Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 27—ደስተኝነት እና አመስጋኝነት

    መልካም ተጽዕኖ ቤት ውስጥ ይስፈን—ከምንም ነገር በላይ ወላጆች ልጆቻቸውን በደስታ፣ በትህትና እና በፍቅር መንፈስ ይክበቧቸው። ፍቅር ያለበት፣ እና በአተያይ፣ በቃላት፣ እና በድርጊቶች የሚገለጽበት ቤት መላእክት መገኘታቸውን ለመግለጽ የሚደሰቱበት ሥፍራ ነው፡፡CGAmh 138.1

    ወላጆች፣ የፍቅር እና የደስታ እርካታ የፀሀይ ብርሃን ወደ ልባችሁ ይግባ፤ ጣፋጩ፣ አስደሳቹ ተጽዕኖም በቤታችሁ ይስፈን። ርህራሄና ታጋሽ መንፈስን አሳዩ፤ የቤት ውስጥ ህይወትን የሚያፈኩትንም ጸጋዎችን ሁሉ በማዳበር በልጆችዎ ውስጥ ያንኑ ያበረታቱ። ለልጆች የአእምሮ እና የአካል ጥንካሬን የሚያሳድገው በዚህ መንገድ የተፈጠረው ሁኔታ ለአትክልቱ ዓለም አየር እና የፀሐይ ብርሃን እንዳላቸው አይነት ጠቀሜታ ያለው ነው፡፡ 256The Ministry of Healing, 386, 387.CGAmh 138.2

    የፊት ገጽታ ደስታን የሚያሳይ ይሁን—በኢየሱስ ኃይማኖት ውስጥ ምንም ሐዘን ያንዣበበት ነገር የለም፡፡ ምንም እንኳን ምቹ አይደሉም ብሎ ሐዋርያው የተናገረው ቀላልነት፣ ከንቱ እና ፌዝ በፍጹም መወገድ ቢኖርባቸውም በኢየሱስ በመሆን የሚገኝ በፊት ገጽታ ላይ የሚንጸባረቅ አስደሳች ዕረፍት እና ሰላም አለ፡፡ ክርስቲያኖች አዛኞች፣ ጭንቀታሞችና ተስፋ የቆረጡ መሆን የለባቸውም፡፡ እነርሱ ራሳቸውን የሚቆጣጠሩ ናቸው፣ ሆኖም ግን ጸጋ ብቻ ሊሰጥ የሚችለውን ደስታ ለዓለም ያሳያሉ፡፡ 257 The Review and Herald, April 15, 1884.CGAmh 138.3

    ልጆች በደስታ እና ብሩህ ስሜት ይሳባሉ፡፡ ደግነት እና ርህራሄ አሳዩአቸው፣ እነርሱም ለእርስዎ እና ለሌላው ተመሳሳይ መንፈስ ያሳያሉ፡፡3Education, 240.CGAmh 138.4

    ነፍስን ደስታን፣ አመስጋኝነትን፣ እና እግዚአብሔር በወደደን ታላቅ ፍቅሩ ምስጋና መግለጽን ያስተምሩ…፡፡ የክርስቲያን ደስታ የቅድስና ውበት ነው። 258 The Youth’s Instructor, July 11, 1895. CGAmh 139.1

    አስደሳች ቃላትን ይናገሩ—ደስ የሚሉ ቃላት ደስ ከማይሉ እና ከሚያበሳጩ ቃላት የላቀ ወጪ የላቸውም፡፡ ርህራሄ የጎደላቸው ቃላቶች ሲናገርዎ ያስጠለዎታል? ያስታውሱ እንደዚህ ያሉትን ቃላት በሚናገሩበት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ሀይለኛ ነደፋ ይሰማቸዋል…፡፡ ወላጆች፣ ተግባራዊ እግዚአብሔርን መምሰልን ወደ ቤት ያምጡ፡፡ አለመግባባት የሚነግስበት ቤት መላእክትን አይማርካቸውም፡፡ ልጆች ብሩህነትን እና ደስታን የሚያመጡ ቃላቶችን እንዲናገሩ ያስተምሯቸው። 259 The Review and Herald, December 31, 1901. CGAmh 139.2

    ደስተኛ የአእምሮ አስተሳሰብን ያበረታቱ—ያለማቋረጥ ማመስገን ያለበት ማንም ቢኖር ክርስቲያን ነው። በዚህ ምድር ሕይወት ቢሆንም እንኳን ደስታን የሚያጣጥም ካለ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ታማኝ ተከታይ ነው። ደስተኞች መሆን የእግዚአብሔር ልጆች ተግባር ነው። እነርሱ ደስተኛ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበረታታት አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በደመና ሥር በሚኖሩት እና በሚሄዱበት ሁሉ ጥላ በሚጥሉ ልጆቹ ሊከብር አይችልም። ክርስቲያን ከጥላ ይልቅ የፀሐይ ብርሃንን ማምጣት አለበት…፡፡ እርሱ ደስተኛ የፊት ገጽታን ያሳያል። 260 The Review and Herald, April 28, 1859.CGAmh 139.3

    ልጆች የደመና እና የሐዘንን ጨለማ ይጠላሉ። ልባቸው ለብርሃን፣ ለደስታ፣ ለፍቅር ምላሽ ይሰጣል።7Counsels on Sabbath School Work, 98.CGAmh 139.4

    ፈገግታ፣ ወላጆች፣ ፈገግታ—አንዳንድ ወላጆች— እንዲሁም አንዳንድ አስተማሪዎች፣ ራሳቸውም በአንድ ወቅት ልጆች እንደነበሩ የሚረሱ ይመስላሉ። ኮስታሮች፣ ሰብአዊነት የሌላቸው እና የሐዘን ተካፋይነት ስሜት የሌላቸው ናቸው…፡፡ ፊቶቻቸው በተለምዶ ኮስታራ እና የግሳጼ መግለጫን የተላበሰ ነው፡፡ የልጅነት ደስታ ወይም አስቸጋሪነት፣ የልጅነት ህይወት የቁንጥንጥነት እንቅስቃሴ በዓይኖቻቸው ፊት ይቅርታ አያገኝም። እዚህ ግባ የማይባሉ ተራ ስህተቶች እንደ ከባድ ኃጢአቶች ይቆጠራሉ። እንዲህ ዓይነቱ ቅጣት የክርስቶስ ዓይነቱ አይደለም። በዚህ አይነት መንገድ የሠለጠኑ ልጆች ወላጆቻቸውን ወይም አስተማሪዎቻቸውን ይፈራሉ፣ ነገር ግን አይወዷቸውም፡፡ የልጅነት የልምምዶቻቸውን ገጠመኞች አያካፍሏቸውም፡፡ ትልቅ ዋጋ ያላቸው የአዕምሮ እና የልብ ችሎታዎች በጋ ከመፈንዳቱ በፊት እስከ ሞት ድረስ እንደሚቀዘቅዝ ቀንበጥ ተክል ይሆናሉ፡፡ 261The Review and Herald, March 21, 1882.CGAmh 139.5

    ወላጆች፣ ፈገግታ፣ መምህራን ፈገግታ። ልብዎ ያዘነ እንደሆነ ፊትዎ ያለውን እውነታ አይግለጽ፡፡ አፍቃሪ እና አመስጋኝ ከሆነ ልብ የፀሐይ ብርሃን ገጽታዎን ያብራ። አምባገነን ክብራችሁን በመተው፣ ከልጆች ፍላጎቶች ጋር ራሳችሁን በማላመድ እንዲወዷችሁ አድርጉ። ኃይማኖታዊ እውነትን ልባቸው ላይ ማስረጽ ከፈለጋችሁ ወዳጅነትን ማፍራት ይኖርባችኋል፡፡ CGAmh 140.1

    ገጣሚ የሆነ ጸሎት—ሥራዎን በምስጋና መዝሙሮች አስደሳች ያድርጉ። በመንግሥተ ሰማይ መጽሐፍ ውስጥ ንጹህ መዝገብ እንዲኖርዎት የሚፈልጉ እንደ ሆነ በጭራሽ አይበሳጩ ወይም አይሳደቡ፡፡ ዕለታዊ ጸሎታችሁ “ጌታ ሆይ፣ የምችለውን ሁሉ እንድሠራ አስተምረኝ፡፡ የተሻለ ሥራ እንዴት መሥራት እንደምችል አስተምረኝ። ኃይልን እና ደስታን ስጠኝ፡፡”… በሚሰሩት ነገር ሁሉ ውስጥ ክርስቶስን ያሳዩ፡፡ ያኔ ህይወትዎ በብርሃን እና በምስጋና ይሞላል…፡፡ በጌታ አገልግሎት ውስጥ ልቦቻችን በደስተ ተሞልተው በደስታ ወደፊት በመራመድ፣ የምንችለውን ሁሉ እንስራ፡፡ 262Australasian Union Conference Record, November 15, 1903.CGAmh 140.2

    ልጆች አመስጋኝ እንዲሆኑ አስተምሯቸው—“አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ቸርነት ሁሉ ደስ ይበልህ፡፡” እርሱ በሚሰጠን ለጊዜያዊ በረከቶች እና ማናቸውም ምቾቶች ምስጋና እና ውዳሴ ለእግዚአብሔር መገለጽ አለበት። ከጸጋው ለተትረፈረፈው ሀብቱ ለእርሱ ክብርን ሊሰጡት በላይ ባሉት ዘላለማዊ ቤቶች ውስጥ እንዲኖሩ እያዘጋጃቸው ያሉ ቤተሰቦች እግዚአብሔር ይኖሩታል፡፡ ልጆች፣ በቤት ኑሮአቸው ውስጥ የመልካም ነገሮች ሁሉ ሰጪ ለሆነው አመስጋኝ እንዲሆኑ የተማሩ እና የሰለጠኑ ቢሆን ኖሮ ፣ በቤተሰቦቻችን ውስጥ የሰማያዊው ፀጋ አካልን ባየን ነበር። በቤት ኑሮ ውስጥ ደስታን ባየን ነበር፣ ወጣቶች ከእንደዚህ ዓይነት ቤቶች ወደ ትምህርት ቤት ክፍል እና ወደ ቤተ-ክርስቲያን ሲመጡም ከራሳቸው ጋር የአክብሮት እና የአምልኮን መንፈስ ይዘው በመጡ ነበር። እግዚአብሔር ከህዝቡ ጋር በሚገናኝበት መቅደስ ውስጥ በተገኙ፣ ለአምልኮው ስነስርዓቶች ሁሉ አክብሮት በኖራቸው፣ እና ለአምላካዊ ስጦታዎቹ ሁሉ ውዳሴ እና ምስጋና በቀረበ ነበር። CGAmh 140.3

    የእግዚአብሔር ቃል በጥንቷ እስራኤል ላይ በጥብቅ ትዕዛዝ እንደተላለፈው ሁሉ አሁን በትክክል ተፈፃሚ ቢሆን ኖሮ አባቶችና እናቶች ለልጆቻቸው ከፍተኛ ዋጋ ያለው ምሳሌ ይሆኑ ነበር…፡፡ እያንዳንዱን ጊዜያዊ በረከቶችን በአመስጋኝነት በተቀበሉ፣ የእያንዳንዱም የቤተሰብ አባል አመለካከት በእውነቱ ቃል የተቀደሰ ስለሆነ እያንዳንዱ መንፈሳዊ በረከቶች በእጥፍ የከበረ በሆነ ነበር። ጌታ ኢየሱስ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ ዱካ ከለጋሹ፣ ከአፍቃሪው እና ከሚንከባከበን አምላክ እንደሆነ በማወቅ የደግነት ሥጦታዎቹን ለሚያደንቁ፣ እና የምቾትና የመጽናናት ታላቅ ምንጭ፣ የማይቋረጥ የጸጋ ምንጭ መሆኑን ለሚገነዘቡ፣ ጌታ ኢየሱስ በጣም ቅርብ ነው፡፡263Manuscript Releases 6:7, 1907. CGAmh 141.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents