Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 48—የልጁ አጸፋዊ ምላሽ

    ወደ ትንኮሳ— ልጆች ወላጆቻቸውን በጌታ እንዲታዘዙ ተመክረዋል፣ ወላጆችም ደግሞ “ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጯቸው” የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል፡፡ 546Manuscript Releases 38:1895.CGAmh 263.1

    ብዙውን ጊዜ ተዓማኒነትን በማግኘት ከማሸነፍ ይልቅ የትንኮሳን ሥራ እንሰራለን፡፡ አንዲት እናት አንድ ልዩ ደስታን እየሰጠው ያለውን ነገር ከልጇ እጅ ስትነጥቅ አይቻለሁ፡፡ ልጁ ለዚህ ምክንያቱን ባለማወቁ የተነሳ በተፈጥሮ ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ ተሰምቶት ነበር። ይህንንም ተከትሎ በወላጅ እና በልጅ መካከል ጠብ ተከሰተ፣ እናም ከውጫዊ ገጽታ ጋር በተያያዘ ትዕይንቱ በኃይለኛ ቅጣት ተጠናቀቀ፤ ነገር ግን ያ ጦርነት በልጅነት አእምሮው ላይ በቀላሉ ሊጠፋ የማይችለውን ተጽዕኖ አሳደሯል፡፡ ይህች እናት ጥበብ በጎደለው አይነት ሁኔታ እርምጃ ወስዳለች። እርሷም ከመንስኤው ጀምሮ እስከ ውጤቱ ድረስ ያለውን አላስረዳችውም፡፡ የእርሷ ጨካኝ እና ፍትሃዊነት የጎደለው ተግባሯ በልጇ ልብ ውስጥ እጅግ ክፉ ስሜቶችን የሚያነሳሳ ሲሆን ከዚህ ጋር ተመሳሳይ በሆኑ ጊዜያት ሁሉም በተመሳሳይ ጊዜ ሁሉ እነዚህ ምኞቶች ይነሳሳሉ፣ ይጠናከራሉም። 547Counsels to Parents, Teachers, and Students, 117.CGAmh 263.2

    ስህተት ፈላጊነት — ስህተትን በመፈለግ ወይም ተራ በሆኑ ስህተቶች ላይ ጎጂ ተግሳጽን በመሰንዘር በልጆቻችሁ ደስታ ላይ የጨለመ ደመና የማምጣት መብት የላችሁም፡፡ ትክክለኛ ስህተት ልክ እንደ ኃጢያት እንዲታይ መደረግ አለበት፣ እናም ዳግም እንዳይከሰት ለመከላከል ጽኑ እና ቁርጥ ውሳኔ መደረግ አለበት፤ ሆኖም ግን ልጆች ተስፋ አስቆራጭ በሆነ የአእምሮ ሁኔታ ውስጥ መተው የለባቸው ሳይሆን፣ ነገር ግን እንዲሻሻሉ እና በእናንተ ላይ እምነታቸውን እንዲጥሉ እና የእናንተን ማረጋገጫ እንዲያገኙ በተወሰነ ደረጃ ድፍረት እንዲያገኙ መደረግ አለባቸው፡፡ ልጆች መልካምን የሆነውን ለማድረግ ይመኙ ይሆናል፣ በልባቸው ታዛዥ እንዲሆኑ ይፈልጉ ይሆናል፤ ግን እርዳታ እና ማበረታቻ ይፈልጋሉ።3The Signs of the Times, April 10, 1884.CGAmh 263.3

    ከመጠን በላይ አደገኛ ወደ ሆነው ተግሣጽ — የቤተሰብ ሥነ-ምግባር ምን ማለት እንደሆነ በትክክል መረዳት በሌለበት እና ልጆች ተግሣጽ እና ማስተዳደር ማለት ምን እንደሆነ ግራ የሚጋቡበት ቤተሰብ ውስጥ እግዚአብሔር ምን ያህል ይዋረዳል! እጅግ ከባድ ተግሳጽ፣ እጅግ ብዙ ነቀፌታ፣ አላስፈላጊ ሕጎች እና መምሪያዎች ለባለ ሥልጣን አክብሮት ወደማጣት እና በመጨራሻም ክርስቶስ ይፈጽማቸው የነበሩትን እነዚያን መመሪያዎችን ችላ ወደ ማለት ማምራቱ እውነት ነው። 548The Review and Herald, March 13, 1894.CGAmh 264.1

    ወላጆች ስርዓት አልባኝነትን፣ አደገኛነትን፣ የጌትነት መንፈስ ሲያሳዩ በልጆቻቸው ላይ የእብሪት እና ግትርነት መንፈስ ይነሳሳል። ስለሆነም ወላጆች በልጆቻቸው ላይ ሊያሳድሩ የሚችሉትን የማለስለስ ተፅእኖ በእነርሱ ላይ ማሳደር ያዳግታቸዋል፡፡CGAmh 264.2

    ወላጆች፣ ክፉ ቃላት የግትርነትን ስሜትን የሚቀሰቅሱ እንደሆኑ አትመለከቱም? እናንት ትናንሽ ልጆቻችሁን በምትይዙበት አይነት አያያዝ በግዴለሽነት ብትያዙ ምን ታደርጋላችሁ? ከመንስኤ እስከ ውጤት ድረስ ያለውን ማጥናት ኃላፊነታችሁ ነው፡፡ ልጆቻችሁን ስትሰድቡ፣ ራሳቸውን ለመከላከል ገና ትናንሽ የሆኑትን በቁጣ ስትመቷቸው፣ እንዲህ ዓይነቱ አያያዝ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚያስከትል ራሳችሁን ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ? ከነቀፋ ወይም ወቀሳ ቃላት ጋር በተያየዘ ምን ያህል ስሜታዊ እንምትሆኑ አስባችሁ ታውቃላችሁ? አንድ ሰው ችሎታችሁን ሳይገነዘብ ሲቀር ምን ያህል በፍጥነት የመጎዳት ስሜት እንደሚሰማችሁ? እናንተም ልጆች የነበራችሁ አሁን ግን ያደጋችሁ ናችሁ። እንግዲያው ክፉ ቃላትን፣ ጎጂ ቃላትን ስትናገሯቸው፣ በእግዚአብሔር ፊት ግማሽ ያህል እንኳ ቅሬታን ለማይፈጥሩ ስህተቶች ከባድ ቅጣት ስትጧቸው፣ ልጆቻችሁ ምን ሊሰማቸው እንደሚችል አስቡ፡፡ 549Manuscript Releases 4:2, 1903. CGAmh 264.3

    ብዙ ክርስቲያን ነን ባይ ወላጆች አልተለወጡም። ክርስቶስ በእምነት በልባቸው የለም! ክፋታቸው፣ ብልግናቸው፣ ያልተሸነፈ ስሜታቸው፣ ልጆቻቸውን የሚያዋርድ እና ለመላው የሃይማኖታዊ ትምህርቶቻቸው ተቃራኒ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል፡፡6Letter 18b, 1891.CGAmh 264.4

    በቀጣይነት ወደ ትችት — ክፋን ለማረም በምናደርገው ጥረት ውስጥ ከስህተት ፈላጊነት እና ትችት ዝንባሌ መጠበቅ አለብን። ቀጣይነት ያለው ትችት ግራ ያጋባቸዋል እንጂ አያሻሽላቸውም፡፡ ለብዙ አዕምሮዎች፣ እና ብዙውን ጊዜ እጅግ በቀላሉ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች፣ ርህራሄ የጎደለው ትችት የተሞላበት ሁኔታ ለጥረታችሁ አደገኛ ነው። አበቦች በአደገኛ ነፋስ ጊዜ አያብቡም።CGAmh 265.1

    በአንድ የተለየ ስህተት በተደጋጋሚ የሚተች ልጅ አንዳንዴ ከዚያ ለመላቀቅ ጥረት ማድረጉ ከንቱ እንደ ሆነ እስኪታይ ድረስ ያንን ስህተት እንደ መለያው ወደ መቁጠር ይመጣል፡፡ አብዘኛውን ጊዜ በዚህ አይነት መንገድ በግዴለሽነት ወይም በማደፋፈር ሥር ተሰውረው ተስፋ መቁረጥ ይከሰታል። 550Education, 291.CGAmh 265.2

    ወደ ማዘዝ እና ወደ መሳደብ — አንዳንድ ወላጆች ራስን መግዛት ባለመቻላቸው ብዙ ረብሽ ያስነሳሉ፡፡ ልጆቹ ይህንን ወይም ያንን እንዲያደርጉ በትህትና ከመጠየቅ ይልቅ በቁጣ ድምጽ ያዟቸዋል፣ በተመሳሳይ ጊዜም ለልጆቹ የማይገባቸው ትችት ወይም ዘለፋ በከንፈራቸው ላይ ይገኛል፡፡ ወላጆች ሆይ ይህ ከልጆቻችሁ ጋር በተያያዘ የምትሄዱበት አካሄድ ደስታቸውን እና ምኞታቸውን ያጠፋል፡፡ ትዕዛዛችሁን የሚፈጽሙት ከፍቅር የተነሳ ሳይሆን ነገር ግን በተቃራኒው ለመስራት ስለማይደፍሩ ነው፡፡ ልባቸው በጉዳዩ ላይ አይደለም፡፡ ይህ አስደሳች ከሚሆን ይልቅ እንደ ባሪያ ማገልገል ይሆናል፣ እናም ብዙውን ጊዜ ትዕዛዛችሁን ሁሉ መከተልን እንዲረሱ ይመራቸዋል፣ ይህም ቁጣችሁን የሚጨምር እና እንደገና ለልጆቹ ሁኔታዎችን የባሰ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ስህተት ፈላጊነት ይደጋገማል፣ ተስፋ መቁረጥ እስኪደርስባቸው እና ሌሎችን ለማስደሰት ወይም ላለማስደሰት መለየት እስከማይችሉበት ድረስ መጥፎ ምግባራቸውም ከፊት ለፊታቸው በደማቅ ቀለሞች ተሰልፈው ይቆማሉ፡፡ “ግድ የለኝም” የሚል መንፈስ ይይዛቸው እና ቤት ማግኘት የማይችሉትን እንዳሻቸው መሆንን እና ደስታን ከቤት ውጭ፣ ከወላጆቻቸው ርቀው ይፈልጋሉ፡፡ ጎዳና ላይ ከሚገኙ ሰዎች ጋር ይቀላቀሉ እና ወዲያውም እጅግ ብልሹ ይሆናሉ። 551Testimonies For The Church 1:384, 385CGAmh 265.3

    ወደ አምባገነናዊው እርምጃ— የወላጆች ፈቃድ በክርስቶስ ተግሣጽ ስር መሆን አለበት። በእግዚአብሔር ንጹህ መንፈስ ቅዱስ መቀረጽ እና ቁጥጥር ሥር በመሆን፣ በልጆቻቸው ላይ አጠያያቂ ያልሆነ የበላይነት መመስረት አለባቸው። ነገር ግን ወላጆች ከባድ እና በተግሣጻቻው ለመጠን በላይ ጥብቅ ከሆኑ፣ በጭራሽ ራሳቸውም ሊቀለብሷቸው የማይችሉትን ስራ ይሰራሉ። በአምባገነናዊ ተግባራቸው፣ የፍትሕ መጓደልን ያነሳሳሉ። 552Manuscript Releases 7:1899.CGAmh 266.1

    ፍትሕን መጓደል — ልጆች ለትንሿ የፍትሕ መጓደል በቀላሉ የሚጎዱ ናቸው፣ አንዳንዶችም በዚህ ሳቢያ ተስፋ ይቆርጡ እና በጩኸት እና በቁጣ የታዘዙትን ትዕዛዝ አያከብሩም፣ የቅጣት ማስፈራሪያዎችንም አያዳምጡም። ትክክለኛ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ፣ ልጆች ጥሩ እና ስምሙ ባህሪያትን ይመሰርቱ የነበረ ሲሆን፣ ዓመፅ በወላጆች የተሳሳተ ተግሣጽ አማካይነት በልጆች ልብ ውስጥ እጅግ በተደጋጋሚ ይመሰረታል። እራሷን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የማትችል እናት ልጆችን የማስተዳደር ብቃት የላትም፡፡ 553Testimonies For The Church 3:532, 533.CGAmh 266.2

    ማንገላታት ወይም መምታት — እናት ልጇን ስታንገላታ ወይም ስትመታው፣ የክርስትናን ባህርይ ውበት እንዲያይ ያስችለዋል ብለው ያስባሉ? በጭራሽ አይደለም; በልቡ ውስጥ ክፉ ስሜቶችን የሚያነሳሳ እና ልጁም በጭራሽ ያልታረመ ይሆናል። 554Manuscript Releases 4:5, 1911.CGAmh 266.3

    ሻካራ፣ ርህራሄ ያላቸው ቃላት— ክርስቶስ አባትና እናት እውነተኛ አስተማሪዎች እንዲሆኑ ለማስተማር ዝግጁ ነው፡፡ በእርሱ ትምህርት ቤት የሚማሩ… በሻካራ እና ርህራሄ በጎደለው የድምጽ ቃና በጭራሽ አይናገሩም፤ በዚህ መንገድ የተነገሩ ቃላት ጆሮ ላይ የሚሰቀጥጡ፣ ነርቮችን የሚያዳክሙ፣ የአእምሮ ሕመምን የሚያስከትሉ እና እንደነዚህ ያሉ ቃላቶች የሚሰሙ ልጆችን ቁጣ ለመግታት የማይቻል የአእምሮ ሁኔታን ይፈጥራሉ፡፡ ብዙውን ጊዜ ልጆች ለወላጆች አክብሮት በጎደለው መንገድ የሚናገሩት ለዚህ ነው፡፡12Letter 47a, 1902.CGAmh 266.4

    መሳለቅ እና ማሾፍ — እነርሱ [ወላጆች] የማበሳጨት፣ የመሳደብ እና የመሰላቅ ስልጣን አልተሰጣቸውም። ራሳቸው ልጆቻቸው ላይ ያስተላለፉባቸውን ባህሪይ ላይ በጭራሽ ማሾፍ የለባቸውም፡፡ ይህ አይነቱ ተግሳጽ ክፋትን በጭራሽ አይፈውስም፡፡ ወላጆች፣ አስቸጋሪ የሆኑ ልጆችን ለመገሰጽ የእግዚአብሔርን ቃል መመሪያ አምጡ፡፡ እንደ መስፈርት “ጌታ እንደዚህ ይላል” የሚለውን አሳዩአቸው፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል የሚመጡ ተግሳፆች በወላጆች አንደበት በሻካራ እና በቁጣ የድምጽ ቃና ከሚመጡ ይልቅ ውጤታማ ናቸው፡፡ 555Fundamentals of Christian Education, 67, 68.CGAmh 267.1

    ትዕግሥት ማጣት — የወላጆች ላይ ትዕግሥት ማጣት በልጆች ላይ ትዕግሥት ማጣትን ያነሳሳል። ወላጆች የሚያሳዩት ስሜታዊነተት በልጆች ላይ ስሜታዊነትን በመፍጠር ክፋታቸውን ያበረታታል…፡፡ .... ራስን መቆጣጠር ሲያቅታቸው እና ትዕግስት በማጣት በተናገሩ እና በተገበሩ ቁጥር በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ይሰራሉ፡፡ 556Testimonies For The Church 1:398.CGAmh 267.2

    ቁጣ እና ማባበልን እንደ አማራጭ መጠቀም — አንድ እነርሱ የሚፈልጉትን ነገር የተከለከሉ ልጆች ትኩረትን በሚስብ መልኩ እየተራገጡ እና በመጮኽ ወላል ላይ ራሳቸውን ሲጥሉ ብልሃት የጎደላት እናት ልጁን ቀድሞ ወደ ነበረው መልካም ሁኔታ ለመመለስ እንደ አማራጭ ማበባል እና ቁጣን ስትጠቀም በተደጋጋሚ ተመልክቻለሁ፡፡ ይህ አያያዝ የልጁን ስሜት ብቻ የሚያድግ ነው። በሚቀጥለው ጊዜ በተመሳሳይ ሁኔታ በባሰ ግትርነት፣ እንደ ቀድሞው አሻናፊ ለመሆን ይሄዳል፡፡ ስለዚህ በትር ባለመጠቀም ልጁ ብልሹ ይሆናል፡፡ CGAmh 267.3

    እናት ልጇ ለቅጽበትም እንኳ አጋጣሚ እንድታገኝባት መፍቀድ የለባትም፡፡ ይህንንም ስልጣን ጠብቆ ለማቆየት ወደ አስከፊ እርምጃዎች ዘወር ማለት አስፈላጊ አይደለም፤ ልጃችሁ እናንት ስለ እነርሱ ያላችሁን ፍቅር ለማሳመን ጥብቅ፣ ጽኑ እጅ እና ርህራሄ ዓላማውን ይፈጽማሉ። 557Pacific Health Journal, April, 1890.CGAmh 267.4

    ጽናት እና ውሳኔን ማጣት— ጽናት እና ውሳኔን በማጣት ትልቅ አደጋ አደጋ ይከሰታል፡፡ ይህን ወይም ያንን መውሰድ አትችልም፣ የሚሉ እና ከዚያም እጅግ ጥብቅ እንደሆኑ በመሳብ ተጸጽተው መጀመሪያ የከለከሉትን ያንኑ ነገር ለልጁ የሚሰጡ ወላጆችን አውቃለሁ፡፡ በዚህም ሳቢያ የዕድሜ ልክ ጉዳት ይደርስበታል። አንድ በንቀት ሊታይ የማይገባ ነገር አንድ የተመኙት ነገር ሙሉ ተስፋ ተሟጥጦ እስኪጠፋ ድረስ በጽናት በሚከለከልበት ጊዜ ወዲያው አእምሮ ያንን ነገር መመኘቱን ያቆም እና በሌሎች ሥራዎች እንደሚጠመድ መዘንጋት የሌለበት እጅግ ወሳኝ የሆነ የአእምሮ ህግ ነው። ነገር ግን የተፈለገውን ነገር ለማግኘት ተስፋ እስካለ ድረስ እርሱን ለማግኘት ጥረት ይደረጋል…፡፡CGAmh 268.1

    ወላጆች ቀጥተኛ ትእዛዝን እንዲሰጡ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አለመታዘዝ የሚያስከትለው ቅጣት እንደ ተፈጥሮ ሕጎች ሁሉ የማይለዋወጥ መሆን አለበት፡፡ በዚህ ጽኑ እና ወሳኝ ሕግ ስር ያሉ ልጆች አንድ ነገር ሲከለከሉ ወይም ሲነፈጉ፣ ማበሳጨት ወይም ማጭበርበር ዓለማቸውን እንዲሳካ አያደርግም፡፡ ስለሆነም ወዲያው ራሳቸውን መግዛትን የሚማሩ እና ይህን በማድረጋቸውም ይበልጥ ደስተኞች ናቸው። ውሳኔ የሌላቸው እና ከልክ በላይ የሚያሞላቅቁ ወላጆች ልጆች ማባባል፣ ማልቀስ ወይም ቁጡ መሆን ዓለማቸውን እንደሚያሳካላቸው ተስፋ የሚያደርጉ ወይም ሳይቀጡ ላለመታዘዝ እንደሚደፍሩ ዘወትር ተስፋ ያደርጋሉ፡፡ በዚህም መንገድ በምኞት፣ በተስፋ እና እርግጠኛ ባለመሆን ውስጥ ተጠብቀው እንዲቆዩ ይደረጋሉ፣ ይህም ቁንጥንጥ፣ ግልፍተኛ እና የማይታዘዙ ያደርጋቸዋል፡፡ እግዚአብሔር እንደዚህ ያሉ ወላጆችን የልጆቻቸውን ደስታ በማጥፋታቸው ወንጀለኛ ያደርጋቸዋል፡፡ በሺዎች ለሚቆጠሩ ትዕግስት የለሾች እና ኃይማኖት አልባዎች ይህ አያያዝ ቁልፍ ተግባር ነው፡፡ ይህ አያሌ የክርስትና ስም አለን ባዮችን ጥፋት አረጋግጧል፡፡ 558The Signs of the Times, February 9, 1882CGAmh 268.2

    አላስፈላጊ ክልከላዎችን ማድረግ — ወላጆች ሲያረጁ እና የሚያሳድጓቸው ትናንሽ ልጆች ሲኖራቸው አባት ራሱ እየተጓዘበት ያለ አስቸጋሪ እና አባጣ ጎርባጣ ጎዳና ልጆቹ መከተል አለባቸው ብሎ ሊሰማው ይችላል፡፡ ወላጆቻቸው ለእነርሱ ሕይወትን አስደሳች ማድረግ እንዳለባቸው መገንዘቡ ለእርሱ ከባድ ነው፡፡CGAmh 268.3

    አያሌ ወላጆች የማይጎዳ እና ንጹህ የሆነውን የልጆቻቸውን ምኞት ይነፍጓቸው እና ህገ-ወጥ ለሆኑ ነገሮች ያላቸውን ምኞት በውስጣቸው ያድግ ዘንድ እንዳያበረታቱ በመፍራት ልጆች ማግኘት የሚገባቸውን ደስታ እንዲያገኙ እንኳን አይፈቅዱላቸውም። ክፉ ውጤቶችን በመፍራት ራሳቸው እንዲወገድ የሚሹትን ክፋት ማስቀረት የሚችለውን ቀለል ያለ ደስታ የሚገኝበት ነገር ፈቃድ ይነፍጓቸዋል፤ በዚህም መንገድ ልጆች ምንም ዓይነት ውለታ እንዲደረግላቸው መጠበቁ ጥቅም እንደሌለው በማሰብ ስለ ምንም አይጠይቋቸውም፡፡ እንደሚከለክሏቸው የሚያስቧቸውን ተድላ የሚገኝባቸውን ነገሮችን ይሰርቃሉ፡፡ በወላጆች እና በልጆች መካከል ያለው መተማመን በዚህ መንገድ ይጠፋል፡፡ 559The Signs of the Times, August 27, 1912.CGAmh 269.1

    ምክንያታዊ የሆኑ መብቶችን መንፈግ— አባቶች እና እናቶች እራሳቸው ጥሩ የልጅነት ሕይወት ካልነበራቸው በዚህ ረገድ ባጡ ታላቅ ኪሳራ የተነሳ የልጆቻቸው ህይወት ላይ ለምን ይጋርዳሉ? አባት ይህ እነርሱ መከተል ያለባቸው ብቸኛው አስተማማኝ መንገድ ነው ብሎ ሊያስብ ይችላል፤ ነገር ግን ሁሉም አእምሮዎች በተመሳሳይ ሁኔታ የተፈጠሩ እንዳልሆኑ እና ይበልጥ ለመገደብ ጥረቶች በተደረጉት ቁጥር የተነፈጉትን ነገር ለማግኘት ያላቸው ምኞት ይበልጥ ከቁጥጥር በላይ እንደሚሆን፣ ውጤቱም ለወላጆች ስልጣን አለመታዘዝ እንደሚሆን ማስታወስ አለበት። አባት በልጁ ያለመገዛት ነው ብሎ በሚያስበው አካሄድ ያዝናል፣ በማመጹም ልቡ ይጨነቃል፡፡ ነገር ግን ለልጁ አለመታዘዝ የመጀመሪያ ምክንያት ኃጢአት በሌለበት ነገር ምኞቱን ለማርካት ፈቃደኛ አለመሆኑን መገንዘቡ ጥሩ አይሆንም? ወላጅ ያን ነገር ከተነፈገ ጀምሮ ልጁ ምኞቱን ከማርካት እንዲታቀብ በቂ ምክንያት ተሰጥቶታል ብለው ያስባል፡፡ ነገር ግን ወላጆች ልጆቻቸው የማሰብ ችሎታ ያላቸው ፍጡራን መሆናቸውን እና እነርሱን መያዝ ያለባቸው ወላጆች ራሳቸው መያዝ እንደሚፈልጉት መሆን እንዳለበት መዘንጋት የለባቸውም፡፡ 560The Signs of the Times, August 27, 1912.CGAmh 269.2

    መጉዳት— ከገዛ ወላጆቻቸው የተላለፈባቸውን፣ በተግሳጻቸው እና ትዕዛዛቸው መሰረት ልጆችን የማይዛነፉ የሚያደርጋቸው በበላይነት የመግዛት [የአገዛዝ] እና የስልጣንን መንፈስ ተግባራዊ የሚያደርጉ ወላጆች ልጆቻቸውን በትክክል ማሰልጠን አይችሉም፡፡ በስህተታቸው ላይ እጅግ ጥብቅ በመሆን የሰብአዊውን ልብ ክፉ ስሜት በማነሳሳት ልጆቻቸውን ፍትህ በጎደለው እና የስህተት ስሜት ውስጥ ይተውአቸዋል፡፡ ራሳቸው ያካፈሏቸውን ተመሳሳይ ባህሪይ በልጆቻቸው ውስጥ ያገኛሉ፡፡ CGAmh 270.1

    እንደዚህ አይነት ወላጆች ስለ ኃይማኖት ርዕስች ከእነርሱ ጋር በማውራት ልጆቻቸውን ከእግዚአብሔር ያርቃሉ፤ ምክንያቱም እንዲህ ባለ እውነትን አዛንፎ የማቅረብ ሂደት የክርስትና ኃይማኖት የማይማርክ እና እንዲሁም አስቀያሚ ሆኖ ቀርቧል፡፡ ልጆችም “መልካም፣ ያ ኃይማኖት ከሆነ፣ እኛ ከእርሱ ምንም አንፈልግም” ይላሉ፡፡ ለኃይማኖት ያላቸው ጥላቻ በልባቸው ውስጥ የሚፈጠረው በዚህ መንገድ ነው፤ እናም በአምባገነናዊ የስልጣን አስገዳጅት ሳቢያ ልጆች የሰማይ ሕግና መንግስትን እንዲያቃልሉ ይመራሉ፡፡ ወላጆች በተሳሳተ አገዛዛቸው የተነሳ የልጆቻቸውን ዘላለማዊ ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ፡፡ 561The Review and Herald, March 13, 1894. CGAmh 270.2

    ዝግ ያለ፣ የርህራሄ ጠባይ— ወላጆች ልጆቻቸው አስደሳች እንዲሆኑላቸው የሚመኙ ከሆነ በጭራሽ በቁጣ ሊናገሯቸው አይገባም፡፡ ብዙውን ጊዜ እናት ተናዳጅ እና ብስጩ ትሆናለች፡፡ ብዙውን ጊዜ ትነጥቃቸው እና ክፉ ትናገራቸዋለች፡፡ ልጅ በዝግታ እና በርህራሄ ቢያዝ ኖሮ በውስጡ አስደሳች ስሜትን ለመፍጠር ብዙ ይረዳው ነበር፡፡20The Review and Herald, May 17, 1898.CGAmh 270.3

    የፍቅር ምልጃን ማድረግ — የቤተሰቡ ካህን የሆነው አባት፣ ልጆቹን በእርጋታ እና በትዕግስት መያዝ ይኖርበታል። በውስጣቸው የጥላቻ ስሜት እንዳያነሳባቸው መጠንቀቅ አለበት፡፡ መተላለፍ ሳይታረም እንዲታለፍ መፍቀድ የለበትም፣ ሆኖም ግን በሰው ልብ ውስጥ እጅግ ክፉ የሆነ ስሜትን ሳይቀሰቅሱ ማስተካከል የሚችሉበት መንገድ አለ። በአካሄዳቸው አዳኙ ምን ያህል እንዳዘነ በመንገር በፍቅር ከልጆቹ ጋር ይነጋገር፤ ከዚያም ከእነርሱ ጋር በምህረት ወንበር ፊት ተንበርክኮ ክርስቶስ እንዲራራላቸው እና ንስሃ እንዲገቡና ይቅርታን እንዲጠይቁ እነርሱን እንዲመራቸው በመጸለይ በፊቱ ያቅርባቸው፡፡ እንዲህ ዓይነቱ ተግሣጽ ዘወትር እጅግ ግትር የሆነውን ልብ ይሰባብራል።CGAmh 270.4

    እግዚአብሔር ልጆቻችንን ቀለል ባለ መንገድ እንድንይዛቸው ይፈልጋል፡፡ ልጆች በዕድሜ የገፉት ሰዎች ያገኙትን ረጅም ዓመታትን የፈጀውን የሥልጠና አጋጣሚ እንዳላገኙ እንረሳለን፡፡ ትንናሽ ልጆቻችን በሁሉም ረገድ ከሀሳቦቻችን ጋር ተመስማሚ በሆነ መንገድ ያልተጓዙ እንደሆነ አንዳንድ ጊዜ ቁጣ ይገባቸዋል ብለን እናስባለን፡፡ ነገር ግን ይህ ጉዳዮቹን አያስተካክላቸውም። ወደ አዳኙ ውሰዷቸው እና ስለ ጉዳዩ ሁሉ ንገሩት፤ ከዚያም የእርሱ በረከት በእነርሱ ላይ እንደሚወርድ እመኑ፡፡ 562Manuscript Releases 7:0.1903.CGAmh 271.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents