Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ለአንባቢያን

    ወላጆች ልጆቻቸውን ከራሳቸው ጋር ወደ እግዚአብሔር ከተማ መግቢያ በር አምጥተው፣ “ልጆቼ ጌታን ይወዱ ዘንድ፣ ፈቃዱን ያደርጉ ዘንድ እና እርሱን ያከብሩ ዘንድ ለመምራት ሞክሬአለው” በማለት ማምጣት ልዩ መብታቸው ነው፡፡ ለእነዚህ በሩ ይከፈትላቸውና ወላጆችና ልጆች ይገቡበታል፡፡ ነገር ግን ሁሉም አይገቡም፡፡ አንዳንዶች ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን በማስገዛት ያልተለወጡ፣ ከልጆቻቸው ጋር ውጭ ይተዋሉ፡፡ አንድ እጅ ወደ ላይ ይነሳና፣ እንዲህ የሚሉ ቃላት ይነገራል፣ “የቤት ተግባራችሁን ችላ ብላችኋል፡፡ ነፍሳትን ለሰማያዊ ቤት ማዘጋጀት ይችል የነበረውን ተግባር መሥራት አልቻላችሁም፡፡ መግባት አትችሉም፡፡” ልጆች እንዳይገቡ በሮቹ ይዘጋሉ፣ ምክንያቱም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማድረግን አልተማሩም፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ወላጆችም እንዳይገቡ በሮቹ ይዘጋሉ፣ ምክንያቱም በእነርሱ ላይ የተጣለውን ኃላፊነት ችላ ብላዋል፡፡ [Manuscript 31, 1909.]CGAmh 15.1

    አንድም ሰው ኃላፊነቱን በተመለከተ እንዳይስት ከእግዚአብሔር ቃልና ከመንፈሱ ምስክሮች ብርሃን ሲበራ ቆይቷል፡፡ እግዚአብሔር ወላጆች ልጆቻቸው እርሱን እንዲያውቁና መጠይቆቹንም ያከብሩ ዘንድ ይጠብቃል፤ እንደ ጌታ ቤተሰብ ትናንሽ አባላት፣ መልካም ባሕርይና ተወዳጅ አመል ይኖራቸው ዘንድ፣ ሰማያዊውን አዳራሽ ሊያበሩ ብቁ ይሆኑ ዘንድ ትናንሽ ልጆቻቸውን ማሰልጠን ይኖርባቸዋል፡፡ ኃላፊነታቸውን ችላ በማለትና ልጆቻቸው በስህተት ውስጥ እንደፈለጉ ይሆኑ ዘንድ ልቅ በመልቀቅ፣ ወላጆች ልጆቻቸው ላይ የእግዚአብሔርን ከተማ በር ይዘጋሉ፡፡ ይህ እውነታ በወላጆች ልብ ላይ ተጽዕኖ መፍጠር አለበት፤ መንቃትና ለረጅም ጊዜያት ችላ ያሉትን ተግባራቸውን ማንሳት አለባቸው፡፡ [Testimonies for the Church 5:325, 326.] ኤለን ጂ ኋይት፡፡ CGAmh 15.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents