Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 81—የቤት እና ቤተ ክርስቲያን ቅንጅት

    የፀጋ ሥራን ቤት ውስጥ ይጀምሩ— ወላጆች ሆይ ይህንን በማድረጋችሁ ልጆቻችሁ ከሰማያዊ መላእክት ጋር እየተባበራችሁ እንደሆነ እንዲመለከቱ ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለውን የፀጋ ሥራን ከገዛ ቤታችሁ ጀምሩ። በየቀኑ እየተለወጣችሁ እንደሆነ እርግጠኞች ሁኑ፡፡ ራሳችሁን እና ልጆቻችሁን በእግዚአብሔር መንግሥት ውስጥ ለዘላለም ሕይወት አሰልጥኗቸው፡፡ መላእክት ጠንካራ ረዳቶቻችሁ ይሆናሉ፡፡ ሰይጣን ይፈትናችኋል፣ ሆኖም ግን አትሸነፉ፡፡ ጠላት እንደ ዕድል ሊጠቀምበት የሚችልበትን አንድ ቃል አትናገሩ፡፡CGAmh 524.1

    እውነት ንፁህ እና ያልተበከለ ነው፡፡ እርሱ በልባችሁ ውስጥ ይኑር፡፡ የእያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ቁርጠኝነት “እኔ ክርስቲያን እሆናለሁ፣ ምክንያቱም እዚህ ታች ባለው ትምህርት ቤት ውስጥ በመንግሥተ ሰማይ ውስጥ ወደ ከፍተኛው ክፍል እንድገባ የሚያስችለኝን ባህሪይ መፍጠር አለብኝ። ወደ ሰማይ መግባት የሚችሉት በዚህ ዓለም ውስጥ ክርስቶስን የሚያንጸባርቁ ብቻ ስለሆነ ሌሎች እንዲያደርጉልኝ የምፈልገውን እኔም ለሌሎች ማድረግ አለብኝ፡፡” CGAmh 524.2

    የቤትን ሕይወት በተቻለ መጠን ልክ እንደ ሰማይ ቤት አድርጉት፡፡ የቤተሰብ አባላት በቤተሰብ መሰውያ ዙሪያ ሲሰበሰቡ በእግዚአብሔር ሥራ በኃላፊነት ላይ ላሉት ሰዎች መጸለይን አይርሱ፡፡ 1100Manuscript Releases 9:3, 1901.CGAmh 524.3

    ቤተሰቦቻቸውን በትክክለኛው መንገድ የሚያስተዳድሩ ሰዎች የሥርዓት እና የአክብሮት ተጽዕኖን ወደ ቤተክርስቲያን ያመጣሉ፡፡ እነርሱ እጅ ለእጅ በመያያዝ የምህረት እና የፍትህ ባህሪያትን ወክለው ይቆማሉ። የክርስቶስን ባሕርይ ለልጆቻቸው ይገልጣሉ፡፡ በከንፈሮቻቸው ላይ ያለው የርህራሄ እና የፍቅር ሕግ ትዕዛዛቸውን ደካማ እና ስልጣን አልባ አያደርጋቸውም፣ ትዕዛዛቸውም ተቀባይነት ሳያገኙ አይቀሩም፡፡ 1101The Review and Herald, February 19, 1895.CGAmh 524.4

    ሞዴል ቤቶች ሞዴል ቤተክርስትያን ይፈጥራሉ— እያንዳንዱ ቤተሰብ ወላጆቹ የሚመሩበት ቤተክርስቲያን ነው፡፡ ወላጆች መጀመሪያ ከግምት ውስጥ ማስገባት ያለባቸው ነገር ለልጆቻቸው መዳን መሥራት መሆን አለበት፡፡ አባት እና እናት የቤተሰቡ ካህን እና አስተማሪ ሆነው በክርስቶስ ጎን ሙሉ በሙሉ አቋማቸውን ሲያደርጉ ቤት ውስጥ ጥሩ ተጽዕኖ ያርፋል፡፡ ደግሞም ይህ የተቀደሰ ተጽዕኖ ቤተክርስቲያንን ይነካል፣ በእያንዳንዱ አማኝ ዘንድም የተዋቀ ይሆናል። ቤት ውስጥ ካለ ታላቅ የኃይማኖተኝነት እና የቅድስና ጉድለት ሳቢያ የእግዚአብሔር ሥራ በጣም ተደናቅፏል። ማንም ሰው በቤት ውስጥ ህይወት እና በንግድ ግንኙነቱ ላይ ማሳረፍ የማይችለውን ተጽዕኖ ወደ ቤተክርስቲያን ማምጣት አይችልም፡፡ 1102Manuscript Releases 5:7, 1903.CGAmh 525.1

    ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ሥነ ምግባር ቤት ውስጥ ይለመዳል— ቤት ሁሉም በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዴት መሆን እንዳለባቸው የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነው። ሁሉም የንጉሣዊ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ በቤት ሕይወት ውስጥ እውነተኛ ጨዋነት ይኖራል፡፡ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለሌላው እያንዳንዱ አባል አስደሳች እንዲሆን ይጥራል። የድነት ወራሾች የሆኑትን የሚያገለግሉ የእግዚአብሔር መላእክት ቤተሰቦቻችሁን የሰማያዊ ቤተሰብ አርአያ ለማድረግ ይረዷችኋል፡፡ በቤት ውስጥ ሰላም ሲኖር፣ ቤተ ክርስቲያንም ሰላም ይሆናል፡፡ ወደ ቤተክርስቲያን የሚመጠው ይህ ውድ ተሞክሮ አንዳችን ለሌላው የርህራሄ ስሜትን የምንፈጥርበት መንገድ ይሆናል፡፡ ጭቅጭቅ ይቆማል። እውነተኛ የክርስቲያን ጨዋነት በቤተክርስቲያን አባላት መካከል ይታያል፡፡ ዓለም ከኢየሱስ ጋር ከነበሩ እና ከእርሱ ከተማሩት እውቀትን ይወስዳል። ሁሉም ምዕመናን ክርስቲያናዊ ሕይወት ቢኖሩ ቤተ ክርስቲያኒቱ በዓለም ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ ታሳድራለች!4Manuscript Releases 6:0.1903.CGAmh 525.2

    ቤተክርስቲያን ውስጥ ድክመት ያለበት ምክንያት— ብዙዎች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለው ማሽቆልቆል፣ እየጨመረ የመጣው የተድላ ፍቅር ከቅስና ሥራ መመንመን የተነሳ ነው ብለው የሚያስቡ ይመስላል። እውነት ነው፣ ቤተክርስቲያን ታማኝ መሪዎችን እና ፓስተሮችን ልታገኝ ይገባታል፡፡ አገልጋዮች ራሳቸውን ለክርስቶስ ላልሰጡት ወጣቶች እና እንዲሁም ስማቸው በቤተክርስቲያን መዝገብ ላይ ቢሰፍርም እንኳ ኃይማኖተኞች ላልሆኑ እና ክርስቶስ የለሽ ለሆኑ ወጣቶች በትጋት መሥራት አለባቸው፡፡ አገልጋዮች ሥራቸውን በታማኝነት እና በጥሩ ሁኔታ ሊሠሩ ይችላሉ፣ ሆኖም ወላጆች ሥራቸውን ችላ ካሉ በጣም እምንት ይሆናል። ቤት ሕይወት ውስጥ ያለው የክርስትና እጦት ነው ቤተክርስቲያን ውስጥ ላለው የኃይል ጉድለት ምክንያት የሆነው፡፡ ወላጆች ሥራቸውን እስኪሰሩ ድረስ ወጣቱን ለኃላፊነት ስሜት ለመቀስቀስ ይከብዳል፡፡ ኃይማኖት ቤት ውስጥ ከነገሰ ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣል፡፡ ለእግዚአብሔር ሲሉ ሥራቸውን የሚሰሩ ወላጆች ለመልካም ነገር ኃይል ናቸው፡፡ በጌታ እንክብካቤ እና ተግሳጽ እያሳደጓቸው፣ ልጆቻቸውን ሲገድቡ እና ሲያበረታቱ የሚኖሩ ጎረቤትን ይባርካሉ፡፡ እንዲሁም ቤተክርስቲያኗ በታማኝ ስራቸው ትጠናክራለች፡፡ 1103The Signs of the Times, April 3, 1901.CGAmh 525.3

    ቸልተኛ ወላጆች ቤተክርስቲያንን ከፍ ማድረግ አይችሉም— በቤት ውስጥ ሕይወት አለመታዘዝ ከነገሰ፣ የልጆች ልብ የእግዚአብሔርን መንግሥት በመቃወም ይሞላል። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ልባቸውን ለማለዘብ እና ለማስገዛት ውጤታማ እንዳልሆነ ይረጋግጣል፡፡ በኋለኞቹ ዓመታት በልዩ ሁኔታዎች ለክርስቶስ ወንጌል እጅ ከሰጡ፣ ታማኝነት ያሌላቸውን ፈቀድ ወደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለማምጣት አስፈሪ ጦርነቶችን መዋጋት ይኖርባቸዋል። ብዙውን ጊዜ አባላት በልጅነታቸው በተቀበሉት የተሳሳተ ትምህርት ሳቢያ ቤተክርስቲያን መከራ ትቀበላለች፡፡ ልጆች ሆነው ሳሉ የራሳቸውን መንገድ ለመከተል አታላይነትን ይለማመዱ ነበር፤ እናም ቤት ውስጥ ዓመፀኛ እንዲሆን የተፈቀደለት መንፈስ የእግዚአብሔርን ቃል መስፈርቶች ለመታዘዝ የመጨረሻው ይሆናል፡፡ 1104The Review and Herald, March 30, 1897.CGAmh 526.1

    መንፈሳዊነት በትችት ሊሞት ይችላል— ክፉ ቃላትን ለመናገር በምትፈተኑበት ጊዜ፣ ፈተናውን ለመቋቋም ጸጋ ለማግኘት ጸልዩ፡፡ ልጆቻችሁ እናንተ ስትናገሩ የሚሰሙትን እንደሚናገሩ አስታውሱ፡፡ በምሳሌያችሁ እያስተማራችኋቸው ነው፡፡ ለቤተክርስቲያን አባላት ክፉ ቃላትን የምትናገሩ ከሆነ ወደ ሰማይ ቤት እንድትገቡ ቢፈቀድላችሁ ተመሳሳይ ዓይነት ቃላትን እንደምትናገሩ አስታውሱ…፡፡ CGAmh 526.2

    ቤተክርስቲያን የሚመጣው ከቤተሰብ ቀጥሎ ነው፡፡ የቤተሰብ ተጽዕኖ ቤተ ክርስቲያንን የሚያግዝ እና በረከት የሚሆን አይነት መሆን አለበት፡፡ በጭራሽ የቅሬታ ወይም የስህተት ፍለጋ ቃል አትናገሩ፡፡ የሀሜት መንፈስ እንዲገባ ስለተፈቀደ መንፈሳዊነታቸው የሞተባቸው አብያተ ክርስቲያናት አሉ፡፡ ለምን የወቀሳ እና የውግዘት ቃላት እንናገራለን? ዝምታ ለእናንተ ክፉ እና ሥርዓት የጎደለው ንግግር ለሚናገራችሁ ሰው መስጠት የሚችሉት እጅግ ጠንካራ ወቀሳ ነው፡፡ ፍጹም ዝምታ ይኑራችሁ፡፡ ብዙ ጊዜ ዝም ማለት አንደበተ ርቱዕነት ነው፡፡7Manuscript Releases 21:1903.CGAmh 527.1

    ላልታደሉ ወጣቶች ጥንቃቄ ማድረግ— በቤት ውስጥ ተጽዕኖ ሥር ያልሆኑ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች አንድ የሚጠነቀቅላቸው እና በእነርሱ ላይ ፍላጎት እንዳለው የሚያሳያቸው ሰው ይፈልጋሉ፤ በመድረክ ላይ እንደ ሚያገለግለው አገልጋይ ሁሉ ይህን የሚያደርጉ ደግሞ እጅግ ትልቁን ክፍተት እየሞሉ በእርግጥም ለእግዚአብሄር እና የነፍስ ማዳን ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ይህ ለወጣቶች ጥቅም ሲባል አድልኦ የሌለበት የቸርነት ሥራ እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን ከሚፈልገው በላይ የሆነ አይደለም፡፡ ልምድ ያለው ክርስቲያን በማይጠፋ አይነት ሁኔታ ባህሪይን የሚያጎድፉ ልማዶች እንዳይፈጠሩ ለመከላከል ምን ያህል ከልብ ሊሠራ ይገባል! የክርስቶስ ተከታዮች የእግዚአብሔርን ቃል ለወጣቶች ማራኪ ያድርጓቸው፡፡ 1105Fundamentals of Christian Education, 51CGAmh 527.2

    አገልጋዩ ልዩ እድል አለው— በእያንዳንዱ ምቹ አጋጣሚ የኢየሱስ ፍቅር ታሪክ ለልጆች ተደጋግሞ ይነገራቸው፡፡ በእያንዳንዱ ስብከት ላይ እነርሱን የሚጠቅም ትንሽ ሥፍራ አስቀሩላቸው፡፡ የክርስቶስ አገልጋይ ከእነዚህ ከታናናሾቹ ዘላቂ ጓደኞች ሊያገኝ ይችላል። ከዚያም በቅዱሳን ጽሑፎች እውቀት የበለጠ አስተዋዮች እንዲሆኑ ለመርዳት ምንም አጋጣሚ እንዳያጠፋ። ይህ የሰይጣን ዘዴዎች ላይ መንገድ ለመዝጋት ከምንገነዘበው በላይ ይሰራል፡፡ ልጆች ከእግዚአብሔር ቃል እውነቶች ጋር በደንብ ቢተዋወቁ ኖሮ ክፋትን የሚገታ መሰናክል ይቆም ነበር፣ ደግሞም “ተፃፏል” በሚል ቃል ጠላትን መግጠም ይችላሉ። 11066 Gospel Workers, 208.CGAmh 527.3

    አምልኮ ላይ እንደሚሆነው ሁሉ ቤት ውስጥም ታማኞች ሁኑ— ወላጆች ሆይ፣ ለውዶቻችሁ አስተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን በቃል እና በተግባርን በመመራት በሕሊናችሁ እና በአስተሳሰባችሁ ላይ የመቆጣጠር ኃይል ሊኖራቸው ይገባል፡፡ በእግዚአብሔር አምልኮ ላይ እንደሚሆነው ሁሉ በቤታችሁም ሕይወት ላይም ታማኞች ሁኑ፡፡ ቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ ትክክለኛ ባህሪይ አሳዩአቸው፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት የጌታ ቤተሰብ ተናናሽ አባላት እንዴት እንደሚያዙ ለመመዝገብ ይገኛሉ፡፡ የቤት ውስጥ ኃይማኖት በእርግጠኝነት ወደ ቤተክርስቲያን ይመጣል፡፡ 1107Manuscript Releases 8:4, 1897.CGAmh 528.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents