Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል 9—የባህሪይ ግንባታ መሰረታዊ ነገሮች

    ምዕራፍ 36—የልጅነት ዕድሜ ጠቀሜታዎች

    የልጅነት ጊዜ በጣም ወሳኝ ጊዜ ነው—በልጆች የልጅነት ጊዜ ሥልጠና ላይ ከመጠን በላይ የሆነ ጫና ማረፍ የለበትም። በመጀመሪያዎቹ ሰባት ዓመታት ልጁ የሚማራቸው ትምህርቶች በመጪዎቹ ዓመታት ከሚማረው ሁሉ በላይ ባህሪይውን ከመቅረጽ ጋር እጅግ የተዛመዱ ናቸው፡፡ 346Manuscript Releases 2:1903. CGAmh 183.1

    ከልጅነቱ ጀምሮ የልጁ ባሕርይ በመለኮታዊ ዕቅድ መሠረት መቀረጽ እና መሠራት አለበት። እየተከፈተ ባለው አእምሮው ውስጥ በጎነት መቀረጽ አለበት፡፡ 347 The Signs of the Times, September 25, 1901. CGAmh 183.2

    ዓለም የራሷን ማህተም በአእምሮው እና በልቡ ላይ ከማሳረፏ በፊት የወላጆች ሥራ ከልጁ የጨቅላነት ጊዜ መጀመር አለበት። 348The Review and Herald, August 30, 1881 CGAmh 183.3

    የተጋላጭነት ዕድሜ—በልጁ ሕይወት የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ አዕምሮ ወደ መልካምነት ወይም ክፋት ለመቀረጽ በጣም ተጋላጭ ነው፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በትክክለኛውም ሆነ በተሳሳተ አቅጣጫ ወሳኝ እድገት ይካሄል፡፡ በአንድ በኩል ብዙ እርባነ-ቢስ መረጃ፤ በሌላ በኩል ደግሞ፣ በጣም ወሳኝ፣ ዋጋ ያለው እውቀት ይገኛል። የአዕምሮ ጥንካሬ፣ ከፍተኛ ዕውቀት፣ የኦፊር ወርቅ ሊገዛቸው የማይችል ንብረቶች ናቸው። ዋጋቸው ከወርቅ ወይም ከብር የላቀ ነው። 349Counsels to Parents, Teachers, and Students, 132. CGAmh 183.4

    መጀመሪያ የተቀረጹ ስሜቶች እምብዛም የማይረሱ ናቸው—ጨቅላ ሕፃናት፣ ልጆች፣ ወይም ወጣቶች ከአባት፣ ከእናት ወይም ከማናቸውም የቤተሰብ አባል ትዕግሥት የለሽ ቃል መስማት የለባቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ ገና በልጅነታቸው የተቀረጹባቸውን ስሜቶችን ይወስዳሉ፣ እና ዛሬ ወላጆች እንደሚያደርጓቸው፣ ነገ፣ እና በሚቀጥለው እና በሚቀጥለው እነርሱም እንዲሁ ይሆናሉ። በልጅ ላይ የተቀረጹ የመጀመሪያዎቹ ትምህርቶች እምብዛም አይረሱም…፡፡CGAmh 183.5

    በልጅነት መጀመሪያ ላይ በልብ ላይ የተቀረጹ ስሜቶች ከዓመታት በኋላ ይገለጣሉ፡፡ ተቀብረተው ሊቆዩ ይችላሉ፣ ነገር ግን እምብዛምም አይጠፋም፡፡ 350Manuscript Releases 5:7, 1897. CGAmh 184.1

    መሠረቱ በመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ሊጣል ይገባል—እናቶች፣ በሕይወታቸሁ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ ልጆቻችሁን በትክክል ሥርዓት ማስያዛችሁን እርግጠኛ ሁኑ፡፡ ፍላጎቶቻቸውን እና ምኞቶቻቸውን እንዲመሰርቱ አትፍቀዱላቸው፡፡ እናት ለልጅዋ አእምሮ መሆን አለበት፡፡ የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ትናንሾቹ ቀንበጦች የሚቃኑበት ጊዜ ነው፡፡ እናቶች ከዚህ ወቅት ጋር ተያይዞ ያለው ዋጋ ሊገነዘቡ ይገባል፡፡ መሠረቱ የሚጣለው በዚያን ጊዜ ነው፡፡CGAmh 184.2

    አብዛኛውን ጊዜ እንደሚሆነውም እነዚህ የመጀመሪያ ትምህርቶች ጉድለቶች ካሉባቸው፣ ስለ ክርስቶስ ስትሉ፣ ስለ ልጆቻችሁ መጻኢ ጊዜ እና ዘላለማዊ ጥቅም ስትሉ፣ የሠራችሁትን ስህተት አርሙ። ራስን መግዛትንና መታዘዝን ማስተማርን ለመጀመር ልጆቻችሁ ሦስት ዓመት እስኪሆናቸው ድረስ ከጠበቃችሁ፣ ምንም በጣም ከባድ ቢሆንም እንኳን፣ ይህን ለማድረግ አሁን እሹ፡፡ 351Manuscript Releases 6:4, 1899. CGAmh 184.3

    በጥቅሉ የሚታሰበውን ያህል ከባድ አይደለም—ሕፃናት ፍቃዳቸው ሕግ እንዳይሆን እና ድንገት ደራሽ አምሮታቸው እርካታን እንዳያገኝ ልጆች ከጨቅላነታቸው ጀምሮ ቢማሩ ኖሮ ብዙ የወላጅ ጭንቀት እና ሀዘን መቀረት በቻለ ነበር፡፡ ትንሹ ልጅ ቁጣው እንዲበርድ ማድረግ እና ፍላጎቱን መግራትን ማስተማር እንደሚታሰበው በጣም ከባድ አይደለም። 352Pacific Health Journal, April, 1890 CGAmh 184.4

    ይህንን ስራ ለሌላ ጊዜ አያስተላልፉ—ብዙዎች ወላጆች ሕጻናት ካደጉ በኋላ ስህተትን ለማገድ እና ትክክለኛውን ነገር ለማስተማር እጅግ ጠንቃቃ ይሆናሉ ብለው በማሰብ በልጆቻቸው ሕይወት የመጀመሪያ ዓመታት ላይ ኃላፊነታቸውን ችላ ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህንን ሥራ የሚያከናውኑበት ምቹ ጊዜ ልጆቻቸው በእቅፎቻቸው ውስጥ ሕፃናት ሳሉ ነው፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን ያለአግባብ እንክብካቤ ማድረግ እና ቀልደኞች እንዲሆኑ ማድረግ ትክክል አይደለም፣ እነርሱን መበደልም ትክክል አይደለም፡፡ ጽኑ፣ ቆራጥ፣ ቀጥተኛ የሆነ አካሄድ ጥሩ ውጤቶችን ያስገኛል፡፡ 353Testimonies For The Church 4:313.CGAmh 184.5

    በጨቅላ ልጆቻቸው ውስጥ እነርሱ እያበረታቱ ወዳለው የተሳሳቱ ልማዶች የወላጆችን ትኩረት በምማርክበት ጊዜ አንዳንድ ወላጆች በፍጹም ግድ የለሾች ይሆናሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ በፈገግታ “ትናንሽ ውዶች! በምንም መንገድ እነርሱን መቃረንን ልታገሥ አልችልም፡፡ ሲያድጉ የተሻለ ነገር ያደርጋሉ፡፡ በዚያን ጊዜ በእነዚህ ግልፍተኛ ስሜቶቻቸው ያፍራሉ፡፡ ትናንሽ ልጆች ላይ ከሚገባ በላይ ጠንቃቃ እና ጥብቅ መሆን እጅግ መልካም አይደለም። እነርሱ እነዚህን ውሸት የመናገር፣ የማታለል እና ሰነፍ እና ራስ ወዳድ የመሆንን ልምዶችን እያስወገዱ ይሄዳሉ” ይላሉ፡፡ በእርግጥም ለእናቶች ጉዳዩን ለመተው እጅግ ቀላሉ መንገድ ይህ ነው፣ ሆኖም ግን ይህ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚጣጣም አይደለም፡፡ 354Manuscript Releases 4:3, 1900. CGAmh 185.1

    ሰይጣን ጨቅላ ሕፃናት ላይ ያለውን የይገባኛል ጥያቄ ጥረት ማስተጓጎል—ወላጆች፣ በአጠቃላይ ስራዎቻችሁን በጊዜ መጀመር ይሳናችኋል፡፡ የመጀመሪያውን የሰብል የዘር በመዝራት ሰይጣን የልብን መሬት ቀድሞ እንዲይዝ ትፈቅዱለታላችሁ። 355The Review and Herald, April 14, 1885.CGAmh 185.2

    ሰይጣን ልጆቻችሁን እንዳይቆጣጠር እና ከእቅፋችሁ ሳይወጡ እንዳይወስድባችሁ መሥራት ያለባችሁ ሥራ አለ፡፡ እናቶች ሆይ፣ የጨለማ ኃይላት ትናንሽ ልጆቻችሁን እንዳይቆጣጠሩ መመልከት አለባችሁ፡፡ ጠላት በቤታችሁ ውስጥ የጨለማን ባንዲራ እንዳያቆም ፈቃዳችሁን አስተካከሉ፡፡ 356 The Signs of the Times, July 22, 1889. CGAmh 185.3

    ለተግባራዊ ሕይወትም ማዘጋጀት—ለልጅ ጊዜያዊ እና ዘላለማዊ ጉዳዮች በመጀመሪያዎቹ አሥራ ሁለት ወይም አስራ አምስት ዓመታት ውስጥ ምን ያህል እውቀት ሊገኝ እንደሚችል በጥንቃቄ ለመመርመር ጊዜ የሚወስዱት በጣም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። በእነዚህ የመጀመሪያዎቹ የህይወት ዓመታት ውስጥ ልጆች የመፅሀፍትን ዕውቀት ማግኘት ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊ ህይወት አስፈላጊ የሆነውን ስነ-ጥበባት መማር አለባቸው፤ የሁለተኛው ለመጀመሪያው ሲባል ቸል ሊባል አይገባም፡፡ 12Manuscript Releases 4:3, 1900. CGAmh 185.4

    የናፖሊዮን ቅርስ—የናፖሊዮን ቦናፓርቴ ባህሪይ ላይ የልጅነት ሥልጠናው ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሮበታል፡፡ ጥበብ የጎደላቸው አስተማሪዎች ሠራዊት በማስመሰል እና እንደ አዛዥ በራሳቸው ላይ እርሱን በመሾም ድል የማድረግን ፍቅር በውስጡ አነሳሱ። ለጠብና ደም መፋሰስ ተግባሩ መሠረት የተጣለው እዚህ ጋር ነበር። የወጣቱን ልብ በወንጌል መንፈስ በመሙላት ጥሩ ሰው እንዲሆን ተመሳሳይ እንክብካቤ እና ጥረት ቢደረግለት ኖሮ የእርሱ ታሪክ ምን ያህል ልዩ መሆን በቻለ ነበር፡፡ 357 The Signs of the Times, October 11, 1910. CGAmh 186.1

    ሐም እና ቮልቴይር—ተጠራጣሪው ሐም በልጅነቱ በእግዚአብሔር ቃል ላይ ጠንቃቃ አማኝ ነበር ይባላል፡፡ ከተከራካሪ ማህበረሰብ ጋር ከመገናኘቱ የተነሳ ክህደትን በመወገን ክርክሮችን እንዲያቀርብ ተሰየመ፡፡ በቆራጥነት እና በትጋት በማጥናት ብልህ እና ንቁ አዕምሮው በአደናጋሪ ጥርጣሬ ተሞላ። ወዲያውኑ አሳሳች ትምህርቶቹን ማመን ጀመረ፣ እናም ቀጥሎ ያለው ሕይወቱ ሙሉ በሙሉ የክህደት ጥቁር አሻራን ይዞ ቀረ፡፡ CGAmh 186.2

    ቮልቴይር የአምስት ዓመት ልጅ እያለ የክህደት ግጥም በማህደረ ትውስታው ነበር፣ አደገኛ ተጽዕኖውም በጭራሽ ከአእምሮው አልጠፋም፡፡ እርሱ ሰዎች ከእግዚአብሔር እንዲርቁ የሰይጣን እጅግ ውጤታማ ወኪሎች አንዱ ሆነ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፍርድ ቀን በመነሳት ስለ ነፍሳቸው ጥፋታ ቮልቴይርን ተወቃሽ ያደርጉታል፡፡ CGAmh 186.3

    እያንዳንዱ ወጣት በልጅነት ዕድሜው በሚንከባከባቸው ሐሳቦች እና ስሜቶች የሕይወት ታሪኩን እየወሰነ ነው፡፡ በወጣትነት የተቀረጹ ትክክለኛ፣ ደግ፣ እና ጨዋ ልማዶች የባህሪይ አካል ይሆኑና በተለሞዶ በግለሰቡ መላ የህይወት ጉዞ ላይ አሻራቸውን ይጥላሉ፡፡ ወጣቶች እንደ ምርጫቸው ምግባረ ብልሹ ወይም ጥሩ ሥነ-ምግባር ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ትልቅ ወንጀል እና ክፋት እንደሚሠሩ ሁሉ ለእውነተኛ እና ለከበሩ ሥራዎች ተለይተው ሊታወቁ ይችላሉ፡፡ 358Ibid. CGAmh 186.4

    የሃና ሽልማት—የማይገመት ዋጋ ያላቸው ዕድሎች፣ ወሰን የለሽ ውድ የሆኑ እድሎች ለእያንዳንዷ እናት ተሰጥቷታል፡፡ በነቢዩ ሳሙኤል ሕይወት የመጀመሪያዎቹ ሦስት ዓመታት ውስጥ እናቱ መልካምና ክፉውን መለየት እንዲችል በጥንቃቄ አስተማረችው፡፡ በዙሪያው ባሉት የተለመዱ ነገሮች ሁሉ ሀሳቡን ወደ ፈጣሪ ለመምራት ፈለገች፡፡ ልጇን ለጌታ ለመስጠት የገባችውን ስእለት ለመፈጸም በእግዚአብሔር ቤት ለማገልገል እንዲሠለጥን በሊቀ ካህኑ በኤሊ እንክብካቤ ሥር አደረገችው…፡፡ የልጅነት ሥልጠናው ክርስቲያናዊ ሐቀኝነቱን ጠብቆ ለማቆየት እንዲመርጥ መርቶታል። የሐና ሽልማት ምን ያህል ይሆን! የእርሷ የታማኝነት ምሳሌ እንዴት ያለ ማበረታቻ ነው! 359The Review and Herald, September 8, 1904. CGAmh 187.1

    የዮሴፍ አዕምሮ እንዴት እንደተጠበቀ—ዮሴፍ በወጣትነቱ በእግዚአብሔር ላይ ያለውን እምነት እንዲገልጽ ያዕቆብ የሰጠው ትምህርት እና ስለ እርሱ የፍቅር ደግነት ውድ መረጃዎች ደጋግሞ ለእርሱ መንገሩ እና የማይቋርጠው እንክብካቤው እርሱ በጣኦት አምላኪዎች መካካል በግዞት በነበረበት ጊዜ የሚያስፈልጉት ትምህርቶች ነበሩ፡፡ በፈተና ጊዜ እነዚህን ትምህርቶች ተግባራዊ አደርጓቸዋል፡፡ እጅግ ከባድ ፈተና ውስጥ በነበረበት ወቅት እንዲተማመንበት ወደ ተማረው የሰማይ አባቱ ተመለከተ። የዮሴፍ አባት መመሪያዎች እና ምሳሌነት ተቃራኒ ባህርይ የነበረው ቢሆን ኖሮ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ምሪት የፃፈው ቀለም በቅዱሱ ታሪክ ላይ በዮሴፍ ባህሪይ ላይ የተንጸባረቀውን ሐቀኝነት እና መልካምነት ባልዘገበ ነበር፡፡ በልጅነቱ በአዕምሮው ላይ የተቀረጹ ትምህርቶች በታላቅ የፈተና ሰዓት ልቡን ጠብቀው “እንዴት ይህን ታላቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ኃጢአትን እሠራለሁ?” ብሎ እንዲናገር መራው፡፡ 16 Good Health, January, 1880.CGAmh 187.2

    የጥበብ ስልጠና ፍሬ—በእናቶች ላይ ያለ ማንኛውም ድክመት እና ውሳኔ ያለ ማድረጋቸው በፍጥነት በልጆቻቸው መታየቱ እና ከዚያም ዝንባሌያቸውን በመከተል እንዲቀጥሉ በማድረግ ፈታኙ በአዕምሮአቸው ላይ መሥራቱ አሳዛኝ እውነታ ነው። ወላጆች ለልጆቻቸው ተገቢውን ሥልጠና ለመስጠት እንዲጠቀሙባቸው አስፈላጊ የሆኑትን ችሎታዎቻቸውን ቢያዳብሩ፣ ልጆች ሊከተሏቸው የሚገባቸውን ህጎች በግልፅ ቢያስቀምጡላቸው እና እነዚህ ህጎች እንዲጣሱ ባይፈቅዱ ኖሮ፣ ጌታ ከወላጆች እና ከልጆችም ጋር አብሯቸው ይሠራል፣ እናም ይባርካቸዋል፡፡ 360Manuscript Releases 13:3, 1898.CGAmh 187.3

    ልጆች ገና በለጋ ዕድሜያቸው ለምግባረ-ብልሹነት ተጽዕኖዎች ተጋላጭ ይሆናሉ፣ ነገር ግን ክርስቲያን ነን ባይ ወላጆች የራሳቸውን የአስተዳደር ክፋት አይገነዘቡትም፡፡ ምነው በመጀመሪያዎቹ ዓመታት ለልጅ ማድላት የባህሪውን ዝንባሌ እና ዘለአለማዊ ሕይወቱ ወይም ለዘላለማዊ ጥፋቱ ዕጣ ፈንታን እንደሚወስን በተገነዘቡ! ልጆች ለሥነ-ምግባራዊ እና ለመንፈሳዊ ተጽዕኖዎች የተጋለጡ ናቸው፣ እናም በልጅነት በብልሃት የሰለጠኑ ልጆች አንዳንድ ጊዜ ሊሳሳቱ ይችሉ ይሆናል፣ ነገር ግን ከትክክለኛው መንገድ እጅግ ርቀው አይጠፉም። 361The Signs of the Times, April 16, 1896. CGAmh 188.1