Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 74—እያንዳንዱ ቤት ቤተ ክርስቲያን ነው

    ወላጆች የእግዚአብሔር ተወካዮች መሆን አለባቸው— በቤት ሕይወት ውስጥ እያንዳንዱ ቤተሰብ የሰማዩ አምላክ ቤተ ክርስቲያን ውብ ምሳሌ የሆነ ቤተ ክርስቲያን መሆን አለበት፡፡ ወላጆች ለልጆቻቸው ያለባቸውን ኃላፊነት ከተገነዘቡ በማንኛውም ሁኔታ በእነርሱ ላይ መበሳጨት እና መናደድ የለባቸውም፡፡ ይህ ማንኛውም ልጅ ሊማረው የሚገባ ዓይነት ትምህርት አይደለም፡፡ እጅግ አያሌ ልጆች ስህተት ፈላጊዎች፣ ግልፍተኞች፣ ተናዶች፣ ስሜታዊ የሆኑበት ምክንያት ቤት ውስጥ ስሜታዊ እንዲሆኑ ስለሚፈቀድላቸው ነው፡፡ ወላጆች ቀና የሆነውን መርህ የሚያደፋፍሩ እና ማንኛውንም የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚያርሙ ለልጆቻቸው በእግዚአብሔር ቦታ የተቀመጡ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ 960Letter 104, 1897.CGAmh 458.1

    የልጆች የግብረ ገብ ባህሪይ በወላጆች እና በመምህራን ችላ ከተባለ ፣ ፈር መልቀቃቸው እርግጥ ነው፡፡ 961The Review and Herald, March 30, 1897.CGAmh 458.2

    ብቸኛው ከለላ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖት ነው— በጥቅሉ ሲታይ ወጣቱ ብዙም የግብረ ገብ ጥንካሬ የለውም። ይህ በልጅነት ጊዜ ችላ የተባለ ትምህርት ውጤት ነው። ስለ እግዚአብሔር ባሕርይ እና ለእርሱ ያለብንን ግዴታዎችን ማወቅ አነስተኛ ውጤት እንዳለው መታየት የለበትም። ለወጣቶች ብቸኛው ከለላ የመጽሐፍ ቅዱስ ሃይማኖት ነው፡፡3Testimonies For The Church 5:23, 24.CGAmh 458.3

    የእግዚአብሔር ተስፋዎች እና ትዕዛዛት በልጁ ውስጥ አመስጋኝነት እና አክብሮትን እንዲያነቃቁ ህይወታቸው የመለኮታዊ እውነተኛ ነፀብራቅ የሆኑ ወላጆች ደስተኞች ናቸው፤ የወላጆች ርኅራኄ፣ ፍትህ እና ትዕግሥት የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ፍትህ እና ትዕግስት ለልጁ የሚያብራራ፤ እና ልጁ እንዲወዳቸው፣ እንዲያምናቸው እና እንዲታዘዛቸው የሚያስተምሩ ወላጆች የሰማይ አባቱን እንዲወድድ፣ እንዲያምን እና እንዲታዘዘው እያስተማሩት ናቸው፡፡ ለልጁ እንዲህ ዓይነቱን ስጦታ የሚሰጡ ወላጆች በዘመናት ሁሉ ካለው ስጦታ ውድ የሆነውን ማለትም እስከ ዘላለም ድረስ የሚዘልቅ ሀብት ሰጥተውታል ማለት ነው፡፡ 962Prophets and Kings, 245.CGAmh 458.4

    የቤት ውስጥ ኃይማኖት ከሌለ እናምናለን ብሎ መናገር ዋጋ ቢስ ነው— የዕለት ተዕለት የሕይወት እንቅስቃሴዎች ጸባያችን እና ባሕሪያችንን የሚመዝን እና የሚቀርጽ ነው፡፡ የቤት ውስጥ ሃይማኖት ከሌለ እናምናለን ብሎ መናገር ዋጋ የለውም። ስለዚህ የቤቱ ክበብ ውስጥ ካሉ ሰዎች ከንፈሮች ላይ ርህራሄ የጎደለው ቃል አይውጣ። ከባቢውን አየር ለሌሎች ሰዎች በርህራሄ በማሰብ መልካም መዓዛ እንዲሞላ አድርጉ፡፡ ወደ ሰማይ የሚገቡት በሙከራ ጊዜ ውስጥ የሰማያዊ ተጽዕኖን የመተንፈስ ባህርይ የቀረጹ ብቻ ናቸው። በመንግሥተ ሰማያት ቅዱስ መሆን የሚሻ አስቀድሞ በምድር ላይ ቅዱስ መሆን አለበት። 963The Signs of the Times, November 14, 1892.CGAmh 459.1

    ያ ቤት ውስጥ ባህሪይን ተወዳጅ የሚያደርገው በሰማያዊ ቤት ውስጥም ተወዳጅ የሚያደርግ ነው፡፡ የክርስትናችሁ መስፈሪያ በቤት ሕይወት ባህርይ ይለካል፡፡ የክርስቶስ ጸጋ ያላቸው ሰዎች ቤትን የደስታ፣ ሰላምና ዕረፍት የተሞላበት ስፍራ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፡፡ የክርስቶስ መንፈስ ከሌላችሁ የእርሱ የሆናችሁ አይደላችሁም ደግሞም በመንግሥቱ ውስጥ በሰማይ ደስታ ከእርሱ ጋር የሚካፈሉትን የሚሆኑትን የተቤዡ ቅዱሳንን በፍፁም ማየት አትችሉም፡፡ እግዚአብሔር ራሳችሁን ሙሉ በሙሉ ለእርሱ እንድትቀድሱ እና በቤት ክበብ ውስጥ ባህሪይውን እንድትወክሉ ይፈልጋል፡፡ 964The Signs of the Times, November 14, 1892.CGAmh 459.2

    የቅድስና ሥራ የሚጀምረው ከቤት ነው፡፡ ቤት ውስጥ ክርስቲያኖች የሆኑት በቤተክርስቲያን እና በዓለም ውስጥም ክርስቲያኖች ይሆናሉ፡፡ የቤት ውስጥ ሃይማኖትን ማሳደግ ባለመቻላቸው በጸጋ የማያድጉ ብዙዎች አሉ፡፡7The Signs of the Times, February 17, 1904.CGAmh 459.3

    ወላጆች ቤት በምትገኝ ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደ አስተማሪዎች— እኔ ለአባቶች እና ለእናቶችን እናገራለሁ፤ በቤታችሁ በምትገኘው ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ አስተማሪዎች መሆን ትችላላችሁ፤ መንፈሳዊ ሚስዮናዊ ወኪሎች መሆን ትችላላችሁ፡፡ አባቶች እና እናቶች የቤት ውስጥ ሚስዮናውያን የመሆን አስፈላጊነት፣ ቤት ውስጥ ያለውን ከባቢ አየር ርህራሄ ከጎደለው እና ከችኮላ ንግግር ተጽዕኖ ነጻ የማድረግን አስፈላጊነት እና ቤት ውስጥ የሚገኝ ትምህርት ቤት የእግዚአብሔር መላእክት የሚገቡበት ስፍራ እና የሚደረጉትን ጥረቶች የሚባረኩ እና ስኬትን ማጎናጸፍ እንዳለባቸው ይሰማቸው፡፡ 965Manuscript Releases 3:3, 1908.CGAmh 460.1

    ለኃይማኖታዊ ግዴታዎች ክንውን መሰናዶ የቤተሰብ ተቋም የሥልጠና ትምህርት ቤት እንደሆነ አስቡ፡፡ ልጆቻችሁ በቤተክርስቲያን ተግባር ውስጥ አንድ አካል ሆነው መሥራት አለባቸው፣ ደግሞም እያንዳንዱ የአእምሮ ኃይል፣ እያንዳንዱ አካላዊ ችሎታ ለክርስቶስ አገልግሎት ጠንካራ እና ንቁ ሆኖ መቆየት አለበት። እውነት ስለሆነ እውነትን እንዲወዱ መማር አለባቸው፤ እያንዳንዳቸው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ቤት ለመግባት ብቃታቸውን ለመለየት እና የሰማያዊው ንጉሥ ልጅ ለመሆን እና የንጉሣዊ ቤተሰብ አባል ለመሆን ረዘም ላለ ጊዜ በሚካሄደው ታላቅ ግምገማ ውስጥ ጸንተው እንዲቆሙ በእውነት ሊቀድሳቸው ይገባል፡፡ 966Manuscript Releases 12:1898.CGAmh 460.2

    ወጥ ሕይወት መምራት አለባቸው— እያንዳንዱ ነገር በወጣቶች አእምሮ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። ገጽታ ይጠናል፣ ድምጽ የራሱ ተጽዕኖ አለው፣ ደግሞም ጸባይን በጣም ይኮርጃሉ፡፡ በቀላሉ የሚበሳጩ እና የሚነጫነጩ አባቶች እና እናቶች ራሳቸው ቢሆኑ የማይማሩትን በልጆቻቸው ሕይወት የተወሰነ ጊዜ ለዓለም ሁሉ የሚያበረክቱትን ትምህርት እየሰጧቸው ነው፡፡ ልጆች በወላጆቻቸው ሕይወት ውስጥ ከወላጆች እምነት ጋር ተስማሚ የሆነ ወጥነትን ማየት አለባቸው፡፡ ወጥነት ያለው ሕይወት በመመራት እና ራስን በመቆጣጠር ወላጆች የልጆቻቸውን ባሕርይ መቅረጽ ይችላሉ። 967Testimonies For The Church 4:621.CGAmh 460.3

    ልጆችን እንደ የክርስቶስ ሠራተኞች አሰልጥኗቸው— በተፈጥሮ ትስስር የተዋሃዱ ሰዎች እርስ በእርሳቸው በጣም ጠንካራ የይገባኛል ጥያቄዎች አሏቸው፡፡ የቤተሰብ አባላት ርህራሄን እና ፍቅርን ማሳየት አለባቸው። የሚነገሩት ቃላት እና የሚከናወኑ ድርጊቶች በክርስቲያን መርሆዎች መሠረት መሆን አለባቸው፡፡ በዚህ መንገድ ቤት ሠራተኞች ለክርስቶስ የሚሰለጥኑበት ትምህርት ቤት መሆን ይችላል።CGAmh 461.1

    ቤት እንደ ቅዱስ ስፍራ ሊቆጠር ይገባል ...፡፡ በየቀኑ ሕይወታችን እራሳችንን ለእግዚአብሄር አሳልፈን መስጠት አለብን፡፡ በዚህ መንገድ ልዩ እርዳታ እና የዕለት ተዕለት ድሎችን ማግኘት እንችላለን። መስቀሉን በየቀኑ መሸከም ተገቢ ነው፡፡ በተቻለ መጠን የክርስቶስን ባሕርይ በሕይወታችን ውስጥ የማሳየት ለእግዚአብሄር ኃላፊነት ስላለብን እያንዳንዱ ቃል ሊጠበቅ ይገባል፡፡ 968Manuscript Releases 14:0.1897CGAmh 461.2

    ብዙዎች የሚፈጸሙት ከባድ ስህተት— ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻችንን በተለምዶ አክብሮት የሚገባው ሕይወት፣ ክርስቲያን ነን ባይ፣ ነገር ግን የእርሱን ራስን መሠዋት የጎደለው ሕይወት፣ እውነት የሆነው እርሱ “አላወቅኋችሁም” የሚል ብይን የሚተላለፍበት ሕይወት እናስተምራቸዋለን? በሺዎች የሚቆጠሩ ይህንን እያደረጉ ነው፡፡ መንፈሱን እየካዱ የወንጌልን ጥቅም ለልጆቻቸው ያስጠበቁ ይመስላቸዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሊሆን አይችልም፡፡ በአገልግሎት ከክርስቶስ ጋር አብሮ የመሆን መብትን የማይቀበሉ ሰዎች በክብሩ ከእርሱ ጋር ለመሆን ብቃት የሚሰጠውን ብቸኛ ሥልጠና አይቀበሉም፡፡ በዚህ ሕይወት ውስጥ ለባህርይ ጥንካሬ እና ክብር የሚሰጠውን ስልጠና ውድቅ ያደርጋሉ፡፡ አያሌ አባቶች እና እናቶች ልጆቻቸው ወደ ክርስቶስ መስቀል እንዳይመጡ ከልክለው፣ በዚህም ሳቢያ ለእግዚአብሔር እና ለሰው ጠላት ለሆነው አሳልፈው እንደሰጧቸው ዘግይተው ይረዳሉ፡፡ ለመጻኢውም ብቻ ሳይሆን ለአሁናዊ ሕይወት ጥፋታቸውን አትመዋል፡፡ ፈተና አሸንፏቸዋል፡፡ እነርሱ ለዓለም እርግማን፣ ለወለዷቸውም ሀዘን እና ሀፍረት በመሆን ያድጋሉ፡፡ 969Education, 264, 265.CGAmh 461.3

    ልጆቻችን በየትኛው መስመር እንዲያገለግሉ ሊጠሩ እንደሚችሉ አናውቅም፡፡ ህይወታቸውን ቤት ውስጥ ሊያሳልፉ ይችላሉ፤ በሕይወት የተለመደ ሙያ ውስጥ ሊሳተፉ ወይም የወንጌል አስተማሪዎች ሆነው ወደ አሕዛብ አገሮች ሊሄዱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ሁሉም የእግዚአብሔር ሚሲዮኖያውን፣ ለዓለም የምህረት አገልጋዮች እንዲሆኑ በተመሳሳይ መልኩ ተጠርተዋል፡፡ ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ አገልግሎት ከክርስቶስ ጎን ለመቆም የሚረዳቸውን ትምህርት ማግኘት አለባቸው፡፡ 970Prophets and Kings, 245.CGAmh 462.1

    በመለኮታዊ እርዳታ ላይ እንዲደገፉ አስተምሯቸው— ልጆቻችሁ መልካም ለማድረግ ትልቅ አቅም እንዲኖራቸው ከፈለጋችሁ መጻኢውን ዓለም አጥብቀው እንዲይዙ አስተምሯቸው። በችግሮቻቸው እና በአደጋዎቻቸው ላይ በመለኮታዊ እርዳታ ላይ እንዲተማመኑ መመሪያ ከተሰጣቸው ስሜትን ለመግታት እና ስህተት የመሥራት ውስጣዊ ፈተናዎችን ለመቆጣጠር ኃይል አያጥራቸውም፡፡ ከጥበብ ምንጭ ጋር ግንኙነት ማድረግ ብርሃን እና ትክክል እና ስህተት በሆነው መካከል የመለየት ኃይል ይሰጣል። በዚህ የታደሉ ሰዎች በግብረ ገብ እና በእውቀት ጠንካራ ሲሆኑ በጊዜያዊ የኑሮ ጉዳዮችም እንኳ የበለጠ የጠራ እይታ እና የተሻለ ፍርድ ይኖራቸዋል፡፡ 971The Health Reformer, November 1, 1878.CGAmh 462.2

    ድነት በእምነት እና በመተማመን ይረጋገጣል— በቤተሰቦቻችን ውስጥ የእግዚአብሔርን ማዳን ማግኘት እንችላለን፤ ነገር ግን ይህን ለማግኘት ማመን አለብን፣ መኖር አለብን፣ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ዘላቂ እምነት እና በእግዚአብሔር መታመን ሊኖረን ይገባል...፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በእኛ ላይ የሚጭነው ክልከላ ለእኛው ጥቅም የታለመ ነው፡፡ ለቤተሰቦቻችንን እና በዙሪያችን ለሚገኙ ሁሉ ደስታን ይጨምርላቸዋል። እርሱ ምርጫችንን ያስተካክላል፣ ፍርዳችንን ይቀድሳል ደግሞም ለአእምሮ ሰላምን ያመጣል፣ በመጨረሻም የዘላለም ሕይወት ይሰጣል...፡፡ አገልጋዮች መላእክት በመኖሪያችን ውስጥ ይቆያሉ፣ እናም በመለኮታዊው ሕይወት ረገድ ስለ መሻሻላችን ዜና በደስታ ወደ ሰማይ ይዞ ይሄዳሉ፣ መዝጋቢ መላእክቶችም አስደሳች ዘገባ ያሰፍራሉ። 972Pacific Health Journal, January, 1890.CGAmh 462.3

    የክርስቶስ መንፈስ በቤት ሕይወት ውስጥ ዘላቂ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ወንዶችና ሴቶች ልባቸውን የሰማያዊ ተጽዕኖ ለሆኑት እውነትና ፍቅር የሚከፍቱ ከሆነ፣ እነዚህ መርሆዎች እንደገና ሁሉንም በማደስ እና አሁን ምድረ በዳ እና እጦት ባለበት ማንሰራራት እንዲሆን ጅረት ይፈሳል፡16Manuscript Releases 14:2, 1898.CGAmh 463.1

    ልጆቻችሁ የቤት ውስጥ ትምህርት ውድ ተፅእኖን ወስደው ይሄዳሉ። ስለዚህ በልጆች የመጀመሪያ ዓመታት ላይ በቤት ክበብ ላይ ሥሩ እና ተጽዕኖአችሁን ወደ ትምህርት ቤት ይዘው ይሄዳሉ፤ ይህ ተጽዕኖ ሌሎች ብዙ ሰዎችን ይነካቸዋል። በዚህ መንገድ ጌታ ይከብራል። 973Manuscript Releases 14:2, 1898.CGAmh 463.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents