Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 2—የመጀመሪያ መምህር

    ወላጆች ኃላፊነታቸውን መረዳት አለባቸው— አባትና እናት የልጆቻቸው የመጀመሪያ መምህራን መሆን አለባቸው፡፡ 10Manuscript Releases 6:7, 1903 CGAmh 21.1

    አባቶችና እናቶች ኃላፊነታቸውን መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ ዓለም ለወጣቶች እግር በወጥመድ የተሞላች ናት፡፡ ብዙዎች በራስ ወዳድነትና በፍትወታዊ ደስታ ተመርከዋል፡፡ የደስታ ጎዳና የሚመስላቸው መንገድ ላይ ያለውን ስውር አደጋ ወይም አስፈሪ ፍጻሜ መለየት አይችሉም፡፡ ልቅ የምግብ ፍላጎታቸውን በማርካትና በስሜት ጉልበታቸውን ሲያባክኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩት ለዚህና ለሚመጣውም ዓለም ጠፊዎች ሆኑ፡፡ ልጆቻቸው እነዚህን ፈተናዎች መጋፈጥ እንዳለባቸው ወላጆች ማስታወስ አለባቸው፡፡ ልጁ ከመወለዱም አስቀድሞ እንኳ ከክፋት ጋር ያለውን ጦርነት በስኬት መጋደል የሚያስችለው ቅድመ ዝግጅት መጀመር አለበት፡፡ 11The Ministry of Healing, 371CGAmh 21.2

    ወላጆች ልጆቻቸው ጠቃሚና በዚህ ዓለም ሕይወታቸው ደስተኞች እንዲሆኑና ከዚህም በኋላ ታላቅ አገልግሎትና ደስታ ይኖራቸው ዘንድ እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማስተማር እንዳለባቸው ይረዱ ዘንድ በእያንዳንዱ ደረጃ ከሰብአውያን የላቀ ጥበብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ 12The Review and Herald, September 13, 1881.CGAmh 21.3

    አስፈላጊ የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል የሆነው የልጆች ሥልጠና — የክርስትናን ኃይል ለማሳየት የልጆች ሥልጠና አስፈላጊ የእግዚአብሔር ዕቅድ አካል ነው፡፡ ልጆቻቸው ወደ ዓለም ሲወጡ ከሚጎደኟቸው ሁሉ ጋር መልካምን እንጅ ክፉን እንዳያደርጉ ዘንድ ወላጆች ልጆቻቸውን የማሠልጠን የተከበረ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል፡፡13The Signs of the Times, September 25, 1901.CGAmh 21.4

    ወላጆች ልጆቻቸውን የማሠልጠን ሥራን አቅልለው መመልከትም ሆነ በማንኛውም አይነት ሁኔታ ችላ ማለት የለባቸውም፡፡ አካላችንን የሚቆጣጠረውን ህግ በጥንቃቄ በማጥናት ብዙ ጊዜ ማሳለፍ አለባቸው፡፡ ጥሩ አካል ውስጥ ጥሩ አዕምሮን ለመፍጠር ልጆቻቸውን እንዴት በአግባቡ መቅረብ እንዳለባቸው ማወቅን ቀዳሚ ዓላማ ማድረግ አለባቸው፡፡CGAmh 21.5

    ብዙዎች የክርስቶስ ተከታዮች ነን ባዮች አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ የቤት ተግባራቸውን ችላ ባዮች ናቸው፤ እግዚአብሔር በእጃቸው ላይ ያስቀመጠውን ልጆቻቸው የወጣቶችን እግር የሚያጠምዱ አያሌ ፈተናዎችን መቋቋም እንዲችሉ የግብረ-ገብ ጥንካሬ ይኖራቸው ዘንድ ባህሪይን የመቅረጽ የቅዱሱን አደራ አስፈላጊነትን አይረዱትም፡፡13Pacific Health Journal, April, 1890.CGAmh 22.1

    ከእግዚአብሔር ጋር መተባበር ያስፈልጋል— ክርስቶስ አባቱን የለመነው ደቀ መዛሙርቱን ከዓለም እንዲያወጣቸው ሳይሆን ከዓለም ክፋት እና በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ ሊገጥሟቸው ለሚችሉ ፈተናዎች እጃቸውን እንዳይሰጡ እንዲጠብቃቸው ነው፡፡ ይህንን ፀሎት አባቶችና እናቶች ስለ ልጆቻቸው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔርን እየለመኑ ልጆቻቸው እንዳሰኛቸው ይሆኑ ዘንድ መተው ይችላሉን? ወላጆች ከእርሱ ጋር በመተባበር የማይሰሩ ከሆነ እግዚአብሔር ልጆቻቸውን ከክፉ አያድንም፡፡ ወላጆች በድፍረትና በደስታ ሥራቸውን በማንሳት በማይዝል ጥረት ወደ ፊት ማስኬድ ይገባቸዋል፡፡ 14The Review and Herald, July 9, 1901. CGAmh 22.2

    ቅን በሆነ ፀሎትና ተግባር ከእግዚአብሔር ጋር በመተባበር ወላጆች ልጆቻቸውን ለእርሱ የማስተማርና የማሰልጠንን ሸክም ፍፁም ያልተው እንደሆነ፣ ሥራቸውን በተማኝነት የሚሠሩ ከሆነ፣ ልጆቻቸውን ወደ አዳኙ በማምጣት ረገድ የተሳካለቸው ይሆናሉ፡፡7The Signs of the Times, April 9, 1896. CGAmh 22.3

    ጥንዶቹ ኃላፊነታቸውን እንዴት እንደተወጡ— የክርስቶስ የመጀመሪያ ምጻትን ያውጅ ዘንድ መልዕክተኛን በማዘጋጀት ረገድ ከእግዚአብሔር ጋር ስምሙ ሆኖ ይሰራ ዘንድ፣ ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ልጃቸውን እንዴት ማሰልጠንና ማስተማር እንዳለባቸው መመሪያ ለመስጠት አንድ መልዓክ ከሰማይ መጣ፡፡ እንደ ብቁ ሠራተኛ እግዚአብሔር ዮሐንስ ያከናውነው ዘንድ የሰየመውን ሥራ እንዲሰራ የሚያስችለውን በርሱ ውስጥ የነበረውን አይነት ባህርይ ለመቅረጽ እነርሱ እንደ አንድ ወላጅ ከእግዚአብሔር ጋር በተማኝነት መተባበር ነበረባቸው፡፡ CGAmh 22.4

    ዮሐንስ የእርጅና ልጃቸው ነበር፣ የተዓምር ልጅም ነበር፣ ስለዚህ ወላጆቹ እርሱ ለጌታ የተለየ ተግባር ስላለው ጌታ ራሱ ለእርሱ የሚያስፈልገውን ሁሉ ያድርግ የሚል ሰበብ ማቅረብ ይችሉ ነበር፡፡ ነገር ግን ወላጆቹ እንዲህ አይነቱን ምክንያት አላቀረቡም፤ ልጃቸው ለከተማ ሕይወት ፈተናዎች ወይም ወላጆቹ ከሚሰጡት ምክርና መመሪያ ፈቀቅ እንዲል ሊያግባቡት ለሚችሉ ነገሮች እንዳይጋለጥ ገለልተኛ ወደ ሆነው ገጠራማ ሥፍራቸው ተንቀሳቀሱ፡፡ በማናቸውም አይነት ሁኔታዎች እግዚአብሔር ለእርሱ ላቀደው ዓለማ ብቁ ይሆን ዘንድ የልጃቸውን ባህርይ በመቅረጽ ረገድ ሚናቸውን ተጨውተዋል፡፡ ….ግዴታቸውን በቅድስና ፈጽመዋል፡፡ 15The Signs of the Times, April 16, 1896CGAmh 23.1

    ልጆችን እንደ አደራ መቁጠር— ወላጆች ልጆቻቸውን ለላይኛው ቤተሰብ ይበቁ ዘንድ እንዲያስተምሩ ከእግዚአብሔር አደራ እንደተጣቸው መቁጠር አለባቸው፡፡ በእግዚአብሔር ፍርሃትና ፍቅር አሰልጥኗቸው፤ “እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው” ነውና፡፡16Ibid.CGAmh 23.2

    ለእግዚአብሔር ታማኝ የሆኑ ሰዎች በቤታቸው ሕይወት ውስጥ የርሱ ወኪል ይሆናሉ፡፡ ልጆችን የማሰልጠን ሥራን ከሁሉ የበላይ የሆነው አምላክ እንደሰጣቸው ቅዱስ አደራ ይቆጥራሉ፡፡17Manuscript Releases 10:3, 1902.CGAmh 23.3

    ወላጆች የክርስቲያን መምህር ለመሆን ብቁ መሆን አለባቸው — ብዙ ነገር የሚጠበቅበት የወላጆች ሥራ በእጅጉ ችላ ተደርጓል፡፡ ወላጆች ሆይ ከመንፈሳዊ እንቅልፋችሁ በመንቃት ልጅ መቀበል ያለበት የመጀመሪያው ትምህርት በእናንት ሊሰጠው እንደሚገባ ተረዱ፡፡ ልጆቻቸው ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ማስተማር ይጠበቅባችኋል፡፡ ሰይጣን የራሱን ዘር በልባቸው ከመዝራቱ በፊት ይህን ሥራ መስራት አለባችሁ፡፡ ክርስቶስ ልጆችን ይጠራቸዋል፣ እነርሱም አምራች መሆንን፣ ንጹህና እና የስነ-ሥርዓትንትን ልምድ በመማር ወደ እርሱ ሊመሩ ይገባል፡፡ ክርስቶስ እነርሱ እንዲቀበሉ የሚፈልገው ስነ-ስርዓት ይህ ነው፡፡ 18.CGAmh 23.4

    ወላጆች ጠቢባንና ጠንቃቆች መምህራን ለመሆን ራሳቸውን ብቁ ካላደረጉ በስተቀር ኃጢአት በደጃቸው ትሆነለች፡፡ 19.CGAmh 24.1

    በቤተሰብ መካከል አንድነት አስፈላጊ ነው—ባልና ሚስት ቤት ውስጥ ባለው የተግባር ትምህርት ቤት በጥብቅ የተባበሩ መሆን አለባቸው፡፡ ሰይጣን የፈተና በር አግኝቶ በመግባት ድልን በድል ላይ እንዳይቀዳጅ እነርሱ በንግግራቸው እጅግ ሩህሩህና ጠንቃቆች መሆን ይገባቸዋል፡፡ አንዱ ለሌላው አክብሮትን በማሳየት እርስ በርስ ሩህሩህና ትሁት መሆን አለበት፡፡ ቤት ውስጥ ደስታንና ጤናማ ሁኔታን ለመፍጠር ሲሉ እርስ በርስ መረዳዳት አለባቸው፡፡ በልጆቻቸው ፊት ልዩነታቸውን ማንጸባረቅ የለባቸውም፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የክርስትና አክብሮት ጠብቆ ማቆየት አለበት፡፡ 20.CGAmh 24.2

    ለልጆች ሁሉ የተሰጠ ልዩ አስተማሪ — በዚህ ልጆችን በማሠልጠን ሥራ ውስጥ እናት ሁልጊዜ ልቃ መገኘት አለባት፡፡ እጅግ ታላቅና ወሳኝ ኃላፊነቶች አባት ላይ የተጣሉ ቢሆንም እንኳ፣ እናት ሁልጊዜ፣ በተለይም በልጆቿ የጨቅላነት ዕድሜ ላይ ሁሌም ከእነርሱ ጋር በመሆን ልዩ አስተማሪና ጓደኛ መሆን አለባት፡፡ 21.CGAmh 24.3

    ትምህርት መምሪያ ከመስጠትም የሰፋ ነው — ወላጆች በቃሉ ውስጥ ለእነርሱ የሚናገረውን የእግዚአብሔርን ድምጽ ሙሉ በሙሉ መታዘዝን መማር ይኖርባቸዋል፡፡ ይህንንም ትምህርት ከተማሩ፣ አክብሮት እና መታዘዝ በቃልም ሆነ በድርጊት ምን እንደሆነ ልጆቻቸውን ማስተማር ይችላሉ’ ይህ በቤት ውስጥ መሰራት ያለበት ሥራ ነው’ እንዲህ የሚያደርጉ ሰዎች ልጆቻቸውን ከፍታ ላይ ማድረስ እንደሚገባቸው በመገንዘብ ራሳቸውን እዚያ ከፍታ ላይ ያደርሳሉ’ ይህ ትምህርት መምሪያ ብቻ ከመስጠትም በላይ ነው' 15 The Signs of the Times, April 16, 1896.CGAmh 24.4

    ያለ ዕቅድ የሚሰራ ስራ ተቀባይነት የለውም —በቤት ውስጥ ያለ ዕቅድ የሚሰራ ስራ ግምገማዊ ፍርድን መለፍ አይችልም’ በክርስቲያን ወላጆች እምነትና ሥራ መጣመር አለባቸው፡፡ አብርሃም እርሱን ይከተል ዘንድ ቤተሰቡን እንደመራ ሁሉ እነርሱም ቤተሰቦቻቸው ይከተሏቸው ዘንድ መምራት አለባቸው፡፡ ሁሉም ወላጅ ሊያነሳ የሚገባው ዓርማ “የጌታን መንገድ ይጠብቃሉ” የሚል መሆን አለበት፡፡ ሌላም መንገድ ወደ እግዚአብሔር ከተማ ሳይሆን ወደ አጥፊው ጎራ የሚያመራ ነው፡፡ 22 The Review and Herald, March 30, 1897. 17Good Health, January, 1880.CGAmh 25.1

    ወላጆች ሥራዎቻቸውን ይመርምሩ — ወላጆች ልጆችን የማስተማርና የማሰልጠን ሥራቸው፣ እነዚህም ልጆች በጌታ በየሱስ ቀን የደስታ አክሊል ይሆኑ ዘንድ በተስፋና በእምነት ኃላፊነታቸውን መወጣታቸውን ይመረምራሉን? ኢየሱስ ከሰማይ ወደ ታች በመመልከት በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ጥረታቸውን እንዲቀድስ ስለ ልጆቻቸው ደህንነት ሰርተዋል ወይ? ወላጆች ሆይ በዚህ የምድር ህይወት ውስጥ ልጆቻችሁ እጅግ የላቀ ጠቀሜታ ይኖራቸው ዘንድ ለማዘጋጀት እና ወደፊት የሚመጣውን ክብር እንዲካፈሉ ማድረግ የእናንተ ኃላፊነት ነው፡፡ 17Manuscript Releases 10:3, 1902 CGAmh 25.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents