Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 26—ስድስት- ትህትና እና ቁጥብነት

    ትህትና ከቤት ይጀምራል [ማስታወሻ: የአድቬንቲስት ቤት፣ 421-429፣ “ትህትና እና ደግነት” የሚል ርዕስ ያለው ምዕራፍ ይመልከቱ— ወላጆች፣ ልጆቻችሁ በእውነተኛ ትህትና ቤት ውስጥ እንዴት መኖር እንዳባቸው አስተምሯቸው…፡፡ አንዳቸው ለሌላው ደግነትና ርኅራሄን እንዲያሳዩ ያስተምሯቸው። የራስ ወዳድነት ስሜት በልብ ውስጥ እንዲኖር ወይም በቤት ውስጥ ሥፍራ እንዲያገኝ አይፍቀዱ፡፡ 248Manuscript Releases 7:4, 1900.CGAmh 135.1

    በቃላት እና በምግባር በግዴለሽነት እና በብልግና ያደጉ ወጣቶች ቤታቸው ውስጥ የሰለጠኑትን ባህሪያቸውን ያሳያሉ፡፡ ወላጆች የመጋቢነት ሥራ አስፈላጊነታቸውን አልተገነዘቡም፣ የዘሩትንም አዝመራ አጭደዋል፡፡ 249Manuscript Releases 11:7, 1899.CGAmh 135.2

    የሰማይ መርሆዎች መስፈን አለባቸው—የሰማይ መርሆዎች ወደ ቤት አስተዳደር መግባት አለበት። እያንዳንዱ ልጅ ጨዋ፣ ርኅሩኅ፣ አፍቃሪ፣ አዛኝ፣ ትሑት፣ ሆደ ባሻ እንዲሆን መማር አለበት። 250Manuscript Releases 10:0.1902. CGAmh 135.3

    ሁሉም የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ፣ ቤት ውስጥ እውነተኛ ትህትና ይኖረል፡፡ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለሌላው ማንኛውም አባል አስደሳች ለማድረግ ይሻል። 251 Manuscript Releases 6:0.1903.CGAmh 135.4

    በመመሪያ እና ምሳሌ ያስተምሩ—ልጆች እና እንዲሁም አዛውንት ለፈተና የተጋለጡ ናቸው፣ እናም አዛውንት የቤተሰብ አባላት በትህትና፣ በደስታ፣ በፍቅር እና የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን በታማኝነት በመወጣት ውስጥ ያለውን ትምህርት በመመሪያ እና ምሳሌ ሊሰጧቸው ይገባል። 252Manuscript Releases 2:7, 1896.CGAmh 135.5

    ወደ ዕረፍታቸው የቀረቡ የዛሉ እግሮችን ማክበር—እግዚአብሔር በተለይ ለአዛውንቶች አክብሮት እንዲሰጥ አዝዟል፡፡ እርሱም እንዲህም ይላል፣ “የሸበተ ጠጉር የክብር ዘውድ ነው፣ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል።” ምሳሌ 16፡31፡፡ እርሱም ስለ ተዋጉበት ጦርነቶች እና ስለ ተቀዳጁት ድሎች፣ ስለ ተሸከሟቸው ሸክሞች እና ስለ ተቋቋሟቸው ፈተናዎች ይናገራል፡፡ ወደ እረፍታቸው እየቀረቡ ስላሉ የዛሉ እግሮች፣ በቅርቡም ክፍት ስለሚሆኑ ሥፍራዎቻቸው ይናገራል። ልጆች ይህን እንዲያስቡ እርዷቸው፣ እናም እነርሱም የአዛውንትን ጎዳና በርህራሄና በአክብሮት ምቹ ያደርጋሉ፣ “በሽበታሙ ፊት ተነሣ፣ ሽማግሌውንም አክብር” ዘሌዋውያን 19:32 የሚለውን ሲታዘዙ በወጣትነት ሕይወታቸው ጸጋና ውበትን የማጣሉ፡፡ 253Education, 244.CGAmh 135.6

    ቁጥብነትን እና ልከኝነትን ያስተምሩ—ኩራት፣ ለራስ ከፍተኛ ግምት መስጠት እና ደፋርነት የዚህ ዘመን ልጆች ምልክቶች ናቸው፣ የዘመኑም እርግማን ናቸው…፡፡ የልከኝነት እና የትህትና እጅግ ቅዱስ ትምህርቶች በቤት እና በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ለልጆች መስተማር አለባቸው።254Counsels on Sabbath School Work, 46. CGAmh 136.1

    እናነት አሁን እነዚህ ቃላት የምነግራችሁ የተሰጣችሁን መመሪያ ታከብራላችሁን? ወጣቱ ይጠንቀቅ፤ በንግግራቸው ልከኛ እና ጭምት ይሁኑ እንጂ አይን አውጣ አይሁኑ፡፡ ነፍስን የሚጠቅሙ ነገሮችን ለመስማት ፈጣኖች ይሁኑ፣ እና ኢየሱስን ለመወከል እና እውነትን ለመመስከር ካልሆነ በስተቀር ለመናገር የዘገዩ ይሁኑ፡፡ የአዕምሮን ትሕትና ራስን ዝቅ በማድረግ ልከኝነት ያሳዩ፡፡8The Youth’s Instructor, July 11, 1895.CGAmh 136.2

    የመልካም ግብረ-ገብ ጠባቂ—ውድ የሆነውንና ዋጋው ሊገመት ለማይችለው በመጠን መኖር ከፍ ያለ ዋጋ ይስጡ፡፡ ይህ መልካም ግብረ-ገብን ይጠብቃል…፡፡ እግዚአብሔርን መምሰል አለን የሚሉ እህቶች የአካሄድ ልከኝነት እና ማራኪ ቁጥብነት እንዲኖራቸው እንዳደፋፍራቸው የእግዚአብሔር መንፈስ ሲያስገድደኝ ይሰማኛል…፡፡ ወጣት እህቶች በጨዋነት መልካም ምግባር የሚፈጽሙት መቼ ነው? ብዬ ጠይቄአለሁ፡፡ ወላጆች ልጆቻቸውን በትክክል ለማስተማር ከፍተኛ ጥንቃቄ የማድረግን አስፈላጊነት እስከሚገነዘቡበት ጊዜ ድረስ ለመሻሻል የሚደረግ ቆራጥነት የተሞላበት ለውጥ እንደማይመጣ አውቃለሁ፡፡ በቁጥብነት እና በመጠን እንዲኖሩ አስተምሯቸው፡፡255Testimonies For The Church 2:458, 459.CGAmh 136.3

    እውነተኛ ፀጋዎች—የልጁ የእውነት ፀጋዎች በመጠን መኖርን እና መታዘዝን ይይዛል—ይህም መመሪያዎችን ለመስማት ትኩረት በሚሰጡ ጆሮዎች፣ በተግባር ጎዳና ለመጓዝ እና ለመስራት ፈቃደኛ በሚሆኑ እግሮች እና እጆች ነው። የልጁ እውነተኛ መልካምነት በዚህ ሕይወትም ቢሆን የራሱን ሽልማት ያስገኛል፡፡10The Review and Herald, May 10, 1898.CGAmh 137.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents