Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 49—የዘመዶች አመለካከት

    የሚያሞላቅቁ ዘመዶች አስቸጋሪዎች ናቸው— የልጆቻችሁን አስተዳደር ለሌሎች እንዴት እንደምትተው ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ አምላክ ከሰጣችሁ ኃላፊነት በአግባቡ ማንም ሊገታችሁ አይችልም። ብዙ ልጆች በቤታቸው አስተዳደር ውስጥ በዘመዶቻቸው ወይም በጓደኞቻቸው ጣልቃ ገብነት ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል፡፡ እናቶች እህቶቻቸውን ወይም እናቶቻቸውን በልጆቻቸው የአያያዝ ጥበብ ውስጥ ጣልቃ እንዲገቡ ፈጽሞ መፍቀድ የለባቸውም፡፡ ምንም እንኳን እናት እጅግ በጣም የተሻለውን ሥልጠና ያገኘችው ከእናቷ እጅ ቢሆንም፣ ነገር ግን አያት ከአሥር ጉዳዮች በዘጠኙ የልጇን ልጆች በማቆላመጥ እና ፍትሃዊነት በጎደለው ውዳሴዋ ታባልጋቸዋለች፡፡ የእናት ትዕግስት የታከለበት ጥረት ሁሉ በዚህ አያያዝ ዘዴ ሊቀለበስ ይችላል፡፡ አያቶች የልጅ ልጆቻቸውን ለማሳደግ ብቁ አለመሆናቸው እንደ ምሳሌ የሚጠቀስ ጉዳይ ነው፡፡ ወንዶች እና ሴቶች ለወላጆቻቸው የሚገባቸውን አክብሮት ሁሉ መስጠት አለባቸው፤ ነገር ግን የገዛ ልጆቻቸውን ማስተዳደርን በተመለከተ ምንም ዓይነት ጣልቃገብነት መፍቀድ የለባቸውም፣ ነገር ግን የአስተዳደር ንግስናውን በእጆቻቸው ውስጥ ማድረግ አለባቸው፡፡ 563Pacific Health Journal, January, 1890.CGAmh 272.1

    በአክብሮት መንፈግ እና ስሜታዊነት ላይ በሚስቁበት ጊዜ— በሄድኩበት ሥፍራ ሁሉ ተገቢ የሆነ የቤት ተግሣጽ እና ክልከላ ችላ ሲባል በጣም አዝናለሁ። ትናንሽ ልጆች የትኞቹንም ታላላቆችን መናገር በማይፈቀድላቸው ቋንቋ በመጠቀም፣ መልስ እንዲሰጡ፣ አክብሮት ማጉደልን እና ብልግናን እንዲያንጸባርቁ ይፈቀድላቸዋል። ተገቢ ያልሆነ ቋንቋ እንዲጠቀሙ የሚፈቅዱ ወላጆች ከልጆቻቸው የበለጠ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ብልግና ለአንድ ጊዜም እንኳ ቢሆን ፈቃድ ማግኘት የለበትም፡፡ ነገር ግን አባቶች እናቶች፣ አጎቶች እና አክስቶች እና አያቶች የአንድ አመት ዕድሜ ያለው ትንሽ ፍጡር ቁጣውን ሲገልጽ ይስቃሉ፡፡ አክብሮት የጎደለው ኮልታፋ ንግግሩ፣ የልጅነቱ ግትርነት፣ እንደ ብልጠት ይታያሉ፡፡ በዚህም መንገድ የተሳሳቱ ልማዶች ማረጋገጫን ያገኙ እና ልጁ በዙሪያው ላሉት ሁሉ የጥላቻ ቁስ በመሆን ያድጋል፡፡ 564The Signs of the Times, February 9, 1882.CGAmh 272.2

    ትክክለኛ እርማትን በሚያጣጥሉበት ጊዜ — በተለይ እናቶች እንዲህ እጅግ ዕውር ሆነው ሳያቸው እና እናቶች ላይ የሚያርፉ ኃላፊነቶችን ያን ያህል ያነሰ ስሜት ሲሰማቸው ለእነርሱ በፍርሃት እብረከረካለሁ። የራሱ ፍላጎት ብቻ ለማሳከት በሚፈል የጥቂት ወራት ዕድሜ ባለው ልጅ ውስጥ እንኳ ሰይጣን ሲሠራ ያዩታል። በእልሀኝነት ሲሞላ ሰይጣን ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ይመስላል። ነገር ግን ይህ ወላጅ ያንን ልጅ ማረሙ ጭካኔ ነው ብሎ እንዲያምን ጥረት የሚያደርጉ ምናልባትም አያት፣ አክስት፣ ወይም ሌላ ዘመድ ወይም ጓደኛ ቤት ውስጥ ሊኖሩ ይችላል፤ ነገር ግን ተቃራኒውም እውነት ነው፤ እናም ሰይጣን ያንን ቀንበጥ እና ራዳት አልባውን ልጅ እንዲቆጣጠር መፍቀድ ትልቁ የጭካኔ ድርጊት ነው፡፡ ሰይጣን መገሰጽ አለበት፡፡ በልጁ ላይ ያለው ተጽዕኖ መሰባበር አለበት፡፡ እርማቱ አስፈላጊ ከሆነ ታማኝ ሁኑ እውነተኛ ሁኑ። የእግዚአብሔር ፍቅር፣ ለልጁ ያለ እውነተኛ ርህራሄ፣ ኃላፊነትን ወደ መወጣት ታማኝነት ይመራል፡፡3The Review and Herald, April 14, 1885.CGAmh 273.1

    የቤተሰብ ማህበረሰብ ግራ መጋባት — በጋብቻ የተሳሰሩ የአንድ፣ የሁለት ወይም የሦስት ቤተሰቦች ልጆችን በጥቂት ማይሎች ርቀት ውስጥ ማስፈር ተመራጭ መመሪያ አይደለም፡፡ በተጋቢዎቹ ላይ የሚያርፈው ተጽዕኖ ጥሩ አይደለም፡፡ የአንዱ ሥራ የሁሉም ሥራ ነው፡፡ ይበልጥም ይነስ እያንዳንዱን ቤተሰብ የሚገጥመው ግራ መጋባቶችና ችግሮች እንዲሁም በተቻለ መጠን በቤተሰብ ክልል ውስጥ ተወስኖ መቅረት ያለበት፣ ለቤተሰብ ግንኙነቶች ይገለጥ እና በሃይማኖታዊ ስብሰባዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ይሆናል፡፡ ምንም ያህል የሚገግባቡ እና የቅርብ ጓደኛ ቢሆኑም እንኳን ለሦስተኛ ሰው መታወቅ የሌለባቸው ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚያን ጉዳዮች ግለሰቦች እና ቤተሰቦች ይሸከሙ፡፡ ነገር ግን የዘወትር ግንኙነትን የፈጠረ የብዙ ቤተሰቦች የቅርብ ግንኙነት በእያንዳንዱ ቤተሰብ ውስጥ ሊጠበቅበት የሚገባውን ክብር የማፍረስ ዝንባሌ አለው፡፡ አጅግ ከባድ ጥንቃቄ የሚሻውን የተግሣጽ እና የምክር ተግባርን በምናከናውንበት ጊዜ በታላቅ ርህራሄ እና ጥንቃቄ በቀር ስሜቶችን የመጉዳት አደጋ አለው፡፡ ምርጥ የተባሉ የባህሪይ ሞዴሎች ለስህተቶች እና ለጉድለቶች ተጋላጭ ናቸው፣ እና በትናንሽ ነገሮች ብዙ ጉዳዮች እንዳይጠፉ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ አለበት።CGAmh 273.2

    እንዲህ ዓይነቱ የቤተሰብ እና የቤተክርስቲያን ግንኙነት… ለተፈጥሮአዊ ስሜቶች እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፤ ነገር ግን ሁሉ ነገር ከግንዛቤ ውስጥ ሲገባ ለሚዛናዊ የክርስቲያን ባህሪይ ዕድገት እጅግ የተሻለ አይደለም፡፡ ተለያይቶ በመቆየት እና አልፎ አልፎ መጎበኛኘቱ ሁሉንም ሰዎች የሚያስደስት ይሆናል፣ አንዱ በሌላው ላይ ያላቸውም ተጽዕኖ በአስር እጥፍ የበለጠ ይሆናል፡፡CGAmh 274.1

    እነዚህ ቤተሰቦች በጋብቻ ሲጣመሩ፣ እና አንዱ ከሌላው ጋር በሕብረት ሲቀላቀል፣ አንዱ የሌላውን ጥፋቶች እና ስህተቶችን ወደ ማወቅ ይመጣል፣ እናም እነዚያን ስህተቶች ለማረም ግዴታ እንዳለባቸው ይሰማቸዋል፤ እነዚህ ዘመዶች በእውነት እርስ በእርስ ስለሚዋደዱም በጣም ቅርብ በሆኑት ሰዎች ላይ በሚያስተውሏቸው ትናንሽ ነገሮች ያዝናሉ፡፡ የሚገባቸውን ነገሮች ሁሉ በማሰብ አንዳንዶች አድልኦ በሌለበት ሁኔታ አልተስተናገድንም የሚል ስሜት ስለሚያነሱ የማያቋርጥ የአእምሮ ሥቃይ ጸንቶ ይቆያል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጥቃቅን ቅናቶች ይነሳሉ፣ እና ፍልፈል የሰራቸው ቁልሎች ተራሮች ይሆናሉ። እነዚህ ትናንሽ አለመግባባቶች እና ጥቃቅን ልዩነቶች ከሌሎች ምንጮች ከሚመጡ መከራዎች ይልቅ በጣም ከባድ የአእምሮን ስቃይ የሚያስከትሉ ይሆናሉ። 565Testimonies For The Church 3:55, 56CGAmh 274.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents