Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል 7—የክርስቲያን ባህሪያትን ማጎልበት

    ምዕራፍ 25—ቀላል የአኗኗር ዘይቤ

    የተፈጥሮ ቀላልነትን ይማሩ—ትናንሽ ልጆች የልጅነት ቀላልነትን መማር አለባቸው፡፡ በትናንሽ፣ አጋዥ ሥራዎች እና ለእድሜዎቻቸው የሚመጥኑ ደስታ እና ልምዶች እንዲረኩ ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ በምሳሌው ውስጥ ልጅነት ለቡቃያ መልስ ይሰጣል፣ ቡቃያውም በራሱ የራሱ የሆነ ውበት አለው። ልጆች ያለዕድሜያቸው ወደ ብስለት እንዲደርሱ መገደድ የለባቸውም፣ ነገር ግን በተቻለ መጠን የልጅነታቸውን ዕድሜ ንጽህና እና ፀጋ ሊኖራቸው ይገባል። የልጅ ሕይወት ይበልጥ የተረጋጋ እና ቀላል በሆነ ቁጥር— ከሰው ሰራሽ ደስታ የነጻ እና ከተፈጥሮ ጋር ይበልጥ በተጣመረ ቁጥር— ለአካላዊ እና ለአእምሮ ጥንካሬ እና ለመንፈሳዊ ጥንካሬ ይበልጥ ምቹ ይሆናል።239Education, 107 CGAmh 131.1

    ወላጆች በምሳሌነት ቀላል የኑሮ ዘይቤን የመቅረጽ ልምዶችን ማበረታታት እና ልጆቻቸውን ከሰው ሠራሽ ወደ ተፈጥሮአዊ ህይወት እንዲሳቡ ማድረግ አለባቸው። 240The Signs of the Times, October 2, 1884.CGAmh 131.2

    ሰው ሰራሽ ውበት የሌላቸው ሕፃናት እጅግ ማራኪ ናቸው—እነዚያ ተፈጥሮአዊ የሆኑ እና ሰው ሰራሽ ውበት የሌላቸው ልጆች በጣም ማራኪ ናቸው፡፡ ለልጆች ትኩረት መስጠት ብልህነት አይደለም…፡፡ መልኮቻቸውን፣ ቃሎቻቸውን ወይም ድርጊቶቻቸውን በማወደስ ከንቱነት መበረታታት የለበትም፡፡ እንዲሁም ውድ እና ታይታ በበዛበት መንገድ መልበስ የለባቸውም። ይህ በእነርሱ ውስጥ ኩራትን ያበረታታል፣ በባልደረባዎቻቸውም ልብ ውስጥ ቅናትን ያስነሳል። እውነተኛው ውበት ውጫዊ እንዳልሆነ ልጆችን አስተምሯቸው፡፡ “ለእናንተም ጸጉርን በመሸረብና ወርቅን በማንጠልጠል ወይም ልብስን በመጎናጸፍ በውጭ የሆነ ሽልማት አይሁንላችሁ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ዋጋው እጅግ የከበረ የዋህና ዝግተኛ መንፈስ ያለውን የማይጠፋውን ልብስ ለብሶ የተሰወረ የልብ ሰው ይሁንላችሁ፡፡”-1 ጴጥሮስ 3፡3፣4፡፡ 241Counsels to Parents, Teachers, and Students, 141, 142.CGAmh 131.3

    የእውነተኛ ውበት ምስጢር—የሴትነት እውነተኛ ውበት ቁንጅና ወይም መልከ መልካምነት ወይም የተግባራት አፈጻጸም ባለቤት መሆን ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን በትህትና ዝግ ባለ መንፈስ፣ በትዕግሥት፣ በለጋስነት፣ በደግነት፣ እና ለሌሎች ለመስራት እና ለመቸገር ፈቃደኛ በመሆን እንደሆነ ሴት ልጆች መማር አለባቸው። እነርሱ መሥራትን፣ ለአንድ ግብ ማጥናትን፣ ለአንድ ዓላማ መኖርን፣ በእግዚአብሔር ለመታመን እና እርሱን ለመፍራት እና ወላጆቻቸውን ማክበርን መማር አለባቸው፡፡ ከዚያም ዕድሜያቸው እየጨመረ ሲሄድ፣ ይበልጥ ንጹህ አስተሳሰብ ያላቸው፣ በራስ መተማመን ያላቸው እና የተወደዱ ሆነው ያድጋሉ፡፡ እንዲህ ዓይነቷን ሴት ማዋረድ የማይቻል ነው፡፡ ለብዙዎች ጥፋት የሆኑትን ፈተናዎች ታመልጣለች። 242 Health Reformer, December, 1877.CGAmh 132.1

    የከንቱነት ዘሮች—በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ በልጆች ልቦች ውስጥ የከንቱነት እና የራስ ወዳድነት ዘሮች ገና በልጅነታቸው ጊዜ ይዘራሉ። ተንኮል የተሞላባቸው ትናንሽ አባባሎቻቸው እና ድርጊቶቻቸው በእነርሱ ፊት ይነገራሉ፣ ይወደሳሉም እንዲሁም በሌሎች ሰዎች በግነት ይደጋገማሉ፡፡ ትናንሽ ልጆች ይህንን በማስተዋል በኩራት ያብጣሉ፤ ንግግሮችን ማቋረጥ እንዳለባቸው ያስባሉ፣ አይን አውጣና ባለጌዎችም ይሆናሉ። ትንሽ ልጅ አባትና እናትን ጨምሮ መላውን ቤተሰብ እስኪያስተዳድር ድረስ ከንቱ ውዳሴ እና ቁልምጫ ከንቱነታቸውን እና ችኮነታቸውን ያሳድጋሉ። CGAmh 132.2

    በእንደዚህ ዓይነቱ ሥልጠና የተፈጠረው ባህሪይ ልጁ ባሳል ወደ ሆነ ፍርድ ሲያድግም ሊጠፋ አይችልም፡፡ ከእድገቱ ጋር ያድጋል፣ እና በህፃኑ እይታ ብልህነት ይመስል የነበረው፣ በጎልማሳ ወንድ ወይም ሴት እይታ አስጸያፊ እና ክፉ ይሆናል። በጓደኞቻቸውም ላይ በበላይነት መግዛት ይሻሉ፤ ማንም ለፍላጎታቸው ለመገዛት ፈቃደኛ ካልሆነ ግን ቅር እንደተሰኙና እንደ ተዘለፉ ይቆጠራሉ። ይህ የሆነበት ምክንያት የህይወት መከራዎችን እና ሸክሞችን ለመሸከም አስፈላጊ የሆነውን ራስን መካድ ከመማር ይልቅ በወጣትነታቸው ላይ ሲደርስባቸው ለነበረው ጉዳት ስለተሞላቀቁ ነው፡፡ 243Testimonies For The Church 4:200, 201.CGAmh 132.3

    ውዳሴን መውደድን አያበረታቱ—ልጆች አድናቆት፣ ርህራሄ እና ማበረታቻ ያስፈልጋቸዋል፤ ነገር ግን በእነርሱ ውስጥ ውዳሴ መውደድን ላለማሳደግ ጥንቃቄ መደረግ አለበት…፡፡ የእውነተኛ ባህሪይ ፍጹምነት እና የስኬት እድሎችን የሚመለከት ወላጅ ወይም አስተማሪ ለራስ ብቃት ከፍተኛ ዋጋ ወይም ማበረታቻ መስጠት አይችልም። በወጣቶች ውስጥ ችሎታቸውን ወይም ብቃታቸውን ለማሳየት ያላቸውን ፍላጎት ወይም ጥረት አይበረታታም፡፡ ከራሱ በላይ ከፍ አድርጎ የሚመለከት ትሑት ይሆናል፣ ነገር ግን በውጫዊ ታይታ ወይም በሰብአዊ ሰው ታላቅነት የማይፈራ ወይም የማይሸበር ክብር ያገኛል። 244Education, 237.CGAmh 133.1

    በአመጋገብ እና በአለባበስ ቀላል የአኗኗር ዘይቤን ማበረታታት—ወላጆች ልጆቻቸውን በቤት ውስጥ ሸክሞችን እንዲሸከሙ፣ በንጹህ እና በቀላል ምግብ እንዲረኩ፣ እና ግሩም እና ውድ ያልሆነ አለባበስ እንዲኖራቸው በማስተማር ረገድ የተቀደሰ ተግባር አላቸው። 245Counsels to Parents, Teachers, and Students, 158. CGAmh 133.2

    ምነው እናቶች እና አባቶች በእግዚአብሔር ፊት ኃላፊነታቸውን እና ተጠያቂነታቸውን በተገነዘቡ! በሕብረተሰቡ ውስጥ እንዴት ያለ ለውጥ በመጣ ነበር! ልጆች በሙገሳና በቁልምጫ አይበላሹም ወይም የአለባበስ ፍላጎትን በማርካት ከንቱ አይሆኑም ነበር።246The Review and Herald, April 13, 1897. CGAmh 133.3

    ቀላል የአኗናር ዘይቤን እና መታመንን ያስተምሩ—ለልጆቻችን ቀላል የአኗኗር ዘይቤን እና የመታመን ትምህርቶችን ማስተማር አለብን። ፈጣሪያቸውን እንዲወዱት፣ እንዲፍሩት እና እንዲታዘዙት ሊናስተምራቸው ይገባል። በሕይወት ዕቅዶች እና ዓላማዎች ሁሉ ውስጥ የእርሱ ክብር ከፍ ተደርጎ መያዝ አለበት፣ የእርሱ ፍቅር የእያንዳንዱ ተግባር ዋና ምንጭ መሆን አለበት።9The Review and Herald, June 13, 1882.CGAmh 133.4

    ምሳሌያችን የሆነው ክርስቶስ—ቤዛችን የሆነው ኢየሱስ በምድር ላይ በንጉስነት ክብር ተመላለሰ፣ ሆኖም ግን በልቡ ገር እና ትሑት ነበር፡፡ እርሱ ደስታ፣ ተስፋ እና ማበረታቻ ስለ ነበረው በእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ብርሃን እና በረከት ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከዕንቁዎች በላይ ከፍ አድርጎ የሚመለከታቸው፣ የዋህ እና የረጋ መንፈስ ዋጋ ሳይሰጣቸው፣ ባነሰ የልብ-ናፍቆት፣ ለማግኘት አስቸጋሪ በሆኑ የቤታችን ማስዋቢያ ነገሮች ከመታገል በመቆጠብ ረክተን ቢሆን ኖሮ ምን አለበት፡፡ የቀላል አኗኗር ዘይቤ፣ የዋህነት እና የእውነት ፍቅር ጸጋ ኤደን ገነትን ትሁት ቤት ያደርጋታል። በሰላም እና በእርካታ ጮቤ ከመርገጥ ይልቅ እያንዳንዱን ችግር በደስታ መታገሱ ይሻላል። 247Testimonies For The Church 4:622.CGAmh 134.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents