Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 72—ለተሃድሶ የሚደረግ ጦርነት

    ልባዊ ንስሃ እና ቆራጥነት የተሞላበት ጥረት አስፈላጊ ነው— አካሎቻቸውን የሚያበላሹ ሰዎች ልባዊ ንስሃ እስኪገቡ ድረስ፣ ጌታን በመፍራት ሁለንተናዊ ተሃድሶ እና ፍጹም ቅድስና እስኪኖራቸው ድረስ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን አያገኙም፡፡ 927An Appeal to Mothers, 29.CGAmh 442.1

    ወራዳ ልማዶችን ለሚፈጽሙ ሰዎች ብቸኛው ተስፋ ለጊዜያዊ ጤንነት እና ዘላለማዊ ድነት ዋጋ እስኪሰጡ ድረስ እነርሱን መተው ነው፡፡ እነዚህ ልማዶች ለረጅም ጊዜያት የተፈጸሙ እንደሆነ ፈተናን ለመቋቋም እና ብልሹ ምኞትን ማርካትን ለመተው ቆራጥነት የተሞላበት ጥረት ያስፈልጋል፡፡ 928An Appeal to Mothers, 27.CGAmh 442.2

    ሀሳብ ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል [ማሳሰቢያ:- እነዚህ በድብቅ ብልግና ለሚለማመድ ግትር ወጣት ከተጻፈ ደብዳቤ የተወሰዱ ናቸው]— ሀሳቦችህን መቆጣጠር አለብህ፡፡ ይህ ቀላል ሥራ አይደለም፤ እንዲያውም ያለ ጥብቅ እና ከባድ ጥረት ማከናወን አትችልም .... አዕምሮህ እርኩስ ጉዳዮች ላይ እንዲጠመድ በመፍቀድ በከንቱ ምናብ እርካታ የምታገኝ ከሆነ፣ ልክ ሀሳቦችህ ወደ ተግባር የተለወጡ ያህል በእግዚአብሔር ፊት ጥፋተኛ ትሆናለህ፡፡ ተግባርን የከለከለው ዕድል ያለማግኘት ነው፡፡ የቀንና የሌሊት ሕልምና በሐሳብ መባከን መጥፎ እና እጅግ አደገኛ የሆኑ ልማዶች ናቸው፡፡ አንዴ ከተመሠረቱ እንደነዚህ ያሉትን ልምዶች ማፍረስ እና ሀሳቦቹን ወደ ንጹህ፣ ከፍ ወዳሉ ርዕሰ ጉዳዮች መምራት የማይቻል ነው፡፡ አእምሮህን ለመቆጣጠር እና ከንቱ እና እርኩስ ሀሳቦች ነፍስህን እንዳያረክሱ ከፈለግህ በዓይኖችህ፣ በጆሮዎችህ እና በሁሉም ስሜቶችህ ላይ ታማኝ ጠባቂ መሆን ይኖርብሃል፡፡ ይህንን እጅግ ተፈላጊ ሥራ ማከናወን የሚችለው የፀጋው ኃይል ብቻ ነው፡፡ 929Testimonies For The Church. 2:561CGAmh 442.3

    ምኞቶችን እና ስሜቶችን ለምክንያታዊነት አስገዛ፡፡ *ማስታወሻ፡- 452 ገጽ ላይ ያለውን ማስታወሻ ይመልከቱ፡፡— እግዚአብሄር ሀሳቦችህን ብቻ ሳይሆን ምኞቶችህን እና ስሜቶችህንም ጭምር እንድትቆጣጠር ይፈልጋል፡፡ ድነትህ በእነዚህ ነገሮች ራስህን በመግዛት ላይ የተመሠረተ ነው፡፡ ምኞት እና ስሜት ኃይለኛ ወኪሎች ናቸው፡፡ በተሳሳተ መልኩ ከተተገበሩ፣ በተሳሳተ ተነሳሽነት ከተፈጸሙ፣ የተሳሳተ አቅጣጫ ከያዙ፣ አንተን ያለ እግዚአብሔር እና ያለ ተስፋ በማድረግ ጥፋትህን ለመፈፀም እና የተጣልክ ጎስቋላ ለማድረግ ኃይለኞች ናቸው፡፡CGAmh 443.1

    ምኞቶች እና ስሜተቶች ለምክንያታዊነት፣ ለህሊና እና ለባህሪይ ተገዥ እንዲሆኑ ከተፈለገ ሀሳብ በአዎንታዊ እና በጽናት ቁጥጥር ስር መሆን አለበት ...፡፡ CGAmh 443.2

    ሀሳብህን፣ ንባብህን እና ቃላቶችህን መገደብ እስካልቻልክ ድረስ አስተሳሰብህ ተስፋ በሚያስቆርጥ ሁኔታ በሽተኛ ይሆናል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት፣ በጸሎት አንብብ እና በአስምህሮው ተመራ። ይህ ደህንነትህ ነው። 930Testimonies For The Church 2:561-563.CGAmh 443.3

    ስሜቶችን ከክፋት መጠበቅ— ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነውን ጥበብ የሚፈልጉ ሰዎች ጥበበኞች ለመሆን ከፈለጉ ለዘመኑ ኃጢአተኛ እውቀት ሞኞች መሆን አለባቸው፡፡ የትኛውንም ክፋት ላለማየት እና ላለመማር አይኖቻቸውን መጨፈን አለባቸው፡፡ ክፉውን እንዳይሰሙ እና የአስተሳሰባቸውን እና የድርጊቶቻቸውን ንፅህና የሚያበላሸውን እውቀት ላለማግኘት ጆሯቸውን መዝጋት አለባቸው፣ እንዲሁም ብልሹ ንግግሮች እንዳይናገሩ እና ተንኮል በአፋቸው እንዳይገኝ ምላሳቸውን ሊጠብቁ ይገባል፡፡ 931An Appeal to Mothers, 31.CGAmh 443.4

    የረከሱ አስተሳሰቦችን የሚያሳስቡ ነገሮችን መንበብ እና ማየትን አስወግድ፡፡ ግብረ ገብ እና የአዕምሮ ኃይሎችን አጎልብት፡፡ 932 2:410.CGAmh 444.1

    ከአለመንቀሳቀስ ጋር የተጣመረ ከመጠን በላይ ጥናትን አስወግዱ— ከመጠን በላይ የሆነ ጥናት፣ ወደ አንጎል የሚሄደውን የደም ፍሰትን በመጨመር ራስን የመቆጣጠር ሀይልን የመቀነስ እና ብዙውን ጊዜ ለስሜት ወይም ለጭንቀት ሥፍራ የመልቀቅ አዝማሚያ እንዲኖረው የሚያደርገውን አደገኛ ሽብርን ይፈጥራል። በዚህ መንገድ ለርኩሰት በር ይከፈታል፡፡ የአካል ኃይሎችን አላግባብ መጠቀም ወይም ጭራሹን አለመጠቀም በአለም ላይ ተንሰራፍቶ ለሚገኝ የእርኩሰት ማዕበል በዋናነት ተጠያቂ ይሆናል። “ትዕቢት፣ እንጀራን መጥገብ እና ሥራ ፈትነት” የሰዶምን ጥፋት እንዳስከተለ ሁሉ በዚህ ትውልድም ለሰው ልጅ ዕድገት አደገኛ ጠላት ነው፡፡ CGAmh 444.2

    መምህራን እነዚህን ነገሮችን መረዳት እና ተማሪዎቻቸውን ስለዚህ ነገር ማስተማር አለባቸው፡፡ ቀና አኗኗር ቀና አስተሳሰብ ላይ የተመሰረ እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለአስተሳሰብ ንጽህና ወሳኝ እንደሆነ ተማሪዎችን አስተምሯቸው፡፡ 933Education, 209.CGAmh 444.3

    ለመዋዠቅ ጊዜ የለም— የሕይወት ንጹህና እና በመለኮት ሞዴል መሰረት የተቀረጸ ባህሪይ ከልባዊ ጥረት እና ጽኑ መርሆዎች ውጭ የሚገኝ አይደለም፡፡ የሚዋዥቅ ሰው የክርስትና ፍጽምና በማግኘት ረገድ ስኬታማ አይሆንም፡፡ እነዚህ በሚዛን ተመዝነው ቀለው የሚገኙ ናቸው፡፡ ልክ እንደሚያገሳ አንበሳ ሰይጣን የሚያድነውን ይፈልጋል፡፡ እርሱ በማይጠረጥረው ወጣት ላይ የማታለል ብልሃቱን ይሞክራል ...፡፡ ሰይጣን እነርሱ ሁለተኛ ላይደግሙ አንድ ጊዜ ብቻ በኃጢአት እና በእርኩሰት እንዲረኩ ገና ብዙ ጊዜ እንዳላቸው ለወጣቶች ይነግራቸዋል፤ ዳሩ ግን ያ አንድ ጊዜ ያለአግባብ የሚገኝ እርካታ ሙሉ ሕይወታቸውን ይመርዛል፡፡ ለአንድ ጊዜ እንኳ በተከለከለ ሥፍራ ላይ መሆንን አትድፈሩ፡፡ እያንዳንዱ ሰው ለክፋት እና እርኩሰት በሚማረክበት በዚህ አደገኛ ክፉ ዘመን፣“ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል?” የሚል ከልብ የመነጨ፣ ልባዊ ጩኸት ወደ ሰማይ ይነሳ፡፡ ደግሞም ጆሮዎቹም “ቃልህን በመጠበቅ ነው” በሚለው ምላሽ የተሰጠውን መመሪያ ለመስማት እና ልቡም ለመታዘዝ ያዘነበለ ይሁን። 934 Testimonies For The Church 2:408, 409..CGAmh 444.4

    በዚህ ዓለም የሙከራ ጊዜ ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም ለድርጊቶቻቸው ተጠያቂ ናቸው። ሁሉም ከፈለጉ ድርጊታቸውን ለመቆጣጠር ኃይል አላቸው፡፡ በመልካምነት እና በሀሳብ ንጽህና እና ድርጊቶች ደካማ ከሆኑ፣ ረዳት አልባ ለሆኑት ጓደኛ ከሆነው እርዳታ ማግኘት ይችላሉ። የሱስ የሰውን ተፈጥሮ ድክመቶች ሁሉ ያውቀዋል፣ ከተለመነም በጣም ኃይለኛ የሆኑ ፈተናዎችን ለማሸነፍ ብርታትን ይሰጣል፡፡ በትህትና የሚፈልጉት ሁሉ ይህንን ብርታት ማግኘት ይችላሉ፡፡ 935An Appeal to Mothers, 31.CGAmh 445.1

    በዚህ የእርኩሰት ዘመን ለወጣቶች ብቸኛው ደህንነት እግዚአብሔርን መታመን ነው፡፡ ያለ መለኮታዊ እርዳታ የሰብአዊውን ሰው ምኞቶች እና ስሜቶችን መቆጣጠር አይቻልም፡፡ በክርስቶስ ውስጥ ተፈላጊው እርዳታ አለ፣ ግን ለእዚያ እርዳታ ወደ እርሱ የሚመጡት ምንኛ ጥቂቶች ናቸው፡፡ የሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ “ሕይወት እንዲሆንላችሁ ወደ እኔ ልትመጡ አትወዱም” ብሏል፡፡ ሁሉም በክርስቶስ ድል መንሳት ይችላሉ፡፡ ከሐዋሪያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” ደግሞም “ነገር ግን ሥጋዬን እየጎሰምሁ አስገዛዋለሁ” ማለት ትችላላችሁ፡፡936Testimonies For The Church 2:409..CGAmh 445.2

    በእርሱ እውነተኛ ደስታ ሊገኝ ይችላል— ልጆቻችንን ከማናቸውም መጥፎ ምግባሮች ለመጠበቅ ብቸኛው አስተማማኝ ደህንነት ወደ ክርስቶስ ጉያ መግባት እና በታማኝ እና በእውነት እረኛ ጥበቃ ስር እንዲገቡ መሻት ነው። እርሱ ከክፉ ሁሉ ያድናቸዋል፤ ቃሉንም ቢሰሙ ከአደጋዎች ሁሉ ይጠብቃቸዋል። እርሱ “በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፣ ይከተሉኝማል” ይላል፡፡ በክርስቶስ መሰማሪያ ያገኛሉ፣ ብርታትን እና ተስፋን ያገኛሉ፣ ደግሞም አዕምሮን ወደ ሌላ መንገድ የሚያዞር እና ልብን የሚያረካ አንድ ነገር ለማግኘት ሲሉ እረፍት በሌለው ናፍቆት አይቸገሩም፡፡ እጅግ ውድ ዋጋ ያለው ዕንቁ ስላገኙ አዕምሮም በሰላማዊ ዕረፍት ላይ ይሆናል፡፡ ደስታቸው ንጹህ፣ ሰላማዊ፣ የከበረ እና ሰማያዊ ባሕርይ ያለው ነው። እነዚህ ምንም ዓይነት አሳዛኝ ትውስታ ወይም የጸጸት ጠባሳን ጥለው አያልፉም። እንደነዚህ ያሉት ደስታዎች ጤናን አይጎዱም ወይም አዕምሮን አያዳክሙም፣ ነገር ግን ጤናማ ተፈጥሮአዊ ባህሪይ ያላቸው ናቸው፡፡CGAmh 445.3

    ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግ እና እርሱን መውደድ፣ የቅድስና ልምምድ፣ የኃጢአት መውደም፣ ሁሉም አስደሳች ናቸው፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ እንደ ልብ ወለድ የታሪክ መጽሐፍ አዕምሮን የሚያፈዝዝ እና ስሜቶችን የሚያስቆጣ ሳይሆን ልብን ሩህሩህ፣ የተረጋጋ፣ የከበረ እና የተቀደሰ የሚያደርግ ነው፡፡ በችግር ጊዜ፣ በኃይለኛ ፈተናዎች ሲጠቁ፣ የመጸለይ ልዩ መብት አላቸው፡፡ እንዴት ያለ ታላቅ መብት ነው! አቧራ እና አመድ የሆነ ፍጥረት፣ በክርስቶስ ምልጃ አማካይነት ወደ ልዑሉ ጉባኤ አዳራሽ መታደም ማለት ነው። በእንደዚህ ዓይነቶቹ ልምምዶች ነፍስ ከእግዚአብሄር ጋር ወደ የተቀደሰ ቅርበት የምትመጣ እና በእውቀት እና በእውነተኛ ቅድስና በመታደስ ከጠላት ጥቃቶች የተመሸገች የምትሆንበት ነው፡፡ 937An Appeal to Mothers, 23, 24.CGAmh 446.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents