Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 60—የሕይወት ሕጎችን ማወቅ እና መታዘዝ

    አስደናቂው የሰው አካል— እኛ የእግዚአብሔር የእጅ ሥራዎች ነን፣ ቃሉም “ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁ” ሲል ይናገራል። እርሱ ይህን ሕያው መኖሪያ ያዘጋጀው ለአእምሮ ነው፤ እርሱም “በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሠራ”፣ ጌታ ራሱ ለመንፈስ ቅዱስ መኖሪያ ያዘጋጀው መቅደስ ነው። አዕምሮ መላውን ሰውነት ይቆጣጠራል፡፡ ድርጊቶቻችን ሁሉ ጥሩም ሆነ መጥፎ ምንጫቸው ከአዕምሯችን ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመልክ እና ከሰማያዊ ፍጡራን ጋር የሚያገናኘን አእምሮ ነው፡፡ ሆኖም ብዙዎች ይህን ሀብት የያዘውን ዕቃ (የሰው አካል) በተመለከተ ግንዛቤ ሳይኖራቸው ሕይወታቸውን በሙሉ ያጠፋሉ፡፡CGAmh 342.1

    ሁሉም የአካል ክፍሎች የአእምሮ አገልጋዮች ናቸው፣ እናም ነርቮች የህያው ማሽን እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ ትዕዛዞቹን ወደ መላው የሰውነት ክፍሎች የሚያስተላልፉ መልእክተኞች ናቸው። 688Fundamentals of Christian Education, 425, 426. CGAmh 342.2

    የሰውነት አሠራር ሲጠና፣ ከመንስኤ እስከ ውጤት ድረስ ላለው አስደናቂ ስምሙነት፣ ለተለያዩ አካላት ተግባቦታዊ እርምጃ እና ጥገኝነት ትኩረት መሰጠት አለበት፡፡ የተማሪው ፍላጎት በዚህ ሁኔታ ሲነቃቃ እና የአካላዊ አሰራር አስፈላጊነትን እንዲመለከት ሲደረግ፣ ተገቢ እድገትን እና ትክክለኛ ልማዶችን ለማስጠበቅ በአስተማሪው ብዙ መከናወን ይችላል፡፡2Education, 198.CGAmh 342.3

    ጤና ሊጠበቅ ይገባል— አእምሮ እና ነፍስ በሰውነት ውስጥ ስለሚገለጡ፣ አእምሯዊም ሆነ መንፈሳዊ ኃይል በከፍተኛ ደረጃ በአካላዊ ጥንካሬ እና እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፣ አካላዊ ጤንነትን የሚያበረታታ ማንኛውም ነገር፣ ጠንካራ አእምሮን እና ሚዛናዊ ባህሪን ያሳድጋል፡፡ ያለጤንነት ማንም ሰው ለራሱ፣ ለባልንጀሮቹ ወይም ለፈጣሪው ግዴታውን በግልፅ ሊረዳ ወይም ሙሉ በሙሉ ሊፈጽም አይችልም፡፡ ስለሆነም ጤና እንደ ባህሪይ ሁሉ በታማኝነት ሊጠበቅ ይገባል፡፡ የሥነ አካል እና የንፅህና አጠባበቅ ዕውቀት ለሁሉም የትምህርት ጥረቶች መሠረት መሆን አለበት፡፡ 689Education, 195.CGAmh 342.4

    ብዙዎች የጤና ህጎችን ለማጥናት ፈቃደኞች አይደሉም— ብዙዎች የሕይወት ህጎች እውቀት እና ጤንነትን ለማደስ የሚረዱ ቀላል ዘዴዎችን ለማግኘት አስፈላጊውን ጥረት ለማድረግ ፈቃደኞች አይደሉም። እራሳቸውን ከህይወት ጋር በትክክለኛው ግንኙነት ላይ አያደርጉም፡፡ ሕመም የተፈጥሯዊ ሕግን የመተላለፋቸው ውጤት ሆኖ ሳለ ስህተቶቻቸውን ለማረም አይፈልጉም፣ ከዚያም የእግዚአብሔርን በረከት ይጠይቃሉ። 690Christian Temperance and Bible Hygiene, 112, 113.CGAmh 343.1

    እኛ ከጤና ህጎች ጋር ተስማምተን ለመኖር ብቻ ሳይሆን ሌሎችን በተሻለ መንገድ ለማስተማር እራሳችንን ማስተማር አለብን፡፡ ብዙዎች፣ የወቅቱን ልዩ እውነትን እናምናለን ከሚሉት መካከልም እንኳ ጤንነትን እና መሻት መግዛትን በተመለከተ በሚያሳዝን ድንቁርና ውስጥ ናቸው። እነርሱ ሥርዓት በሥርዓት፣ ትእዛዝ በትዕዛዝ መማር ያስፈልጋቸዋል፡፡ ርዕሱ ከፊታቸው አዲስ ሆኖ መቆየት አለበት። እያንዳንዱ ቤተሰብ ማለት በሚቻል ሁኔታ በጥያቄው ላይ መነሳት ስለሚኖርበት ይህ ጉዳይ አላስፈላጊ እንደሆነ መታላፍ የለበትም፡፡ ሕሊና የእውነተኛ ተሃድሶ መርሆዎችን በመለማመድ ግዴታ መነቃቃት አለበት፡፡ 691Christian Temperance and Bible Hygiene, 117. CGAmh 343.2

    የንፅህና አጠባበቅ መርሆዎች በአመጋገብ፣ በአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ በልጆች አያያዝ፣ በሕመምተኞች አያያዝ እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ አሁን ካለቸው ተራ ትኩረት የላቀ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡6Education, 197.CGAmh 343.3

    የመከላከል እርምጃዎችን ማጥናት—በጣም በሰለጠኑ እና ተወዳጅ በሆኑ ሀገራት ውስጥ እንኳን በአሁኑ ጊዜ ለሞት፣ ለበሽታ እና ለማሽቆልቆል መንስኤዎች በጣም አናሳ እሳቤ ተሰጥቷቸዋል። የሰው ዘር እያሽቆለቆለ ነው ...፡፡ በሰው ዘር ላይ መከራን እና ጥፋትን የሚያመጡ አብዛኛዎቹ ክፋቶች መገታት ይችሉ ነበር፣ እነዚህንም የማድረግ ሥልጣን በከፍተኛ ደረጃ ወላጆች ጋር ያርፋል፡፡ 692The Ministry of Healing, 380.CGAmh 343.4

    ልጆችን ከመንስኤ እስከ ውጤት ድረስ ያለውን ማገናዘብ እንዲችሉ አስተምሯቸው—ልጆቻችሁን ከመንስኤ እስከ ውጤት እንዲያገናዝቡ አስተምሯቸው፡፡ የአካላቸውን ህጎች ከጣሱ በመሰቃየት ቅጣቱን መክፈል እንዳለባቸው አሳዩአቸው። የምትመኙትን ያህል ፈጣን መሻሻል ማየት ካልቻላችሁ ተስፋ አትቁረጡ፣ ነገር ግን በትእግስት አስተምሯቸው፣ ድልም እስኪገኝ ድረስ ቀጥሉበት። 693Counsels to Parents, Teachers, and Students, 126.CGAmh 344.1

    የቀናውን የኑሮ መርሆዎች የሚያጠኑ እና የሚተገብሩ ሰዎች በአካልም ሆነ በመንፈስ እጅግ ይባረካሉ። ስለ ጤና ፍልስፍና ግንዛቤ ማግኘት ያለማቋረጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ ላሉት ብዙ ክፋቶች ከለላ ይሆናል፡፡ 694Counsels to Parents, Teachers, and Students, 138.CGAmh 344.2

    ትምህርቱ ቀስ በቀስ እየጨመረ የሚሄድ ይሁን— ልጆች ቀላል፣ ከባድ ያልሁኑ ትምህርቶችን፣ የሥነ አካል እና የንፅህና አጠባበቅ መሰረታዊ መመሪያዎችን ቀደም ብለው መማር አለባቸው። ስራው ቤት ውስጥ በእናት መጀመር አለበት፣ በትምህርት ቤትም በታማኝነት ወደፊት መቀጠል አለበት፡፡ ተማሪዎች በዕድሜያቸው እየገፉ ሲሄዱ፣ የሚኖሩበትን ቤት የመያዝ ብቃት እስከሚኖራቸው ድረስ በዚህ ዘርፍ የሚሰጠው መመሪያ ሊቀጥል ይገባል፡፡ የእያንዳንዱን አካል ብርታት በመጠበቅ በሽታን የመከላከልን አስፈላጊነት መገንዘብ አለባቸው እንዲሁም የተለመዱ በሽታዎችን እና አደጋዎችን እንዴት እንደሚያክሙ መማር አለባቸው፡፡10Education, 196.CGAmh 344.3

    ተጨባጭ ዕውቀት በቂ አይደለም— የሥነ-አካል ተማሪ የጥናት ዓላማ የእውነታዎችን እና የመርሆችን እውቀት ማግኘት ብቻ አለመሆኑን መማር አለበት። ይህ ብቻውን አነስተኛ ጥቅም እንዳለው ያረጋግጣል። እርሱ የአየር ማናፈሻን አስፈላጊነት ሊረዳ ይችላል፣ ክፍሉ በንጹህ አየር ሊሞላ ይችላል፤ ነገር ግን ሳንባውን በትክክል ካልሞላ በስተቀር በተስተጓጎለ የአተነፋፈስ ሥርዓት 695Education, 200. ውጤት ሊሰቃይ ይችላል፡፡ እንዲሁ የንጽህና አስፈላጊነትን ሊረዳ ይችላል፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችም ሊቀርቡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ጥቅም ላይ ካልዋለ በስተቀር ሁሉም ፋይዳ የሌላቸው ይሆናሉ፡፡ እነዚህን መርሆዎች በማስተማር ረገድ እርሱ በዕውቀት በተግባር ላይ እንዲያውላቸው ትልቁ የመጀመሪያው ግዴታ ተማሪውን ስለ አስፈላጊነቱ ማሳመን ነው፡፡696Education, 196, 197. CGAmh 344.4

    የተፈጥሮ ሕጎች ዕውቀት አስፈላጊ ነው— ብዙውን ጊዜ ሊታሰብባቸው የሚገቡ በሥነ-አካል ጥናት ውስጥ የማይካተቱ ጉዳዮች አሉ— እነዚህ ለተማሪው በዚህ አመራር ስር በተለምዶ ከሚስተምረው በርካታ ቴክኒካዊ ጉዳዮች እጅግ የላቀ ጠቀሜታ አላቸው፡፡ በእነዚህ ዘርፎች ውስጥ እንዳሉ የሁሉም ትምህርት መሠረታዊ መርኾ እንደመሆኑ ወጣቶች የተፈጥሮ ሕጎች የእግዚአብሔር ሕጎች እንደሆኑ — እንደ አሥርቱ ትዕዛዛት መመሪያዎች ሁሉ እውነትም ከመለኮት እንደ ሆኑ መማር አለባቸው፡፡ እግዚአብሔር አካላዊ ቅንጅትን የሚመሩ ህጎችን በእያንዳንዱ ነርቭ፣ ጡንቻ እና የአካል ጅማት ላይ ጽፏቸዋል። በግድየለሽነት እና ሆን ተብሎ እነዚህን ሕጎች መጣስ በፈጣሪያችን ላይ ኃጢአት መስራት ነው። እንግዲያው ስለ እነዚህ ሕጎች ጥልቅ እውቀት ማካፈል ምንኛ አስፈላጊ ነው! CGAmh 345.1

    በምግብ እና በእንቅልፍ መደበኛነት መጠበቅ— በምግብ እና በእንቅልፍ ሰዓት የመደበኛነት አስፈላጊነት ሊናቅ አይገባም፡፡ ሰውነትን የመገንባት ተግባር በእረፍት ሰዓታት ስለሚከናወን፣ በተለይም ለወጣቶች እንቅልፍ መደበኛ እና የተትረፈረፈ መሆኑ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡13Education, 205.CGAmh 345.2

    የእንቅልፍ ሰዓታትን በመቆጣጠር ረገድ ያለ ዕቅድ ድንገት ብቅ ያለ ሥራ ሊኖር አይገባም፡፡ ተማሪዎች የእኩለ ሌሊት ዘይትን የማቃጠል እና የቀኑን ሰዓታት በእንቅልፍ የማሳለፍ ልማድ መፍጠር የለባቸውም፡፡ ቤት ውስጥ ይህን ማድረግ የለመዱ እንደሆነ፣ በጊዜው በመተኛት፣ ልማዱን ማረም አለባቸው፡፡ ከዚያ ለቀኑ ግዴታዎች ታድሰው ጠዋት ይነሳሉ፡፡ 697 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 297.CGAmh 345.3

    በትክክለኞቹን የጤና ልማዶችን አጥብቆ መያዝ— የምግብ፣ የመጠጥ እና የአለባበስ ትክክለኛ ልማዶች በጥብቅ መያዝ አለባቸው፡፡ የተሳሳቱ ልምዶች ወጣቱን ለመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት በቀላሉ ተጋላጭ እንዳይሆኑ ያርጓቸዋል፡፡ ልጆች የምግብ አምሮትን ልቅ ከማድረግ እና በተለይም አነቃቂ እና አደንዛዥ እጾችን ከመጠቀም ሊጠበቁ ይገባል፡፡ የክርስቲያን ወላጆች የምግብ ጠረጴዛዎች ቅመማ ቅመሞች ባላቸው ምግቦች መከመር የለባቸውም፡፡ 698Counsels to Parents, Teachers, and Students, 126.CGAmh 346.1

    አካላዊ ወይም አእምሯዊ ጥንካሬን የሚያዳክም ወይም ኃይሎቻችንን በምንም መንገድ አላግባብ በሚጠቀም በማንኛውም ልማድ ውስጥ መግባት የለብንም፡፡ የአመለካከት መልካምነት እና ንፁህ አዕምሮ እንዲኖረን፣ ቅዱሱን ከተራው መለየት እንድንችል እና የእርሱ በሆነው በሰውነታችን እና በመንፈሳችን እግዚአብሔርን ማክበር እንድንችል እራሳችንን በጤንነት ለመጠበቅ ባለን አቅም ሁሉ የተቻለንን ማድረግ አለብን፡፡ 699The Youth’s Instructor, August 24, 1893. CGAmh 346.2

    የተስተካከለ አቀማመጥ እና አቋቋም አስፈላጊነት— ሊታቀድባቸው ከሚገቡ የመጀመሪያ ነገሮች መካከል በአቀማመጥም ሆነ በአቋቋም ትክክለኛ አቋም መየዝ መሆን አለበት፡፡ እግዚአብሔር ሰውን ቀና አድርጎ ነው የፈጠረው፣ በመሆኑም አካላዊ ብቻ ሳይሆን ለአዕምሮ እና ግብረ ገብ ጥቅም፣ ለፀጋና ለክብር እና ራስ ለመቆጣጠር፣ ለድፍረት እና በራስ ለመተማመን ይህ ቀጥ ያለ ብሎ መቀመጥ ወይም መቆም ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። መምህር በዚህ ነጥብ ላይ በምሳሌ እና በትእዛዝ መመሪያ ይስጥ። ትክክለኛ አቋም ምን እንደሆነ አሳዩ፣ ተግባራዊ እንዲሆንም አጥብቃችሁ እዘዙ፡፡17Education, 198.CGAmh 346.3

    የአተነፋፈስ እና የድምፅ አሠራር— ከትክክለኛው አቀማመጥ እና አቋቋም ቀጥሎ አስፈላጊው ነገር የአተነፋፈስ እና የድምፅ አሠራር ነው፡፡ ቀጥ ብሎ የሚቀመጥ እና የሚቆም ሰው ከሌሎች በበለጠ በትክክል መተንፈስ ይችላል፡፡ ነገር ግን አስተማሪ ስለ ጥልቅ አተነፋፈስ አስፈላጊነት ለተማሪዎቹ ማሳወቅ አለበት፡፡ የመተንፈሻ አካላት ጤናማ አተገባበር የደም ስርጭትን በመርዳት መላውን ስርዓት የሚያነቃቃ፣ የምግብ ፍላጎትን የሚቀሰቅስ፣ የምግብ መፈጨትን ሂደት የሚጨምር እና ጥሩ፣ ጣፋጭ እንቅልፍን እንደሚያመጣ፣ በዚህም ሳቢያ ሰውነትን ማደስ ብቻ ሳይሆን፣ አዕምሮን እንዴት እንደሚያረጋጋ እና ሰላማዊ እንደሚያደርግ አሳዩ፡፡ እንዲሁም ጥልቀት የመተንፈስ አስፈላጊነት በሚታይበት ጊዜ እንዲተገበር አጥብቆ ማሳሰብ ተገቢ ነው፡፡ ይህንን የሚያበረታቱ መልመጃዎችን በመስጠት ልማዱ እየተመሰረተ መሆኑን ተመልከቱ ...፡፡ CGAmh 346.4

    የድምፅ ስልጠና ሳንባዎችን የማስፋት እና የማጠናከር አዝማሚያ ያለው በመሆኑ በሽታን በመከላከል አካላዊ አሰራር ላይ ትልቅ ቦታ አለው፡፡ በንባብ እና በንግግር ትክክለኛውን አቀራረብ ለማረጋገጥ የሆድ ጡንቻዎች በአተነፋፈስ ሙሉ እንቅስቃሴ እንዳላቸው እና የመተንፈሻ አካላት ያልተገደበ መሆናቸውን እዩ፡፡ ውጥረቱ ከጉሮሮ ላይ ሳይሆን በሆዱ ጡንቻዎች ላይ ይሁን፡፡ በዚህ መንገድ የሳንባ አደገኛ ድካም እና ከባድ በሽታ ሊገደብ ይችላል፡፡ ግልጽ ንግግር ለማድረግ፣ ለስላሳ እና በጥሩ ሁኔታ የተስተካከሉ ድምፆችን ለማሰማት እና በጥድፊያ ላለመናገር ጥንቃቄ የተሞላበት ትኩረት መሰጠት አለበት፡፡ ይህ ጤናን ከፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የተማሪውን ሥራ ተቀባይነት ማግኘትን እና ቅልጥፍን በእጅጉ ይጨምራል። 700Education, 198, 199.CGAmh 347.1

    ለቤተሰብ ደስታ የሚሰጡ ሦስት አስፈላጊ ነገሮች— በንፅህና ጥናት ውስጥ ቅን አስተማሪ የግል ልማዶችም ሆነ የአከባቢ ሁሉ ፍጹም ንፅህና አስፈላጊነትን ለማሳየት እያንዳንዱን አጋጣሚ ያሻሽላል፡፡ በየዕለቱ ገላን መታጠብ ጤናን ከፍ ለማድረግ እና የአዕምሮ እንቅስቃሴን ለማነቃቃት ያለው ጠቀሜታ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ለፀሀይ ብርሀን እና ለአየር ማናፈሻ፣ ለመኝታ ክፍል እና ለማዕድ ቤት ንፅህና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ጤናማ የመኝታ ክፍል፣ በደንብ ንፁህ የሆነ ማዕድ ቤት እና በጥሩ ሁኔታ የተስተካከለ፣ የተሟላ የምግብ ጠረጴዛ፣ ዕቃ ክፍል ውስጥ ከሚቀመጡ ማናቸውንም ውድ ዕቃዎችን ከማቅረብ ይልቅ የቤተሰቡን ደስታ እና የእያንዳንዱን አስተዋይ ጎብኝዎች ትኩረት በመሳብ ልቆ እንደሚሄዱ ተማሪዎችን አስተምሯቸው፡፡ ያ “ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣል” (ሉቃ 12፡ 23) የሚለው ከአንድ ሺህ ስምንት መቶ ዓመታት በፊት መለኮታዊው አስተማሪ ከተሰጠበት ጊዜ ባልተናነሰ መልኩ አሁንም አስፈላጊ ትምህርት ነው። 701Education, 200.CGAmh 347.2

    የተፈጥሮን መድኃኒቶች መረዳትን እሹ—ንጹህ አየር፣ የፀሐይ ብርሃን፣ መሻትን መግዛት፣ እረፍት፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ተገቢ አመጋገብ፣ ውሃን መጠቀም፣ በመለኮታዊ ኃይል መታመን— እነዚህ እውነተኛ መድኃኒቶች ናቸው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ስለ ተፈጥሮ ፈዋሽ ወኪሎች እና እንዴት እንደሚተገበሩ ዕውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ በሕመምተኞች ሕክምና ውስጥ የተካተቱትን መርሆዎች መረዳቱ እና ለአንድ ሰው ይህን እውቀት በትክክል ለመጠቀም የሚያስችለውን ተግባራዊ ሥልጠና ማግኘቱ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡CGAmh 348.1

    ተፈጥሯዊ መድሃኒቶችን መጠቀም ብዙዎች ለመስጠት ፈቃደኛ የማይሆኑትን ጥንቃቄ እና ጥረት ይጠይቃል፡፡ የተፈጥሮ የመፈወስ እና የማነጽ ሂደት ቀስ በቀስ የሚሆን ነው፣ ትዕግሥት ለሌለውም ዘገምተኛ ይመስላል። ጎጂ የሆኑ ምኞቶችን ማስወገድ መስዋእትነትን ይጠይቃል። ነገር ግን በመጨረሻ ተፈጥሮ ሳትስተጓጎል ስራዋን በጥበብ እና በጥሩ ሁኔታ እንደምትሰራ ተይቷል፡፡ ህጓን በመታዘዝ የሚፀኑ በአካል ጤና እና በአእምሮ ጤና ሽልማታቸውን ያጭዳሉ፡፡ 702The Ministry of Healing, 127.CGAmh 348.2

    ሁሉን አቀፍ ሕግ— ለራሳችን ማድረግ ስለምንችለው ነገር በተመለከተ፣ በጥንቃቄ፣ በጥልቀት መመርመርን የሚጠይቅ ነጥብ አለ። ከራሴ ጋር መተዋወቅ አለብኝ፡፡ እግዚአብሄር የሰጠኝን አካል፣ ይህንን ህንፃ እንዴት መንከባከብ እንደምችል፣ በጣም ጥሩ በሆነ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንዴት ማቆየት እንዳለብኝ ለማወቅ፣ ሁሌም ተማሪ መሆን አለብኝ ፡፡ ለአካሌ በጣም ጥሩ የሚሆነኝን መብላት አለብኝ፣ እንዲሁም ለጤናማ የደም ዝውውር ምቹ የሆነ ልብስ ለመልበስ ልዩ ጥንቃቄ ማድረግ አለብኝ፡፡ ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና ከአየር ራሴን መገደብ የለብኝም፡፡ ማግኘት የምችለውን የፀሐይ ብርሃን ሁሉ ማግኘት አለብኝ፡፡ ለሰውነቴ ታማኝ ጠባቂ ለመሆን ጥበብ ሊኖረኝ ይገባል፡፡CGAmh 348.3

    ባላበኝ ጊዜ ወደ ቀዝቃዛ ክፍል በመግባቴ እጅግ ጥበብ የጎደለውን ነገር እየደረግኩ መሆን አለበት፤ በቅዝቃዜ ውስጥ ለመቀመጥ ለራሴ በመፍቀድ በዚህም ሳቢያ ለብርድ ራሴን በማገለጤ ብልህ ያልሆነ መጋቢ መሆኔን እያሳየሁኝ መሆን አለበት። በቀዝቃዛ እጆች እና እግሮች ቁጭ ብዬ ደምን ከጽንፈ-አካል ወደ አንጎል ወይም ወደ ውስጣዊ አካላት በመመለሴ ብልህነት የጎደለውን ነገር እያደረግኩ መሆን አለበት፡፡ በእርጥበታማ የአየር ጠባይ ውስጥ ሁልጊዜ እግሮቼን መሸፈን አለብኝ፡፡ እጅግ ጥሩውን የደም ጥራት ከሚያስገኝ በጣም ጤናማ ምግብ አዘውትሬ መመገብ አለብኝ፣ ከመጠን በላይ መስራትን በተቻለኝ መጠን ማስወገድ ከቻልኩኝ እንዲሁ አደርጋለሁ፡፡ እንዲሁም እግዚአብሔር በሰውነቴ ውስጥ ያቋቋማቸውን ህጎች ስጥስ ንስሃ መግባት እና መታደስ አለብኝ፣ ደግሞም እግዚአብሔር ባዘጋጃቸው ሀኪሞች ሥር— ንጹህ አየር፣ ንፁህ ውሃ እና ፈውስ በሆነው ውድ የፀሐይ ብርሃን፣ እራሴን በጥሩ ሁኔታ ላይ ማድረግ አለብኝ፡፡ 703Medical Ministry, 230.CGAmh 349.1

    እኛ በግለሰብ ደረጃ ለእግዚአብሔር ተጠያቂዎች ነን—አካላችን ክርስቶስ የገዛው ንብረት ነው፣ በመሆኑም እኛ እንደፈለግን በእርሱ ለማድረግ ነፃነት የለንም። የጤና ህጎችን የተገነዘቡ ሁሉ እግዚአብሔር በውስጣቸው ያቋቋማቸውን እነዚህን ህጎች የመታዘዝ ግዴታቸውን መገንዘብ አለባቸው፡፡ ለጤና ህጎች መታዘዝ የግለሰብ ግዴታ ጉዳይ መሆን አለበት፡፡ እኛ እራሳችን በተጣሰ ህግ ውጤቶች እንሰቃያለን፡፡ ስለ ልማዶቻችን እና ተግባሮቻችን በተናጠል ለእግዚአብሄር መልስ መስጠት አለብን፡፡ ስለዚህ እኛ መጠየቅ ያለብን ጥያቄ “የዓለም አሠራር ምንድነው?” የሚል ሳይሆን “እንደ ግለሰብ እግዚአብሔር የሰጠኝን መኖሪያ እንዴት መያዝ እችላለሁ?” የሚል መሆን አለበት፡፡ 704The Ministry of Healing, 310.CGAmh 349.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents