Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፳—የቤተ ክርስቲያን ምሥክሮች፡፡

    ፍጻሜ ሲቃረብና ለዓለም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሥራ ሲስፋፋ የሶስተኛው መልአክ መልእክት ሥራውን ከተጀመረ አንስቶ እግዚአብሔር በቸርነቱ የጣመራቸውን ምስክሮች ባሕርያቸውንና አንቃቂነታቸውን ያሁኑን እውነት የሚቀበሉት በገልጽ የስተውሉት ዘንድ በጣም የሚያስፈልጋቸው (ጠቃሚያቸው) ነው፡፡CCh 143.1

    በጥንት ጊዜያት እግዚአብሔር በነቢያትና በሐዋርያት አፍ ለሰወች ይናገር ነበር፡፡ በነዚህ ከናትም በመንፈሱ ምሥክሮች ይናገራቸዋል፡፡ ስለ ፈቃዱና እንዲከተሉ የሚፈልግባቸው እርምጃ አሁን ከሚያስተምራቸው (ከሚመክራቸው) ይበልጥ አጥብቆ ሕዝቡን ያስተማረበት ጊዜ ከቶውን የለም፡፡CCh 143.2

    በሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስት መኻከል ያሉት ተሳሳቾች የሆኑት ሕይወታቸው በስም ቤተ ክርስቲያናት ከሆኑት አፍዓውያን ክርስቲያኖች ሕይወት ይበልጥ መነወር የሚገባቸው ስለሆነ ማስጠንቀቂያዎችና ግሣጼዎች የተሰጡ ለዚህ አይደለም፤ ነገር ግን ትልቅ በርሃን ስላላቸውና በዝናቸው ሥራቸውን (ሥፍራቸውን) ይዘው የተለዩ የተመረጡ የምላክ ሕዝብ ሆነው ያምላክ ሕግ በልባቸው ውስጥ ተጽፎ ስላላቸው ነው፡፡CCh 143.3

    ለልዩ ልዩ ሰዎች የተሰጡኝ መልእክቶች እነሱ ባቀረቡልኝ አስቸኳይ ጥያቄ መሠረት ይህን ሳደርግ አብዛኛውን ጊዜ ለነሱ ብዙ ጊዜ ጽፌላቸዋለሁ፡፡ ሥራዬ አየተስፋፋ ሲሔድ፤ የህ የሥራዎቼ ዋናና (ጠቃማና) አቢይ ተግባሬ ሆነ፡፡CCh 143.4

    ከሀያ ዓመታት በፊት (፲፰፻፸፩ ዓ.ም.እ.አ.አ) በተሰጠኝ ትይንት ሁሉም እንዲጠነቀቅበት እንዲገሠጽና እንዲመከር በመናገርና በመጻፍ በዚያኑ ጊዜም ያንዳንዶቹ ሰዋች አሥጊነት ስህተቶችና ኃጢአቶች እዘረዝር ዘንድ በዚያን ጊዜ ጠቅላላው ፕበራፊፕል እነዳቀረብ ተመራሁ፡፡ እነሱ ሌሎች የታረሙበትን እነዚያኑ ስህተቶች አላደረጉ እነደሆንና ለሌሎችም የተሰጡ ማስጠንቀቂያዎች የራሳቸውን ጉዳዮች የማይመለከቱ መሆናቸውን መመርመር እንዳለባቸው አየሁ፡፡ እንዲህም ከሆነ ምክሩና ግሣፄዎቹ በተለይ ለነሱ እንደ ተሰጡ ሊሰማቸው አለባቸው፤ ለራሳቸውም በተለይ አነደ ተነገሩ አድርገው እነሱን የሚመለከቱ መሆናቸውን መቀበል ይኖርባቸዋል፡፡CCh 143.5

    እግዚአብሔር የክርስቶስ ተከተዮች ነን የሚሉትን ሁሉ ሃይማኖታቸውን ሊፈትን ያስባል፡፡ተግባራቸውንም አጥብቀው ለማወቅ እንፈልጋለን የሚሉትን ሁሉ የጸሎታቸውን ልበ ቅንነት ይፈትናል፡፡ ተግባራቸውንም ይገልጽባቸዋል፡፡ በልባቸው ውስጥ ያለውንም ያሻሽሉ ዘንድ ሰፋ ያለ ምቹ ጊዜ ለሁሉም ይሰጣል፡፡CCh 143.6

    ጌታ ሕጉን እንጠብቃለን የሚሉትን ይገስጻል፤ የርማልም፡፡ ኃጢአትንና ዓመፃን ሁሉ ከነሱ ሊያስወግድ ስለሚፈልግ ኃጢአታቸውንም ያመለክትል፤ ዓመፃቸውንም ይገልባቸዋል፤ እሱን በመፍራት ወደ ቅድስና ፍጹምነት ይደርሱ ዘንድ እግዚአብሔር የጠሩ የተቀደሱ፤ ከፍ ያሉና የመጨረሻም በዙፋኑ ላየ በመቀዳጀት የላቁ እንዲሆኑ አግዚአብሔር ይገስጻል፤ ይመክራል፤ ያርማቸዋልም፡፡ ፩15T654—662,CCh 143.7

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents