Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ ፫—ለነቢዩ ብርሃን እንዴት እንደመጣለት፡፡

    አንድ ጊዜ በእሥራኤል ልጆች በደረሰባቸው ሁኔታ አስቀድመን እንዳየነው ጌታ በነቢያት አማካይነት እንደምን እንደሚነጋገራቸው ለሕዝቡ ነገረ፡፡CCh 7.1

    «በመኻኸላችሁ ነቢይ ሰው ቢኖር እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ” ዘሁልቁ ፲፪ ፡ ፮፡፡CCh 7.2

    በእነዚህ ቮሊዩምስ ውስጥ በሌላ ሥፍራ በአካል ላይ የሚታይ ለውጥ የተከተላቸው ስለ ታላቁ ተጋድሎ የታዩት ራእዮች ታሪካቸውን ታነባለህ፡፡ ራእዮቹ በዚህ ጐዳና ለምን ተሰጡ ብሎ ማንም ይጠይቅ ይሆናል፡፡ ለዚህ መልሱ ያለ ጥርጥር የሰዎችን እምነት ለማጽናትና እግዚአብሔር ለነቢዩ በውነቱ መናገሩን ሁሉ ለማረጋገጥ ነው፡፡ ሚስስ ኋይት ራእይ ስታይ ሳለች ስለርስዋ ሁናቴ ዘርዝራ ብዙ ጊዜ የምታወሳ አይደለችም፤ ግን አንድ ጊዜ «እነዚህ መልእክቶች የተሰጡት በኒህ መጨረሻ ቀናት በትንቢት መንፈስ እምነት ይኖረን ዘንድ የሁሉን ኃይማኖት ለማጠንከር ነው» ስትል ተናገረች፡፡CCh 7.3

    «የሚስስ ኋይት ሥራ «ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ» እንዳለው በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ሊፈተን ይቻላል፡፡ ግን ፍሬው ለማፍራት ጊዜ ይጠይቃል፤ እግዚአብሔርም በመጀመሪያ ለማመን ሰዎችን የረዳቸውን ራእይ ከመስጠቱ ጋር አያይዞ ማስረጃ ሰጠ፡፡CCh 7.4

    ነገር ግን ራእይ ሁሉ በሕዝብ ፊት በአካል ላይ የሚታይ ለውጥን እያስከተለ የተሰጠ አይደለም፡፡ ይህ ምዕራፍ ሲከፈት በተጠቀሰው ጥቅስ እግዚአብሔር፤ «በራእይም» ወይም ደግሞ «በሕልም እናገረዋለሁ” እያለ ራሱን የሚያስታውቅ መሆኑን ተነግረናል፡፡ ይህም ዳንኤል እንደሚያወሳው የትንቢት ሕልም ነው፡፡CCh 7.5

    «በቤልሻጽር በባቢሎን ንጉሥ በመጀመሪያው ዓመት ዳንኤል ሕልም አየ የራሱንም ራእይ ባልጋው ላይ፡፡ ከዚያም በኋላ ሕልሙን ጻፈ አውራውንም ነገር አሳጠረ» ዳንኤል ፯፡፩፡፡CCh 7.6

    ዳንኤል የተገለጸለትን ሲናገር ብዙውን ጊዜ «በሕልሜ አይ ነበርሁ በሌት” ይላል፡፡ ብዙ ጊዜም በሚስስ ኋይትም በደረሰባት ሁኔታ ራእዮቹን የምታየው አእምሮዋ በዕረፍት ላይ ሳለ በሌት ሰዓታት ነበር፡፡ እሷ የተናገረችውን እንደሚከተለው እናነባለን ፤ «በሌት ራእዮች አንዳንድ ነገሮች በግልጽ ቀርበውልኝ ነበር»፡፡ እግዚአብሔር ለነቢያት በትንቢታዊ ሕልሞች ዘወትር ይናገር ነበር፡፡ በትንቢታዊ ሕልም ወይም በሌት ራእይና በተለመደው ሕልም መኻኸል ስላለው ግንኙነት ጥያቄዎች ይነሱ ይሆናል፡፡ ስለዚሁ ሚስስ ኋይት በ ፲፰፻፷፰ ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ጽፋለች፡፡CCh 7.7

    «ከእግዚአብሔር መንፈስ ያልሆኑ ብዙ ተራ ሕልሞች ይታያሉ፡፡ በሰይጣን መንፈስ የተነሳሱ የአሰት ራእዮችም ሕልሞችም አሉ፡፡ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሆኑት ሕልሞች ቁጥራቸው በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ከራእዮች ጋር ነው፡፡ እንዲህ ያሉ ሕልሞች ያለሙትን ሰዎችና በምን ሁናቴ የታለሙ መሆናቸውን በመገመት የእውነተኝነታቸው ማስረጃዎች ሊኖራቸው ይገባል»፡፡CCh 7.8

    ሚስስ ኋይት በዕድሜ ገፍታ ሳለች አንድ ጊዜ ልጅዋ ኤልደር ወ ሲ ኋይት ስለ እርስዋ ብዙ እንፎርሜሽን ላላገኙት ይረዳ ዘንድ ከርስዋ እንፎርሜሽን ሲፈልግ ይህን ጥያቄ ጠየቃት፤ «እማማ በሌሊት ጊዜ ስለ ተገለጹልሽ ነገሮች ብዙ ጊዜ ትናገሪያለሽ፤ ብርሃን ስለሚያመጡልሽም ሕልሞች ትናገሪያለሽ ፤ ሁላችን ሕልም እናያለን ፤ አንቺ ዘወትር የምትናገሪው እግዚአብሔር በሕልም የሚናገርሽ መሆኑን እንደምን ታውቂያለሽ?CCh 8.1

    ለዚህ ምክንያት ስትሰጥ «ያው መልአክ በቀኑ በማያቸው ራእዮች በአጠገቤ ቁሞ እንደሚነግረኝ፤ እንዲሁም በሌት በማያቸው ራእዮች በአጠገቤ ቁሞ ይነግረኛል» አለች፡፡ የሰማያዊ ፍጡር ተብሎ የተወሳው በሌላ ጊዜያት፤ «መልአክ»፤ «መሪዬ»፤ «አስተማሪዬ” ተብሎ ተነግሮለታል፡፡CCh 8.2

    በነቢይ ሐሳብ ውስጥ ምንም መደናገር የለም፤ በሌሊት ሰዓታት ስለ ተገለጠለት ራእይ ምንም ጥርጣሬ የለም፤ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሆነው ነገር ከእግዚአብሔር የተነገረው ምክር መሆኑን ይገለጽ ነበርና፡፡CCh 8.3

    በሌላ ጊዜያት ሚስስ ኋይት ስትጸልይ ስትናገር ወይም ስትጽፍ ሳለች ራእዮች ይታዩዋት ነበር፤ ጥቂት ጊዜ አቋርጣ ስትናገር ወይም በጉባዔ ስትጸልይ ካልሆነ በቀር በአካባቢዋ ያሉ ስለ ራእዩ ምንም አያውቁም ነበር፡፡ ስለዚህ አንድ ጊዜ እንዲህ ብላ ጻፈች፤CCh 8.4

    «ጸሎት ስጸልይ በዙርያዬ ያለው ነገር ሁሉ ጠፋኝ ክፍሉ በብርሃን ተመላ፤ ለጉባዔ የተሰጠውን መልእክት ስሰማ ነበር፤ ይህም ጉባዔ ጀኔራል ኮንፈረስ ይመስለኝ ነበር »፡፡CCh 8.5

    ሚስስ ኋይት ፸ ዓመታት ባገለገለችው የረዥም ጊዜ አገልግሎት ውስጥ ከተሰጧት ብዙዎች ራእዮች እጅግ ረዘም ያለው ራእይ አራት ሰዓታት ሙሉ ያየችው ራእይ ነው፤ በአጭሩም ለአንድ አፍታ የሚታያት ነበር፡፡ ብዙ ጊዜም ስታይ የነበረው ለግማሽ ሰዓት ወይም ትንሽ ረዘም በሚል ጊዜ ውስጥ ነው፡፡ ላየቻቸው ራእዮች ሁሉ ምንም ደንብ ሊነገርላቸው አይቻልም፤ ልክ ጳውሎስ እንደ ጻፈው ነበርና፡፡CCh 8.6

    «እግዚአብሔር አስቀድሞ በብዙ ነገር በልዩ ልዩ አይነትም ላባቶቻችን በነቢያት አፍ ከተናገረ በኋላ” ዕብ ፩ ፡ ፩፡፡CCh 8.7

    በራእዮች አማካይነት ብርሃን ለነቢይ ይሰጥ ነበር፤ ነቢዩ ግን በራእይ ሳለ አይጽፍም ነበር፡፡ ሥራው የችኩል ተግባር አልነበረም፡፡ አንዳንዴ በቀር ጌታ ያንኑ ቃላት እንዲናገር አልሰጠውም፤ ወይም መልአኩ ልክ እነዚያኑ ቃላት ይጽፋቸው ዘንድ የነቢዩን እጅ አልመራም፡፡ መልእክቱንም ለሚሰጡ ወይም ለሚያነቡ ብርሃንና ምክርን ስለሚሰጡት ቃላት ነቢዩ ይናገር ወይም ይጽፍ የነበረው ባያቸው ራእዮች አማካይነት ከተብራራለት ሐሳብ ነው፡፡CCh 8.8

    ነቢዩ አእምሮው እንዴት ተብራራለትና ለሕዝቡ የሚሰጠውን እንፎርሜሺንና ምክር እንዴት አገኘ? ብለን እንጠይቅ ይሆናል፡፡ ስለሚሰጡት ራእዮች አንድ ደንብ ሊቋቋምለት የማይቻል እንደሆነ እንደዚሁም ነቢዩ በመንፈስ የተሰጠውን መልእክት የተቀበለበትን ጐዳና የሚመራ አንድ ደንብ ሊቋቋምለት አይቻልም፡፡ ሆኖም በየጊዜው በነቢዩ አእምሮ የተቀረጸው ሐሳብ የማይጠፋ በመሆኑ በጣም የጠለቀ ሁኔታ ነው፡፡ ከምንሰማው ይልቅ የምናየውና በግብር የተለማመድነው በአእምሮዋችን ውስጥ በጣም የምናስታውሰው እንደ መሆኑ መጠን እንደዚሁም ለነቢያት የተሰጡት መልእክቶች የተብራሩላቸውን ሁኔታዎች ያዩ ይመስላቸው የነበረው በአእምሮዋቸው የማይጠፋ ይሆናል፡፡CCh 8.9

    ከዚህ ቀደም በገለጽነው ክፍል ስለ ታላቁ የተጋድሎ ራእይ የተነገረውን ታሪክ ስንናገር፤ ስለ ታሪካዊ ሁኔታዎቹ እንፎርሜሺኑን መርምሮ ማግኘት እንደምን እንደመጣላት እያወሳን የተናገረችውን ቃላት ጠቅሰናል፡፡ በሌላ ጊዜም ብርሃኑ እንዴት እንደመጣላት ስታወሳ፤ በራእይ ሳለች «ሐሳቤ ብዙ ጊዜ በምድር ላይ በሚሆኑት ሁኔታዎች ላይ ይጣል ነበር፤ በየጊዜያቱ ወደ ፊት ጉዳይ እሩቅ ወደፊት ተመርቼ የሚሆነውም ይታየኝ ነበር፤ ከዚያ በኋላ ባለፉት እንደሆኑት ሁነው ነገሮቹ እንደገና ይታዩኛል»፤ ስትል ተናገረች ፡፡CCh 9.1

    ከዚህ ኤሌን ኋይት እነዚህን ሁኔታዎች ሲሆኑ ማየትዋ፤ የዓይንም ምሥክር መሆንዋ ግልጽ ነው፡፡ ራዕይ በማየት በፊቷ እንደና ግልጽ ሁነው ተገለጹላት፤ እንደዚሁም በእእምሮዋ የጠለቀ ሐሳብ ይቀረጽ ነበር፡፡CCh 9.2

    በሌላ ጊዜያትም ራእይ ስታይ ሳለች ሚስስ ኢ ጂ ኋይት በቀረበላት ሁኔታ ተካፋይ እንደሆነችና በአካልዋ እዚያ ሁና ሲሰማት፣ ስታይ፣ ስትሰማና ስትታዘዝ እንደነበረች ይመስላት ነበር፤ ደግሞ በአእምሮዋ በማይረሳ አኳኋን ይህ ሐሳብ ይቀረጽባት ነበር፡፡ መጀመሪያ ያየችውም ራእይ የዚሁ ብጤ ነበር፡፡CCh 9.3

    በሌላ ጊዜያትም ራእይ ስታይ ሳለች ሚስስ ኤ ጂ ኋይት በስብሰባዎች በቤቶች ወይም በሩቅ ሥፍራዎች ባሉት መሥሪያ ቤቶች ያለች ይመስላት ነበር፡፡ በእንዲህ ያሉ ስብሰባዎች ሁና በልዩ ልዩ ሰዎች የተደረጉትንና የተነገሩትን ቃላት ዘርዝራ ለመስጠት መቻልዋ የሚያስገርም ነበር፡፡ አንድ ጊዜ በራእይ ሳለች፤ ሚስስ ኋይት ከሕክምና መሥሪያ ቤቶቻችን እንዱን ልትጐበኝ እንደ ሔደች መስሎ ይታየት ነበር፤ ከፍሎቹን እየጐበኘች የሚደረገውን ሁሉ ታይ ነበር፡፡ ስለዚሁ ሁኔታ እንዲህ ስትል ጻፈች፤CCh 9.4

    ልክስክስ ንግግር፤ የጅልነት ቀልድ፤ ፍች የሌለው ሳቅ በሚያሰቅቅ አኳኋን ተሰማኝ፡፡ … የቅናትን ሐሳብ፤ የምቀኝነትን ቃላት ባየሁ ጊዜና የእግዚአብሔርን መላእክት ያሳፈሩትን ግድ የለሽ ንግግር በሰማሁ ጊዜ ተደነቅሁ»፡፡CCh 9.5

    ከዚያ በኋላ ሌሎች በጣም የሚያስደስቱ ሁኔታዎች ከዚያው መሥሪያ ቤት ተገለጹ፡፡ ወደ ክፍሎቹም ተመራች፤ «ከዚሁ የጸሎት ድምፅ መጣ፡፡ ድምፁ ምንኛ ጥሩ ነበር!» ይህን መሥሪያ ቤት የምትጐበኝ ይመስላት በነበረው ሐሳብ መሠረትና በልዩ ልዩ መሥሪያ ቤቶችና ክፍሎች ውስጥ የሚመራት ይመስላት በነበረው በመልአኩ ሐሳብ መሠረት የምክር መልእክት ተጽፎአል፡፡CCh 9.6

    ብዙ ጊዜ በጠለቀው ምሳሌ ብርሃን ለሚስስ ኋይት ተሰጥቷታል፡፡ እንዲህ ያለ ትርእይት በሚያሠጋ ላይ ሁኖ ለታየው የሥራ መሪ ራሷ ከላከችለት መልእክት በሚከተሉት ሶስት ዓረፍተ ነገሮች ውስጥ በግልጽ እናወሳለን፡፡CCh 9.7

    «በሌላ ጊዜ እንደ ጀኔራል ሁነህ በፈረስ ተቀምጠህ ባንዲራ ይዘህ ታየኸኝ፡፡ አንዱ መጣና «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት የየሱስንም ሃይማኖት” የሚሉትን ቃላት የያዘውን ባንዲራ ከእጅህ ወሰደ፤ በአዋራም ውስጥ ረገጠ፡፡ ከዓለም ጋር በሚያቆራኙህ ሰዎች ተከብበህ አየሁህ»፡፡CCh 10.1

    ሁለት ልዩ ልዩ ሐሳቦች ለሚስስ ኋይት የቀረቡላት ጊዜያት ደግሞ ነበሩ፤ አንደኛው የተለዩ እቅዶች፤ ወይም ፖሊሲ ቢከተሉ ምን እንደሚሆን የሚገልጽ ሲሆን ሌላውም ሌሎች እቅዶችን ወይም ፖሊሲን የማቀድ ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚሁ የሚገልጽ እጅግ የተሻለው መግለጫ፤ የጤና ምግብ ፋክቶሪ በአሜሪካ ምዕራባዊ ክፍል በሎማ ሊንዳ ከማቋቋም ጋር ተያይዞ የሚገኝ ነው፡፡ ሥራ አስኪያጁና ጓደኞቹ በዋናው ሆስፒታል አቅራቢያ ትልቅ ቤት ለመሥራት ያስቡ ነበር፡፡ እቅዱ ሲታቀድ ሳለ፤ ሚስስ ኋይት ብዙ መቶ ማይልስ ርቃ ከቤትዋ ሁና አንድ ሌሊት ራእዮች አየች፡፡ ከነዚሁ ስለ መጀመያው እንዲህ ትላለች ፤CCh 10.2

    «ብዙዎች ምግቦች ይሠሩበት የነበረው ትልቅ ቤት ታየኝ፡፡ በመጋገሪያው ቤት አቅራቢያ ደግሞ ትንንሾች ቤቶች ነበሩ፡፡ አጠገቡ ቁሜ ሳለሁ ስለተሠራው ሥራ ሲከራከሩ ከፍ ያለ ድምፅ ሰማሁ፡፡ በሠራተኞች መኻኸል ስምምነት አጥተው ነበርና ብጥብጥ ገባባቸው፡፡CCh 10.3

    ከዚያ በኋላ የተጨነቀው ሥራ አስኪያጁ ስምምነት ያደርግላቸው ዘንድ ከሠራተኞቹ ጋር ለመመካከር ሲሞክር አየሁ፡፡ ይህን ክርክራቸውን የሰሙ በሽተኞች «የምግብ ፋክቶሪ በዚህ ባማረው መሬት ላይ ሕክምና ቤት አቅራቢያ ስለ መቋቋሙ የሐዘን ቃላት ሲናገሩ የነበሩትን አየች፤ ከዚያ በኋላ አምላክ በዚህ ሁኔታ ላይ ታየና እንዲህ አለ ፤ «ይህ ሁሉ በፊትሽ ትምህርት ሁኖ እንዲተላለፍ (እንዲቀርብ) ተደረገ፤ የተለዩትን እቅዶች በማካሔድ ውጤቱን ትመለከቺ ዘንድ ነው»፡፡CCh 10.4

    ከዚያ በኋላ ሁኔታው ተለወጠ፤ እርሷም የምግብ ፋክቶሪ «ከሕክምና ቤቶች ራቅ ያለ ሆኖ ወደ ባቡር መንገድ የሚመራው መንገድ ላይ ሁኖ» አየች፡፡ እዚህ ሥራው በትሕትና ጐዳና፤ ከእግዚአብሔርም ሐሳብ ጋር በማስማማት ተካሔደ ፡፡ ራእዩን ካየች ጥቂት ሰዓታት ቆይታ ሚስስ ኋይት በሎማ ሊንዳ ላሉት ሠራተኞች ጻፈች፤ ይህም የምግብ ፋክቶሪ የት ሊሠራ እንደሚገባ ጥያቄውን ልክ አገባ፡፡ የመጀመሪያ ሐሳባቸው ቢካሔድ ኑሮ፤ በኋላ ዓመታት ትልቅ የንግድ ቤት በሕክምና ቤት አቅራቢያ በመኖሩ በብዙ እንጨነቅበት ነበር፡፡CCh 10.5

    እንግዲህ በቀን ወይም በሌት ባየችው ራእዮች የጌታ መልእክተኛ በልዩ ልዩ ጐዳናዎች እንፎርሜሽንና ምክር እንደተቀበለች ሊታይ ይቻላል፡፡ ነቢይ ሲባል፤ የተናገረው ወይም የጻፈው ለሕዝብም የምክርና የእንፎርሜሽን መልእክት ያደርስ የነበረው ከተብራራለት ሐሳብ ነው፡፡ ይህን ስታደርግ ሚስስ ኋይት የተረዳችው በእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ግን የችኩል አመራር አልነበረባትም፡፡ መልእክቱን የምታደርስባቸውን ቃላት ትመርጥ ዘንድ ተፈቀደላት፡፡ በአገልግሎትዋ የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ውስጥ በቤተ ክርስቲያን ጋዜጣችን እንዲህ ስትል ጻፈች፤CCh 10.6

    «በምቀበላቸው መጠን ሐሳቦቼን ስጽፍ በእግዚአብሔር መንፈስ ርዳታ ላይ የምታመን ብሆን እንኳ በመልአኩ ከተነገሩኝ፤ ያውም እነዚህኑ ሁልጊዜ በጥቅስ ምልክቶች ከምጠቅሳቸው በቀር ያየሁትን ለመግለጽ የምጠቀምባቸው ቃላት የገዛ ራሴ ነው»፡፡CCh 11.1