Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ 56—የአካደሚ እና የኮሌጅ ስልጠና

    ብዙዎች በአለማዊ ተቋማት ውስጥ መንገድ በመሳት ላይ ይገኛሉ — የወጣቶች አእምሮ እንዲሰለጥን እና እንዲገራ በተላኩባቸው በርካታ ትምህርት ቤቶችና ኮሌጆች ውስጥ ባህሪይን የሚያዛቡ፣ አእምሮን ከህይወት እውነተኛ ዓላማዎች የሚያዛንፉ እና ግብረ ገብን የሚያዋርዱ ተጽዕኖዎች መስፋፋታቸው አስፈሪ ሐቅ እና የወላጆችን ልብ ሊያብረከርክ የሚገባ ነገር ነው፡፡ ኃይማኖተኞች ካልሆኑ፣ ተድላን ከሚወዱ እና ብልሹ ከሆኑት ጋር በመገናኘት አያሌ ወጣቶች ክርስቲያን አባቶች እና እናቶች በጠንቃቃ መመሪያ እና ልባዊ ጸሎት የተንከባከቧቸውን እና ጠብቀው ያቆዩአቸውን ቀለል ያለ የአኗኗር ሁኔታ እና ንጽህናን፣ በእግዚአብሔር ላይ እምነት መጣልን እና ራስን የመሠዋት መንፈስን ያጣሉ፡፡ CGAmh 311.1

    ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት ራሳቸውን ለማብቃት ሲሉ ወደ ትምህርት ቤት የሚገቡ አያሌ ሰዎች በዓለማዊ ጥናቶች ይጠመዳሉ። ነጻ የትምህርት ዕድልን በከፍተኛ ልዩነት ለማሸነፍ እና በአለም ውስጥ ሥፍራ እና ክብርን ለማግኘት ምኞት ይነሳሳል። ወደ ትምህርት ቤት የገቡበት አላማ ይዘነጋ እና ህይወት ለራስ ወዳድነት እና ዓለማዊ ጉዳዮች ይሰጣል። እናም ብዙውን ጊዜ ለጊዜያዊውም ሆነ ለመጪው ዓለም ህይወትን አደጋ ላይ የሚጥሉ ልማዶች ይመሰረታሉ፡፡ 636The Ministry of Healing, 403.CGAmh 311.2

    ኃይማኖታዊ የቤት ውስጥ ተፅእኖዎች ይጠፋሉ— “ወደ ፈተና አታግባን” ብላችሁ ጸልዩ፡፡ ከዚያም ልጆቻችሁ አላስፈላጊ ፈተናዎች ጋር በሚጋጠሙበት ቦታ እንዲቀመጡ አትስማሙ፡፡ በልባቸው መስክ እንደተዘራ እንክርዳድ ከሚሆኑ ተጽዕኖዎች ጋር ወደሚያገናኟቸው ትምህርት ቤቶች አትላኳቸው።CGAmh 311.3

    ልጆቻችሁን በለጋ ዕድሜያቸው በቤት ትምህርት ቤት ውስጥ፣ እግዚአብሔርን መፍራትን አሠልጥኗቸው፣ አስተምሯቸውም፡፡ ስለዚህም የተቀበሉት ኃይማኖታዊ አሻራዎች የሚጠፉበት እና የእግዚአብሔር ፍቅር ከልባቸው ውስጥ የሚወሰድበት ሥፍራ እንዳታደርጓቸው ተጠንቀቁ፡፡ ከፍተኛ ደመወዝ ወይም ግልጽ በሆነ ሁኔታ ከፍተኛ የትምህርት ጥቅሞችን ማግኘት ልጆቻችሁ ከተጽዕኖዎቻችሁ ተለይተው ለታላላቅ ፈተናዎች ወደሚጋለጡባቸው ስፍራዎች እንዲላኩ እንዳያመራችሁ፡፡ “ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያድል ምን ይጠቅመዋል? ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?” ማርቆስ 8፡36፣ 37፡፡ 637Manuscript Releases 3:0.1904CGAmh 311.4

    ኮሌጆቻችን በእግዚአብሔር የተሰየሙ ናቸው— ለወጣቶች ትምህርት ተቋም መቋቋም እንዳለበት መልዓክ ባሳየኝ ጊዜ ፣ ይህ ለነፍሳት ድነት እግዚአብሔር ከሰየማቸው መንገዶች ትልቁ እንደሆነ ተመልክቻለሁ…፡፡ በኮሌጃችን ውስጥ ያለው ተጽዕኖ ይሆን ዘንድ እንደሚጠበቀው ከሆነ እዚያ የተማሩ ወጣቶች እግዚአብሔርን ለማወቅ እና በሥራው ሁሉ ለእርሱ ክብር እንዲሰጡ ያስችላቸዋል፤ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ችሎታዎችን በማዳበር ተግባር ላይ በሚሆኑበት ጊዜ ይበልጥ ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት ይዘጋጃሉ፡፡ 638Testimonies For The Church 4:419-422.CGAmh 312.1

    ወጣቶች ይበልጥ እንደ ነቢያት ትምህርት ቤቶች መሆን ባለባቸው ትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አበረታቷቸው። ትምህርት ቤቶቻችን በጌታ የተቋቋሙ ናቸው፡፡639Fundamentals of Christian Education, 489. CGAmh 312.2

    በቤት ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ የልምድ ጥቅሞች— በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ትምህርት ለመቀበል የሚፈለጉ ልጆች የተሳሳተ ትምህርት ከሚያገኙበት የቤተሰብ ክበብ ቢለዩ እጅግ በጣም ዘላቂ እድገት ያሳያሉ። አንዳንድ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን የሚያሳፍሩበትን እና ወጪያቸውን የሚቆጥቡበትን ቦታ መፈለግ አስፈላጊ ይሆናል፣ ነገር ግን በብዙ ሁኔታዎች ለልጆቻቸው በረከት ከመሆን ይልቅ መሰናክልን ይሆናል፡፡ 640Fundamentals of Christian Education, 313.CGAmh 312.3

    የቤት ትምህርት ቤት ለአስቸጋሪ ሴት ልጅ— ጥረቱ እንደ ብረት ማሰሪያ እስኪይዛት ድረስ ጠላት ከሴት ልጃችሁ ጋር ተራምዷል፣ ነፍሷንም ለማትረፍ ጠንካራ፣ የማያቋርጥ ጥረት ይጠይቃል። በዚህ ጉዳይ ላይ ስኬት ካገኛችሁ የግማሽ መንገድ ሥራ ሊኖር አይገባም፡፡ የዓመታት ልምዶች በቀላሉ ሊፈርሱ አይችሉም፡፡ እርሷ ጽኑ፣ ጠንካራ ተጽዕኖ በዘለቄታ ተግባራዊ የሚደረግበት ቦታ መሆን አለባት። እርሷን -—ኮሌጅ ውስጥ እንድታኖሯት እመክራለሁ; እርሷ የአዳሪ ቤት ሥነ-ምግባር ይኑራት፡፡ ይህ እርሷ ከዓመታት በፊት መሆን የነበረባት ሥፍራ ነው፡፡ 641Testimonies For The Church 5:506.CGAmh 312.4

    አዳሪ ቤቱ ጥሩ ቤት እንዲሆን በሚያደርገው እቅድ የሚመራ ነው፡፡ ይህ ቤት የአንዳንዶችን ዝንባሌ ላያሟላ ይችላል፣ ነገር ግን እነርሱ ሀሰተኛ ፅንሰ-ሀሳቦችን፣ ራስን ማስደሰት እና ራስን ማርካትን የተማሩ በመሆናቸው ነው፤ ልምዶቻቸው እና ባህሎቻቸው በተሳሳተ ሰርጥ ውስጥ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ውዷ እህቴ ወደ ዘመኑ መጨረሻ እየተቃረብን ነው፤ እናም አሁን የምንፈልገው ከዓለም ምርጫ እና ልምዶች ጋር መስማማት ሳይሆን ከእግዚአብሔር አዕምሮ ጋር መስማማት፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ምን እንደሚሉ ማየት እና ከዚያም እግዚአብሔር እንደ ሰጠን ብርሃን መመላለስ ነው፡፡ ዝንባሌዎቻችን፣ ልምዶቻችን እና ባህሎቻችን ተመራጭ መሆን የለባቸውም፡፡ የእግዚአብሔር ቃል መለኪያችን ነው። CGAmh 313.1

    ነዋሪ ተማሪዎች— አንዳንድ መምህራን በትምህርት ቤት አቅራቢያ ከሚኖሩ ወላጆች ልጆች እና ወጣቶች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከአስተማሪዎቻቸው ጋር አብረው ካልኖሩ በስተቀር የትምህርት ቤት መብቶችን ማግኘት አይገባቸውም ብለው ያስባሉ፡፡ ይህ ለእኔ አዲስ እና እንግዳ ሀሳብ ነው፡፡CGAmh 313.2

    በመልካም ቁጥጥር ስር ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ ለመኖር የቤት ውስጥ ተጽዕኖዎች በጣም የሚጠቅማቸው ወጣቶች አሉ። የትምህርት ቤት መብቶችን ተካፋይ ለመሆን የግድ ቤታቸውን ለቀው ለሚኖሩ ሁሉ፣ ትምህርት ቤቶች ትልቅ በረከት ናቸው። ነገር ግን እግዚአብሔር የሚፈራበት እና የሚታዘዝበት፣ ዘወትርም እንዲሁ በመሆን የሚቆይ የወላጅ ቤት ለትንንሽ ልጆች ተመራጭ ቦታ ነው፣ እናም በወላጆቻቸው ተገቢ ሥልጠና ሥር በመሆን በገዛ ወላጆቻቸው በሚተዳደር የሃይማኖት ቤተሰብ እንክብካቤ እና ሥልጠናን ሊያጥሙ ይችላሉ።… CGAmh 313.3

    አዳሪ ትምህርት ቤት መከታተል በሚያስችላቸው ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶችን በተመለከተ በትምህርት ቤቶቻችን አካባቢ ከሚኖሩ ከወላጆቻቸው የሚለይ አላስፈላጊ እና አምባገነናዊ ሕጎችን ከመደንገግ እንቆጠብ፡፡ …CGAmh 314.1

    ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ቤቱ ሥነ-ሥርዓት ሥር መሆናቸው ለልጆቻቸው ጥቅም እንደሆነ ካልተገነዘቡ በስተቀር በተቻለ መጠን እነርሱንበእራሳቸው ቁጥጥር ሥር እንዲያደርጓቸው ሊፈቀድላቸው ይገባል። በአንዳንድ ቦታዎች በትምህርት ቤቱ አቅራቢያ የሚኖሩ ወላጆች ልጆቻቸው በገዛ ቤቶቻቸው በደንብ ማግኘት የማይችሉትን የተወሰኑ መመሪያዎችን ማግኘት በሚችሉበት ትምህርት ቤት ውስጥ በመኖራቸው ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የማናቸውንም የትምህርት ቤቶቻችንን ጥቅሞች ለማግኘት ልጆች በማንኛውም ሁኔታ ከወላጆቻቸው እንዲለዩ መገፋፋት ተገቢ አይደለም፡፡…CGAmh 314.2

    ወላጆች የልጆቻቸው ተፈጥሯዊ አሳዳጊዎች ናቸው፣ እናም ትምህርታቸውን እና ሥልጠናቸውን የመቆጣጠር የከበረ ኃላፊነት አለባቸው።CGAmh 314.3

    የልጆቻቸውን እድገት ለዓመታት ሲመለከቱ የነበሩ ወላጆች በውስጣቸው ምርጥ ባህሪያትን ለማምጣት እና ለማዳበር ምን ዓይነት ሥልጠና እና አመራር ሊኖራቸው እንደሚገባ በሚገባ ማወቅ እንዳለባቸው ልንገነዘብ አንችልምን? ከትምህርት ቤት በሁለት ወይም በሦስት ማይል ርቀት ውስጥ በሚገኙ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ልጆች በወላጅ ተጽዕኖ ጥቅሞች ሥር በመሆን ትምህርት ቤቱን እንዲከታተሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል፡፡ በሚቻልበት ቦታ ሁሉ ቤተሰቡ አብረው እንዲኖር ይደረግ፡፡ 642Letter 60, 1910.CGAmh 314.4

    ሁሉም ልጆች የትምህርት ዕድል ሊኖራቸው ይገባል— ቤተክርስቲያን ስላንቀላፋች ህፃናትን እና ወጣቶችን የማስተማር ጉዳይ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ አልተገነዘበችም። አንደኛው “ወጣቶቻችንን በጥልቀት ለማስተማር ልዩ ትኩረት መስጠት ለምን ያስፈልጋል? ለእኔ ይመስለኛል የስነ-ጽሁፍ ጥሪን ወይም አንድ የተወሰነ የትምህርት ዘርፍን የሚጠይቅ ሌላ ጥሪ ለመከተል የወሰኑ ጥቂቶች ከተወሰዱ እና ለእነርሱ ተገቢው ትኩረት ከሰጠ የሚፈለገው ይህ ብቻ ነው፡፡ መላው የወጣቶቻችን ብዛት ይህን ያህል በደንብ እንዲሰለጥን አይጠየቅም። ይህ ለሁሉም አስፈላጊ መጠይቆች መልስ አይሰጥምን? ይላል፡፡ እኔ እመልሳለሁ፣ አይሆንም፣ በጭራሽ አይሆንም፡፡.... ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሠራተኞች ለመሆን መነሳሳት እንዲችሉ ወጣቶቻችን ሁሉም በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ የትምህርት ዕድሎች እና መብቶች እንዲኖራቸው ሊፈቀድላቸው ይገባል፡፡ በግል እና በማህበረሰብ ሕይወት ውስጥ ለኃላፊነት ቦታዎች ብቁ እንዲሆኑ፣ ፋይዳ ለመስጠት ብቁዎች እንዲሆኑ ሁሉም ትምህርት ያስፈልጋቸዋል፡፡ 643The Review and Herald, February 13, 1913.CGAmh 314.5

    ሚዛናዊ የሆነ የትምህርት ቤት መርሃ ግብር— የአእምሮ ችሎታዎች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲውሉ ማደግ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እያንዳንዳቸው በልዩ የተግባር መስኮቻቸው ላይ ወደ ትግበራ እንዲገቡ በማድረግ የተለያዩ የአእምሮ አካላት እኩል ጥንካሬ ሊኖራቸው እንዲችል ለአእምሮ አሰራር ጥንቃቄ መሰጠት አለበት፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው ግዴታቸውን ችላ ብለው የራሳቸውን የአዕምሮ ጥመት፣ የራሳቸውን ዝንባሌ እና ተድላን፣ እንዲከተሉ ከፈቀዱላቸው፣ ባህሪያቸው ከዚህ ንድፍ አንጻር ይመሰረታል፣ እናም በህይወት ውስጥ ምንም ዓይነት ኃላፊነት ላለው ቦታ ብቁ አይሆኑም። የወጣቶቹ ፍላጎቶች እና ዝንባሌዎች መገደብ፣ ደካማ የባህርይ ነጥቦቻቸው መጠናከር እና ከመጠን በላይ የጠነከሩ ዝንባሌዎቻቸው መዳከም አለባቸው፡፡ CGAmh 315.1

    አንዱ የአካል ክፍል ዋልጌ ሆኖ እንዲቆይ ከተተወ ወይም ከትክክለኛው ተግባሩ ከተዛነፈ የእግዚአብሔር ዓላማ ተፈጻሚነትን አያገኝም፡፡ ሁሉም የአካል ክፍሎች በደንብ መጎልበት አለባቸው፡፡ ለእያንዳንዳቸው ጥንቃቄ መደረግ አለበት፣ ምክንያቱም እያንዳንዱ ለሌላኛው የራሱ አስተዋጽኦ አለው፣ እናም አዕምሮው በትክክል ሚዛናዊ እንዲሆን ሁሉም እንቅስቃሴ ላይ መሆን አለበት፡፡ የሌሎች የአእምሮ ሀይልን ችላ በማለት የአእምሮ ጥንካሬን በአንድ አቅጣጫ ማድረግ የልጆቻችሁ ምርጫ በመሆኑ አንድ ወይም ሁለት የአካል ክፍሎች ተግባር ላይ ቢሆኑ እና በቀጣይነት አገልግሎት የሚሰጡ ከሆነ ሚዛናዊ ያልሆነ አዕምሮ እና የማይጣጣም ባህሪያትን ይዘው ወደ መጎልመስ ይመጣሉ፡፡ እነርሱ በአንድ አቅጣጫ ንቁ እና ጠንካራ ይሆናሉ፣ ነገር ግን እንደዚሁ አስፈላጊ በሆኑ በሌሎች አቅጣጫዎች በእጅጉ ብቃት የጎደላቸው ይሆናሉ፡፡ ብቁ ወንዶች እና ሴቶች መሆን አይችሉም፡፡ ጉድለቶቻቸው የጎላ እና መላውን ባሕርይ የሚያበላሽ ይሆናል፡፡ 644Testimonies For The Church 3:26.CGAmh 315.2

    ዓመቱን ሙሉ የማያቋርጥ የጥናት ክፋቶች— ብዙ ወላጆች ዓመቱን ሙሉ ልጆቻቸውን በትምህርት ቤት ያቆያሉ። እነዚህ ልጆች የጥናቱን መደበኛ ሂደት ሳያስቡበት እንደ ማሽን ያደርጋሉ፣ ነገር ግን የተማሩትን በአዕምሮአቸው መያዝ አይችሉም፡፡ ከእነዚህ መደበኛ ተማሪዎች ብዙዎቹ በእውቀት ሕይወታቸው የደሀዩ ይመስላሉ፡፡ አሰልቺ ጥናት አእምሮን እንዲዝል ያደርጋል፣ ለትምህርታቸውም ብዙም ፍላጎት እንዳይኖራቸው ያደርጋል፤ ብዙውን ጊዜም ከመጽሐፍት ጋር ማሳለፍ አስቸጋሪ ነው፡፡ ውስጣዊ የማሰላሰል ፍቅር እና እውቀትን የማግኘት ፍላጎት የላቸውም፡፡ በጥልቀት የማሰብ እና የመመርመር ልምዶችን በውስጣቸው አያበረታቱም፡፡… CGAmh 316.1

    ሐሰተኛ ተጽዕኖዎች የአእምሮ እድገትን ከመግታቱ የተነሳ አርቆ አሳቢዎች እና የአመክንዮ አሳቢዎች ጥቂቶች ናቸው፡፡ የማያቋርጥ ጥናት አዕምሮን ያጠነክራል የሚለው የወላጆች እና የመምህራን አስተሳሰብ በብዙ ሁኔታዎች ተቃራኒ ውጤት በማምጣቱ የተሳሳተ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ 645Counsels to Parents, Teachers, and Students, 84, 85.CGAmh 316.2

    ትችት ብዙውን ጊዜ በእርግጥም የወላጆች ነው— አስተማሪው የወላጆችን ሥራ እንዲሠራ መጠበቅ የለበትም፡፡ ብዙ ወላጆች አስፈሪ ግዴታን ችላ የማለት ነገር አላቸው። እንደ ኤሊ ሁሉ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አይችሉም፤ ከዚያም በኋላ ወላጆች በቤት ውስጥ ሊሰጧቸው የሚገባውን ሥልጠና እንዲቀበሉ ሥነ ምግባር የጎደላቸው ልጆቻቸውን ወደ ኮሌጅ ይልካሉ፡፡ CGAmh 316.3

    መምህራኖቹ ጥቂቶች የሚያደንቋቸው ተግባር አላቸው፡፡ እነዚህን ጠማማ ወጣቶች በማስተካከል ረገድ ከተሳካላቸው የሚያገኙት ዕውቅና አነስተኛ ነው። ወጣቶቹ ክፋት የተጠናወታቸውን ህብረተሰብ ከመረጡ እና ከመጥፎ ወደከፋ የሚሸጋገሩ ከሆነ መምህራኑ ይተቻሉ፣ ትምህርት ቤቱም ይወገዛል፡፡ በብዙ ሁኔታዎች በእርግጥ ትችቱን መውሰድ ያለባቸው ወላጆቹ ናቸው፡፡ መንፈሳቸው መማር በሚችልበት ጊዜ እና አእምሮ እና ልብ በቀላሉ ተጽዕኖ ሥር መውደቅ በሚችልበት ጊዜ ልጆቻቸውን ለመቆጣጠር እና ለማሰልጠን የመጀመሪያ እና በጣም ምቹ እድል ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በወላጆች ሀኬተኝነት ልጆች በክፉ ጎዳና እስኪደነዱ ድረስ የራሳቸውን ፈቃድ እንዲከተሉ ይፈቀድላቸዋል፡፡ 646Counsels to Parents, Teachers, and Students, 91..CGAmh 317.1

    ወላጆች የመምህራንን ስልጣን መደገፍ አለባቸው— መምህራን ከሚቃወሟቸው ታላላቅ ችግሮች መካከል አንዱ የኮሌጁን ስነ-ስርዓት በማስተጠበቅ ረገድ በወላጆች በኩል ትብብር አለመኖሩን ነው፡፡ ወላጆች የአስተማሪውን ስልጣን ለመደገፍ ቃል ገብተው ቢቆሙ ብዙ አለመታዘዝ፣ ምግባረ ብልሹነት እና ብልግና መታገድ ይችል ነበር፡፡ ወላጆች ልጆቻቸው አግባብነት ያለውን ስልጣን እንዲያከብሩ እና እንዲታዘዙ ማድረግ አለባቸው፡፡ አግባብነት ያላቸው ልማዶች በጽናት እስኪመሰረቱ ድረስ ልጆቻቸውን ለማስተማር፣ ለመምራት እና ለመገደብ በማያቋርጥ እንክብካቤ እና ትጋት መሥራት አለባቸው፡፡ ወጣቱ በእንደዚህ ዓይነት ሥልጠና ለማህብረተሰቡ ተቋማት እና ለአጠቃላይ የግብረ ገብ የገደብ ግዴታዎች ተገዢዎች ይሆናሉ፡፡12Testimonies For The Church 5:89.CGAmh 317.2

    የኮሌጁ ሥነ ሥርዓት ምክንያታዊ ወይም ምክንያታዊ ያለመሆኑ ዳኝነት ለልጆች መተው የለበትም፡፡ ወላጆቹ ልጆቻቸውን ለመላክ በአስተማሪዎች እና ትምህርት ቤቱ በሚያራምደው የትምህርት ስርዓት ላይ በቂ እምነት ካላቸው ጥሩ ስሜት እና የሞራል ጥንካሬ በማሳየት ሥነ ሥርዓትን በማስከበር ረገድ አስተማሪውን ይደግፉ፡፡… CGAmh 317.3

    ጥበበኛ የሆኑ ወላጆች ማንኛውም ዓይነት ሕገ-ወጥነት የማይታገስባቸው፣ እና ልጆች እንዳሻቸው ከመሆን ይልቅ ታዛዥ እንዲሆኑ የሚሠለጥኑባቸው እና በእነርሱመልካም ተጽዕኖዎች ላይ የሚያሳድሩ ትምህርት ቤቶች በመኖራቸው እጅግ አመስጋኝነት ይሰማቸዋል።CGAmh 318.1

    በቤት ውስጥ የማይታረሙ በመሆናቸው ምግባረ ብልሹ ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት የመላክ ዓላማ ያላቸው አንዳንድ ወላጆች አሉ፡፡ እነዚህ ወላጆች መምህራንን ሥነ ሥርዓት በማስከበር ሥራቸው ይደግፋሉ ወይንስ እያንዳንዱን የሐሰት ዘገባ ለማመን ዝግጁ ይሆናሉ? 647Manuscript Releases 11:9, 1899.CGAmh 318.2

    በትምህርት ቤት ስነ-ስርዓት ማስከበርን መደገፍ አለባቸው— ልጆቻቸውን ወደ --- የላኩ አንዳንድ ወላጆች ለማንም ቢሆን ምክንያታዊ ላልሆነ ነገር እንዲታዘዙ ቢፈለግባቸው መታዘዝ እንደሌለባቸው ነግረዋቸዋል። ይህ ለልጆች ምን አይነት ትምህርት ይሰጣል! ልምድ ሳይኖራቸው ምክንያታዊ እና ምክንያታዊ ባልሆነ ነገር መካከል እንዴት ይፈርዳሉ?CGAmh 318.3

    እነርሱ በሌሊት ርቀው ለመሄድ ይፈልጉ ይሆናል፣ የት እንደሆነ ማንም አያውቅም፣ እና በመምህራን ወይም በአሳዳጊዎች ስለራሳቸው እንዲወስዱ ከተጠየቀ ይህ ምክንያታዊ ያልሆነ እና የመብት ጥሰት ነው ይሏቸዋል። በነፃነታቸው ጣልቃ እንዲገባ አይፈልጉም፡፡ ማንኛውንም ሥነ-ሥርዓት የማስከበር ሥራ አግባብነት እንደሌለው የነፃነት እገዳ ሲቆጥሩ ሳለ፣ እነዚህን ወጣቶች የትኛው ደንብ ወይም ስልጣን ሊገዛቸው ይችላል?CGAmh 318.4

    በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች እነዚህ ወጣቶች በትምህርት ቤት ሊኖራቸው የማይችለውን ያልተገራ እና ስነምግባርን የጎደለው ፍላጎት የመከተል ነፃነት ይኖራቸው ዘንድ በትምህርት ቤት ቆይታቸው አጭር ቆይታ ያልተጠናቀቀ ትምህርት ይዘው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ፡፡ ብልህ ያልሆነ አባት ወይም እናት ያስተማሯቸው እንዳሻቸው የመሆን ትምህርቶች ለምድራዊው እና ለዘላለሙ ሥራውን ሠርቷል፣ ለእነዚህም ነፍሳት መጥፋት ተጠያቂዎች እነርሱ ናቸው። 648Manuscript Releases 11:9, 1899.CGAmh 318.5

    ከኮሌጁ ሥርዓተ-ትምህርት ውጭ ያለ ትምህርት— ልጆችና ወጣቶች በትምህርቱ ረገድ የተጠናከረ ልምዶችን ማዳበር አለባቸው፡፡ የኮሌጁ ትምህርት ሊያገኙዋቸው የሚገቡትን ትምህርቶች በሙሉ አያካትትም፡፡ ከሚያዩት እና ከሚሰሟቸው ነገሮች ዘወትር ትምህርቶችን ሊቀስሙ ይችላሉ፡፡ እነርሱ ከመንስኤ እስከ ውጤት፣ ከአካባቢያቸው እና ከኑሮ ሁኔታዎች ላይ መማር ይችላሉ፡፡ ባህሪይ በመጎልበት እና የከበረ ወንድ እና ሴት ለመሆን መሠረት የሆኑትን መርሆዎች በውስጣቸው በማጠናከር ከፍ ከፍ የሚያደርጋቸው እና የሚያስከብራቸውን፣ በየቀኑ ሊያስወግዱ የሚገባቸውን እና ሊለማመዱት የሚገባቸውን አንድ ነገር ሊማሩ ይችላሉ፡፡CGAmh 318.6

    በግዴለሽነት ዓላማዎቻቸው ወደ ትምህርታቸው ከገቡ እና የድርሻቸውን ምንም ልዩ ጥረት ባለማድረግ በማሳለፍ ደስተኞች ከሆኑ፣ በዚህም ሳቢያ እግዚአብሔር እነርሱ እንዲያገኙ ወደ ሚፈልገው ደረጃ ላይ መድረስ አይችሉም፡፡ 649The Youth’s Instructor, April 21, 1886CGAmh 319.1