በትጋት ለሚሰሙ እና ለቤተሰቦቻቸው በትጋት ለሚያስተምሩ የተሰጠውን የበረከት ቃልኪዳን አናውቅም፡፡ ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ ሕይወታችን እና ደስታችን ነው፡፡ ወደ ዓለም ስንመለከት የእግዚአብሔርን ሕግ ዝቅ በማድረጋቸው ሳቢያ በእርግማንና ብጥብጥ ሥር ሲቃትቱ እናገኛቸዋለን፡፡ እርሱ በረከቱን ከፍራፍሬና ከወይን ማሳ አስወግዷል፡፡ በምድር ላይ በሚኖሩ ትዕዛዛት ጠበቂ ሕዝብ ምክንያት ባይሆን ኖሮ፣ ፍርዱን ባላዘገየ ነበር፡፡ እርሱን ለሚወዱና ለሚፈሩት ጻድቃን ሲል ምህረቱን አብዝቷል፡፡ 119Manuscript Releases 6:4, 1899.CGAmh 76.2

    ልጆችን ወደ ታዛዥነት ጎዳና ይምሯቸው —ልጆቻቸውን ወደ ጥብቅ ታዛዥነት የመምራት የተቀደሰ ኃላፊነት ወላጆች ላይ ተጥሏል፡፡ የአሁኑም ሆነ የመጻኢ ሕይወት እውነተኛ ደስታ “ጌታ እንዲህ ይላል” የሚለውን መታዘዝ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ወላጆች፣ የክርስቶስ ሕይወት ሞዴል ይሁናችሁ፡፡ ሰይጣን ይህን ቅዱስ የላቀ መስፈርትን አንድ ላይ እጅግ ጥብቅ ነው ለማስባል የተቻለውን ዘዴ ሁሉ ይጠቀማል፡፡ ልጆቻችሁን በልጅነታቸው ዓመታት በእግዚአብሔር አምሳያ መቅረጽ ሥራችሁ ነው፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም የመጣው ሁሉም መሆን ስላለበት ሕያው ምሳሌ ለመስጠት ነው፣ የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉ ወላጆችም ልጆቻቸው እግዚአብሔርን ይወዱና ሕጉንም ይታዘዙ ዘንድ ማስተማር አለባቸው፡፡ ይህ አባቶችና እናቶች ማድረግ የሚችሉት ትልቁና እጅግ አስፈላጊው ሥራ ነው፡፡… ልጆችና ወጣቶችም ቢሆኑ በኃጢአትና በጽድቅ፣ በመታዘዝና ባለመታዘዝ መካከል ለይቶ በማወቅ፣ እግዚአብሔር የሚጠይቀውን በብልሃት ይረዱ ዘንድ የእግዚአብሔር ዕቅድ ነው፡፡ 120.CGAmh 76.3

    ታዛዥነት ደስታ መሆን አለበት—ወላጆች ሥርዓት በሥርዓት፣ ትዕዛዝ በትዕዛዝ፣ ጥቂት ከዚህ፣ ጥቂት ከዚያ፣ የእግዚአብሔርን ቅዱስ ሕግ ችላ እንዲሉ ባለመፍቀድ ልጆቻቸውን ማስተማር አለባቸው፡፡ ታማኝነት የጎደላቸውን ወደ ታማኝነታቸው እንዲመለሱ አንዲያ ልጁን ለሰጠው ልጆቻቸው በታማኝነት ይቆዩ ዘንድ እርሱን እንዲረዳቸው በመለመን፣ የመለኮትን ኃይል መታመን አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር የተትረፈረፈውን የፍቅሩን ጅረት ለወንዶችና ለሴቶች ልጆቹ ሊያፈስላቸው ይናፍቃል፡፡ ለክርስቶስ ሲባል ቅዱስ ሆኖ መቆጠር ማለት ሕጉን መታዘዝ እንደሆነ፣ በአገልግሎቱ ውስጥ የተሰጣቸውን እያንዳንዱን ኃይል በመጠቀም፣ በተጽኖአቸው ክልል ውስጥ የሚገቡትን ሁሉ በማስተማር ፍቃዱን ለማድረግ ደስተኞች ይሆኑ ዘንድ ይናፍቃል፡፡ 121Manuscript Releases 3:6, 1900.CGAmh 77.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents