Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 70—ጥንቃቄዎች እና ምክሮች

    ብዙ ጉዳዮች ተገለጧል— ብዙ ጉዳዮች ከፊቴ ቀርበው ነበር፣ ስለ ውስጣዊ ሕይወታቸውም እንደ ተመለከትኩኝ፣ ነፍሴ ታመመ፣ እግዚአብሔርን ስለ መምሰል የሚናገሩ እና ተለውጠው ወደ ሰማይ ስለ መሄድ የሚያወሩ የሰው ልጆች ልብ ብልሹነትንም ተጸየፍኩኝ፡፡ ማንን ማመን እችላለሁ ስል ራሴን ደጋግሜ እጠይቃለሁ? ከአመጽ ነፃ የሆነ ማን ነው? 903 2:349CGAmh 426.1

    የወቅቱን እውነት እናምናለን የሚሉ ቤተሰቦች ሁኔታ በፊቴ ሲከፈት በፍርሀት ተሞልላሁኝ፡፡ የወጣቶች እና የልጆች ብልግና በጣም የሚያስደንቅ ነው። ወላጆች ምስጢራዊ ብልግና ከልጆቻቸው ውስጥ የእግዚአብሔርን ምስል እያጠፋ እና እያበላሸ መሆኑን አያውቁም፡፡ የሰዶማውያንን ዓይነተኛ ኃጢአቶች በመካከላቸው አሉ። ልጆቻቸው እግዚአብሔርን እንዲወዱ እና እንዲታዘዙ ስላላስተማሩ ወላጆች ሃላፊነት አለባቸው፡፡ ወላጆች እነርሱን አልገደቧቸውም ወይም የጌታን መንገድ በትጋት አላስተማሯቸውም፡፡ በመረጡበት ጊዜ እንዲወጡ እና እንዲገቡ፣ ከዓለም ልጆች ጋር ጓደኝነት እንዲፈጥሩ ፈቅደዋል፡፡ የወላጅ ትምህርትን እና ስልጣንን የሚጻረሩ እነዚህ ዓለማዊ ተጽዕኖዎች በብዛት በጥሩ ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በአለባበሳቸው፣ በገጽታቸው፣ በመዝናኛዎቻቸ፣ የክርስቶስን ተቃራኒ በሆነ ሁኔታ አየር ዙሪያቸውን ይከብባሉ፡፡CGAmh 426.2

    ብቸኛ ደህንነታችን እንደ የእግዚአብሔር ልዩ ህዝብ መቆም ነው። እኛ ከብልሹ እና ከጣኦት አምልኮ ድርጊቶች ጋር ሳንደራደር በግብረ ገብ ነጻነት እንቆማለን እንጂ፣ ለዚህ ላሽቆለቆለ ዘመን ልማድ እና ፋሽኖች አንድ ኢንች መሸነፍ የለብንም።2 5:78.CGAmh 427.1

    አላዋቂዎች እንዲያውቁ መደረግ አለበት— አንድ ሰው ምንም ያህል እውቀት ቢኖረው የሥጋ ምኞትን ለማርካት ፈቃደኛ የሆነ እንደሆነ ክርስቲያን መሆን አይችልም፡፡ እንደ ክርስቶስ አገልጋዮች ተግባራቸው፣ የሚያሰላስሏቸው ነገሮች፣ እና ደስታቸው በላቁ ነገሮች ላይ መሆን አለበት፡፡ ብዙዎች የእነዚህ ልምዶች ኃጢአት እና ስለ ውጤቶቻቸው እርግጠኛነት አያውቁም። እንዲህ ዓይነቶቹን እንዲያውቁ ሊደረጉ ይገባል፡፡ 904An Appeal to Mothers, 25.CGAmh 427.2

    ለፈውስ የጸሎት አደራ ያቀረበ ሰው— አንድ ጊዜ እኔና ባለቤቴ ስብሰባ በተሰበሰብንበት ሥፍራ ስሜታችን ቀስ በቀስ በመመንመን ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት ወደ ነበረ አንድ ወንድም ተሳበ፡፡ የገረጣ እና ከሲታ ሆኗል፡፡ እርሱ የእግዚአብሔርን ህዝብ ጸሎት ጠየቀ፡፡ ቤተሰቡ እንደታመሙ እና ልጅም እንዳጣ ተናገረ፡፡ በሐዘን ስሜት ነበር የተናገረው፡፡ ወንድም እና እህት ኋይትን እስከሚያገኝበት ጊዜ ድረስ እየተጠባበቀ እንደ ነበረ ተናገረ፡፡ እነርሱ ቢጸልዩለት እንደሚድን ያምን ነበር፡፡ ስብሰባው ከተዘጋ በኋላ ወንድሞች ለጉዳዩ ትኩረት እንድንሰጥ አደረጉን፡፡ ባለቤቱ ስለ ታመመች እና ልጁም ስለሞተ ቤተክርስቲያኗ እየረዳቻቸው እንደ ነበረ ነገሩን፡፡ ወንድሞች በቤቱ ተሰብስበው ለተጎዱት ቤተሰቦች በአንድነት ጸለዩ፡፡ በስብሰባው ወቅት በጣም የደከመን እና የሥራው ሸክም ስለነበረብን ይቅርታ መጠየቅ ፈልገን ነበር፡፡ የጌታ መንፈስ ካላስገደደኝ በስተቀር ለማንም ላለማጸለይ ወሰንኩኝ…፡፡CGAmh 427.3

    የዚያን ቀን ምሽት በጸሎት ተንበርክከን ጉዳዩን በጌታ ፊት አቀረብን፡፡ ስለ እርሱ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ምን እንደሆነ እንድናውቅ ተማጸንን፡፡ የሁላችንም ምኞት እግዚአብሔር እንዲከብር ነበር፡፡ ለዚህ ለተሰቃየ ሰው እንድንጸልይ ጌታ ይፈልጋልን? ሸክሙን ለጌታ ትተን ተኛን፡፡ የዚያ ሰው ሁኔታ በሕልም በግልጽ በፊቴ ቀረበ፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የነበረው ሁኔታ እና በልቡ ውስጥ ክፋት ስላለ የምንጸልይለት ከሆነ ጌታ እንደማይሰማን ታየኝ፡፡ በሚቀጥለው ጠዋት ሰውየው እንድንጸልይለት መጣ። ወዲያ ወስደነው ጥያቄውን ላለመቀበል በመገደዳችን እንደምናዝን ነገርነው፡፡ አልሜ የነበረውን ህልሜን ነገርኩት፣ እርሱም እውነት መሆኑን አምኖ ተቀበለው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ ራስን የመጉዳት ልምምድ ሲፈጽም የነበረ እና በትዳር ህይወቱ ውስጥም ልምምዱን እንደቀጠለ እና ይህንንም ለመተው እንደሚሞክር ተናገረ፡፡ ይህ ሰው ማሸነፍ ያለበት ከረጅም ጊዜ በፊት ሥር የሰደደ ልማድ ነበረው፡፡ እሱ በመካከለኛው ዕድሜ ላይ ነበር፡፡ የሞራል መርሆዎቹ በጣም ደካማ ከመሆናቸው የተነሳ ለረጅም ጊዜ ሥር ከሰደደ አግባብነት የሌለው ፍላጎት ማርካት ጋር ሲዋጉ ሲሸነፉ ነበር…፡፡ CGAmh 428.1

    በየቀኑ እራሱን እያዋረደ በእግዚአብሔር መገኘት ፊት ለመቅረብ የሚደፍር እና ቢሰጠው ኖሮ በሥጋ ምኞት የሚያጠፋውን በክፋት ያባከነውን ብርታት እንዲጨመረለት የሚጠይቅ ሰው እዚህ ነበር፡፡ እግዚአብሔር እንዴት ታጋሽ ነው! እንደ ክፉ መንገዱ ለሰው ቢመልስለት ኖሮ በፊቱ ማን ይኖር ነበር? ጠንቃቆች ባንሆን እና ይህ ሰው በደል እየፈጸመ ሳለ የእርሱን ጉዳይ በእግዚአብሔር ፊት ብናቀርብ ኖሮ እግዚአብሔር ይሰማልን ነበርን? እርሱ መልስ ይሰጥ ነበርን? “አንተ በደልን የማትወድድ አምላክ ነህና፤ ክፉ ከአንተ ጋር አያድርም፡፡ በከንቱ የሚመኩ በአይኖችህ ፊት አይኖሩም፤ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ፡፡” …፡፡ CGAmh 428.2

    ይህ ብቸኛው ጉዳይ አይደለም፡፡ ይህን ሰው የጋብቻ ግንኙነት እንኳን ከወጣትነት ብልሹ ልማዶቹ ሊጠብው አልቻለም፡፡ እኔ እንዳቀረክኳቸው አይነት ጉዳዮች እምብዛም ቢሆኑ እመኝ ነበር፣ ነገር ግን ብዙ እንደ ሆኑ አውቃለሁ፡፡ 9052:349, 351.CGAmh 428.3

    ራስን ማጥፋት— አቶ----- ራሱን የሰጠ የክርስቶስ ተከታይ ይባል ነበር፡፡ እርሱ በጣም በደካማ ጤንነት ላይ ነበር፡፡ ስለ እርሱ የርህራሴ ስሜት ተሰምቶን ነበር…፡፡ CGAmh 429.1

    የእርሱን ጉዳይ በራዕይ ተመልክቼ ነበር፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ እንዳለገኘ ስለ ራሱ የነበረው ሐሳብ ስህተት እንደሆነ ተመልክቻለሁ፡፡ ጎስቃላ ሰብአዊ ሰው እስኪሆን ድረስ ራስን የመበደል ተግባር ላይ ነበር፡፡ ይህ ክፋት በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ እንደሆነ ተመልክቻለሁ…፡፡ CGAmh 429.2

    ለረጅም ጊዜያት እነዚህን ልማዶች በመለማመዱ ራሱን መቆጣጠር ያቃተው ይመስላል፡፡ እርሱ በተፈጥሮ ከተራ ችሎታዎች በላይ መተግበር የሚችል ፈጣን ሰው ነበር፡፡ ዳሩ ግን እነዚህ ሁሉ የአካል እና የአዕምሮ ኃይሎች በሰይጣን ቁጥጥር ሥር እንዴት ይሆናሉ፣ በእርሱስ መሰውያ ላይ እንዴት ይሰዋሉ፡፡ CGAmh 429.3

    ይህ ሰው እጅግ ረጅም ርቀት በመጓዙ እግዚአብሔር የተወው ይመስላል፡፡ እርሱ ይህን ታላቅ ኃጢአት እንዲያሸንፍ እና ድሮ ልማዶቹ ይመለስ ዘንድ ወደ ጫካ በመሄድ ቀንና ሌሊት በጾምና በጸሎት ያሳልፍ ነበር፡፡ እግዚአብሔር ጸሎቱን አልሰማም ነበር። በራሱ አቅም ለራሱ ማድረግ የሚችለውን እግዚአብሔር እንዲያደርግለት ይጠይቃል፡፡ ደጋግሞ ለእግዚአብሔር ስእለት ይሳል ነበር፣ ደግሞም ብዙውን ጊዜ ስዕለቱን በማፍረስ ራሱን እንዲያጠፋ እግዚአብሔር እስኪተወው ድረስ ራሱን ለሥጋዊ ምኞት አሳልፎ ሰጠ፡፡ እርሱ የራሱ ገዳይ ነበር፡፡ የሰማይ ንጽህና በእርሱ መገኘት መበላሸት አይገባውም፡፡ 906An Appeal to Mothers, 24-28.CGAmh 429.4

    ለምኞቷ ለተገዛች ሴት ልጅ የተደረገ ጥሪ [ማስታወሻ፡- እነዚህ የምስጢር ብልግናን ለምትፈጽም እና ለራስ-ምኞት ለተገዛች ሴት ልጅ ከተጻፉ ደብዳቤዎች የተወሰዱ ናቸው]— አዕምሮሽ ረክሷል፡፡ ለረጅም ጊዜ ከተግባር እና ሥራ ራስሽን ነጻ አድርገሻል፡፡ የቤት ውስጥ ሥራዎች ሊኖርሽ ከሚገባ የላቁ በረከቶች አንዱ መሆን ነበረበት፡፡ ደካማ አስተሳሰብ እና ባህሪይ የጎዳሽን ያህል መዛል አንድ አሥረኛውን ያህል አይጎዳሽም ነበር፡፡ ወንድ እና ሴት ልጆች ጋር አብረው ስለ መሆናቸው የተሳሳቱ ሀሳቦችን አሉሽ፣ ደግሞም ከወንዶቹ ልጆች ጋር አብሮ መሆን ለአእምሮሽ እጅግ ደስታን ይሰጣል፡፡ በልብሽ እና በአዕምሮሽ ንጹህ አይደለሽም፡፡ የፍቅር ታሪኮችን እና ስሜታዊ ታሪኮችን በማንበብ ተጎድተሻል፣ ደግሞም አዕምሮሽ በረከሱ ሀሳቦች ይደሰታል፡፡ ሀሳቦችሽን ለመቆጣጠር ኃይል እስኪያጥርሽ ድረስ አስተሳሰብሽ ብልሹ ሆኗል። ሰይጣን እንደ ፍላጎቱ እንደ ምርኮኛ ይመራሻል…፡፡ CGAmh 429.5

    ባህሪሽ ንጹህ፣ ዝግ ያለ ወይም ያማረ አልነበረም፡፡ በዓይኖችሽ ፊት የእግዚአብሔር መፍራት የለም፡፡ ዓለማሽን ለማሳካት ብዙ ጊዜ የተበላሸ ሕሊና እንዳለሽ ትደብቂያለሽ፡፡ ውድ ልጄ፣ የደረስሽበት ሥፍራ ካልቆምሽ በስተቀር ጥፋት በእርግጠኝነት በፊትሽ ነው፡፡ በሐሳብ መባከንሽን፣ ግንብ መገንባትሽን አቁሚ፡፡ ሐሳብሽን በሞኝነት እና በብልሹ መስመር ውስጥ ከመጓዝ አቁሚ፡፡ CGAmh 430.1

    ከወንዶች ጋር ያለሽ ግንኙነት ሰላማዊ አይደለም፡፡ የፈተና ማዕበል፣ መርኾ፣ የሴትነት ባህሪይ እና እውነተኛ ዝግተኝነተን ነቅሎ በሚያስወግድ አዝማሚያ በልብሽ ውስጥ ይነሳሳል፣ ይናወጥማል። በችኮ እና አንገተ ደንዳና በሆነው ጎዳናሽ ላይ የምትጓዢ ከሆነ ዕጣ ፈንታሽ ምን ይሆናል? … ዘለአለማዊ ዓለማሽን በስሜት መሠዊያ ላይ እየሰዋሽ በመሆኑ አደጋ ላይ ነሽ፡፡ ስሜት መላ ሰውነትሽ ላይ አዎንታዊ ቁጥጥር እያገኘ ነው — የትኛው ስሜት ነው? ወራዳ፣ አጥፊ ባህሪይ ያለው ስሜት ነው። ለዚህ በመገዛት፣ የወላጆችሽን ሕይወት ታስመርሪያለሽ፣ እህቶችሽ ላይ ሀዘንና እፍረት ታመጪያለሽ፣ የራስሽን ባህርይ ትሰዊያለሽ፣ ደግሞም ሰማይ እና የማይጠፈውን ባለ ክብር ሕይወት ታጪያለሽ፡፡ ይህንን ለማድረግ ዝግጁ ነሽ? … CGAmh 430.2

    አይን አውጣ ነሽ፡፡ ወንዶችን ትወጂያለሽ፣ የንግግርሽም ርዕሰ ጉዳይ ታደርጊያቸዋለሽ፡፡ “በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና፡፡” ልማዶች አንቺን ለመቆጣጠር ሀይለኛ ሆነዋል፣ ዓለማዎችሽን ለመተግበር እና ምኞቶችሽን ለመፈጸም ማታለልን ተምረሻል፡፡ ያንቺ ጉዳይ ተስፋ እንደሌለው አልቆጥርም፤ ያ ቢሆን ኖሮ፣ ብዕሬ እነዚህን መስመሮች አይጽፍም ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ብርታት ያለፈውን ጊዜ መቤዠት ትችያለሽ…፡፡ CGAmh 431.1

    ከወንዶች ልጆች በንጽህና ራቂ፡፡ ከእነርሱ ጋር ስትሆኚ ፈተናዎችሽ ጠንካራ እና ኃይለኛ ይሆናሉ፡፡ ጋብቻን ከሴት ልጅነት አዕምሮሽ ውስጥ አውጪ፡፡ በምንም አይነት ሁኔታ ለዚህ ብቁ አይደለሽም፡፡ ኃላፊነቶችን ለማወቅ እና የጋብቻ ሕይወት ሸክሞችን ለመሸከም ብቁ ከመሆንሽ በፊት የልምድ ዓመታት ያስፈልጉሻል፡፡ ሀሳቦችሽን፣ ምኞቶችሽን እና ስሜቶችሽን በጥብቅ ጠብቂያቸው፡፡ እነዚህ ሥጋዊ ምኞትን እንዲያገለግሉ አታዋርጂያቸው፡፡ ወደ ንጽህና ከፍ አድርጊያቸው፤ ለእግዚአብሔር አሳልፈሽ ስጭያቸው፡፡ CGAmh 431.2

    ብልህ፣ ዝግተኛ፣ ጨዋ ሴት መሆን ትችያለሽ፣ ዳሩ ግን ያለ ልባዊ ጥረት አይደለም፡፡ ንቁ መሆን፣ መጸለይ፣ ማሰላሰል፣ ተነሳሽነትሽን እና ድርጊቶችሽን መመርመር አለብሽ። ስሜትሽን እና ድርጊቶችሽን በጥልቀት ተንትኚያቸው። በአባትሽ ፊት ርኩስ ተግባር ትሠሪያለሽን? በእርግጥ አትሰሪም፡፡ ዳሩ ግን እጅግ በጣም ከፍ ባለው ቅዱስ እና እጅግ ንጹህ በሆነው የሰማዩ አባትሽ ፊት ይህንን ታደርጊያለሽ፡፡ አዎ; በንጹህ፣ ኃጢአት በሌለባቸው መላእክቶች ፊት እና በክርስቶስ ፊት የራስሽን ሰውነት ታረክሺያለሽ፤ እንዲሁም ይህንን ማድረግ የምትቀጥይው ከሕሊና ውጭ፣ የተሰጠሽን ብርሃን እና ማስጠንቀቂያዎችን ከግምት ሳታስገቢ ነው። አስታውሺ፣ ሁሉም ድርጊቶችሽ ተመዝግቧል፡፡ እንደገና በሕይወትሽ ውስጥ እጅግ ሚስጥራዊ የሆኑትን ነገሮች መገናኘት አለብሽ…፡፡ CGAmh 431.3

    የሁሉም ሰው ጉዳይ በሚወሰንበት በዚያ ቀን እነዚህን ተግባራት እንደሚገናኝ አንድ ሰው አስጠነቅቅሃለሁ። ሳትዘገይ እራስህን ለክርስቶስ አሳልፈህ ስጥ; እርሱ ብቻ፣ በጸጋው ኃይሉ፣ ከጥፋት ሊቤዥኅ ይችላል። የግብረ ገብ እና የአእምሮ ኃይልህን ወደ ጤናማ ሁኔታ ሊያመጣ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ፍቅር ልብህ ሊሞቅ ይችላል፤ መረዳትህ ግልጽ እና በሳል፤ ህሊናህ ፣ ብሩህ፣ ፈጣን እና ንጹህ፤ ፈቃድህ የቀና እና የተቀደሰ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ቁጥጥር ሥር የሆነ ይሆናል፡፡ ራስህን እንደ ምርጫህ ማድረግ ትችላለህ፡፡ አሁን በትክክል ፊት ለፊት የምትጋፈጥ ከሆነ፣ ክፉ ማድረግህን አቁም እና መልካም ማድረግን ተማር፣ ከዚያም በእርግጥ በእውነቱ ደስተኛ ትሆናለህ፤ በሕይወት ውጊያዎች ውስጥ ስኬታማ ትሆናለህ፣ ደግሞም ከዚህ በተሻለ ሕይወት ላይ ወደ ሞገስ እና ወደ ክብር ትመጣላችሁ፡፡ “የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ።” 907Testimonies For The Church 2:559-565.CGAmh 432.1

    ሰይጣን ወላጆች በሚተኙበት ጊዜ ነው የሚሰራው— ይህ ፈጣን ዘመን ነው። ትናንሽ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች በሕፃናት መንከባከቢያ ሥፍራ የፀባይ ዝግተኝነት ትምህርት ማግኘት ባለባቸው ጊዜ አንዳቸው ለሌላው ትኩረት መስጠታቸውን ይጀምራሉ፡፡ የዚህ የልታረመ ቅልቅል ውጤት ምንድነው? የወጣቶቹ በዚህ መንገድ መገናኘት የባህሪይ ንጽህናቸውን ይጨምራልን? በጭራሽ! የመጀመሪያዎቹን ሥጋዊ ምኞቶችን ይጨምራል፤ ከእንደዚህ አይነት ስብሰባዎች በኋላ ወጣቶች በዲያቢሎስ ይቀውሱና እራሳቸውን ለክፉ ድርጊቶቻቸው አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡ CGAmh 432.2

    ወላጆች ተኝተዋል ደግሞም ሰይጣን በቤተሰቦቻቸው ውስጥ ሲኦላዊ ሰንደቅ ዓላማውን እንደተከተለ አያውቁም። በዚህ ብልሹ ዘመን ውስጥ ወጣቶች ምን እንደሚሆኑ እንድጠይቅ ተመራሁኝ? እደግመዋለሁ፣ ወላጆች ተኝተዋል። ልጆች አይን በሚያሳውር ፍቅር ተሞልተዋል፣ እውነት ስህተትን ለማረም ኃይል የለውም፡፡ የክፋት ማዕበልን ለመግታት ምን ሊደረግ ይችላል? ወላጆች ቢፈለጉ ብዙ ማድረግ ይችላሉ።CGAmh 432.3

    ገና በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ በመግባት ላይ ያለች ወጣት ሴት ልጅ በእርሷ የእድሜ ክልል ያለውን ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ወንድ ልጅ ጋር የተላመደች ከሆነ እንደዚህ አይነት ሁኔታ ተባብሶ በጭራሽ እንዳይደገም በዚህ ጉዳይ እንድትቆጭ መማር አለባት፡፡ ወንዶች ልጆች ወይም ወጣት ወንዶች በተደጋጋሚ የሴት ልጅን ጓደኝነት የሚሹ ከሆነ አንድ ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ያች ወጣት ሴት ማዕረግዋን የምታሳየት፣ እርሷን የምትገድባት እና በእርሷ እድሜ ያለች ሴት ምን ማድረግ እንደሚገባት የምታስተምራት እናት ያስፈልጋታል፡፡ CGAmh 433.1

    ከጤና አንፃር እንደሚታየው፣ የተለያዩ ጾታዎች አንድ ላይ መቀላቀል አለባቸው የሚል የተስፋፋ ብልሹ አስተምህሮ፣ የማጭበርበር ሥራውን ሰርቷል፡፡ ወላጆች እና አሳዳጊዎች የሰይጣን የሆነውን አንድ አስረኛ ብልጠትን ሲያሳዩ ይህ የተለያዩ ጾታዎች ውህደት ምንም ጉዳት የሌለው ሊሆን ይችላል። እንደዚያም ሆኖ፣ ሰይጣን የወጣቶችን አእምሮ ለማፍዘዝ በሚያደርገው ጥረት እጅግ ስኬታማ ነው፤ ደግሞም የወንዶች እና የሴቶች ውህደት ክፋቱን በሀያ እጥፍ ይጨምራል። 908Testimonies For The Church 2:482, 483.CGAmh 433.2

    ሥዕሉ አልተቀለመም— ሆነም ቀረ ይህ ጉዳይ በተጋነነ ብርሃን በፊቴ ቀርቧል በሚል እምነት እራስህን አታታልል። ስዕሉን ቀለም አልቀባሁትም፡፡ የፍርድን ምዘና ማለፍ የሚችሉ እውነታዎችን ገልጫለሁ፡፡ ንቁ! ንቁ! ስህተቶችን ለማረም እጅግ የዘገየ ከመሆኑ በፊት፣ እናም አንተ እና ልጆችህ በአጠቃላዩ ጥፋት እንዳትጠፉ እለምናችኋለሁ። የከበረውን ሥራህን ጀምር እና በጎዳናህ ላይ ከፈነጠቀው እና ካልታዘዝካቸው በላይ መሰብሰብ የምትችላቸውን የብርሃን ጨረሮች ሁሉ እንዲረዱህ ተጠቀምባቸው፤ ደግሞም አሁን በሚያበራው ብርሃን ከሚገኝ እርዳታ በተጫማሪ ልክ በእግዚአብሔር የፍርድ ችሎት ፊት እንዳለህ የህይወትህን እና የባህሪይህን ሁኔታ መመርመር ጀምር። 909Testimonies For The Church 2:401.CGAmh 433.3

    ወላጆች እስኪነቁ ድረስ፣ ለልጆቻቸው ተስፋ አይኖርም፡፡ 910Testimonies For The Church 2:406.CGAmh 434.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents