Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 75—ትናንሽ ልጆችን ወደ ጌታ መምራት

    ልጆች በምን ያህል ዕድሜ ክርስትያኖች ሊሆኑ ይችላሉ?— በልጅነት ጊዜ አእምሮው በቀላሉ ተጽዕኖ ሥር የሚወድቅ እና የሚቀረጽ ነው፣ በመሆኑም ወንዶችና ሴቶች ልጆች እግዚአብሔርን እንዲወዱ እና እንዲያከብሩ መማር ያለባቸው በዚያ ጊዜ ነው። 974Manuscript Releases 11:5, 1903.CGAmh 464.1

    እግዚአብሔር በለጋ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆች ሁሉ የእርሱ ልጅ እንዲሆኑ፣ ወደ ቤተሰቡ በማደጎነት እንዲቀላቀሉ ይፈልጋል። ምንም እንኳን ልጆች ቢሆኑም ወጣቶች የእምነት ቤተሰብ አባላት ሊሆኑ እና እጅግ ውድ ተሞክሮ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ዘላቂ የሆኑ ተጽዕኖዎችን ለመቀበል ሩህሩህ እና ዝግጁ የሆኑ ልብ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ልባቸውን በራስ መተማመን እና የሱስን በመውደድ እንዲዘልቅ ማድረግ እና ለአዳኝ ሊኖሩ ይችላሉ። ክርስቶስ ትናንሽ ሚስዮናውያን ያደርጋቸዋል፡፡ ኃጢአት የሚደሰቱበት ነገር ሳይሆን ሊሸሹት እና ሊጠሉት የሚገባ ሆኖ እንዲታያቸው የመላ ሀሳባቸው ፍሰት ሊለወጥ ይችላል፡፡ 974Counsels to Parents, Teachers, and Students, 169.CGAmh 464.2

    ምንም ውጤት የማያስገኝበት ዕድሜ— በአንድ ወቅት አንድ ልጅ ተስፋ የሚጣልበት ምክንያታዊ ክርስቲያን ለመሆን ዕድሜው ስንት መሆን አለበት የሚል ጥያቄ ለዝነኛ የመለኮት ሊቅ ቀርቦለት ነበር። መልሱ “ዕድሜ ከዚያ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም” የሚል ነበር፡፡ “ኢየሱስን መውደድ፣ እምነት መጣል፣ ማረፍ፣ መተማመን ሁሉም ከልጁ ተፈጥሮ ጋር የሚስማሙ ባህሪዎች ናቸው፡፡ አንድ ልጅ እናቱን መውደድ እና መተማመን በቻለበት ቅጽበት ኢየሱስን እንደ እናቱ ጓደኛ አድርጎ መውደድ እና መተማመን ይችላል። ኢየሱስ ተወዳጅ ክቡር ጓደኛው ይሆናል፡፡” ከላይ ከተጠቀሰው እውነተኛ አረፍተ-ነገር አንጻር ወላጆች በእነዚያ ንቁ ጥቃቅን ዓይኖች እና ስለታም ህሊናዎች ፊት መመሪያ እና ምሳሌን በማቅረብ ረገድ በጣም መጠንቀቅ ይችላሉን? ኃይማኖታችን ተግባራዊ ሊሆን ይገባል፡፡ በቤተ-አምልኮ ውስጥ እንደሚሆነው ሁሉ በቤታችንም ውስጥ ይፈለጋል፡፡ በባህሪያችን ውስጥ ምንም አይነት ጭካኔ፣ ኃይለኝነት እና ማስፈራራት ሊኖር አይገባም፤ ነገር ግን ሞቅ ያለ እና አፍቃሪ ልቦች እንዳሉን ቸርነትና ርህራሄ ማሳየት አለብን። ኢየሱስ በቤተሰብ ክልል ውስጥ የተከበረ እንግዳ መሆን አለበት፡፡ ከእርሱ ጋር መነጋገር ፣ ሸክማችንን ሁሉ ወደ እርሱ ማምጣት፣ እና ስለ ፍቅሩ፣ ስለ ፀጋው እና ስለ ባህርይው ፍጽምና መነጋገር አለብን። ፈርሃ እግዚአብሔር ያላቸው ወላጆች ራሳቸው መፍትሄ መስጠት በማይችሉበት ኑሮ እና ግራ መጋባቶች ላይ ከመጨነቅ እና ከበድ ያሉ ወቀሳዎችን ከመሰንዘር ይልቅ ችግሮቻቸውን ሁሉ ሸክሞችን ወደ ሚሸከመው ወደ ኢየሱስ በማምጣት በየዕለቱ እጅግ መልካም ትምህርት መስጠት ይችላሉ፡፡ አበባ ክፍት ቀንበጦቹን ወደ ፀሐይ እንደሚያዞራቸው ሁሉ የትንንሾቹ ልጆች አእምሮ ወደ ኢየሱስ እንዲዞር ማስተማር ይቻላል፡፡ 976Good Health, January, 1880.CGAmh 464.3

    በእያንዳንዱ ትምህርት ውስጥ የእግዚአብሔርን ፍቅር ማስተማር ተገቢ ነው— ልጆች ሊማሩት የሚገባቸው የመጀመሪያው ትምህርት እግዚአብሔር አባታቸው መሆኑን ነው፡፡ ይህ ትምህርት በልጅነት ዕድሜያቸው ላይ መሰጠት አለበት፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው ከሰማይ አባታቸው ጋር እንዲተዋወቁ በማድረግ ረገድ በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂዎች መሆናቸውን መገንዘብ አለባቸው…፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር መሆኑን በእያንዳንዱ ትምህርት ውስጥ ማስተማር ተገቢ ነው፡፡ 977The Review and Herald, June 6, 1899.CGAmh 465.1

    አባቶች እና እናቶች የኢየሱስን ፍቅር ጨቅላ ሕጻንን፣ ልጅን እና ወጣቶችን ማስተማር አለባቸው። የመጀመሪያው የሕፃን ልጅ ኮልታፋ ንግግሮች ስለ ክርስቶስ ይሁኑ፡፡ 978The Review and Herald, October 9, 1900.. ክርስቶስ ለልጆች ከሚሰጡ ትምርቶች ሁሉ ጋር የተቆራኘ መሆን አለበት፡፡6The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 465.2

    ከልጁ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጀምሮ ከነገረ- እግዚአብሔር ጋር እንዲተዋወቅ ማደረግ አለበት። ቀላል ባሉ ቃላት እናት ክርስቶስ በምድር ላይ ስላሳለፈው ሕይወት ትንገረው፡፡ ከዚያም በላይ፣ የአዳኙን ትምህርቶች ወደ ዕለታዊ ህይወቷ ታምጣ። ይህ ሕይወት የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር ከተማ የሚያሰገባቸውን ባህሪያትን መቅረጽ የሚችሉበት፣ ለመጪው ሕይወት ዝግጅት የሚያደርጉበት ጊዜ መሆኑን ምሳሌ በመሆን ለልጇ ታሳይ፡፡ 979Manuscript Releases 2:1903.CGAmh 466.1

    በተልመዶ አንድን ነገር ከማሳወቅ የላቀ ይፈልጋሉ— ለልጆቻችን እና ለወጣቶቻችን በአጠቃላይ ብዙም ትኩረት አልተደረገም፣ በመሆኑም በክርስቲያናዊ ሕይወት እንደሚፈለገው ማደግ አልቻሉም፣ ምክንያቱም የቤተክርስቲያን አባላት በመለኮታዊ ሕይወት እንዲሻሻሉ በመሻት በርህራሄ እና ሐዘኔታ አልተመለከቷቸውም፡፡ 980The Review and Herald, February 13, 1913.CGAmh 466.2

    ልጆች ችላ ሲባሉ እና ሲታለፉ ጌታ አይከብርም…፡፡ በተለምዶ አንድን ነገር ከማሳወቅ የላቀ፣ ከማበረታቻ ቃላት የላቀ ነገር ይፈልጋሉ፡፡ ከፍተኛ ሥራ፣ ጸሎት እና ጥንቃቄ የተሞላበት ተግባር ያስፈልጋቸዋል፡፡ በፍቅር እና ሐዘኔታ የተሞላ ልብ ግልጽ በሆነ ሁኔታ ግድየለሾች እና ተስፋ ቢስ ወጣቶችን ተደራሽ ማድረግ ይችላሉ፡፡9Counsels on Sabbath School Work, 77.CGAmh 466.3

    የሱስ “እነዚህን ልጆች አሰልጥኑልኝ” ይላል— ወላጆች ልጆቻቸውን ለአምላክ መኖሪያ ማሰልጠን እንዳለባቸው መረዳትን መሻት አለባቸው፡፡ ልጆች በአደራ ሲሰጧቸው፣ ልክ ክርስቶስ በእቅፋቸው አስቀምጦ “በአምላክ መኖሪያ ውስጥ ያበሩ ዘንድ እነዚህን ልጆች አሰልጥኑልኝ” ሲል እንደተናገረ መቆጠር አለበት፡፡ ትኩረታቸውን መሳብ ካለባቸው ድምጾች አንዱ የኢየሱስ ስም ነው፣ በመሆኑም ገና በለጋ ዕድሜያቸው ወደ ጸሎት መጸለይያ ኩርሲ መመራት አለባቸው፡፡ አዕምሮአቸው በጌታ ሕይወት ታሪክ መሞላት አለበት፣ ሕሊናቸውም የመጻኢውን ዓለም ክብር እንዲቀርጽ መደፋፈር አለበት፡፡ 981The Review and Herald, February 19, 1895.CGAmh 466.4

    በልጅነታቸው የክርስትና ልምምድ ሊኖራቸው ይችላል— ልጆቻችሁ ክርስቶስ እርሱን ለመወዱት ሊያዘጋጅ ለሄደው መኖሪያ ቤት እንዲዘጋጁ እርዷቸው፡፡ እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ያለው ዕቅድ እንዲሰምር እርዷቸው፡፡ ስልጠናችሁ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ዘላለማዊውን ሕይወት ለእነርሱ ለማረጋገጥ ለሞተው ክብር ይሆኑ ዘንድ የሚረዳቸው አይነት ይሁን፡፡ “ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡ ቀንበሬም ልዝብ ሸክሜም ቀሊን ነውና” ለሚለው ጥሪ ምላሽ እንዲሰጡ አስተምሯቸው፡፡ 982Manuscript Releases 13:8, 1903.CGAmh 467.1

    ወንድም እና እህቴ ሆይ፣ ልጆቻችሁን በማሰልጠን ረገድ የተቀደሰ ሥራ አላችሁ፡፡ ገና በልጅነታቸው ልባቸው እና አዕምሮአቸው ለቀና ተጽዕኖ የተጋለጡ ናቸው…፡፡ ገና በልጅታቸውም እንኳ መስራት ያለባቸው የግል ድርሻ እንዳላቸው እና ማካበት ያለባቸው የክርስትና ልምምድ እንዳለ አስተምሯቸው፡፡ 983Letter 10, 1912.CGAmh 467.2

    ወላጆች የልጆቻቸውን እግሮች ከልጅታቸው ጀምሮ ወደ ጽድቅ መምራትን የሕይወታቸው ግንባር ቀደም ሥራ ካላደረጉ በስተቀር ከቀናው ጎዳና ይልቅ የስህተትን ጎዳና ሊመርጡ ይችላሉ፡፡ 984The Review and Herald, April 14, 1885.CGAmh 467.3

    የፈቃድ ታዛዥነት የመለወጥ መመዘኛ ነው— ለእግዚአብሔር ፈቃድ በፈቃደኝነት መታዘዝ ክርስትያኖች ነን የሚሉ ሰዎች በእርግጥም ክርስትያኖች ስለ መሆናቸው ማረጋገጫ እንደሆነ ልጆቻችንን አናስተምራቸውምን? ጌታ ማለት እርሱ የተናገራቸውን እያንዳንዱ ቃላት ናቸው፡፡ 985Manuscript Releases 6:4, 1899.CGAmh 467.4

    የእግዚአብሔር ሕግ የተሃድሶ መሰረት ነው— የእግዚአብሔር ሕግ ቤተሰብ የሚስተማርበት መንገድ መሆን አለበት፡፡ ወላጆች ጥብቅ ስለ ሆነው ጨዋነት ለልጆቻቸው ምሳሌ በመተው በእግዚአብሔር ሕግ የመሄድ እጅግ የከበረ ግዴታ ሥር ናቸው…፡፡CGAmh 467.5

    የእግዚአብሔር ሕግ የዘላቂ ተሃድሶ መሰረት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሕግን የመታዘዝ አስፈላጊነትን በግልጽ እና በማያወላዳ መልኩ ለዓለም ማቅረብ አለብን፡፡ ታላቁ የተሃድሶ እንቅስቃሴ ከቤት መጀመር አለበት፡፡ ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ ለትጋት፣ ለኢኮኖሚ፣ ለታማኝነት እና በሰው እና በሰው መካከል በፍትህ ለመፍረድ ታላቅ የሚገፋፋ ኃይል ነው፡፡15Letter 74, 1900.CGAmh 468.1

    እርሱን ልጆችን አስተምሯቸው— ልጆች ከልጅነታቸው ጀምሮ የእግዚአብሔርን ሕግ እንዲጠብቁ አስተምራችኋልን? … ክርስቶስ ራሱን እንዲገልጥላቸው፣ በመለኮት አምሳል ባህሪያቸውን እንዲቀርጹ አስተምሯቸው፡፡ እርሱ ራሱን ለልጆች ለመግለጥ ፈቃደኛ ነው፡፡ ይህንን ከዮሴፍ፣ ከሳሙኤል እና ከዳንኤል ታሪክ እንረዳለን፡፡ ከእነርሱ የሕይወት መዝገብ ላይ እግዚአብሔር ከልጆች እና ከወጣቶች ምን እንደሚጠብቅ አንመለከትምን? 986Manuscript Releases 6:2, 1901.CGAmh 468.2

    ወላጆች… ልጆቻቸው ገና በልጅነታቸው ለእርሱ ብቁ በመሆን የኢየሱስ ክርስቶስ ተከታይ መሆን ምን ምን እንደሚያካትት የላቀ ዕውቀት እንዲኖራቸው አድረገው ለእግዚአብሔርየማቅረብ ግዴታ አላቸው፡፡ 987Manuscript Releases 5:9, 1900..CGAmh 468.3

    የተለወጠ ልጅ ምስክርነት— ኃይማኖት ልጆች የተሸለ ጥናት እንዲያደርጉ እና የላቀ ታማኝነት የተሞላበት ሥራ እንዲሰሩ ይረዳቸዋል፡፡ አንዲት ትንሽ የአሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ክርስቲያን ስለ መሆኗ ቀላል ባለ መንገድ መረጃ ታቀርባለች፡፡ “መጫወት እንጂ ማጥናት አልፈልግም ነበር፡፡ ትምህርት ቤት ውስጥም ሥራ ፈት እና ብዙውን ጊዜ ከትምህረቴ እቀር ነበር፡፡ አሁን እግዚአብሔርን ለማስደሰት የሚረዳኝን ትምህርት በደንብ አግኝቻለሁ፡፡ ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ አስተማሪው ሳያየኝ ሲቀር ልጆች እንዲመለከቱኝ አስቂኝ ነገሮችን በመስራት ተንኮል እሰራ ነበር፡፡ አሁን መልካም ባህሪይ በማሳየት እና የትምህርት ቤቱን ሕጎች በመጠበቅ እግዚአብሔርን ማስደሰት እሻለሁ፡፡ ቤት ውስጥ ራስ ወዳድ ነበርኩኝ፣ መላክ አልወድም ነበር፣ ደግሞም እናቴ በሥራ እንድረዳት ከጨዋታ ላይ ስትጠራኝ አኩራፊ ነበርኩኝ፡፡ አሁን በማናቸውም ነገሮች እናቴን መርዳት እና እንደምወዳት ለእርሷ ማሳየት እውነተኛ ደስታ ይሰጣኛል፡፡” 988Counsels on Sabbath School Work, 79.CGAmh 468.4

    ሥራን ከማዘግየት ተጠበቁ— ወላጆች፣ ልጆቻችሁ ገና በልጅነታቸው ክርስቲያኖች እነዲሆኑ በማለም አእምሯቸውን ማሰልጠንን መጀመር ይኖርባችኋል…። ኃላፊነትን ለመሸከም ገና ልጆች ናቸው፣ ስለ ኃጢአታቸው ንስሃ ለመግባት እና ከክርስቶስ ጋር ቃለ-መሃላ ለመፈጸም ገና አልበቁም በሚል የተሳሳተ አመለካከት በጥፋት ገደል ላይ እነርሱን ከማባበል ተጠበቁ፡፡19Testimonies For The Church 1:396.CGAmh 469.1

    የስምንት፣ አሥር ወይም አሥራ ሁለት ዓመት ልጅ በግላዊ ኃይማኖት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ተደራሽ መሆን የሚያስችለው በቂ ዕድሜ ላይ ነው ያለው፡፡ ልጆቻችሁ ወደ ፊት ሲያድጉ ንስሃ እንደሚገቡ እና እውነትንም ማመን እንዳለባቸው አታስተምሯቸው፡፡ በተገቢ ሁኔታ የተማሩ እንደሆነ ትናንሽ ልጆች ስለ ኃጢአተኛ ሁኔታቸው እና በክርስቶስ አማካይነት ስለ ሆነው የድነት መንገድ ትክክለኛ እይታ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ 989Testimonies For The Church 1:400.CGAmh 469.2

    በልጅነታቸው አዳኛቸውን ሲሹ የነበሩ ሰዎች መዝገብ ላይ ያሉትን በርካታ ውድ ተስፋዎችን እንድመለከት ተመራሁ፡፡ መክብብ 12፡1፡- “የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፤ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም አመታት ሳይደርሱ፡፡” ምሳሌ 8፡17፡- “እኔ የሚወዱኝን እወድዳለሁ፣ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል፡፡” ታላቁ የእስራኤል እረኛ አሁንም እንዲህ ይላል፣ “ሕጻናትን ተውአቸው፣ ወደ እኔም ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው፤ መንግስተ ሰማያት እንደነዚህ ላሉ ናትና፡፡” ወጣትነት ጌታ የሚፈለግበት በጣም ጥሩ ጊዜ እንደሆነ አስተምሯቸው፡፡ 990Testimonies For The Church 1:396, 397.CGAmh 469.3

    ከጨቅላነት እስከ ወጣትነት ድረስ ምሯቸው— ልጅ የተፈጥሮ ስሜቶቹን እንዲከተል መፍቀድ፣ እንዲበላሽ እና በክፋት ብቃት እንዲኖረው ማድረግ ማለት ነው፡፡ የተሳሰቱ ስልጠና ውጤቶች በልጅነቱ መገለጥ ይጀምራሉ፡፡ ገና በልጅነት ዕድሜ የራስ ወዳድነት ስሜት ያድጋል፣ ደግሞም ወጣቱ ወደ አከለ መጠን ባደገ ቁጥር በኃጢአት እያደገ ይሄዳል፡፡ የራሳቸውን ምርጫ እንዲከተሉ የተፈቀደላቸው ልጆች ላይ የወላጅ ችላ ባይነት ዘላቂ ምስክርነት ይደመጣል፡፡ እንዲህ አይነቱ ቁልቁል ጉዞ የሚወገደው ክፋትን በሚጻረር ተጽዕኖ ዙሪያቸውን በመከለል ብቻ ነው፡፡ ልጆች ከጨቅላነት እስከ ወጣትነት እና ከወጣትነት እስከ ለአከለ መጠን እስኪደርሱ ድረስ ወደ መልካም በሚያመራቸው ተጽእኖ ሥር መሆን አለባቸው፡፡ 991Testimonies For The Church. , September 15, 1904..CGAmh 470.1

    ከመጪዎቹ ፈተናዎች ልጆችን መከለል— ወላጆች ሆይ ራሳችሁን የከበረ ጥያቄ ጠይቁ፣ “ልጆች ለወላጅ ሥልጣን እንዲገዙ እና በዚህም ሳቢያ እግዚአብሔርን እንዲታዘዙ፣ እርሱን እንዲወዱ፣ ሕጉ የጸባይ እና የሕይወት ታላቅ መሪ እንደሆነ እንዲይዙ አስተምረናቸዋል ወይ? የክርስቶስ ሚሲዮናውያን እንዲሆኑ አስተምረናቸዋል ወይ? መልካም እያደረጉ ስለ መሄድስ?” አማኝ ወላጆች ሆይ፣ ልጆቻችሁ በተጋድሎ ቀን ወሳኝ ተጋድሎ ማድረግ አለባቸው፤ ለሰላም ንጉስ ድሎችን ሲቀዳጁ፣ ለራሳቸውም ድል እየተቀዳጁ ነው፡፡ ነገር ግን በፈርሃ እግዚአብሔር ያላደጉ እንደሆነ፤ የክርስቶስ እውቀት ከሌላቸው፣ ከሰማይ ጋር ግንኙነት ከሌላቸው፣ የግብረ ገብ ኃይል አይኖራቸውም፤ ደግሞም ሐሰተኛውን ሰንበት የያህዌ ሰንበት ሥፍራ እንዲይዝ በማቋቋም ከሰማይ አምላክ በላይ ራሳቸውን ከፍ ለሚያደርጉ ኃያላን ሰዎች ይገዛሉ፡፡ 992Testimonies For The Church , April 23, 1889.CGAmh 470.2