Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 47—ልል ተግሳጽ እና ፍሬው

    የተሳሳተ የስልጠና መላ ሃይማኖታዊ ሕይወት ላይ ተጽዕኖ ያሳርፋል— ልጆቻቸው እግዚአብሔርን እንዲፈሩ ባላሠለጥኗቸው ነገር ግን ሳይገሩ እና ቁጥጥር ሳይደረግባቸው ጎልማሳ ወንድ እና ሴት ሆነው እንዲያድጉ በሚፈቅዱላቸው ወላጆች ላይ ወዮ ያርፍባቸዋል፡፡ እነርሱ በልጅነት ጊዜያቸው ስሜትን እና ግትርነትን እንዲያንጸባርቁ እና በስሜታቸው ምሪት አንድ ነገር እንዲያደርጉ ስለተፈቀደላቸው ይህንኑ መንፈስ ወደ ራሳቸው ቤት ያመጣሉ፡፡ በስሜት ጉድለት ያላቸውና እና በአስተዳደራቸው ግልፍተኞች ናቸው፡፡ ክርስቶስን ሲቀበሉ እንኳን በልጅነታቸው ልብ ውስጥ እንዲነግሱ የተፈቀደላቸውን ስሜቶችንም አላሸነፉም፡፡ የልጅነታቸውን የሥልጠና ውጤቶችን በመላ ሃይማኖታዊ ሕይወታቸው ይዘው ይኖራሉ፡፡ ያን ጊዜ በጌታ ተክል ላይ የተቀረጸውን ማስወገድ በጣም ከባድ ነገር ነው፤ ምክንያቱም ቀንበጡ ሲጎብጥ፣ ዛፉ ዘንበል ይላል። እንደነዚህ ያሉት ወላጆች እውነትን ከተቀበሉ ሊዋጉት የሚገባቸው ከባድ ትግል አለባቸው፡፡ በባህሪያቸው ሊለወጡ ይችላሉ፣ ነገር ግን መላው ሃይማኖታዊ ልምምዶቻቸው በልጅነት ሕይወታቸው ሲለማመዱ በነበረ ልል ስልጠና ሳቢያ ተጽዕኖ ደርሶበታል፡፡ እናም ልጆቻቸው ጉድለት ባለው ሥልጠና ምክንያት መሰቃየት አለባቸው፤ ምክንያቱም እነርሱ ጉድለቶቻቸውን በሦስተኛውና በአራተኛው ትውልድ አሻራቸውን አሳርፈዋል። 538The Review and Herald, October 9, 1900. CGAmh 259.1

    የዛሬዎቹ ኤሊዎች — ወላጆች ኤሊ እንዳደረገው የልጆቻቸውን ስሕተቶችን ሲያጸድቁ እና በዚያውም እንዲቀጥል ሲያደርጉ፣ እግዚአብሔር የራሳቸውን ተጽዕኖ እንዳጠፉ ብቻ ሳይሆን፣ መቆጣጠር የነበረባቸውን የወጣቶቹንም ተጽዕኖ እንዳጠፉ ማየት የሚችሉበት ሥፍራ ላይ በእርግጥ ያመጣቸዋል…፡፡ መማር የሚገባቸው መራራ ትምህርቶች አሏቸው፡፡2Manuscript Releases 3:3, 1903.CGAmh 259.2

    በየትኛውም ሥፍራ የልጆቻቸውን አስቸጋሪነት ሲያስተባብሉ የሚገኙ የዛሬዎቹ ኤሊዎች ልጆቻቸውን ለመቆጣጠር እና ለማረም እግዚአብሔር የሰጣቸውን ሥልጣናቸውን አቤት በፍጥነት ባረጋገጡ! በጥበቃቸው ስር ያሉትን ልጆች ኃጢአት በንቀት የሚመለከቱ እና የሚያስተባብሉ ወላጆች እና አሳዳጊዎች በዚህ ሁኔታቸው የእነዚህ ስህተቶች አጋዦች መሆናቸውን ያስታውሱ፡፡ ገደብ የለሽ ምኞታቸውን ከማርካት ፈንታ በስሜታዊነት ሳይሆን በፍቅርና በጸሎት አዘውትረው የቅጣት በትርን ተጠቅመው ቢሆን ኖሮ ደስተኛ ቤተሰቦችን እና የተሻለውን የህብረተሰብ ሁኔታ ማየት በቻልን ነበር፡፡ 539The Signs of the Times, November 24, 1881.CGAmh 260.1

    የኤሊ ቸልተኝነት በአገሪቱ በሚኖሩ በእያንዳንዱ አባትና እናት ሁሉ ፊት በግልጽ ቀርቧል፡፡ ባልተቀደሰ ፍቅሩ ወይም ደስ ያልተሰኘበትን ኃላፊነቱን ለመወጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ፣ በጠማማ ልጆቹ አማካይነት የኃጢአት ፍሬን አጭዷል። ክፋቱን የፈቀደው ወላጅም ሆነ ያንን ይፈጽሙ የነበሩ ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በደለኞች ነበሩ፣ እርሱም ስለ መተላለፋቸው መስዋእት ወይም ቁርባንን አይቀበልም፡፡ 540The Review and Herald, May 4, 1886.CGAmh 260.2

    በባህሪይ ጉድፈት የተረገመ ማህበረሰብ — አቤት! ወላጆች ጥበበኛ የሚሆኑት መቼ ነው? በእግዚአብሔር ቃል መመሪያ መሰረት ታዛዥነትን እና አክብሮትን እንደ መስፈርት ከማቅረብ ችላ ሲሉ የሥራቸውን ባህሪይ መቼ ይመለከታሉ፣ መቼስ ይገነዘባሉ? የዚህ ልል ሥልጠና ውጤት ልጆች ወደ ዓለም ወጥተው የገዛ ቤተሰቦቻቸው ላይ ራስ ሲሆኑ የሚታይ ይሆናል፡፡ የወላጆቻቸውን ስህተቶች ቀጣይ ያደርጋሉ፡፡ የባህሪይ ጉድለቶቻቸው ሙላት ላይ ደርሷል፤ እንዲሁም በባህሪያቸው ውስጥ እንዲጎለብቱ የተፈቀደላቸውን የተሳሳቱ ምርጫዎቻቸውን፣ ልማዶቻቸውን እና ስሜቶቻቸውን ለሌሎች ያስተላልፋሉ፡፡ ስለዚህ ለህብረተሰቡ በረከት ከመሆን ይልቅ እርግማን ይሆናሉ፡፡ 541Testimonies For The Church 5:324, 325.CGAmh 260.3

    በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ያለው ክፋት ዱካው ቢፈለግ ወላጆች እራሳቸውን እና ልጆቻቸውን ለማረም ቸልተኞች በመሆናቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል። በሺዎች የሚቆጠሩ የሰይጣን ሰለባዎች አሁን ያሉበት ሁኔታ ውስጥ የገቡበት ምክንያቱ በልጅነት ዕድሜያቸው የተያዙበት ሥርዓት ዓልባ ሁኔታ ነው፡፡ ጥብቅ የእግዚአብሔር ተግሣጽ በዚህ ላይ የአስተዳደር ጉደለት ላይ ነው፡፡ 542Manuscript Releases 4:9, 1901.CGAmh 260.4

    የተግሳጽን ልጓም ማላላት— በተሳሳተ መንገድ የተገዙ፣ መታዘዝ እና አክብሮትን ያልተማሩ ልጆች፣ ራሳቸውን ከዓለም ጋር በመቆራኘት ወላጆቻቸው ላይ ልጓም በማድረግ በእጃቸው አስገብተው ራሳቸው ወደ መረጡት ሥፍራ ይመሯቸዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ ልጆች ለወላጆቻቸው ምክር ያለ ምንም ጥያቄ አክብሮት እና ታዛዥነት ማሳየት በነበረባቸው ጊዜ፣ ወላጆች የተግሣጽን ልጓም ያላላሉ። እስከ ዛሬ ድረስ የጽኑ ኃይምኖተኝነት ምሳሌ ሆነው የቆዩ ወላጆች አሁን በልጆቻቸው ይመራሉ። ጽናታቸው ጠፍቷል። የክርስቶስን መስቀል የተሸከሙና የጌታ የሱስን ምልክት እንደ ብቸኛ ዓላማ የጠበቁ አባቶች በልጆቻቸው አጠያያቂ እና እርግጠኛ ባልሆኑ መንገዶች ይመራሉ። 543The Review and Herald, April 13, 1897. CGAmh 261.1

    የትላልቅ ልጆችን አግባብነት የሌላቸውን ምኞቶች ማርካት— የተሰጣቸውን ኃላፊነት መገንዘብ የነበረባቸው አባቶችና እናቶች በማደግ ላይ ያሉ የወንዶችና የሴቶች ልጆች ዝንባሌን ለማሟላት ሲሉ ተግሣጻቸውን ላላ ያደርጋሉ። የልጁ ፍላጎት እውቅና የተሰጠው ሕግ ነው፡፡ መሠረታዊ መርኾን በመከተል ረገድ ጽኑ፣ ወጥ እና የማያወላውሉ፣ ቀላል የአኗኗር ዘዴን እና ታማኝነትን የሚጠብቁ እናቶች ወንዶች እና ሴቶች ልጆቻቸው ለአካለ መጠን ሲደርሱ አግባብነት የሌላቸውን ፍላጎቶቻቸውን ያረካሉ። ከሃዲዎቹ አይሁዶች ልጆቻቸውን ለሞሎክ በእሳት ውስጥ እንደሚያሳልፉ ሁሉ እነርሱም ለታይታ ባላቸው ፍቅር የተነሳ ልጆቻቸውን ለሰይጣን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡8Manuscript Releases 11:9, 1899.CGAmh 261.2

    በልጆች ዘንድ ተወዳጅነትን ለማግኘት እግዚአብሔርን ማዋረድ— አባቶች እና እናቶች እግዚአብሔርን የማያምኑ ልጆችን ዝንባሌ መንገድ በመስጠት እና በዓለም እንዲታዩ በገንዘብ እና በመገልገያ መሰሪያዎች እየረዷቸው ይገኛሉ፡፡CGAmh 261.3

    አቤት፣ እንደነዚህ ያሉ ወላጆች ለአምላክ ምን አይነት ሰበብ ያቀርቡ ይሆን! ከዚህ በፊት ከመርህ የተነሳ ሲኮንኑ የነበሩትን የፈንጠዚያ በሮችን በመክፈት እግዚአብሔርን በማዋረድ ለክፉ ልጆቻቸው አክብሮታቸውን ሁሉ ያሳያሉ፡፡ ልጆቻቸው ለአለም እንዲማረኩ የካርድ ጨዋታዎችን፣ ጭፈራዎችን እና የዳንስ ምሽቶችን ይፈቅዱላቸዋል፡፡ እውነተኛ ክርስቲያን ምን እንደሆነ በማስመስከር በልጆቻቸው ላይ ያላቸው ተጽዕኖ ጠንካራ መሆን በነበረበት ጊዜ፣ እንደ ኤሊ በልጆቻቸው ዘንድ ተወዳጅንነትን ለማግኘት ሲሉ እግዚአብሔርን በማዋረድ እና መስፈርቶቹን ችላ በማለት በእግዚአብሔርን እርግማን ሥር ራሳቸውን ያደርጋሉ፡፡ ነገር ግን ለሞት በተቃረቡበት ጊዜ የፋሽን ቀናተኛ አምላኪ መሆን ብዙ ዋጋ አይኖረውም፡፡ ምንም እንኳን አንዳንድ የወንጌል አገልጋዮች እንደዚህ ዓይነቱን ሃይማኖት ሊያፀድቁ ቢችሉም ወላጆች ምንም ዋጋ የሌላቸውን የክብር ማዕረጎችን ለማግኘት የክብር አክሊልን እየተው እንደሆነ ይገነዘባሉ፡፡ አባቶች እና እናቶች ለኃላፊነታቸው ይነሳሱ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳቸው! 544The Review and Herald, April 13, 1897.CGAmh 262.1

    ልጆቻችሁ እንዲሆኑ የምትፈልጉት አይነት ሰው ሁኑ — ልጆቻችሁ እንዲሆኑ የምትፈልጉት አይነት ሰው ሁኑ፡፡ ወላጆች የራሳቸውን የባህሪይ ማህተም በመመሪያ እና ምሳሌነት ከትውልድ ወደ ትውልድ በማስተላለፍ ራሳቸውን ያዘልቃሉ። የሚዋልሉ፣ ጨካኝ፣ ትህትና የጎደላቸው ስሜቶች እና ቃላት በልጆች እና በልጅ ልጆች ላይ ይቀረጻሉ፣ እና በዚህ መንገድ በወላጆች አስተዳደር ላይ ያሉ ጉድለቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እየመሰከረባቸው ይሄዳል። 545The Signs of the Times, September 17, 1894CGAmh 262.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents