Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 54—መምህራን እና ወላጆች በጋራ ይስሩ

    የርህራሄ ማስተዋል አስፈላጊነት— በቤት ውስጥ ያሉ አስተማሪዎች እና በትምህርት ቤት ያሉ አስተማሪዎች አንዳቸው ስለ ሌላኛው ስራ የርህራሄ ማስተዋል ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በተመሳሳይ የሚስዮናዊነት መንፈስ ልጆችን በአካላዊ፣ በአእምሯዊና በመንፈሳዊ ሁኔታ ለመጥቀም አብረው ጥረት በማድረግ እንዲሁም ፈተናን መቋቋም የሚችል ባህሪይን ለማዳበር አብረው መሥራት አለባቸው፡፡ 611Counsels to Parents, Teachers, and Students, 157.CGAmh 301.1

    ወላጆች ልጆቻቸው በእንደዚህ ዓይነት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚያገኙትን ጥቅም ራሳቸው ቢገነዘቡ እና ከልባቸው ከአስተማሪው ጋር ቢተባበሩ በቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት አመካይነት የበለጠ መከናወን እንደሚችል ማስታወስ አለባቸው። ወላጆች ትዕግሥት በማጣት እና ጥበብ በጎደለው ቸልተኝነት ሳቢያ የተሰሩትን ስህተቶችን በጸሎት፣ በትዕግሥት፣ እና በይቅር ባይነት ማስተካከል ይችላሉ። ወላጆች እራሳቸው ትጉህ እና እግዚአብሔርን የሚፈራ መምህር ማህበረሰብ ውስጥ በመኖሩ ራሳቸውም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በማስታወስ፣ ከመምህሩ በጋራ አብረው ስራውን ይስሩ።612Counsels to Parents, Teachers, and Students, 155, 156. CGAmh 301.2

    አለመስማማት መልካሙን ተፅእኖ ዋጋ ያሳጣዋል — በጥቂቶች ልብ ውስጥ ተይዞ ያለ ያለመስማማት መንፈስ ሌሎች ላይ በመተላለፍ ትምህርት ቤቱ ማሳረፍ የሚችለውን ተጽዕኖ ያጠፋል፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ድነት ከመምህሩ ጋር ለመተባበር ዝግጁ እና የሚያሳስባቸው ካልሆነ በስተቀር በመካከላቸው ትምህርት ቤትን ለመመስረት ዝግጁ አይደሉም።3Testimonies For The Church 6:202.CGAmh 301.3

    የቡድን ሥራ ከቤት ውስጥ ይጀምራል— የትብብር ሥራ በቤት ኑሮ ከአባት እና ከእናት መጀመር አለበት፡፡ በልጆቻቸው ስልጠና ውስጥ የጋራ ኃላፊነት አለባቸው፣ አብረው መስራትም የእነርሱ ቀጣይ ጥረት መሆን አለበት፡፡ እርስ በእርስ ለመደጋገፍ ከእርሱ እርዳታን በመፈለግ እራሳቸውን ለእግዚአብሔር ይስጡ፡፡ ልጆቻቸው ለአምላክ ተማኝ፣ ለመርኾ ታማኝ፣ እና ለእራሳቸው እና ከእነርሱ ጋር ግንኙነት ለሚያደርጉ ሁሉ ታማኝ እንዲሆኑ ያስተምሯቸው፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ስልጠና ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ሲላኩ የረብሻ ወይም የጭንቀት መንስኤ አይሆኑም፡፡ እነርሱ ለመምህራኖቻቸው ድጋፍ እና ለተማሪ ጓደኞቻቸው ምሳሌ እና ማበረታቻ ይሆናሉ፡፡ 613Education, 283.CGAmh 301.4

    ልጆች የሥልጠናችሁን ተጽዕኖዎች ወደ ትምህርት ቤት ክፍል ይዘው ይሄዳሉ፡፡ ኃይማኖተኛ ወላጆች እና መምህራን በአንድነት በሚሰሩበት ጊዜ፣ የልጆች ልብ በቤተክርስቲያን ውስጥ ላለው የእግዚአብሔር ሥራ ጥልቅ ፍላጎት ለማሳየት ዝግጁ ይሆናሉ፡፡ ቤት ውስጥ የበለጸገው ፀጋ ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣል፣ እግዚአብሔርም ይከብርበታል፡፡ 614 Letter 29, 1902.CGAmh 302.1

    ወላጆች የልጆቻቸውን ተገቢ የሆነውን ተግሣጽ ችላ እስከሚሉበት ድረስ በጊዜያዊ ኑሮ ሥራ እና ተድላዎች እጅግ የተጠመዱ ከሆነ፣ የመምህሩ ስራ እጅግ ከባድ እና አዳጋች ብቻ ሳይሆን ብዙውን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ፍሬ አልባ ይሆናል። 615The Review and Herald, June 13, 1882.CGAmh 302.2

    የመምህሩ ሥራ ተጨማሪ ነው— በባህሪይ ምስረታ የቤት ውስጥ ተጽዕኖ ያህል ሌሎች ተጽዕኖዎች ዋጋ አይኖራቸውም፡፡ የመምህሩ ሥራ በወላጆች ሥራ ላይ ተጨማሪ መሆን አለበት፣ ነገር ግን የወላጆችን ሥፍራ መውሰድ የለበትም፡፡ የልጁን ደህንነት በሚመለከቱ ጉዳዮች ሁሉ የወላጆች እና የመምህራን የትብብር ጥረት መሆን አለበት፡፡7Education, 283.CGAmh 302.3

    በቤት ውስጥ ለልጁ የሚሰጠው መመሪያ አስተማሪውን የሚረዳ መሆን አለበት፡፡ በቤት ውስጥ የንጽናን፣ የሥርዓታዊነትን እና የጠንቃቃነትን አስፈላጊነት ልጁ ቤት ውስጥ መማር አለበት፤ እነዚህ ትምህርቶች በትምህርት ቤትም ውስጥ መደጋገም አለባቸው። 616Manuscript Releases 4:5, 1912.CGAmh 302.4

    ልጁ ወደ ትምህርት ቤት ለመላክ ዕድሜው ሲደርስ፣ መምህሩ ከወላጆቹ ጋር መተባበር አለበት፣ እንዲሁም በጉልበት የሚሰሩ ስራዎች ስልጠና የትምህርት ቤቱ ጥናቶች አካል ሆኖ መቀጠል አለበት። ትምህርት ቤቶች ውስጥ እንደዚህ ዓይነቱን ሥራ የሚቃወሙ ብዙ ተማሪዎች አሉ፡፡ ጠቃሚ የሆኑ የንግድ ሥራን የመሳሰሉትን መማር፣ እንደ ውርደት ይቆጥራሉ፤ ነገር ግን እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ስለ እውነተኛ ክብር የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው፡፡ 617Counsels to Parents, Teachers, and Students, 146.CGAmh 302.5

    ቤት በትምህርት ቤት በኩል ሊባረክ ይችላል— እርሱ [መምህሩ] በትእግስት፣ በትጋት፣ እና በጽናት፣ ክርስቶስ በሰራባቸው መስመሮች ውስጥ ቢሠራ፣ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የተደረገው የታሃድሶ ተግባር ይበልጥ ንጹህ እና ሰማያዊ ከባቢ አየርን በማምጣት በልጆቹ ቤት ውስጥ ይስፋፋል፡፡ ይህ በእውነቱ ከፍተኛው ደረጃ ያለው የሚስዮናዊነት ሥራ ነው። 618Counsels to Parents, Teachers, and Students, 157. CGAmh 303.1

    ንቁ መምህር ተማሪዎቹን አጋዥ ወደ ሆኑ ተግባራት ለመምራት ብዙ እድሎችን ያገኛል። ትናንሽ ልጆች በተለይም መምህር ላይ ያልተገደበ እምነት እና አክብሮት እንዳላቸው ይስተዋላል፡፡ ቤት ውስጥ በምን መንገድ መርዳት እንዳለባቸው፣ ለዕለታዊ ሥራዎች ማሳየት ያለባቸውን ታማኝነት፣ ለታመሙ ወይም ለችግረኞች የሚደረግ አገልግሎት በተመለከተ እርሱ ሐሳብ ሲሰጥ ፍሬ ሳያፈራ የሚቀረው አልፎ አልፎ ብቻ ነው፡፡ በዚህ መንገድ እንደገና እጥፍ ትርፍ ያገኛል። በርህራሄ የቀረበ ሀሳብ ወደ ተናጋሪው ተመልሶ ይመጣል፡፡ በወላጆች በኩል የሚታይ አመስጋኝነት እና ትብብር የመምህሩን ሸክም ያቀልላል፣ ጎዳናውንም ብሩህ ያደርጋል።11Education, 213.CGAmh 303.2

    ወላጆች የአስተማሪውን ሥራ ማቅለል ይችላሉ— ወላጆች የእነርሱን ድርሻ በታማኝነት ካከናወኑ፣ የአስተማሪው ስራ በጣም ቀለል ያለ ይሆናል። ተስፋው እና ድፍረቱ ይጨምራል፡፡ ልባቸው በክርስቶስ ፍቅር የተሞሉ ወላጆች ስህተት ከመፈለግ ይቆጠቡ እና ለልጆቻቸው አስተማሪ እንዲሆኑ የመረጡትን ለማበረታታት እና ለመርዳት አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እርሱም ልክ እንደ እነርሱ ሁሉ በሥራው ጠንቃቃ እንደሆነ ለማመን ፈቃደኞች ይሆናሉ፡፡ 619Counsels to Parents, Teachers, and Students, 157.CGAmh 303.3

    ወላጆች ኃላፊነቶቻቸውን ሲገነዘቡ፣ መምህራኑ እንሲሰሩ የሚቀረው ሥራ እጅግ አናሳ ይሆናል፡፡ 620Counsels to Parents, Teachers, and Students, 148.CGAmh 304.1

    ወላጆች ለመምህሩ አማካሪ ሊሆኑ ይችላሉ— የእግዚአብሔርን ፍቅር ቤታችን ውስጥ ማውራት አለብን፤ በትምህርት ቤታችን ውስጥ ልናስተምር ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች ወደ ቤት እና ወደ ትምህርት ቤት ሕይወት እንዲመጣ መደረግ አለባቸው። ወላጆች ለተገለጠው የጌታ ፈቃድ የመገዛት ግዴታቸውን በሙላት ከተገነዘቡ በትምህርት ቤታችን እና በትምህርት ጉዳዮች ላይ ጥበበኛ አማካሪዎች መሆን ይችላሉ፤ ምክንያቱም እነርሱ ቤት ውስጥ ያላቸው የስልጠና ልምድ ልጆች እና ወጣቶች ከሚመጡባቸው ፈተናዎች እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ያስተምራቸዋል። ወጣቱን ለሰማይ በማሰልጠን ሥራ አስተማሪዎች እና ወላጆች ከእግዚአብሔር ጋር አብረው የሚሠሩ ሠራተኞች የሚሆኑት በዚህ መንገድ ነው፡፡ 621Letter 356, 1907.CGAmh 304.2

    የልጆችን ባህሪይ እንዲሁም የአካላቸውን ከተለምዶ ወጣ ያለ ሁኔታ ወይም ጉድለቶች በተመለከተ የወላጆችን ጥልቅ እውቀት ለመምህሩ ቢያካፍሉ ለእርሱ ትልቅ ድጋፍ ነው፡፡ በጣም ብዙ ሰዎች ይህንን ባለመገንዘባቸው መጸጸት አለባቸው፡፡ በአብዛኛዎቹ ወላጆች የመምህሩ ብቃትን ራሳቸው በማሳወቅ ወይም ከእርሱ ጋር ተባብሮ በመስራት ረገድ አነስተኛ ፍላጎት ይንጸባረቃል፡፡ 622Education, 284.CGAmh 304.3

    እነርሱ [ወላጆች] መምህሩ ጋር መተባበርን፣ ብልሃታዊ ተግሣጽን ማበረታታትን እና ልጆቻቸው ለሚያስተምረው ሰው ብዙ መጸለይን ግዴታቸው እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል። 623Fundamentals of Christian Education, 270.CGAmh 304.4

    መምህራን ለወላጆች አማካሪዎች ሊሆኑ ይችላሉ — ወላጆች ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን ከመምህሩ ጋር ማስተዋወቅ የተለመደ ባለመሆኑ፣ መምህራን ከወላጆች ጋር ራሳቸውን ለማስተዋወቅ መፈለጉ በጣም አስፈላጊ ነው። የተማሪዎቹን ቤቶች መጎብኘት እና የሚኖሩበትን ተጽዕኖ እና አከባቢ ማወቅ አለበት። ከቤታቸው እና ከህይወታቸው ጋር በአካል በመገናኘት፣ ከተማሪዎቹ ጋር የሚያቆራኙትን ግንኙነቶች ይጠነክራል፣ የተለያዩ ፀባዮቻቸው እና ስሜቶቻቸው ይበልጥ በተሳካ ሁኔታ እንዴት መያዝ እንዳለባቸውም ይማራል፡፡CGAmh 304.5

    መምህሩ በቤት ውስጥ ትምህርት ላይ ትኩረት ካደረገ፣ ሁለት እጥፍ ጥቅሞችን ያስገኛል፡፡ ብዙ ወላጆች በሥራና በኑሮ ተጠምደው ለልጆቻቸው መልካም ሕይወት በጎ ተጽዕኖ ማሳደር የሚችሉባቸውን አጋጣሚዎች ያጣሉ፡፡ መምህሩ እነዚህ ወላጆች ችሎታዎቻቸው እና ዕድሎቻቸውን በማወቅ ወደ ማነቃቃት እንዲመጡ ብዙ ነገር ማድረግ ይችላል፡፡ የኃላፊነታቸው ስሜት ከባድ ሸክም የሆነባቸውን፣ ልጆቻቸው ጥሩ እና ጠቃሚ ወንዶች እና ሴቶች እንዲሆኑ የሚጨነቁ ሌሎች ሰዎችን ያገኛል፡፡ ብዙውን ጊዜ መምህሩ እነዚህን ወላጆች ሸክማቸውን ይሸከሙ ዘንድ ሊረዳቸው ይችላል፣ እናም መምህሩና ወላጆች እርስ በእርስ በመመካከር ይበረታታሉ እንዲሁም ይጠናከራሉ፡፡ 624Education, 284, 285.CGAmh 305.1