Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 15—ንብረት አያያዝ ላይ ሊደረግ የሚገባ ጥንቃቄ

    የአጥፊነት ዝንባሌዎችን መግታት—ትምህርት ሁለንተናዊ እና አንድ ወጥ መሆን አለበት፡፡ እያንዳንዷ እናት ትጉህ መሆን አለባት፡፡ ምንም ሐሳቧን እንዲያስለውጣት መፍቀድ የለባትም፡፡ ልጆቿ ቤት ውስጥ ያልሰለጠነ የነገሮች አያያዝ ፍላጎታቸውን እንዲከተሉ መፍቀድ የለባትም፡፡ በነገሮች አያያዝ ለራሳቸው ደስታ ሲሉ ቤቱን በዘላቂነት የተመሰቃቀለ ማድረግ እንደሌለባቸው መማር አለባቸው፡፡ እናቶች ልጆቻችሁን ቤት ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ነገር መጫወቻቸው እንደሆነ እንዳይሰማቸው ከልጅነታቸው ዓመታት ጀምራችሁ አስተምሯቸው፡፡ በእነዚህ ጥቃቅን ነገሮች ነው ሥርዓታዊነት የሚስተማረው፡፡ ልጆች ምንም ያህል ትርምስ ቢያደርጉም፣ በጨቅላነትና በልጅነት አይሎ የሚታየው የአጥፊነት ተግባር እንዲበረታና እንዲያድግ አይደረግ፡፡ እግዚአብሔር “አድርግ” እና “አታድረግ” ይላል፡፡ ወላጆች በንዴት ሳይገነፍሉ፣ ነገር ግን በቆራጥነት ለልጆቻቸው አይደለም ማለት፣ አይደለም ነው ማለት አለባቸው፡፡ CGAmh 95.1

    ቤት ውስጥ ያሉትን ነገሮች ሁሉ እንዳሻቸው እንዲያንገላቱና ወለል ወይም ቆሻሻ ላይ እንዲወረውሩ መፍቀድን በጽናት መከልከል አለባቸው፡፡ ልጅ ይህን መንገድ እንዲከተል የሚፈቅዱ ትልቅ ስህተት እርሱ ላይ እየሰሩ ናቸው፡፡ ልጁ መጥፎ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን የተማረው ትምህርት እጅግ ችግር ፈጣሪና አጥፊ ያደርጋዋል፡፡ 166Manuscript Releases 6:4, 1899.CGAmh 95.2

    ለሌሎች ሰዎች ንብረት አክብሮት እንዲኖራቸው አስተምሯቸው—አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው አጥፊ እንዲሆኑ፣ ለመንካት መብት የሌላቸውን ነገሮች እንደ መጫወቻ እንዲጠቀሙ ይፈቅዱላቸዋል፡፡ ልጆች የሌላ ሰውን ንብረት መንካት እንደሌለባቸው መማር ይገባቸዋል፡፡ ለቤተሰቡ ምቾት እና ደስታ ከንብረት ጋር የተያየዙትን ሕጎችን መጠበቅ እንዳለባቸው መማር አለባቸው፡፡ CGAmh 95.3

    ልጆች ደስተኞች የሚሆኑት የሚመለከቱትን ነገሮች በሙሉ እንዲነካኩት ሲፈቀድላቸው አይደለም ፡፡ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ባይማሩ፣ ደስ በማያሰኝ፣ አጥፊ ባህሪይ ያድጋሉ፡፡ 167The Signs of the Times, September 25, 1901.CGAmh 96.1

    መጫወቻዎች ጠንካራና ረጅም የአገልገሎት ጊዜ የሚኖራቸው ይሁኑ—በቀላሉ የሚሰበሩ መጫወቻዎችን ለልጆች አይስጡ፡፡ ይህን ማድረግ ማለት የአጥፊነትን ትምህርት ማስተማር ነው፡፡ የተወሰኑ መጫወቻዎች ይኑራቸው፣ እነርሱም ጠንካራና የረጅም አገልግሎት ጊዜ የሚራቸው ይሁኑ፡፡ እነዚህ አስተያየቶች፣ ዋጋ የሌላቸው ቢመሽሉም እንኳ፣ በልጆች ትምህርት ውስጥ ትልቅ ትርጉም አላቸው፡፡ 168 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 123.CGAmh 96.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents