Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 80—ቅዱስ ለሆነው አክብሮት መስጠት

    የአክብሮት ውድ ጸጋ— በጥንቃቄ ሊያዝ የሚገባው ሌላ ውድ ጸጋ አክብሮት ነው። 1078Education, 242.CGAmh 514.1

    የወጣቶች ትምህርት እና ሥልጠና የተቀደሱ ነገሮችን ከፍ የሚያደርግ እና በቤቱ ውስጥ ለአምላክ እንከን የለሽ አምልኮን የሚያበረታታ ባህሪይ መሆን አለበት። የሰማያዊው ንጉሥ ልጆች ነን የሚሉ ብዙዎች ለዘላለማዊ ነገሮች ቅድስና እውነተኛ አድናቆት የላቸውም፡፡ 1079Testimonies For The Church 5:496.CGAmh 514.2

    እግዚአብሔር በአክብሮት መያዝ አለበት— ለእግዚአብሔር የሚሰጠው እውነተኛ የአክብሮት ስሜት ወሰን የሌለውን ታላቅነቱ እና መገኘቱን ከመገንዘብ የሚመነጭ ነው፡፡ በዚህ በማይታይ ስሜት የእያንዳንዱ ልጅ ልብ በጥልቀት መነቃቃት አለበት፡፡ 1080Education, 242.CGAmh 514.3

    “በቅዱሳን ምክር እግዚአብሔር ክብር ነው፤ በዙሪያው ባሉት ሁሉ ላይ ታላቅና ግሩም ነው፡፡” መዝሙር 89፡7፡፡ CGAmh 514.4

    ስሙ መከበር አለበት— ለእግዚአብሔር ስም አክብሮትም መታየት አለበት። በጭራሽ ያ ስም በቀላሉ ወይም በግዴለሽነት መነገር የለበትም፡፡ በጸሎት ውስጥ እንኳን ማዘውተር ወይም አላስፈላጊ መደጋገም መወገድ አለበት፡፡ “ስሙ የተቀደሰ እና የተፈረ ነው” መዝሙር 111: 9፡፡ መላእክት ሲናገሩ ፊታቸውን ይሸፍናሉ፡፡ እኛ የወደቅን እና ኃጢአተኞች እንዴት ባለ አክብሮት እርሱን በከንፈሮቻችን ማንሳት አለብን! 1081Education, 243.CGAmh 514.5

    ቃሉ የተቀደሰ ነው— የእግዚአብሔርን ቃል ማክበር አለብን። ለታተመው ጥራዝ አክብሮት ማሳየት አለብን፣ በጭራሽ ለተራ ነገሮች መጠቀም ወይም በግዴለሽነት መያዝ አይገባም፡፡ ደግሞም የቀልድ ንግግሮችን ለመጥቀስ ሲባል ቅዱስ መጽሐፍት በቀልድ ወይም በሌላ መንገድ ሊተረጎም በጭራሽ አይገባም፡፡ “የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትናለች”፤ “በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር” (ምሳሌ 30፡5፤ መዝ. 12፡6) ነው፡፡ 1082 Education, 244.CGAmh 514.6

    ልጆች ከእግዚአብሔር አፍ የሚወጣውን ቃል ሁሉ እንዲያከብሩ መማር አለባቸው፡፡ ወላጆች ለዚያ ሕግ መታዘዝን በማሳየት፣ እራሳቸውን በእግዚአብሔር ቁጥጥር ሥር በመኖር፣ በልጆቻቸው ፊት የጌታን ሕግ መመሪያዎች ማጉላት አለባቸው። የሕጉ ቅዱስነት ስሜት ወላጆች ከገዛ፣ ነፍስን በመለወጥ ባሕሪይን በእርግጥ ይለውጣል። 1083 The Review and Herald, May 10, 1898.CGAmh 515.1

    የጸሎት ሥፍራ— እግዚአብሔር አለ— በእያንዳንዱ የክርስቲያን ቤት ውስጥ እግዚአብሔር በማለዳ እና በማታ በጸሎት እና በምስጋና መስዋእት መከበር አለበት። ልጆች የጸሎትን ሰዓት እንዲያከብሩ መማር አለባቸው፡፡ 1084Counsels to Parents, Teachers, and Students, 110..CGAmh 515.2

    ልጅ የጸሎት ሰዓት እና ቦታ እና የሕብረት አምልኮ አገልግሎቶች እግዚአብሔር እዚያ በመሆኑ ቅዱስ አድርጎ መቁጠር እንዳለበት መማር አለበት፡፡ አክብሮት በአመለካከት እና በውጫዊ ገጽታ ሲገለጥ፣ እርሱን የሚያነቃቃው ስሜት ይበልጥ ጠለቅ ያለ ይሆናል፡፡8Education, 242, 243.CGAmh 515.3

    የእግዚአብሔር ቤት— ቅዱስ ቤተመቅደሱ— ወጣቶች እና አዛውንቶች የእግዚአብሔር በተለየ ሁኔታ የሚገኝበት ሥፍራ እንዴት መከበር እንዳለበት የሚያሳዩ እነዚያን የቅዱስ መጽሐፍትን ቃላት ማጥናት ማሰላሰል እና ብዙ ጊዜ መደጋገም መልካም ነው፡፡ CGAmh 515.4

    “አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰች መሬት ናትና ጫማህን ከእግርህ አውጣ” (ዘጸ 3፡5) ሲል እርሱ ሙሴን ከሚነድድ ቁጥቋጦ ውስጥ አዘዘው፡፡ CGAmh 515.5

    ያዕቆብ የመላእክቱን ራዕይ ከተመለከተ በኋላ፣ “በእውነት እግዚአብሔር በዚህ ሥፍራ ነው፣ እኔ አላወቅሁም ነበር…፡፡ ይህ ሥፍራ የእግዚአብሔር ቤት ነው እንጂ ሌላ አይደለም፤ ይህም የሰማይ ደጅ ነው” (ዘፍ. 28፡ 16፣ 17) ሲል ተናገረ፡፡CGAmh 515.6

    “እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፤ ምድርም ሁሉ በፊቱ ዝም ትበል፡፡” ዕንባቆም 2፡20፡፡ Education, 243. 1085Education, 243.CGAmh 516.1

    ብዙዎች ... ለዘላለማዊ ነገሮች ቅድስና እውነተኛ አድናቆት የላቸውም። ሁሉም በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ እራሳቸውን እንዴት መምራት እንዳለባቸው መማር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ራስን በመቆጣጠር እና በአክብሮት ወደ መቅደሱ እንዲገቡ ማስተማር ብቻ ሳይሆን ማዘዝ አለባቸው፡፡ 1086Testimonies For The Church 5:496.CGAmh 516.2

    ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከሚመጣ ግድየለሽነት ይጠብቋቸው— ከምድራዊ መቅደሱ ጋር ከተያያዘው ቅድስና፣ ክርስቲያኖች ጌታ ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝበትን ቦታ እንዴት ማየት እንዳባቸው ሊማሩ ይችላሉ። ከኃይማኖታዊ አምልኮ ጋር በተያያዘ በሰዎች ልማዶች እና ባህል ላይ የተሻለ ሳይሆን የከፋ ለውጥ መጥቷል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኙን ውድ፣ ቅዱስ ነገሮች በአዕምሯችን እና በልባችን ላይ በፍጥነት እየጠፉ እና ወደ ተራ ነገሮች ደረጃ እየወረዱ ናቸው፡፡ የጥንት ሰዎች ለቤተ መቅደስ ማለትም እግዚአብሔር በቅዱስ አገልግሎቱ ለሚገናኛቸው ሥፍራ የነበራቸው አክብሮት በአብዛኛው ጠፍቷል፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር ራሱ የአገልግሎት ሥርዓትን ከማንኛውም የጊዜያዊነት ባህሪይ ካላቸው ነገሮች በላይ ከፍ ያለ ሥፍራ ሰጥቶታል። 1087Testimonies For The Church 5:491.CGAmh 516.3

    የእግዚአብሔር ቤት ብዙውን ጊዜ ይረክሳል፣ ደግሞም ሰንበት በሰንበት አማኞች ልጆች ተጥሷል፡፡ በአንዳንድ ሁኔታዎች በቅድስና ውበት እግዚአብሔርን ለማምለክ በሚሰበሰቡባቸው ስብሰባዎች ውስጥ እንኳን በቤት ዙሪያ እንዲሮጡ፣ እንዲጫወቱ፣ እንዲናገሩ እና ክፉ ቁጣቸውን እንዲገልጹ ይፈቀድላቸዋል፡፡ እንዲሁም ቅዱስ መሆን የነበረበት እና ቅዱስ ፀጥታ ሊነግስበት የሚገባው፣ ፍጹም ስርዓት፣ ንፅህና እና ትህትና ሊኖረው የሚገባው ስፍራ ፍጹም ባቢሎን “ግራ መጋባት” ሆኗል፡፡ ይህ እግዚአብሔርን ቅር እንዲሰኝ እና የእርሱን መገኘት ከጉባኤዎቻችን ለማስወገድ በቂ ነው፡፡ 1088The Review and Herald, September 19, 1854.CGAmh 516.4

    ከዕብራውያኑ የበለጠ አክብሮት የምንሰጥበት ምክንያቶች አሉን— ለእግዚአብሔር ቤት ያለው አክብሮት ሊጠፋ እየተቃረበ መሆኑ እርግጥ ነው። የተቀደሱ ነገሮች እና ቦታዎች አልተለዩም፤ ቅዱስ እና ከፍ ያሉ ነገሮች አድናቆት አላገኙም። በቤተሰቦቻችን ውስጥ ቅን የሆነ እግዚአብሔርን የመፈለግ ምክንያት የለም? የኃይማኖት ከፍተኛው ደረጃ በአፈር ውስጥ ስለተረገጠ አይደለምን? እግዚአብሔር ለጥንት ሕዝቦቹ ፍጹም እና ትክክለኛ የሥርዓታዊነት ሕጎችን ሰጥቷቸዋል፡፡ ባህሪይው ተለውጧል? እርሱ በሰማያት ሰማይ የሚገዛ ታላቁና ኃያል አምላክ አይደለምን? በላያችን ላይ የሚበራ የክብር እውነት ብርሃን ያለን እኛ እነርሱ ለእግዚአብሔር ቤት ያላቸውን አክብሮት እንድንመስል እግዚአብሔር ራሱ ለዕብራውያን የሰጠውን መመሪያ ብዙ ጊዜ ብናነብ አይሻልንምን? ከአይሁዶች የበለጠ ጠንቃቆች እና አክባሪዎች ለመሆን… እንኳን ብዙ ምክንያት አለን፡፡ በክርስቲያን አምልኮ ቅድስና ላይ ያለንን እምነት ለማጥፋት ጠላት በሥራ ላይ ነው፡፡ 1089Testimonies For The Church 5:495, 496.CGAmh 517.1

    ቤተክርስቲያን— የጉባኤው ቤተ መቅደስ— ቤት ለቤተሰብ ቤተ መቅደስ ሲሆን እልፍኝ ወይም መስገጃ ሥፍራ ለግል አምልኮ እጅግ ሰዋራ ሥፍራ ነው፤ ቤተክርስቲያን ግን የማኅበረ ቅዱሳን ቤተ መቅደስ ናት፡፡ ጊዜ፣ ሥፍራ እና የአምልኮ ሁኔታ በተመለከተ ህጎች ሊኖሩ ይገባል፡፡14Testimonies For The Church 5:491.CGAmh 517.2

    ልጆች በአክብሮት እንዲገቡ አስተምሯቸውቸ ወላጆች፣ በልጆቻችሁ አእምሮ ውስጥ የክርስትናን ደረጃ ከፍ አድርጉ፤ ተምክሮአቸው ውስጥ ኢየሱስን እንዲሸምኑ እርዷቸው፤ ለእግዚአብሔር ቤት ከፍ ያለ አክብሮት እንዲኖራቸው እና ወደ ጌታ ቤት ሲገቡ፡- “እግዚአብሔር እዚህ ነው፣ ይህ የእርሱ ቤት ነው፡፡ ንጹህ ሀሳቦች እና የተቀደሱ ዓላማዎች ሊኖረኝ ይገባል፡፡ በልቤ ውስጥ ኩራት፣ ምቀኝነት፣ ቅናት፣ ክፉ ጥርጣሬ፣ ጥላቻ ወይም ማታለል ሊኖረኝ አይገባም፤ ምክንያቱም ወደ ቅዱስ እግዚአብሔር ፊት እየመጣሁ ነኝ። ይህ እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር የሚገናኝበት እና የሚባርክበት ቦታ ነው፡፡ በዘላለማዊነት የሚኖር ከፍ ያለው እና ቅዱስ የሆነው ወደ እኔ ይመለከታል፣ ልቤን ይመረምራል፣ በሕይወቴም ውስጥ እጅግ ሚስጥራዊ ሀሳቦችን እና ድርጊቶችን ያነባል።” በሚሉ ሀሳቦች በለሰለሰ እና በተዋረደ ልብ መሆን እንዳለበት እንዲገነዘቡ አስተምሯቸው፡፡ 1090Testimonies For The Church 5:494.CGAmh 517.3

    ከወላጆቻቸው ጋር ይሁኑ— በአምላክ ቅዱስ መቅደስ ውስጥ ያሉት አምላኪዎች ግብረ ገባዊ ምርጫ የከበረ፣ የጠራ፣ የተቀደሰ መሆን አለበት። ይህ ጉዳይ በሚያሳዝን ሁኔታ ችላ ተብሏል፡፡ አስፈላጊነቱ ችላ ተብሏል፣ እናም በዚህ ሳቢያ ሥርዓት አልበኝነት እና አክብሮት ማጣት ተስፋፍቷል፣ እግዚአብሔርም ተዋርዷል። በቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉት መሪዎች፣ አገልጋዮች እና ሰዎች፣ አባቶች እና እናቶች ስለዚህ ጉዳይ የከበረ እይታ ሳይኖራቸው ልምድ ከሌላቸው ልጆች ምን ይጠበቃል? ብዙውን ጊዜ ኃላፊነት ካላቸው ወላጆች ርቀው በቡድን ሆነው ይገኛሉ፡፡ በእግዚአብሔር መገኘት ሥፍራ ቢኖሩም፣ ዓይኑም ወደ እነርሱ ቢመለከትም እንኳ፣ እነርሱ ቀላል እና የተዋረዱ ናቸው፤ የሾከሹካሉ፣ ይስቃሉም፣ ግድየለሾች፣ አክብሮት የሌላቸው እና ትኩረት የማይሰጡ ናቸው፡፡ 1091Testimonies For The Church 5:496, 497.CGAmh 518.1

    ራስን በመቆጣጠር እና በጸጥታ መኖር— በስብከት ወቅት እርስ በርሳችሁ በመነጋገር ለእግዚአብሔር ቤት እና አምልኮ ይህን ያህል ያነሰ አክብሮት አይኑራችሁ፡፡ ይህንን ጥፋት የሚፈጽሙ የእግዚአብሔርን መላእክት ሲመለከቷቸው እና ድርጊቶቻቸውን ሲፈጽሙ ማየት ቢችሉ ኖሮ በእፍረት እና ራሳቸውን በመጸየፍ ይሞሉ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አስተዋይ ሰሚዎችን ይፈልጋል። ጠላት እንክርዳድን የዘራው ሰዎች በሚተኙበት ጊዜ ነበር፡፡ 17Messages to Young People, 266.CGAmh 518.2

    ተራ በሆነ ሥፍራ ላይ የምትሰሩትን ነገር አትሥሩ— ልክ እንደ ጥንቱ መቅደስ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር የሚገናኝበት ቅዱስ ስፍራ መኖር አለበት፡፡ ያ ቦታ የምሳ ክፍል ወይም የንግድ ክፍል ሳይሆን ለእግዚአብሄር አምልኮ ብቻ ጥቅም ላይ መዋል አለበት፡፡ ልጆች በሰንበት ለማምለክ በሚሰበሰቡበት በዚያው ሥፍራ የቀን ትምህርት ቤት ሲማሩ የቦታውን ቅድስና እንዲመለከቱት እና በአክብሮት ስሜት መግባት መግባት እንዳለባቸው እንዲሰማቸው ማድረግ አይቻልም፡፡ ቅዱስ እና ተራው በጣም የተዋሃዱ ከመሆኑ የተነሳ እነዚህን ለመለየት አስቸጋሪ ሆኗል።CGAmh 518.3

    ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ቤት ወይም መቅደስ ተራ ስፍራ መሆን የሌለበት ለዚህ ነው፡፡ የእርሱ ቅዱስና ከተለመደው የዕለት ተዕለት ስሜት ወይም ከንግድ ሕይወት ጋር መምታታት ወይም መቀላቀል የለበትም፡፡ አምላኪዎች ወደ መቅደሱ ሲገቡ ታላቅ ፍርሃት ሊያድርባቸው ይገባል፣ እናም ተራ ዓለማዊ ሀሳቦችን ሁሉ ወደ ኋላ መተው አለባቸው፣ ምክንያቱም ይህ እግዚአብሔር የእርሱን መገኘት የሚገልጽበት ስፍራ ነው። እርሱ ታላቁ እና ዘላለማዊው እግዚአብሔር የሚደመጥበት አዳራሽ ነው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የጣኦት አምልኮወች እንደሆኑ የተናገራቸው ትዕቢት እና ስሜት፣ አለመግባባት እና በራስ መተማመን፣ ራስ ወዳድነት እና ስግብግብነት ለእንዲህ ዓይነቱ ስፍራ ተገቢ አይደሉም፡፡ 1092Manuscript Releases 2:3, 1886.CGAmh 519.1

    የትኛውንም የቅብጠት መንፈስ አታሳዩ— ወላጆች፣ ልጆቻቸው የንዴት ስሜቶች እና ክፉ ግልፍተኝነትን ሁሉ ቁጥጥር ሥር በማድረግ ፍጹም ተገዢ ማድረግ የእናንተ ግዴታ ነው። ልጆችም ወደ ስብሰባ ሲወሰዱ፣ የት እንዳሉ— ማለትም እቤት ውስጥ እንደሌሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር የሚገናኝበት ቦታ እንዳሉ እንዲያውቁ እና እንዲገነዘቡ መደረግ አለባቸው። ደግሞም ዝም ማለት እና ከማንኛውም ጨዋታ ነፃ መሆን አለባቸው፣ እግዚአብሔርም ፊቱን ወደ እናንተ ይመለሳል፣ ከእናንተ ጋር በመገኘት ይባርካችኋል።CGAmh 519.2

    በቅዱሳን ስብሰባዎች ላይ ሥርዓት ከተጠበቀ እውነቱ በሰሚዎቹ ሁሉ ላይ የተሻለ ውጤት ያስገኛል፡፡ በጣም ተፈላጊ የሆነው ሥነ-ስርዓት ይበረታታል፣ በእውነትም ውስጥ የነፍስን ጥልቀት የሚቀሰቅስ ኃይል ይኖራል፣ በሰሚዎቹም ላይ ሞት የመሰለ መፍዘዝ አይኖርም። አማኞች እና የማያምኑ ይነካሉ፡፡ ቅዱሳን ትእዛዛቱ ስለ ተጣሱ እና የእስራኤል ብርታት በመዳከሙ ሳቢያ በአንዳንድ ስፍራዎች የእግዚአብሔር ታቦት ከቤተክርስቲያን የተወገደ መሆኑ ግልጽ ይመስላል፡፡ 1093The Review and Herald, September 19, 1854.CGAmh 519.3

    የሚረብሽውን ልጅ አውጡት— የእግዚአብሔር ልጆች እርሱን እንደሚታዘዙት ሁሉ ልጃችሁ መታዘዝን መማር አለበት። ይህ ደረጃ ከተጠበቀ፣ የእናንተ ቃል በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሲቁነጠነጥ በነበረው ልጃችሁ ላይ የተወሰነ ክብደት ይኖረዋል። ነገር ግን ልጆች መገደብ ካልቻሉ፣ ወላጆች እገዳው ከመጠን በላይ እንደሆነ የሚሰማቸው ከሆነ ህፃኑ በቅጽበት ከቤተክርስቲያኑ መወገድ አለበት፤ በመናገር ወይም በመሮጥ የሰሚዎችን አእምሮ እንዲስብ መተው የለበትም፡፡ ወላጆች በቤተክርስቲያን ውስጥ ልጆቻቸውን በሚያስተዳድሩበት ልቅ በሆነ መንገድ እግዚአብሔር ተዋርዷል፡፡1094Letter 1, 1877. CGAmh 520.1

    የታይታ አለባበስ አክብሮት ማጣትን እያበረታታ ነው— ሁሉም በአለባበሳቸው ግሩም፣ ንጹህ እና ሥርዓታዊ መሆንን መማር አለባቸው፣ ሆኖም ግን ለቤተ መቅደስ ፈጽሞ ተገቢ ያልሆነው ውጫዊ ጌጣጌጥ ሊበረታታ አይገባም፡፡ የታይታ አለባበስ ሊኖር አይገባም ፣ ምክንያቱም ይህ አክብሮት ማጣትን ያበረታታል ...፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስን ደንብ በጥብቅ በመከተል ሁሉም የአለባበስ ጉዳዮች በጥብቅ ሊጠበቁ ይገባል። ፋሽን የውጭውን ዓለም የገዛች እንስት አምላክ ስትሆን ብዙውን ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ውስጥም ሾልካ ትገባለች፡፡ ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቃል መስፈርቷ ማድረግ አለባት፣ ወላጆችም በዚህ ጉዳይ ላይ በጥበብ ማሰብ አለባቸው፡፡ 1095Testimonies For The Church 5:499, 500..CGAmh 520.2

    ለአገልጋዮች— ለእግዚአብሔር ተወካዮች አክብሮት አሳዩ— ለእግዚአብሔር ተወካዮች— እርሱን ወክለው ለመናገር እና ለመተግበር ለተጠሩ አገልጋዮች፣ መምህራን እና ወላጆች አክብሮት መታየት አለበት ። ለእነርሱ በሚደረግ አክብሮት እርሱ ይከብራል፡፡22Education, 244..CGAmh 520.3

    እነርሱ [ልጆች] አገልጋዩ የእግዚአብሔር አምባሳደር መሆኑን፣ እርሱ የሚያመጣው መልእክት በነፍስ ማዳን ውስጥ እግዚአብሔር ከተሾማቸው ወኪሎች መካከል አንዱ እንደሆነ እና ዕድል የቀረበላቸው ሁሉ ለሕይወት የሚሆን የመዳን ሽታ ወይም ለሞት የሚሆን የሞት ሽታ እንደሚሆን ብዙም አይማሩም፡፡ 1096Testimonies For The Church 5:497.CGAmh 520.4

    ቅዱስ የሆነ፣ የእግዚአብሔር አምልኮ የሚመለከት አንድም ነገር በግዴለሽነት እና በእንዝላልነት መታየት የለበትም፡፡ የሕይወት ቃል በሚነገርበት ጊዜ በተወካይ ባሪያው በኩል የእግዚአብሔርን ድምፅ እያዳመጣላችሁ መሆኑን ማስታወስ ይገባል፡፡ እነዚህ ቃላት በግዴለሽነት እንዳያመልጣችሁ፤ ብትታዘዟቸው እግሮቻችሁን የተሳሳተ ጎዳና ላይ እንዳይቆይ ያደርጋችኋል፡፡24Messages to Young People, 266.CGAmh 521.1

    ትችት የሚያቀርቡ ወላጆች ተጠያቂነት— ወላጆች፣ ለልጆቻችሁ ምን አይነት ምሳሌ እንደምትሆኑ እና ምን አይነት ሀሳቦች እንደምትሰጧቸው ተጠንቀቁ፡፡ አእምሯቸው ፕላስቲክ ነው፣ በቀላሉም ተጽዕኖ ሥር ይወድቃሉ። ከቤተ መቅደስ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ተናጋሪው ጉድለት ካለበት ይህን ከመጥቀስ ፍርሃት ሊያድርባችሁ ይገባል፡፡ በእግዚአብሔር ወኪል በኩል እንደሚመጣ ልትሰሟቸው ስለሚገቡ ጥሩ ሀሳቦች፣ እርሱ ስለ ሰራቸው መልካም ስራዎች ብቻ ተናገሩ፡፡ ልጆች በቃሉ አገልግሎት ለምን ብዙም እንደማይደነቁ እና ለእግዚአብሔር ቤት ያላቸው አክብሮት ያነሰ ለምን እንደሆነ በቀላሉ ሊታይ ይችላል፡፡ ትምህርታቸው በዚህ ረገድ ጉድለት ያለበት ነው፡፡ 1097Testimonies For The Church 5:498.CGAmh 521.2

    ስሱ እና ተጋላጭ የሆነው የወጣቶች አእምሮ የእግዚአብሔር አገልጋዮችን ሥራ ወላጆቻቸው ጉዳዩን በሚያስተናግዱበት መንገድ ይገምታል፡፡ አያሌ የቤተሰብ ኃላፊዎች አገልግሎቱን ቤት ውስጥ የትችት ርዕሰ ጉዳይ ያደርጉታል፣ ጥቂት ነገሮችን ያፀድቃሉ፣ ሌሎችንም ያወግዛሉ፡፡ በዚህ መንገድ ለሰዎች የመጣው የእግዚአብሔር መልእክት ትችት የሚቀርብበት እና ጥያቄ ውስጥ የሚገባ እና የከንቱነት ርዕሰ ጉዳይ ይሆናል፡፡ የሰማይ መዝገብ ብቻ ሊገልጥ በሚችለው እነዚህ የግድየለሽ እና አክብሮት በሌላቸው አስተያየቶች በወጣቶች ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖዎችን ያሳርፋሉ። ወላጆቻቸው ለማሰብ ከመንቃታቸው በፊት ልጆች እነዚህን ነገሮች እጅግ በፍጥነት ይመለከታሉ፣ ይገነዘባሉም፡፡ የግብረ ገብ ስሜቶቻቸው ጊዜ በጭራሽ መለወጥ የማይችለውን የተሳሳተ አድልዎ ይቀበላሉ፡፡ ወላጆች በልጆቻቸው የልብ ጥንካሬ እና ለእግዚአብሔር የይገባኛል ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት የግብረ ገብ ስሜታቸውን ለመቀስቀስ ስላለው ችግር ያዝናሉ፡፡ ነገር ግን የሰማይ መዝገብ መጽሐፍት እውነተኛውን ምክንያት በማይጠፋ ብዕር መዝግቦታል፡፡ ወላጆች አልተለወጡም፡፡ እነርሱ ከሰማይ ወይም ከሰማይ ሥራ ጋር የሚስማሙ አልነበሩም፡፡ የእግዚአብሔር አገልግሎት እና የመቅደሱ ቅድስና ዝቅተኛ፣ተራ ሀሳቦቻቸው ከልጆቻቸው ትምህርት ጋር ተሸምኗል፡፡ CGAmh 521.3

    ለዓመታት በዚህ አጥፊ የቤት ውስጥ የትምህርት ተጽዕኖ ሥር የነበረ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር አገልግሎት እና ለነፍሳት መዳን እርሱ ለሾማቸው ወኪሎች ከፍተኛ አክብሮት ሊኖረው ይችላል ወይ የሚለው አጠያያቂ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር አገልጋዮች የተላከውን መልእክት ከራሱ እግዚአብሔር ለእናንተ እንደተላከ መልእክት እንደምትቆጥሩ ለምትገናኟቸው ሁሉ ለመግለጽ እነዚህ ነገሮች በአክብሮት፣ በትህትና ቋንቋ እና በመልካም ሆደ ባሻነት ልትናገሩ ይገባል፡፡ 1098Testimonies For The Church 5:497, 498.CGAmh 522.1

    ልማድ እስኪሆን ድረስ አክብሮትን ይለማመዱ— ለዚህ ዘመን ወጣቶች አክብሮት በጣም አስፈላጊ ነው። የኃይማኖተኛ ወላጆች ልጆች እና ወጣቶች በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሊከበር ስለሚገባው ሥርዓት እና ጨዋነት የጎደላቸው ሆነው ስመለከት በጣም ደነገጥኩኝ፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሕይወትን ቃል ለሕዝቡ ሲያቀርቡ አንዳንዶቹ ያነባሉ፣ ሌሎቹ ያሾከሹካሉ፣ ይስቃሉም፡፡ ዓይኖቻቸው በዙሪያቸው ያሉትን ሰዎች ትኩረት በመሳብ ኃጢአት እየሠሩ ነው፡፡ ይህ ልማድ ቁጥጥር ካልተደረገበት በማደግ ሌሎች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡ CGAmh 522.2

    ልጆች እና ወጣቶች እግዚአብሔር በሚመለክባቸው ስብሰባዎች ላይ ግድየለሾች እና ቸልተኞች መሆናቸው የሚኮራበት ነገር እንደሆነ በጭራሽ ሊሰማቸው አይገባም፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዱን አክብሮት የጎደላቸውን አስተሳሰቦችን ወይም ድርጊቶችን ያያል፣ በመንግሥተ ሰማያትም ተመዝግቧል። እርሱ “ሥራህን አውቃለሁ” ይላል፡፡ ሁሉን ከሚመረምር ዐይኑ የተደበቀ ነገር የለም፡፡ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በማንኛውም ደረጃ ትኩረት የጎደለው እና የግዴለሽነት ልማድን በውስጣችሁ ከፈጠራችሁ፣ እርሱን ለማረም ያላችሁን ኃይሎች ተጠቀሙ እና ለራሳችሁ አክብሮት እንዳላችሁ አሳዩ፡፡ የራሳችሁ አካል እስኪሆን ድረስ አክብሮትን ተለማመዱ፡፡ 1099The Youth’s Instructor, October 8, 1896.CGAmh 522.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents