Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የልጅ አመራር

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 7—ከተፈጥሮ መጽሐፍ የሚገኙ ተግባራዊ ትምህርቶች

    በእጅ ሥራው ውስጥ ያለ የእግዚአብሔር ድምጽ— ወዴትም ብንዞር የእግዚአብሔርን ድምጽ እንሰማለን፣ የእጅ ሥራውንም እንመለከታለን፡፡ በከፍተኛ ድምጽ ከሚያስተጋባው ባለ ግርማ መብረቅ እና ሳያቋርጥ ከሚያጓራው እድሜ ጠገብ ውቅያኖስ፣ በደስታ መዝሙር ጣእመ ዜማን እስከሚፈጥሩ የዱር ድምጾች ድረስ፣ በአሥር ሺህ የሚቆጠሩ የተፈጥሮ ድምጾች ምስጋናውን ይናገራሉ፡፡ በሚያስገርም ቅልም እና ቀለማቸው ውስጥ በውበታቸው ንጽጽር የተለያዩ ወይም በውህደታቸው የተቀላቀሉ፣ በምድር፣ በሐይቅ እና በሰማይ ውስጥ ክብሩን አየን፡፡ የዘላለም ኮረብታዎች ኃይሉን ይናገራሉ፡፡ አረንጓዴ ሰንደቃቸውን በጸሐይ ብርሃን ውስጥ የሚያውለበልቡ ዛፎች፣ እና በሚያሳሳ ውበታቸው አበቦች ወደ ፈጣሪያቸው ያመለክታሉ፡፡ ቡናማውን መሬት የሸፈኑ ሕያው አረንጓዴዎች እግዚአብሔር እጅግ ዝቅተኛ ለሆነው ፍጥረት ጥንቃቄ እንደሚያደርግ ይናገራሉ፡፡ የባሕር ዋሻዎች እና የምድር ጥልቀቶች የእርሱን መዝገቦች ይገልጣሉ፡፡ እንቁን ውቅያኖስ ውስጥ እና አሜቴስጢኖስን እና ክርስቲሎቤን ድንጋዮች መካከል ያስቀመጠው እርሱ የውበት አፍቃሪ ነው፡፡ በሰማያት ላይ የምትወጣው ጸሐይ ለፈጠራቸው ሁሉ ሕይወትና ብርሃን የሆነው የእርሱ ምሳሌ ናት፡፡ ምድርን ያጌጠ እና ሰማያትን የሚያበራ ድምቀትና ውበት ስለ እግዚአብሔር ይናገራል፡፡ CGAmh 51.1

    ስለዚህ በሥጦታዎቹን እየተደሰትን ሰጭውን እንርሳን? ይልቁንስ መልካምነቱን እና ፍቅሩን እናሰላስል ዘንድ ይምሩን፡፡ በምድራዊ ቤታችን ውስጥ ውብ የሆኑ ሁሉ ስለ መስታወቱ ወንዝ እና አረንጓዴው መስኮች፣ ስለሚወዛወዙ ዛፎችና ሕያው ምንጮች፣ ስለሚያብረቀርቀው ከተማ እና ነጭ ለባሽ መዘምራን፣ አንድም አርቲስት መሳል እና ሟች ምላስ መግለጽ ስለማይችለው ስለ ሰማያዊው ቤታችን ያስታውሰን፡፡ “ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው፡፡” 1 ቆሮ 2፡9፡፡ 74Counsels to Parents, Teachers, and Students, 54, 55.CGAmh 51.2

    ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ባሕርይ— እናት… የእግዚአብሔር ታላቁ መጽሐፍ ከሆነው ተፈጥሮ ልጆቿን ለማስተማር፣ ጨቅላ አዕምሮአቸውን በሚፈኩ ውብ ቀንበጦችና አበቦች ለማስገረም ጊዜ እስክታጣ ድረስ በሰው-ሰራሽ ነገሮች መመሰጥ እና በኑሮ ጫና ሥር መሆን የለባትም፡፡ እጅግ ረጃጅሞቹ ዛፎች፣ ተወዳጆቹ ወፎች የደስታ መዝመሮቻቸውን ለፈጣሪያቸው ሲያዜሙ፣ የእግዚአብሔርን መልካምነት፣ ምህረቱን፣ እና ለጋሽነቱን ለስሜቶቻቸው ይናገራሉ፡፡ ልዩ ልዩ ቀለም ያላቸው ቅጠሎችና አበቦች አየሩን በማወድ፣ እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነ ያስተምሯቸዋል፡፡ በዚህ ዓለም ላይ መልካምና ተወዳጅ እንዲሁም ውብ የሆኑ ነገሮች ሁሉ የሰማዩ አባታችንን ፍቅር ይነግሯቸዋል፡፡ በተፈጥሮ ሥራዎቹ ውስጥ የእግዚአብሔርን ባሕርይ ይረዳሉ፡፡ 75The Signs of the Times, August 5, 1879. CGAmh 52.1

    ስለ እግዚአብሔር ፍጽምና— ተፈጥሮዎች ምድርን ለማስዋብ እና የእግዚአብሔርን ፍጽምና ለመግለጽ የተቻላቸውን በማድረግ ለዋናው ሰራተኛ አድናቆታቸውን ሲያሳዩ፣ የሰው ልጆችም በአድማሱ የፍትህ፣ የምህረት፣ እና የመልካምነት ዓለማውን በእነርሱ አማካይነት እንዲያከናውን በመፍቀድ፣ የእግዚአብሔርን ፍጽምና ለመግለጽ እንዲሁ መጣር አለባቸው፡፡3Letter 47, 1903.CGAmh 52.2

    የፈጣሪና የሰንበት— ምድር እንድታበቅልና እንድታፈራ የጸሐይ ብርሃንን የሚሰጥ ማነው? ፍሬያማውስ ዝናብ የማነው? በላይ በሰማያት ፀሐይን እና በሰማያት ውስጥም ከዋክብትን የሰጠን ማነው? የማሰብ ችሎታን የሰጠህ ማነው፣ ከቀን ወደ ቀን የሚጠብቅህ ማነው? … ወደ ዓለም በምንመለከትበት ጊዜ ሁሉ፣ ወደ መኖር የመጣችበትን ታላቁን እጅ ያስታውሰናል፡፡ በራሳችን ላይ ያለ ጥላ፣ በታች በአረንጓዴ ምንጣፍ የተሸፈነው ምድር፣CGAmh 52.3

    የእግዚአብሔርን ኃይልና የፍቅሩን ርህራሄ ወደ ትውስታችን ያመጠል፡፡ ሣርን ቡናማ ወይም ጥቁር አድርጎ መፍጠር ይችል ነበር፣ ነገር ግን እግዚአብሔር የውበት አፍቃሪ ነው፣ ስለዚህም እንመለከታቸው ዘንድ ውብ ነገሮችን ሰጠን፡፡ እግዚአብሔር አበቦች ላይ በስሱ ያለበሰውን ብስክስኩን ቀለም ማን መቀለም ይችላል? …CGAmh 53.1

    ከተፈጥሮ የተሻለ የመማርያ መጽሐፍ ሊኖረን አይችልም፡፡ “የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ …አይደክሙም አይፈትሉምም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፣ ሰለሞንስ እንኳ በክብሩ ሁሉ ከእነዚህ እንደ አንዱ አልለበሰም፡፡” የልጆቻችን አእምሮዎች ወደ ላይ ወደ እግዚአብሔር ይወሰድ፡፡ የሰባተኛውን ቀን የሰጠን እና የፍጥረቱ ሥራዎች መታሰቢያ አድርጎ የተወልንም ለዚህ ነው፡፡ 76Manuscript Releases 16:1895.CGAmh 53.2

    ለሕግ መታዘዝ— በተፈጥሮ ውስጥ እየሰራ ያለው ኃይል ራሱ በሰውም ውስጥ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ኮከብና አቶምን የሚመራ ታላቅ ሕግ ራሱ የሰብአዊውን ሕይወት ይቆጣጠራል፡፡ የሕይወትን ጅረት ፍሰት በማስተካከል፣ የልብን ተግባር የሚቆጣጠሩ ሕግጋት፣ ነፍስ ላይ ሥልጣን ያለው የታላቁ ሊቅ ሕግጋት ናቸው፡፡ ሕይወት ሁሉ የሚመነጨው ከእርሱ ነው፡፡ የእውነተኛ ትግበራ ክልል ሊገኝ የሚችለው ከእርሱ ጋር በማበር ብቻ ነው፡፡ የፍጥረቱ ሥራ ለሆኑት ሁሉ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው — ማለትም ሕይወትን ከእግዚአብሔር በመቀበል የምትኖር ሕይወት፣ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር በማበር የምትንቀሳቀስ ሕይወት፡፡ የአካል፣ የአዕምሮ፣ ወይም የግብረ-ገብ ሕግን መተላለፍ — አለመስማማትን፣ ሕግ አልባነት፣ ጥፋትን ማስተዋወቅ፣ ራስን ከዩኒቨርስ እብረት ውጭ ማድረግ ማለት ነው፡፡ CGAmh 53.3

    የእርሷን ትምህርት ለመተርጎም በዚህ መልኩ ለሚማር ሰው፣ ተፈጥሮ ሁሉ የተብራራ ይሆንለታል፤ ዓለም የመማሪያ መጽሐፍ፣ ሕይወትም ትምህርት ቤት ናት፡፡ ሰው ከተፈጥሮና ከእግዚአብሔር ጋር ያለው አንድነት፣ ዓለም አቀፋዊ የሕግ የበላይነት፣ የመተላለፍ ውጤቶች፣ አዕምሮን ማስደነቅ እና ባህርይን መቅረጽ አያቅታቸውም፡፡ እነዚህ ልጆቻችን መማር ያለባቸው ትምህርቶች ናቸው፡፡ 77Education, 99, 100. CGAmh 53.4

    ሌሎች ትምህርቶች ከተፈጥሮ ሕጎች—አሳቢ ሰራተኛ በእርሻ ውስጥ ያላለማቸው መዝገቦችን በፊቱ ተከፍተው ያገኛቸዋል፡፡ ማንም ሰው በውስጡ የተካተቱ ሕጎች ላይ ትኩረት ሳያደርግ በእርሻ ወይም በአትክልት ሥራ ስኬትን ማግኘት አይችልም፡፡ የእያንዳንዱ ተክል ዝርያ ልዩ ፍላጎት መጠናት አለበት፡፡ የተለያዩ ዝርያዎች የተለያዩ አፈር እና እንክብካቤ ይፈልጋሉ፣ እናም እያንዳንዱን የሚገዛ ሕጎችን ማክበር የስኬት መሠረት ነው፡፡ CGAmh 54.1

    የሥሩ ድር እንኳ እንዳይጨናነቅ ወይም ያለ ቦታው እንዳይሆን ተክልን ከአንድ ሥፍራ ወደ ሌላ ሥፍራ ወስዶ በመትከል ሂደት ውስጥ የሚያስፈልገው ትኩረት፣ ለለጋ ተክሎች የሚደረግ እንክብካቤ፣ ክርከማና ውሃ ማጠጣት፣ ከሌሊቱ ውርጭ እና ከቀኑ ፀሐይ መጋሸቱ፣ አረምን፣ በሽታን እና ተባይ ነፍሳትን ማስወገዱ፣ ማስልጠኑና ማስተካከሉ፣ ከባህርይ እድገት ጋር በተያያዘ ወሳኝ ትምህርትን ማስተማር ብቻም ሳይሆን፣ ነገር ግን ተግባሩ ራሱ የእድገት አንዱ መንገድ ነው፡፡ ጠንቃቃነትን፣ ትዕግስትን፣ ለጥቃቅን ነገሮች ትኩረት መስጠትን፣ ለሕግ መታዘዝን በማሳደግ፣ እጅግ አስፈላጊ ሥልጠናን ይሰጣል፡፡CGAmh 54.2

    ከሕይወት ምስጢራት ጋር ያለ ግንኙነት እና የተፈጥሮ ተወዳጅነት፣ እና እነዚህን የእግዚአብሔር ውብ ፍጥረቶችን በማገልገል ሂደት ውስጥ የሚመጣ ርህራሄ፣ አዕምሮን ወደ መቀስቀስ እና ባህርይን ወደ ማንጻት እና ከፍ ወደ ማድረግ ያዘነብላል፤ እናም ትምህርቱ ሰራተኛው በተሻለ ስኬታማነት ከሌሎች አዕምሮዎች ጋር እንዲሰራ ያዘጋጀዋል፡፡6Ibid.CGAmh 54.3

    ዘርን ከመዝራት የሚገኝ ትምህርት —የዘሪውና የዘሩ ምሳሌ ጥልቅ መንፈሳዊ ትምህርት ያስተላልፋል፡፡ ዘር በልብ ላይ የተዘራውን መርኾዎችን፣ እንዲሁም ዕድገቱ የባህርይን ዕድገት ይወክላል፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ ያለውን ትምህርት ተግባራዊ ያድርጉ፡፡ ልጆች መሬትን በማዘጋጀት ዘር ሊዘሩ ይችላሉ፤ በሚሰሩበትም ጊዜ፣ ወላጆች ወይም መምህራን እዚያው በተዘራው መልካም ወይም ክፉ ዘር አማካይነት፣ ስለ ልብ የአትክልት ቦታ ሊያብራሩላቸው ይችላሉ፤ ለተፈጥሮ ዘር የአትክልት መሬት እንደሚዘጋጅ ሁሉ፣ ልብም ለእውነት ዘር እንዲሁ መዘጋጀት አለበት፡፡ ተክሉ ሲያድግም፣ በተፈጥሮአዊውና በመንፈሳዊው ዘር መካከል ያለው ዝምድና መቀጠል ይችላል፡፡ 78Counsels to Parents, Teachers, and Students, 142.CGAmh 54.4

    ዘሩ መሬት ላይ በተጣለ ጊዜ፣ ስለ ክርስቶስ ሞት፤ ቡቃያውም ሲበቅል፣ የትንሳኤውን እውነት ትምህርት ያስተምራል፡፡ 79Education, 111.CGAmh 55.1

    የልብ የአትክልት ሥፍራ እንክብካቤ ይፈልጋል —አፈርን ከማረስ ዘወትር ትምህረት መማር ይቻላል፡፡ አንድ ሰው እዳሪ መሬት ላይ ሆኖ በአንዴ ምርት ይሰጠኛል ብሎ አይጠብቅም፡፡ መሬትን በማዘጋጀት፣ ዘርን በመዝራት፣ እና ከሰብል ባህርይ ጋር በተያያዘ ትጋት እና ፅናት የተሞላበት ጥረት ይፈልጋል፡፡ በመንፈሳዊ ዘር መዝራትም እንዲሁ መሆን አለበት፡፡ የልብ የአትክልት ሥፍራም እንክብካቤ ማግኘት አለበት፡፡ አፈሩ በንስሃ መሰባበር አለበት፡፡ መልካሙን ዘር አንቆ የያዘ ክፉ ተክል መነቀል አለበት፡፡ መሬቱ አንዴ በእሾህ ከተሞላ በኋላ ትጋት በተሞላበት ጥረት እንደሚስተካከል ሁሉ፣ እንዲሁ የልብ ክፉ ዝንባሌዎችም ድል የሚነሱት ቆራጥነት በተሞላበት ጥረት በክርስቶስ ስምና ብርታት ብቻ ነው፡፡9Ibid.CGAmh 55.2

    በጸጋ ማደግ —ስለ ተዓምር-ሰሪው የእግዚአብሔር ኃይል ለልጆችህ ንገር፡፡ ታላቁን የተፈጥሮ መጽሐፍ በሚያጠኑበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር አዕምሮዎቻቸውን ይማርካል፡፡ ገበሬው መሬቱን ያርስና ዘሩን ይዘራል፣ ነገር ግን ዘሩ እንዲበቅል ማድረግ አይችልም፡፡ እርሱ ማንኛውም የሰው ኃይል እንዲበቅል ማድረግ በማይችለው ነገር ላይ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ ይኖርበታል፡፡ ጌታ ሕይወት ሰጭውን ኃይል ዘሩ ውስጥ በማስቀመጥ፣ ሕይወት ወደ ማግኘት እንዲመጣ ያደርገዋል፡፡ በእርሱ እንክብካቤ ስር በመሆን የሕይወት ጀርም ሸፍኖት የነበረውን ጠንከራውን ቅርፊት በመሰባበር፣ ፍሬ ለማፍራት ይበቅላል፡፡ በመጀመሪያ ቡቃያ ኋላም ዛላ ኋላም ፍፁም ሰብል ታፈራለች፡፡ ልጆች እግዚአብሔር ለዘሩ የሚሰራው ሥራ ሲነጋራቸው፣ በጸጋ ስለ ማደግ ምስጢር ይማራሉ፡፡80Counsels to Parents, Teachers, and Students, 124, 125.CGAmh 55.3

    ዙሪያችንን ከከበቡን ነገሮች በላይ መውጣት —በአሜሪካ ውሃ ውስጥ የሚገኙ ንጹህ አበቦች አሉን፡፡ እነዚህ ውብ አበቦች ንፁህ፣ እንከን የለሽ፣ እና ያለ አንዳች ጉድለት ሆኖ ይበቅላሉ፡፡ የፍርስራሾችን ክምር ሰንጥቀው ይወጣሉ፡፡ እኔም ለልጄ “በተገኘበት የቅርበት መጠን የዚያን አበባ ግንድ እንድታመጣልኝ እፈገልጋለሁ፡፡ ስለ እርሱ አንድ ነገር እንድትረዳ እፈልጋለሁ፡፡” አልሁት፡፡ CGAmh 56.1

    አንድ መዳፍ ሙሉ አበቦችን ሲያመጣ፣ ተመለከትኳቸው፡፡ ሁሉም ክፍት በሆኑ ሰርጦች የተሞሉ ናቸው፣ ግንዶቹም ከአሻዋው ሥር ንጥረ ነገሮችን ይሰበስቡ ነበር፣ እነዚህም ንጹህና እንከን የለሽ አበባ ሆነው እያደጉ ነበር፡፡ ፍርስራሾችን ሁሉ ችላ ብለው ነበር፡፡ እያንዳንዱን አጸያፊ ነገር ችላ ብለው ነበር፣ ነገር ግን እዚያው ወደ ንጽሕናው ያድጋል፡፡ CGAmh 56.2

    በአሁኑ ጊዜ በእርግጥም በዚህች ዓለም ውስጥ ልጆቻችንን የምናስተምርበት መንገድ ይህ ነው፡፡ አዕምሮዎቻቸውና ልቦቻቸው እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፣ የሱስ ክርስቶስ ማን እንደሆነ፣ እና እርሱ በእኛ ፈንታ ስላደረገው መስዋዕትነት መምሪያ ያግኙ፡፡ ንጽህናን፣ ጥሩነትን፣ ጸጋን፣ መልካም ባህርይን፣ ፍቅርን፣ ትዕግስትን ይሳቡ፤ ከኃይል ሁሉ ምንጭ ይሳቡት፡፡11Manuscript Releases 4:268.CGAmh 56.3

    በእምነትና ፅናት ውስጥ ያለ ትምህርት—” አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ፣ ያስተምሩሃል፣ የሰማይንም ወፎች ጠይቅ፣ ይነግሩህማል፡፡ ወይም ለምድር ተናገር፣ እርሷም ታስተምርሃለች፤ የባሕር አሳዎች ይነግሩሃል፡፡” ” ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፣ መንገድዋንም ተመልከት፡፡” “ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከት፡፡” “ቁራዎችን ተመልከቱ፡፡” ኢዮብ 12፡7፣8፤ ምሳሌ 6፡6፤ ማቴዎስ 6፡26፣ የአሜሪካውያን መደበኛ ትርጉም፤ ሉቃስ 12፡24፡፡ CGAmh 56.4

    ለልጁ የምንነግረው ስለ እነዚህ የእግዚአብሔር ፍጥረታት ብቻ አይደለም፡፡ እንስሶቹ ራሳቸውም አስተማሪዎቹ መሆን አለባቸው፡፡ ጉንዳኖች ትዕግስት የተሞላበትን የታታሪነትን፣ እክሎችን በማለፍ ረግድ የትጋትን፣ ለመጻኢ የሚያስፈልገውን የማዘጋጀትን ትምህርቶች ያስተምራሉ፡፡ እንዲሁም ወፍች አስደሳች የሆነ የመታመን ትምህርት አስተማሪዎች ናቸው፡፡ የሰማዩ አባታችን የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል፤ ነገር ግን ምግባቸውን መሰብሰብ አለባቸው፣ ጎጆአቸውን መገንባትና ልጆቻቸውን ማሳደግ አለባቸው፡፡ ሁል ጊዜ ሊያጠፏቸው ለሚፈልጉ ጠላቶች የተጋለጡ ናቸው፡፡ ይሁን እንጂ ለሥራቸው ሲሄዱ እንዴት ደስተኞች ናቸው! አነስ ያለው መዝሙራቸው እንዴት በደስታ የተሞላ ነው! CGAmh 56.5

    እግዚአብሔር ለዱር ፍጥታቱ እንደሚጠነቀቅ ባለ መዝሙሩ እንዴት ውብ በሆነ አገላለጽ ነው ይገልጻል —“ረጃጅም ተራራዎች ለዋላዎች፣ ድንጋዮችም ለእሽኮኮች መሸሻ ናቸው፡፡” መዝሙረ ዳዊት 104፡18፡፡ ወፎች በሚኖሩበትና “በድንጋዩ ስንጥቅ መካከልም በሚጮኹበት፣” ምንጮች በተራሮች መካከል ይፈሱ ዘንድ ይልካቸዋል፣ መዝሙረ ዳዊት 104፡18፡፡ የዱርና የተራሮች ፍጥረታት በሙሉ የታላቁ ቤተሰብ አካል ናቸው፡፡ እርሱም እጁን ይከፍታል “ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ያጠግባል፡፡” [መዝሙረ ዳዊት 145፡16] 81Education, 117, 118.CGAmh 57.1

    ጥቃቅን ነፍሳት ታታሪነትን ያስተምራሉ — ብልህ ሰዎች ከታታሪዋ ንብ ቢቀዱ መልካም ሊያደርጉ የሚችሉበትን ምሳሌ ትሰጣቸዋለች፡፡ እነዚህ ጥቃቅን ነፍሳት ፍጹም ሥርዓትን ይከተላሉ፣ እንዲሁም አንድም ሥራ ፈት ሆኖ ቀፎው ውስጥ እንዲቀመጥ አይፈቀድለትም፡፡ የተሰጣቸውን ተግባር ከእኛ መረዳት በላይ በብልኃት እና በገቢርነት ይፈጽማሉ፡፡ ብልኁ ሰው ትከረታችንን ወደ የምድር ጥቃቅን ነፍሳት ይስባል፡ “አንተ ታካች ወደ ገብረ ጉነዳን ሂድ፣ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን፡፡ አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት፣ መብልዋን በበጋ ታሰናዳለች፣ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች፡፡” “ገብረ ጉንዳን ኃይል የሌላቸው ሰዎች ናቸው፣ ነገር ግን በበጋ መኖዋቸውን ይሰበስባሉ፡፡ ” ከእነዚህ ትናንሽ መምህራን የታማኝነትን ትምህርት እንማራለን፡፡ በተመሳሳይ ትጋት በሁሉ-ጠቢብ የሆነ ፈጣሪ የሰጠንን ችሎታዎቻችንን ብናሻሽል ኖሮ፣ ለጠቃሚነት ያለን አቅሞቻችን ምን ያህል በእጅጉ ባደጉ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር አይኖች እጅግ ጥቃቅን በሆኑ ፍጥረቶቹ ላይ ናቸው፤ ስለዚህ በአምሳሉ ለፈጠረው ሰው ትኩረት አይሰጥምን ፣ ለሰጣቸውስ አጋጣሚዎች በሙሉ ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ አይፈልግምን? 82Testimonies For The Church 4:455, 456.CGAmh 57.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents