Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 13—የአካል ዕድገት ዋና አስፈላጊነት

    ምዕራፍ 57—የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ጤና

    [ማስታወሻ-የአድቬንቲስት ቤት ፣ 493-530 ፣ ክፍል XVII ፣ “ፈታ ማለት እና መዝናኛ”ን ይመልከቱ ፡፡]CGAmh 321.1

    በደንብ ቁጥጥር የተደረግበት ሥራ እና መዝናኛ— ልጆች እና ወጣቶች ጤናን፣ ደስታን፣ ንቁነትን፣ እና በደንብ ያደጉ ጡንቻዎች እና አንጎሎች እንዲኖራቸው፣ ከቤት ውጭ አየር ላይ ብዙ ጊዜ መሆን እና በደንብ ቁጥጥር የሚደረግበት ሥራ እና መዝናኛ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ 650Counsels to Parents, Teachers, and Students, 83. CGAmh 321.2

    ልጆች ባላቸው ጊዜ የሚሰሩት ነገር ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ትክክለኛ የአእምሮ ጉልበት እና ከቤት ውጭ የሚደረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የወንዶች ልጆችን አካል አይጎዳም፡፡ ፋይዳ ያለው ሥራ እና ከቤት ሥራ ምስጢሮች ጋር መተዋወቅ ለሴት ልጆቻችሁ ጠቃሚ ይሆናል፣ ደግሞም አንዳንድ ከቤት ውጭ የሚሠሩ ሥራዎች ለአካላቸው እና ለጤናቸው አስፈላጊ ናቸው፡፡2Testimonies For The Church 4:97.CGAmh 321.3

    የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ንጹህ አየር— የአካል ክፍሎችን በየቀኑ የማይጠቀሙ ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመስራት ሲሞክሩ ድካም እንደሚሰማቸው ይገነዘባሉ፡፡ በስርዓቱ ውስጥ እያንዳንዱ አካል የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ጅማቶች እና ጡንቻዎች ሥራቸውን ለማከናወን እና ሁሉንም ህይወት ያላቸውን ማሽኖች በጤነኛ ትግበራ ላይ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ላይ አይሆኑም፡፡ እጆች እና እግሮች ጥቅም ላይ ሲውሉ ይጠናከራሉ፡፡ በየቀኑ የሚሰራ መጠነኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለጡንቻዎች ጥንካሬን ይሰጣል፣ ይህም ያለ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብልሹ እና ደካማ ይሆናል፡፡ በየቀኑ ከቤት ውጭ በአየር ውስጥ ንቁ እንቅስቃሴ በማድረግ ጉበት፣ ኩላሊት እና ሳንባም ስራቸውን ለማከናወን ይበረታሉ፡፡CGAmh 321.4

    ቅዝቃዜን በመቋቋም እና ለነርቭ ስርዓት ኃይልን የሚሰጥ የፍቃድ ኃይል እንዲያግዛችሁ አድርጉ፡፡ እነዚህ በረከቶች ሳይኖሩ መኖር እንደማትችሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን እና የንጹህ አየርን ጥቅም በትክክል ትገነዘባላችሁ። አየር የተነፈገው ሳንባችሁ፣ ምግብ እንደተነፈገ የተራበ ሰው ነው፡፡ በእርግጥ እኛ እግዚአብሔር ለሳንባ ከሰጠው ምግብ አየር ይልቅ ያለ ምግብ ረዘም ላለ ጊዜ መኖር እንችላለን፡፡ 651Testimonies For The Church 2:533.CGAmh 322.1

    ተማሪዎች በተለይ አካላዊ ብቃት እንቅስቃሴ ያስፈልጋቸዋል— እንቅስቃሴ-አልባነት ስርዓትን ያዳክማል። እግዚአብሔር ወንዶችንና ሴቶችን ንቁ እና ጠቃሚ እንዲሆኑ አደርጎ ፈጥሯቸዋል፡፡ ሙሉ ጡንቻዎችን ከሚያንቀሳቅስ ፋይዳ ያለው ትክክለኛ እንቅስቃሴን የመሰለ የወጣቶችን ጥንካሬ የሚጨምር ነገር የለም፡፡ 652The Signs of the Times, August 19, 1875.CGAmh 322.2

    ሁሉም ብቃቶች በእንቅስቃሴ ነው የሚጠነክሩት— በትምህርት ቤት ውስጥ ተጠብቀው በመጽሐፍ ብቻ የተያዙ ሕጻናትና ወጣቶች ጤናማ ተክለ ሰውነት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ ተጓዳኝ አካላዊ እንቅስቃሴ ሳይኖር ጥናት ላይ ላይ ተወጥሮ ያለ አዕምሮ ደምን ወደ አንጎል የመሳብ አዝማሚያ አለው፣ በአካል ስርዓት ውስጥ ያለው የደም ዝውውርም ሚዛናዊነት የጎደለው ይሆናል፡፡ አንጎል በጣም ብዙ ደም ሲኖረው፣ ጽንፈ አካላት ደግሞ በጣም አናሳ ደም ይኖራቸዋል፡፡ የልጆችን እና የወጣቶችን ጥናቶች እስከ የተወሰኑ ሰዓቶች የሚቆጣጠሩ ህጎች መኖር አለባቸው፣ ከዚያም የተወሰነ የሰዓት ክፍል አካላዊ የጉልበት ሥራ ላይ መዋል አለበት፡፡ እንዲሁም የአመጋገብ፣ የአለባበስ እና የእንቅልፍ ልማዶቻቸው ከአካላዊ ህግ ጋር የሚስማሙ ከሆነ አካላዊ እና አእምሯዊ ጤናን መስዋዕት ሳያደርጉ ትምህርት ማግኘት ይችላሉ፡፡ 653Counsels to Parents, Teachers, and Students, 83.CGAmh 322.3

    ልጆች ትናንሽ ሆነው ሳሉ የሕይወት ትናንሽ ሀላፊነቶችን መሸከምን ይማሩ፣ እናም በዚህ መሠረት ሥራ ላይ የዋሉ ችሎታዎች በእንቅስቃሴ ይጠናከራሉ፡፡ በዚህ መንገድ ወጣቶች ጌታ ከዚያ በኋላ እንዲሰሩ በሚጠራቸው ታላቅ ሥራ ላይ ውጤታማ ረዳቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡...CGAmh 322.4

    በታታሪነት፣ አሳቢነት እና ተንከባካቢነት ልማዶች የሰለጠኑ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ስንፍና፣ እንቅስቃሴ አልባነትን፣ በዚህ ዘመን ላሉት ሕፃናት ትልቁ እርግማን ነው፡፡ የተሟላ፣ ጠቃሚ የጉልበት ሥራ ጥሩ ልማዶች እና ክቡር ባህሪይን በመፍጠር ትልቅ በረከት ይሆናል፡፡ 654The Review and Herald, August 13, 1881.CGAmh 323.1

    ሥራን ልዩ ልዩ እና ለውጥን ያለበት ለማድረግ ማቀድ— የወጣቶች ንቁ አእምሮ እና እጆች ሥራ ሊኖራቸው ይገባል፣ እናም ጠቃሚ ወደሆኑት፣ ወደሚያሳድጋቸው እና ሌሎችንም ወደሚባረኩ ስራዎች ካልተመሩ፣ ሥራ በሁለቱም በአካል እና በአእምሮ ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሆኖ ያገኙታል፡፡CGAmh 323.2

    ወጣቱ የሕይወትን ሸክም ከወላጆቹ ጋር በደስታ ማካፈል አለበት፣ ይህንንም በማድረግ ለአካላዊ እና ሥነ ምግባራዊ ጤንነት አዎንታዊ አስፈላጊነት ያለውን ንፁህ ሕሊና ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ይህንን ሲያደርጉ እጅግ እርዝማኔ ላለው ጊዜ በተመሳሳይ አቅጣጫ ከመያዝ ሊጠበቁ ይገባል፡፡ ሥራው አሰልቺ እስኪሆን ድረስ ወጣቱ በአንድ ዓይነት ሥራ ላይ በቋሚነት የሚያዙ ከሆነ ሥራውን በመለወጥ ወይም የእረፍት ጊዜ በመስጠት ሊመጣ ከሚችለው ያነሰ ውጤት ይገኛል። አዕምሮ እጅግ በጣም ከተወጠረ ጠንካራ መሆንን ያቆም እና ማሽቆልቆል ይጀምራል፡፡ በሥራ ለውጥ ጤና እና ብርታት ሊጠበቁ ይችላሉ፡፡ የራስ ወዳድነት መዝናኛዎች ለሥነ ምግባር አደገኛ በመሆናቸው ጥቅም ለሌለው ነገር ሲባል የሚጠቅመውን መተው አስፈላጊ አይደለም፡፡655The Youth’s Instructor, July 27, 1893. CGAmh 323.3

    ድካም፣ ጤናማ የሥራ ውጤት ነው— እናቶች ሆይ፣ ከሴቶች ልጆቻችሁ ላይ ሸክሞችን በማንሳት እና ምንም ልዩ ሥራ እንዳይሰሩ እና የራሳቸውን ሥራ እንዲመርጡ፣ በአንድ ነገር እንዲጠመዱ ለማድረግ ሲባል ምናልባትም ትንሽ የጥልፍ ወይም የጌጥ ሥራ እንዲሰሩ ከመስጠት የላቀ ወደ ክፋት የሚወስድ ምንም ነገር የለም፡፡ የእጆች እና የእግሮች እና የጡንቻዎች እንቅስቃሴ እንዲኖራቸው አድርጉ፡፡ ቢደክማቸውስ? እናንተ በስራችሁ ላይ አይደክማችሁምን? ከመጠን በላይ ካልሠሩ በስተቀር፣ ድካም እናንተን ከሚጎዳ ይልቅ ልጆቻችሁን ሊጎዳ ይችላልን? በእርግጥም አይደለም፡፡ 8Testimonies For The Church 2:371.CGAmh 323.4

    ሊደክሙ ይችላሉ፣ ነገር ግን ተገቢ ከሆነ ሥራ በኋላ ያለው እረፍት እጅግ ጣፋጭ ነው፡፡ መልካሙ የተፈጥሮ አዳሽ፣ እንቅልፍ የደከመውን አካል በማነቃቃት ለሚቀጥለው ቀን ኃላፊነቶች ያዘጋጃል፡፡ 656The Signs of the Times, April 10, 1884.CGAmh 324.1

    ድህነት ብዙውን ጊዜ በረከት የሚሆነበት ምክንያት— በአንዳንዶች ሀብትና ሥራ ፈትነት በእርግጥ በረከቶች እንደሆኑ ተደርገው ይታሰባሉ፤ ነገር ግን ሁል ጊዜ ሥራ የሚበዛባቸው እና በደስታ የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን የሚያከናውኑ ሰዎች፣ በጣም ደስተኞች እና እጅግ በጣም ጥሩ ጤንነትን የሚያጣጥሙ ናቸው፡፡… ለእለት እንጀራው ሰው መሥራት አለበት እና መጻኢው የደስታ እና የክብር ተስፋ የሚሉ አረፍተ ነገሮች ከአንድ ዙፋን የመጡ ሲሆን ሁለቱም በረከቶች ናቸው፡፡ 657Christian Temperance and Bible Hygiene, 97.CGAmh 324.2

    ወጣቶች እና ልጆች በእንቅስቃሴ-አልባነት እንዳይጠፉ ስለሚያደርግ፣ ድህነት፣ በብዙ ሁኔታዎች፣ በረከት ነው፡፡ አካላዊ እንዲሁም አእምሯዊ ኃይሎች ሊዳበሩ እና በትክክል ሊያድጉ ይገባል፡፡ የወላጆቻቸው የመጀመሪያ እና የማያቋርጥ ተግባር ልጆቻቸው ጤናማ ወንዶች እና ሴቶች ይሆኑ ዘንድ ጠንካራ ተክለ ሰውነት እንዲኖራቸው ማለም መሆን አለበት፡፡ ያለ አካላዊ እንቅስቃሴ ይህንን ዓላማ ከግብ ማድረስ አይቻልም፡፡CGAmh 324.3

    ለራሳቸው አካላዊ ጤንነት እና ሥነ ምግባራዊ ጥቅም ሲባል ሥራው አስፈላጊ ባይሆንም እንኳ ልጆች እንዲሠሩ ማስተማር አለባቸው፡፡ ንፁህና በጎ ምግባር እንዲኖራቸው ከተፈለገ፣ ሁሉንም ጡንቻዎች ወደ ተግባር የሚያመጣውን በጥሩ ሁኔታ ቁጥጥር የሚደረግበት የሥራ ሥልጠና ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ልጆች ጠቃሚ በመሆናቸው እና ሌሎችን ለመርዳት እራሳቸውን በመገደብ የሚያገኙት እርካታ መቼም ያላጣጣሙት በጣም ጤናማ ደስታ ይሆናል፡፡11Testimonies For The Church 3:151.CGAmh 324.4

    የአእምሮ እና የአካል እንቅስቃሴዎችን ማመጣጠን— ተማሪዎች ለአካላዊ ሥልጠና ጊዜ እስኪያጡ ድረስ ብዙ ትምህርቶችን እንዲወስዱ ሊፈቀድላቸው አይገባም፡፡ በየዕለቱ የተወሰነ ሰዓት አየር ውስጥ ጡንቻዎችን ሥራ ላይ ለማዋል ካልተሰጠ በስተቀር ጤንነትን መጠበቅ አይቻልም፡፡ የተጠቀሱ ሰዓቶች ሁሉንም የሰውነት ክፍሎች ወደ እንቅስቃሴ ለሚጋብዝ የተወሰነ የጉልበት ሥራ መሰጠት አለባቸው፡፡ የአእምሮ እና የአካል ኃይሎች ተግባርን አመጣጥኑ እና የተማሪው አእምሮ ይታደሳል። እርሱ ከታመመ አካላዊ እንቅስቃሴ ብዙውን ጊዜ የአካል ስርዓትን ወደ መደበኛ ሁኔታው ለመመለስ ይረዳል፡፡ ተማሪዎች ከኮሌጅ ሲወጡ ከገቡበት ጊዜ ይልቅ የተሻለ ጤና እና ስለ ሕይወት ህጎች የተሻለ ግንዛቤ ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ጤና እንደ ባህሪይ በቅድስና ሊጠበቅ ይገባል፡፡ 658Christian Temperance and Bible Hygiene, 82, 83.CGAmh 325.1

    የወጣትነት ኃይል— እንዴት በችኮላ እንደሚባክን—ወጣቶች በህይወት አፍላነት እና ጥንካሬ ውስጥ ስለ ተትረፈረፈው የጉልበታቸው ዋጋ ብዙም አይገነዘቡም። ከወርቅ የበለጠ ውድ ሀብት፣ ከመማር ወይም ከማህረተሰብ ደረጃ ወይም ከሀብት የበለጠ ለመለወጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ሀብት — ምን ያህል ቀላል ተደርጎ ተይዟል! ምን ያህል በችኮላ ባክኗል!... CGAmh 325.2

    በሥነ-አካል ጥናት ውስጥ ተማሪዎች የአካላዊ ኃይል ዋጋን እና እንዴት በሕይወት ታላቅ ትግል ውስጥ ስኬታማ ለመሆን በከፍተኛ ደረጃ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት እና እንዴት ሊጠበቅ እና ሊዳብር እንደሚችል ለማየት መመራት አለባቸው፡፡13Education, 195, 196.CGAmh 325.3

    እንቅስቃሴን መምራት እንጂ ማገድ አያስፈልግም— ልጆቻችን ከዚህ ቀደም እንደነበረው መንታ መንገዶች ላይ ቆመዋል። በእያንዳንዱ እጅ ራስን ለማስደሰት የመፈለግ እና እንዳሻቸው የመሆን የዓለም ፈንጠዚያዎች ለጌታ ለተቤዡት ከተዘረገው ጎዳና ሊለዩአቸው ጥሪ ያቀርቡላቸዋል፡፡ ህይወታቸው በረከት ወይም እርግማን መሆኑ በምርጫቸው ላይ የተመሠረተ ነው። ያልተሞከሩ አቅሞቻቸውን ለመሞከር ጓጉተው በሃይል ተሞልተው ሳሉ፣ ከመጠን በላይ ለተትረፈረፈው ህይወታቸው የተወሰነ መውጫ ማግኘት አለባቸው፡፡ ለመልካም ሆነ ለክፉ ንቁ ይሆናሉ፡፡CGAmh 325.4

    የእግዚአብሔር ቃል እንቅስቃሴን በቀና መንገድ ይመራል እንጂ አያግድም። እግዚአብሔር ወጣቶች ለእድገት አናሳ ምኞች እንዲኖራቸው አያዛቸውም፡፡ አንድን ሰው በእውነቱ ስኬታማ እና በሰው ዘንድ የተከበረ እንዲሆኑ የሚያደርጉት የባህርይ ንጥረ ነገሮች— ለአንድ የላቀ ጥቅም የማይበገር ፍላጎት፣ የማይበገር ፈቃድ፣ ብርቱ አተገባበር፣ የማያቋርጥ ጽናት— መደናቀፍ የለባቸውም። በእግዚአብሔር ቸርነት ልክ ሰማያት ከምድር ከፍ እንደሚሉ ሁሉ ከራስ ወዳድነት እና ከዓለማዊ ፍላጎቶች የበለጠ ከፍ ያሉ ዓላማዎችን እንዲያሳኩ ምሪት ማግኘት አለባቸው፡፡ 659The Ministry of Healing, 396.CGAmh 326.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents