Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 59—ጠቃሚ ሙያዎችን ማስተማር

    እያንዳንዱ ልጅ የተወሰነ ሥራን መማር አለበት— በዚህ ጊዜ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ዓለም ለማምጣት ኃላፊነት የወሰዱበትን ሥራ መስጠት ያለመቻላቸው ግድየለሽነት የብዙ ወጣቶችን ሕይወት በማጥፋት እና ጠቀሜታቸውን በእጅጉ እያሽመደመደ የማይነገር ክፋት አስከትሏል፡፡ ወጣት ልጆች የተወሰነ ሙያ ሳይማሩ እንዲያድጉ መፍቀድ ትልቅ ስህተት ነው፡፡ 680 Manuscript Releases 12:1, 1901.CGAmh 337.1

    ከደመናው ዓምድ ውስጥ ኢየሱስ በሙሴ በኩል ለዕብራውያኑ ለልጆቻቸው ሥራ እንዲሠሩ ማስተማር እንዳለባቸው፣ ሙያዎችን ማስተማር እንዳለባቸው እና ማንም ሥራ ፈት መሆን እንደሌለበት መመሪያ ሰጠ፡፡ 681Manuscript Releases 24b, 1894.CGAmh 337.2

    ልጆቻችሁ አስፈላጊ ከሆነ በራሳቸው ጉልበት እንዲኖሩ እውቀት እንዲያገኙ መርዳት አለባችሁ፡፡ የግዴታ ጥሪዎችን በመከተል ረገድ ቆራጦች እንዲሆኑ እነርሱን ማስተማር አለባችሁ፡፡ 682The Signs of the Times, August 19, 1875. CGAmh 337.3

    የመሣሪያዎችን አጠቃቀም አስተምሩ— ልጆች ተገቢ ዕድሜ ላይ ሲደርሱ መሳሪያዎች ሊሰጣቸው ይገባል። ሥራቸው አስደሳች ሆኖ ከተገኘ በመሣሪያዎች አጠቃቀም ረገድ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ሆነው ያገኛሉ፡፡ አባት አናጺ ከሆነ ጌታ የሰውን ልጆች ከህንፃ ጋር ያነጻጸረበትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ወደ ትምህርቱ በመውሰድ ወንዶች ልጆቹን ማስተማር አለበት፡፡4Manuscript Releases 4:5, 1912.CGAmh 337.4

    ወንዶች ልጆችን ስለ ግብርና አሠልጥኗቸው— አባቶች ወንዶች ልጆቻቸውን በሙያቸው እና በሥራዎቻቸው ውስጥ ከእነርሱ ጋር እንዲሳተፉ ማሠልጠን አለባቸው፡፡ አርሶ አደሮች እርሻ ለልጆቻቸው የልከበረ ሙያ ነው ብለው ማሰብ የለባቸውም፡፡ እርሻ በሳይንሳዊ እውቀት መሻሻል አለበት፡፡CGAmh 337.5

    እርሻ ትርፋማ እንዳልሆነ ይገለጻል፡፡ ሰዎች አፈር የተከፈለበትን የጉልበት ዋጋ መልሶ አይከፍልም ይላሉ፣ አፈሩንም ስለሚያርሱት ሰዎች ከባድ ዕጣ ፈንታ ያዝናሉ…። ነገር ግን ተገቢውን ችሎታ ያላቸው ሰዎች ይህን የሥራ ዘርፍ ቢይዙ እና አፈሩን፣ እና እንዴት መትከል እንዳለባቸው፣ እንዴት ማልማት እና መከር መሰብሰብ እንዳለባቸው ቢያጠኑ የበለጠ አበረታች ውጤቶችን ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ብዙዎች “እኛ ግብርናውን ሞክረናል ውጤቱ ምን እንደሆነ እናውቃለን” ይላሉ፣ ነገር ግን እነዚህም አፈርን እንዴት ማልማት እንዳለባቸው እና ሳይንስን ወደ ሥራቸው እንዴት ማምጣት አለባቸው ማወቅ አለባቸው፡፡ ማረሻዎቻቸው ይበልጥ ጥልቀት ያላቸውን፣ ሰፋፊዎቹን ቦዮች ማውጣት መቁረጥ አለባቸው፣ እንዲሁም አፈሩን በማረስ ረገድ በተፈጥሮአቸው ተራ እና ሽርክት መሆን እንደሌለባቸው መማር አለባቸው…። ዘርን በወቅቱ መዝራትን፣ ለተክሎች ትኩረት መስጠት እና እግዚአብሔር የቀየሰውን እቅድ መከተልን ይማሩ። 683The Signs of the Times, August 13, 1896.CGAmh 338.1

    የላቀ እሴት ያለው ሥልጠና— ከእርሻ የላቀ ዋጋ ያለው የእጅ ሙያ ሥልጠና የለም፡፡ በግብርና ሥራዎች ላይ ፍላጎትን ለመፍጠር እና ለማበረታታት የበለጠ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ የሰው ልጅ ምድርን እንዲያርስ የእግዚአብሔር ዕቅድ እንደ ሆነ፣ የመጀመሪያው ሰው፣ የአለም ሁሉ ገዥ፣ ያለማ ዘንድ አንድ የአትክልት ስፍራ እንደተሰጠው እና በእርግጥም የተከበሩ ብዙ የዓለም ታላላቅ ሰዎች መሬት አራሾች እንደ ነበሩ አስተማሪው መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብርና ስለሚናገረው ነገር ትኩረት ይስጥበት፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ ያሉትን ዕድሎች አሳዩ፡፡CGAmh 338.2

    መተዳደሪያውን በግብርና ያደረገ ሰው ከብዙ ፈተናዎች በማምለጥ በታላላቅ ከተሞች ውስጥ ከሚሰሩ ሰዎች የተነፈጉ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን ዕድሎች እና በረከቶችን ያገኛል፡፡ ደግሞም በእነዚህ እጅግ ግዙፍ ባለአደራ ድርጅቶች እና የንግድ ውድድር ውስጥ ልክ እንደ አርሶ አደሩ እውነተኛ ነፃነት እና በእርግጠኝነት ለልፋታቸው ፍትሃዊ ትርፍን የሚያገኙ ጥቂቶች ናቸው፡፡6Education, 219.CGAmh 338.3

    ትኩስ ምርት ልዩ እሴት አለው— ቤተሰቦች እና ተቋማት በመሬት እርሻና ማሻሻያ የበለጠ ለመስራት መማር አለባቸው። ሰዎች መሬት በወቅቱ የሚሰጠውን የምድር ምርቶች ዋጋ ብቻ ቢያውቁ ኖሮ አፈርን ለማልማት የበለጠ ትጋት የተሞላበት ጥረት ይደረግ ነበር፡፡ ሁሉም ከፍራፍሬና አትክልት ማሳ ከሚገኘው የአትክልት እና የፍራፍሬ ልዩ ዋጋ ጋር መተዋወቅ አለባቸው፡፡684Counsels on Diet and Foods, 312. CGAmh 339.1

    ትምህርት ቤቶች ጠቃሚ በሆኑ ሙያዎች ላይ ትምህርት ለመስጠት አለባቸው— የአካል እንቅስቃሴን የሚጠይቅ ሥልጠና እስከ አሁን ከተሰጠው እጅግ የላቀ ትኩረት ሊሰጠው ዘንድ ይገባዋል፡፡ ትምህርት ቤቶች ከከፍተኛ የአእምሮ እና የግብረ ገብ ዕድገት በተጨማሪ ለአካላዊ ዕድገት እና ለአምራችነት ስልጠናዎች እጅግ በጣም የተሻሉ ቁሳቁሶችን ማቅረብ አለባቸው፡፡ በግብርና፣ በአምራችነት፣ በተቻለ መጠን በጣም ጠቃሚ የሆኑ ሙያዎችን የሚያጠቃልል መሆን አለበት— በተጨማሪም በቤተሰብ ምጣኔ ሐብት፣ በጤናማ ምግብ አበሳሰል፣ በልብስ ስፌት፣ በንጹህ የልብስ ሥራ፣ በሕመምተኞች አያያዝ እና በተዛማጅ መስመር ላይ ትምህርት ሊሰጥ ይገባል፡፡ የአትክልት ስፍራዎች፣ ቤተ ሙከራዎች እና የህክምና ክፍሎች መቅረብ ያለባቸው ሲሆን በየዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች በሰለጠኑ አስተማሪዎች አመረር ስር መሆን አለባቸው፡፡ CGAmh 339.2

    ሥራ የተወሰነ ግብ ሊኖረው የሚገባ እና ጥልቅ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዱ ሰው ስለ የተለያዩ የእጅ ሥራዎች ዕውቀት ቢያስፈልጋቸውም ቢያንስ በአንዱ ብቃት ያለው መሆኑ የግድ አስፈላጊ ነው፡፡ እያንዳንዱ ወጣት፣ ከትምህርት ቤት ሲወጣ፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ኑሮውን የሚመራበት የተወሰነ ሙያ ወይም ሥራ እውቀት ሊኖረው ይገባል።8Education, 218.CGAmh 339.3

    የድርብ እሴት ሥልጠና— ከትምህርት ቤቶች ተቋማት ጋር ተያይዞ ተማሪዎች ከትምህርት ሰዓት ውጭ ሥራ እንዲሰሩ እና አስፈላጊ የአካል እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች መቋቋም ነበረባቸው ...፡፡ ከዚያም ሥነ-ጽሑፋዊ ትምህርታቸውን እየተማሩ ተግባራዊ የሥራ ዕውቀትም ማግኘት አለባቸው፡፡ 685Counsels to Parents, Teachers, and Students, 83, 84.CGAmh 339.4

    የአምራችነት ዕውቀት ከሳይንሳዊ ዕውቀት የበለጠ ዋጋ ያለው ነው— በምግብ ዝግጅት ክፍል ውስጥ ላሉት ወጣት ሴቶች ትምህርት የሚሰጡ ልምድ ያላቸው መምህራን መኖር ነበረባቸው፡፡ ወጣት ልጃገረዶች ልብሶችን መቁረጥ፣ መሥራት፣ መጠገን እና በዚህም ለሕይወት ተግባራዊ ግዴታዎች ዝግጁ ለመሆን መማር መቻል ነበረባቸው፡፡CGAmh 340.1

    ለወጣት ወንዶች ፣ጡንቻዎቻቸውን እንዲሁም የአእምሮ ኃይሎቻቸውን ወደ ተግባር የሚያመጡባቸው የተለያዩ ሙያዎችን የሚማሩባቸው ተቋማት መኖር አለባቸው፡፡ ወጣቶች ከየትኛውም የበለጠ ውጤት ባለው ወደ አንድ-ወገን ያዘነበለ ትምህርት ማግኘት ካለባቸው— በጤና እና በሕይወት ላይ ከሚያደርሳቸው ጉዳቶች ሁሉ ጋር የሳይንስ እውቀት ወይስ ለተግባራዊ ሕይወት የሚጠቅመውን የጉልበት ሥራ እውቀት ሊኖረው ይገባል? ያለማወላወል መልስ እንሰጣለን፣ ሁለተኛው መሆን አለበት፡፡ አንድ ሰው ችላ ማለት ካለበት የመጽሐፍት ጥናት ይሁን፡፡ 686Testimonies For The Church 3:156.CGAmh 340.2

    የልጆችን ሥልጠና በተመለከተ የተሳሳተ ሥልጠና የወሰዱ እና የተሳሳተ ሀሳብ ያላቸው ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ልጆች እና ወጣቶች እጅግ በጣም የተመረጠ ሥልጠና ይፈልጋሉ፣ እናም አካላዊ የጉልበት ሥራን ከአእምሮ ሥራ ጋር ማጣመር አለባችሁ— ሁለቱም አብረው መሄድ አለባቸው።11Manuscript Releases 19:1887.CGAmh 340.3

    ኢየሱስ እርካታ ያለው አምራች ምሳሌ ነበር—የአንድ የሥራ ድርሻ ግልጽ በሆነበት እና ከተግዳሮቹ ግማሹ ከዚሁ እውነታ ጋር ተያይዞ በሚወገድበት ግልፅ በሆነ የሥራ መስክ እውቅና ያለው ሚስዮናዊ ከመሆን ይልቅ የክርስትናን መመሪያዎች ወደ ተራው የሕይወት ሙያ በማምጣት፣ መካኒክ፣ ነጋዴ፣ ጠበቃ ወይም አርሶ አደር በመሆን ለእግዚአብሄር ለመስራት እጅግ የበለጠ ፀጋ እና ከባድ የባህሪ ሥልጠና ይጠይቃል፡፡ የዕለት ተዕለት እያንዳንዱን የኑሮ ዝርዝርን በማስቀደስ እና እያንዳንዱን ዓለማዊ ግብይት በመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያናዊ ሚዛን ረገድ በማሰናዳት ሃይማኖትን ወደ ቤተ ሙከራ እና ወደ ሥራ ቢሮ መውሰድ፣ ጠንካራ መንፈሳዊ ጅማት እና ጡንቻ ይጠይቃል፡፡ CGAmh 340.4

    ኢየሱስ፣ በገለልተኛው ናዝሬት በቆየባቸው ሠላሳ ዓመታት ውስጥ ከሳምንት እስከ ሳምንት እና ከዓመት እስከ ዓመት እንደ ተራዎቹ የዘመኑ ሰዎች ይለፋ፣ ያርፍ ይበላ እና ይጠጣ ነበር፡፡ እርሱ እንደ ተለየ ስብዕና ለራሱ ምንም ትኩረት አልሰጠም፤ ሆኖም እርሱ የዓለም አዳኝ፣ በመላእክት የተወደደ፣ ሁል ጊዜም፣ የሰው ልጆች እስከ መጨረሻው ጊዜ ድረስ ሊዘልቅ የሚችል ትምህርት እንዲኮርጁ በኑሮ በማሳየት የአባቱን ሥራ ሲያከናውን ነበር።CGAmh 341.1

    ወሳኝ የሕይወት ግዴታዎች ውስጥ ይህ እርካታ ያለው አስፈላጊ የአምራችነት ትምህርት፣ ምንም እንኳን ተራ ቢሆንም፣ አብዛኛው ክፍል የክርስቶስ ተከታዮች ገና መማር አለባቸው፡፡ ሥራችንን የሚተች የሰው ዐይን ባይኖር ወይም ለማወደስም ሆነ ለመንቀፍ ድምፅ ባይኖር ልክ ወሰን የሌለው ራሱ በግሉ እንደሚመረምር ተደርጎ መሰራት አለበት፡፡ በትላልቅ የሕይወት ጉዳዮች ውስጥ እንደምናደርገው ሁሉ በንግዳችን ጥቃቅን ዝርዝሮችም ታማኞች መሆን አለብን፡፡ 687Health Reformer, October, 1876.CGAmh 341.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents