Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል 3—በቂ በሆነ ሁኔታ የሰለጠኑ መምህራን

    ምዕራፍ 8—ዝግጅት ያስፈልጋል

    የእናት ዝግጁነት እንግዳ በሆነ መልኩ ችላ ተብሏል— የልጅ የመጀመሪያ መምህርት እናት ናት፡፡ በታላቅ የተጋላጭነቱ እና እጅግ ፈጣን የዕድገቱ ጊዜ የእርሱ ትምህርት በእጅጉ በእርሷ እጅ ላይ ነው፡፡ ለመልካም ወይም ለክፉ ባህርይን ትቀርጽ ዘንድ የመጀመሪያው ዕድል ተሰጥቷታል፡፡ የእርሷን ዕድል ዋጋ መረዳት አለባት፣ ከማንኛውም ከሌላ መምህር በላይም በምትችለው ሁሉ አቅም ለመጠቀምም ብቃት ሊኖራት ይገባል፡፡ ሆኖም ግን እንደዚህ ሥልጠና እምዛምም ትኩረት ያልተሰጠው ሌላ የለም፡፡ በትምህርት ውስጥ ተፅዕኖው እጅግ ከፍተኛ እና አድማሱ ሰፊ የሆነው ነገር ለእርዳታው እጅግ ዝቅተኛ ስልታዊ ጥረት የተደረገለት ነገር ነው፡፡ 83Education, 275.CGAmh 59.1

    ጥንቃቄ የተሞላበት እና ጥብቅ ዝግጅት አንገብጋቢ ነው — አብዛኛውን ጊዜ ጨቅላ ሕጻንን እንዲንከባከቡ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ለአካሉ ከሚያስፈልጉት ነገሮች ጋር በተያያዘ አላዋቂዎች ናቸው፤ ስለ ጤና ሕግጋት ወይም ስለ ዕድገት መርኾዎች የሚያውቁት ጥቂት ነው፡፡ የአዕምሮ እና መንፈሳዊ ዕድገቱንም ቢሆን ለመንከባከብ የተሻለ ብቃት የላቸውም፡፡ ምናልባትም ንግድን ለመስራት ወይም በማሕበረተሰቡ ውስጥ ጎልቶ ለመታየት ብቃት ይኖራቸው ይሆናል፤ ምናልባት በስነ-ጽሑፍና በሳይንስ የተመሰከረላቸውን ክንውኖችን ሰርተው ሊሆን ይችላል ፣ ነገር ግን ልጆችን በማሳልጠን ረገድ ጥቂት እውቀት ነው ያላቸው፡፡….CGAmh 59.2

    ቀድሞም ሆነ በኋላ ላይ ልጅን የማሰልጠን ኃላፊነት በአባቶችና በእናቶች ላይ ያርፋል፣ እንዲሁም ለሁለቱም ወላጆች ጠንቃቃና ጥብቅ ዝግጅት እጅግ አንገብጋቢ ነው፡፡ አባትና እናት የመሆንን ዕድል ወደ ራሳቸው ከመውሰዳቸው በፊት፣ ወንዶችና ሴቶች ከአካል ዕድገት ሕግጋት ጋር መተዋወቅ አለባቸው— ይህም ከጤና አጠባበቅ ጥናተ-አካል፣ ከቅድመ ወሊድ ተጽዕኖዎች አቋም፣ ከውርስ፣ ከንጽሕና፣ ከአለባበስ፣ ከአካል እንቅስቃሴ፣ ከበሽታ ሕክምና ሕግጋት ጋር ማለት ነው፤ የአዕምሮ ዕድገትና የግብረ-ገብ ሥልጠና ሕግጋትንም ጭምር መረዳት አለባቸው…. CGAmh 59.3

    የወላጆች ተግባር አስፈላጊነት ሙሉ በሙሉ እውቅና እስኪያገኝ እና ለቅዱስ ኃላፊነቶቻቸውም ሥልጠና እስኪያገኙ ድረስ ትምህርት ማከናወን የሚችለውን እና ያለበትን በሙሉ ማከናወን በፍጹም አይችልም፡፡ 84Education, 275, 276.CGAmh 60.1

    ወላጆች የተፈጥሮ ሕጎችን ማጥናት አለባቸው፡፡ ከሰው ልጅ አካል መዋቅር ጋር መተዋወቅ አለባቸው፡፡ የተለያዩ የአካላት ተግባራትን እና ትስስር እና ጥገኝነታቸውን መረዳት አለባቸው፡፡ አዕምሮ ከአካል ኃይላት ጋር ያለውን ትስስር እና እያንዳንዱ ጤናማ ትግባራን ለማከናወን የሚፈልጉን ቅድመ ሁኔታዎችን ማጥናት አለባቸው፡፡ ያለእንደዚህ ዓይነት ዝግጅት የወላጅነት ሀላፊነቶችን መወሰድ ኃጢአት ነው። 85The Ministry of Healing, 380.CGAmh 60.2

    “ማነው ብቃት ያለው?”—ወላጆች፣ ለዚህ ነገር ማነው ብቃት ያለው?” ሲሉ ጥሩ አድርገው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡ ብቃታቸው እግዚአብሔር ብቻ ነው፣ እናም እርዳታውንና ምክሩን ሳይፈልጉ በመቅረት እርሱን ከጥያቄው ውጭ ከደረጉት፣ ተግባራቸው በእርግጥም ተስፋ አልባ ነው፡፡ ነገር ግን በጸሎት፣ መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት፣ በበኩላቸው ትጋት በተሞላበት ከፍተኛ ጉጉት፣ በዚህ አስፈላጊ በሆነ ኃላፊነት የተከበረ ስኬትን ሊያገኙ ይችላሉ፣ ለጊዜያቸውና ለእንክብካቤአቸውም መቶ እጥፍ ይከፈላቸዋል፡፡… በዚህ አቅጣጫ ተገቢውን እውቀት ሊያገኙበት የሚችሉት፣ የጥበብ ምንጭ ክፍት ነው፡፡ 86Testimonies For The Church 4:198CGAmh 60.3

    አንዳንድ ጊዜ ልብ ለመዛል ይቃጣ ይሆናል፤ ነገር ግን ወላጆች በሚወዷቸው ላይ የሚደርሰው የአሁኑና መጻኢ ደስታቸውን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ግልጽ ሁኔታዎች ከብርታትና ከጥበብ ምንጭ እርዳን አጥብቀው እንዲሹ ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡ እነርሱ ለእነዚህ ነፍሳት ተጠያቂዎች እንደመሆናቸው መጠን፣ አካባቢያቸውን ይበልጥ እንዲመለከቱ ፣ ይበልጥ ውሳኔ እንዲሰጡ ፣ ይበልጥ የተረጋጉ ነገር ግን ጽኑ እንዲሆኑ ሊያደርጋቸው ይገባል፡፡ 87The Review and Herald, August 30, 1881.CGAmh 60.4

    የሕፃናት ስልጠና የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳት ይጠይቃል—ወላጆች የእግዚአብሔርን መንግስት ህጎች ይታዘዙ ዘንድ ግልፅ የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳት ያላገኙ እንደሆነ ሰበብ የላቸውም። ልጆቻቸውን ወደ ሰማይ መምራት የሚችሉት እንዲህ ሲሆን ብቻ ነው ፡፡ ወንድሞቼ እና እህቶቼ ፣ የእግዚአብሔርን መጠይቅ መገንዘብ የእናንት ሀላፊነት ነው። ታዛዥነት የዘላለም ሕይወት እና አለመታዘዝ የዘላለም ሞት መሆኑን ካልተገነዘባችሁ በስተቀር፣ ቀና እና ስህተት የሆነውን ራሳችሁ ካላወቃችሁ በስተቀር ነገረ-እግዚአብሄርን እንዴት ለልጆቻችሁ ማስተማር ትችላላችሁ?CGAmh 61.1

    የእግዚአብሔርን ፈቃድ መረዳትን የሕይወታችን ተግባር ማድረግ አለብን፡፡ ይህን ስናደርግ ብቻ ነው ልጆቻችንን በትክክል ማሰልጠን የምንችለው፡፡ 88Manuscript Releases 10:3, 1902.CGAmh 61.2

    የእግዚአብሔር መመሪያ መጽሐፍ በመመሪያዎች የበለጸገ ነው —ወላጆች የእግዚአብሔርን ቃል የሕይወታቸው ሕግ አድርገው ካልወሰዱ በስተቀር፣ በመጨረሻም የዘላለም ሕይወትን ያገኝ ዘንድ የእያንዳንዱን ውድ ሰብአዊ ኃብት በዚህ መልኩ ማስተማርና መቅረጽ እንዳለባቸው ካልተገነዘቡ በስተቀር፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት አይችሉም፡፡89Manuscript Releases 8:4, 1897.CGAmh 61.3

    በመመሪያ የበለጸገው መጽሐፍ ቅዱስ የመማሪያ መጽሐፍ መሆን አለበት፡፡ ልጆቻቸውን በርሱ ትዕዛዛት መሰረት ቢያሰለጥኗቸው፣ የወጣቶቻቸውን እግሮች ቀና መንገድ ላይ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን ለተቀደሰው ኃላፊነታቸው ራሳቸውንም ያስተምራሉ፡፡ 90Testimonies For The Church 4:198.CGAmh 61.4

    የወላጆች ተግባር አስፈላጊ፣ የተከበረ ሥራ ነው፤ የተሰጣቸው ኃላፊነት ታላቅ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ ቢያጠኑ፣ ተግባራቸውን በታማኝነት እና በጥሩ ሁኔታ የተገበሩ እንደ ሆነ በውስጡ ለእነርሱ የታቀዱ አያሌ መመሪያዎችን እና ብርቅዬ ተስፋዎችን ያገኛሉ፡፡ 91The Signs of the Times, April 8, 1886.CGAmh 62.1

    የወላጆችና የልጆች ሕገ ደንብ —ለወላጆችና ለልጆች መመሪያ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሕገ ደንብን ሰጥቷል፡፡ እነዚህ መመሪያዎች ጥብቅ መታዘዝን ይጠይቃሉ፡፡ ልጆች የወላጆቻቸውን ምክር ሳይጠይቁ የራሳቸውን ምኞት መከተል እንዳለባቸው እንዲያስቡ ሊሞላቀቁና ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡…CGAmh 62.2

    ለወላጆች እና ለልጆች መመሪያ ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ከሰጠው ሕገ ደንብ ውስጥ፣ ኃጢአት-አልባ የሆነ መደናቀፍ ሊኖር አይችልም፡፡ ወላጆች በቃሉ ውስጥ ባሉት መርኾዎች መሰረት ለልጆቻቸው ስልጠና ይሰጡ ዘንድ እግዚአብሔር ይጠብቃል፡፡ እምነትና ተግባር መጣመር አለባቸው፡፡ በቤት ሕይወት ውስጥ እና በትምህርት ቤት ሕይወት ውስጥ የሚሰራ እያንዳንዱ ነገር አጥጋቢ በሆነ መልኩና በሥርዓት መሰራት አለበት፡፡ 92Letter 9, 1904.CGAmh 62.3

    ወደ ሕግና ወደ ምስክር—በቤት ውስጥ የትምህርት ተግባር፣ እግዚአብሔር ያቀደውን ሁሉ ማከናወን ያለበት እንደሆነ፣ ወላጆች የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች እንዲሆኑ የሚጠይቅ ነው፡፡ የታላቁ መምህር ተማሪዎች መሆን አለባቸው፡፡ በየዕለቱ የፍቅርና የርህራሄ ሕግ በከንፈሮቻቸው ላይ መሆን አለበት፡፡ ምሳሌያቸው በሆነው ሕይወት ውስጥ የታየው ጸጋና እውነት በሕይወታቸው መገለጥ አለበት፡፡ ከዚያም የተቀደሰ ፍቅር የወላጆችና የልጆችን ልቦች ያጣምራል፣ ወጣቶችም በእግዚአብሔር ፍቅር ሥር በመስደድ በእምነት ላይ ተመስርተው ያድጋሉ፡፡ CGAmh 62.4

    የእግዚአብሔር ፈቃድ እና መንገድ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ወላጆች ፈቃድና መንገድ ሲሆን፣ ልጆቻቸው እግዚአብሔርን በመውደድ፣ በማክበር እና በመታዘዝ ያድጋሉ፡፡ እነርሱ የጌታን ቃል ከሁሉ ነገር ስለሚያስበልጡ እና የሚመጡባቸውን እያንዳንዱን ተሞክሮ በሕግና በምስክር ስለሚፈትኑ፣ ሰይጣን አዕመሮአቸውን መቆጣጠር አይችልም፡፡ 93Letter 356, 1907.CGAmh 62.5

    ቸልተኞች ከሆኑ፣ ጊዜያቸውን ይዋጁ—ወላጆች ቃለ እግዚአብሔርን ለራሳቸውና ለቤተሰቦቻቸውም ማጥናት አለባቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ አያሌ ልጆች ሳይማሩ፣ ቁጥጥር ሳይደረግባቸው እና ሳይገቱ እንዲያድጉ ይተዋሉ፡፡ ወላጆች አሁን ቸልተኝነታቸውን ለመዋጀት በአቅማቸው የሚችሉትን በማድረግ ልጆቻቸውን እጅግ ጥሩ በሆኑ ተጽዕኖዎች ሥር ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ 94Manuscript Releases 7:6, 1905.CGAmh 63.1

    ስለዚህ ወላጆች ሆይ መጽሐፍትን መርምሩ፡፡ ሰሚዎች ብቻ አትሁኑ፤ የቃሉ አድራጊዎች ሆኑ፡፡ በልጆቻችሁ ትምህርት የእግዚአብሔርን መስፈርት አሟሉ፡፡ 95Manuscript Releases 5:7, 1897.CGAmh 63.2

    የመመሪያ ሕግ፡ ጌታ ምን ይላል? —የወላጆች ሁሉ ሥራ ልጆቻቸውን በጌታ መንገድ ላይ ማሰልጠን ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔርን ቅሬታ ሳያመጣ በንቀት የሚታይ ወይም ወደ ጎን የሚተው ጉዳይ አይሆንም፡፡ ሌሎች መከተል ያለበቸውን መንገድ ወይም እጅግ ቀላል ወደ ሆነው እንዴት መድረስ እንዳለብን ለመወሰን አልተጠራንም፣ ነገር ግን፣ ጌታ ምን ይላል? ወላጆችም ሆኑ ልጆች በማንኛውም ሐሰተኛ መንገድ ላይ ሆነው ሰላም ወይም ደስታ ወይም የመንፈስ እረፍት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን መፍራት ኢየሱስን ከመውደድ ጋር በመጣመር ልብ ላይ ሲነግስ፣ ሰላምና ደስታ እንዲሰማን ይሆናል፡፡ CGAmh 63.3

    ወላጆች፣ ልቦቻችሁን እና ምስጢራችሁን ሁሉ በሚያነብብ ፊት የእግዚአብሔርን ቃል ዘርግታችሁ፣ መጽሐፉ ምን ይላል? ብላችሁ ጠይቁ፡፡ ይህ የሕይወታችሁ መመሪያ መሆን አለበት፡፡ የነፍሳት ፍቅር ያላቸው አደጋዎቻቸውን ተመልክተው ዝም አይሉም፡፡ ከሰብአዊ አዕምሮዎች ጋር በመስራት እና እነርሱንም እንዲሁ በመታደግ ሂደት ውስጥ፣ እነርሱን ለመዋጀት ወላጆችን ጥበበኞች የሚያደርግ ከእግዚአብሔር እውነት ውጭ ሌላ አንዳች ነገር እንደሌለ ማረጋገጫ ተሰጥቶናል፡፡ 96The Review and Herald, March 30, 1897.CGAmh 63.4

    የግለሰባዊ ዝግጅት—አእምሮአዊ እና አካላዊ ኃይሎች ጤናማ ቃና እና ጥንካሬን የሚሹበት የአእምሮ ማጎልበት ከሚያስፈልገው ከሌላው በላይ የሆነ ግዴታ ካለ ፣ እሱ የልጆች ስልጠና ነው።15Pacific Health Journal, June, 1890.CGAmh 64.1

    ከእናቶች የግል ኃላፊነት እይታ አንፃር እያንዳንዷ ሴት እውነተኛ፣ መልካሙን እና ውበትን ብቻ የሚያንፀባርቅ ሚዛናዊነት ያለውን አዕምሮ እና ንፁህ ባህሪይን ማዳበር ይኖርባታል፡፡ ሚስት እና እናት ባሏንና ልጆቿን በማያቋርጥ ፍቅር ፣ ረጋ ባሉ ቃላትና በትህትና ድርጊቶች ከልቧ ጋር ልታቆራኝ ትችላለች፣ ይህንንም እንደ ሕግ ልጆቿ የሚቀዱት ይሆናል፡፡ 97Pacific Health Journal, September, 1890.CGAmh 64.2

    እናት ፣ ይህ የተቀደሰ ሥራዎ ነው—እህቴ ፣ ክርስቶስ ትእዛዛቱን ለልጆችሽ የማስተማር የተቀደሰ የስራን ኃላፊነት ሰጥቶሻል። ለዚህ ስራ ብቁ ለመሆን ራስሽ ለመመሪያዎች ሁሉ በመታዘዝ መኖር አለብሽ። እያንዳንዷን ቃል እና ተግባር በትኩረት መከታተልን አዳብሪ፡፡ ቃላትሽን በጣም በትጋት ጠብቂ። የስሜትሽን ችኩልነት ሁሉ አሸንፊ፤ ምክንያቱም ትዕግሥት ማጣት ከታየ ባላጋራ ለልጆችሽ ቤትን የማይስማማና ደስ የማይል ያደርግ ዘንድ ይረደዋል። 98Letter 47a, 1902.CGAmh 64.3

    ከመለኮት ጋር በመተባበር መሥራት—እናቶች፣ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በመስማማት ረገድ የእናንተን ድርሻ መወጣት እንዳለባችሁ ዘወትር ልብ እያላችሁ የእግዚአብሔርን መመሪያ ለመቀበል ልባችሁ ክፍት ይሁን፡፡ እንዴት መተግበር እንዳለባችሁ ለማወቅ፣ እግዚአብሔር ዋናው ሠራተኛ መሆኑን እውቅና ለመስጠት እና ከእርሱ ጋር አብራችሁ ሰራተኛ እንደሆናችሁ ለመረዳት፣ ራሳችሁን በብርሃን ሥፍራ ማስቀመጥ እና ጥበብን ከእግዚአብሔር መሻት አለባችሁ፡፡ ልባችሁ ሰማያዊ ነገሮችን በማሰላሰል የተማረከ ይሁን፡፡ እንደ እናት እግዚአብሔር የሰጠዎትን ኃላፊነት ለመወጣት እና ከመለኮታዊ ወኪሎች ጋር በአብሮነት ለመስራት እግዚአብሔር የሰጠዎትን ተሰጥኦዎችን ይለማመዱ፡፡ በብልሃት ይስሩ፣ እናም “እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት፡፡” 99The Signs of the Times, April 9, 1896.CGAmh 64.4

    እናት ራሷን እና ልጆቿን ለሩህሩሁ ቤዛ እንክብካቤ አሳልፋ መስጠት አለባት፡፡ የላቁ የአዕምሮ ኃይሎቿን ልጆቿን በማሰልጠን ረገድ በአብባቡ ለመጠቀም በጽናት፣ በትዕግስት፣ በልበ ቆራጥነት፣ ችሎታዎቿን ማዳበርን መሻት አለባት፡፡ የእግዚአብሔርን ማረጋገጫ የሚያገኘውን ለልጆቿ ትምህርት መስጠትን እጅግ ትልቁ ዓለማዋ ማድረግ ይኖርባታል፡፡ ተግባሯን በግንዛቤ መከወን ስትጀምር፣ ድርሻዋን መወጣት ትችል ዘንድ ኃይል ትቀበላለች፡፡ 100The Signs of the Times, April 3, 1901.CGAmh 65.1

    እናት ራሷም ለጌታ መንገድና ፈቃድ ራሷን በመስጠት ረገድ እውነተኛ ልምምድ ይኖራት ዘንድ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት መሻት ሊሰማት ይገባል፡፡ ከዚያም በክርስቶስ ጸጋ ጠቢብ፣ ሩህሩህ እና የልጆቿ አፍቃሪ መምህርት መሆን ትችላለች፡፡ 101The Review and Herald, May 10, 1898.CGAmh 65.2

    ስህተት ብትጀምሩ—የተሳሳተ ሥልጠና ለጀመሩት ወላጆች፣ ተስፋ አትቁረጡ እላለሁ፡፡ በትክክል ወደ እግዚአብሔር መለወጥ ያስፈልግዎታል፡፡ ለእግዚአብሄር ቃል የመታዘዝ እውነተኛ መንፈስ ያስፈልግዎታል፡፡ ህይወትዎትን ከእግዚአብሔር ህግጋት መሰረታዊ መርሆዎች ጋር በማስማማት በራስዎ ልማዶች እና ምግባሮች ላይ ቆራጥ ውሳኔዎችን ማድረግ አለብዎት፡፡ ይህንን ሲያደርጉ፣ እግዚአብሔርን ስለሚወዱ እና ህጉን እንደ ባህሪው ግልባጭ ስለሚገነዘቡ፣ ያንን ህግ የሚያጎላ የክርስቶስ ጽድቅ ይኖርዎታል። በክርስቶስ ችሎታ ላይ ያለው እውነተኛ እምነት ቅዠት አይደለም ፡፡ የክርስቶስን ባህሪዎች በእራስዎ ህይወት እና ባህርይ ውስጥ ማምጣት እና ልጆችዎን ለእግዚአብሔር ትዕዛዛት ታዛዥ እንዲሆኑ ትጋት በተሞላበት ጥረት ማስተማር እና ማሠልጠን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ነው። “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል” የሚለው በትምህርታዊ እቅዶችዎ ሁሉ ውስጥ ሊመራዎት ይገባል….CGAmh 65.3

    በእግዚአብሔር ፊት ጥልቅ እና ጥብቅ ንስሐ ይኑር ፡፡ ባለፉት የሥራ ጊዜያት ውስጥ የነበሩ ጉድለቶች መለየት ይቻል ዘንድ መንፈሳዊ ማስተዋልን ለማግኘት፣ እግዚአብሔርን በጥበብ በመፈለግ...አመቱን ይጀምሩ። እንደ የቤት ውስጥ ሚስዮኖች ችላ ላሏቸው ሥራዎች በእግዚአብሔር ፊት ንስሐ ይግቡ።21Manuscript Releases 12:1898.CGAmh 66.1

    ይህ የታመነበት ቀንዎ፣ የኃላፊነት ቀንዎ እና የዕድልዎ ቀን ነው፡፡ የሚመረመሩበት ቀን በቅርቡ ይመጣል። ስራዎን ቆራጥነት በተሞላበት ጸሎት እና በታማኝነት ጥረት ይጀምሩ። በየቀኑ የመንፈስ ቅዱስን ጥምቀት የመቀበል መብት እንዳላቸው ልጆችዎን ያስተምሯቸው። ዓላማዎቹን ለማስፈፀም ክርስቶስ የእርዳታ እጁ የሆንከውን እርሶን ያግኝዎት፡፡ በጸሎት አማካኝነት ለልጆችዎ የሚያደርጉትን አገልግሎት ፍጹም ስኬታማ የሚያደርግ ልምድን ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ 102Counsels to Parents, Teachers, and Students, 131.CGAmh 66.2