Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አንባቢው መለኮታዊ ማብራሪያ ተስፋ ተሰጥቶታል፡፡

    ያምላክ ቃል እንደ መለኮታዊ ደራሲው ባሕርይ ውስኖች በሆኑት ፍጥረቶች በምሉ ከቶውን ሊሰተዋሉ የማይቻል ምሥጢሮች ያቀርባል፡፡ ‹በብረሃን ወደርሲ ሰው የማይቀርብ› የሚኖር ፈጣሪያችን ሐሳባችንን ይመራል፡፡ (፩ ጢሞቴወስ ፮፡፲፮) የሰብዓዊ ታሪክ ዘመናትን ሁሉ የሚጠቀልልና ፍጻሜ በሌለው በዘልዓለማዋነት ዓላማዎች ላይ ብቻ ወደ አፈጻጸማቸው የሚደርሱበን ሐሳቦች ያቀርብልናል፡፡ ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ሰው መዳረሻ ወሰን የሌለው ጥልቀትና ጠቃሚነት ያለባቸውን ጉዳዮች ያሳስበናል፡፡CCh 153.3

    ወደ ዓለም የኃጢአት መግባት የክርስቶስ ሥጋ መልበስ እንደገና መወለድ ትንሣኤና ሌሎችም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተመለከቱትን ጉዳዮች ለመግለጽ ወይም በምሉ ለማስተዋል እንኳ ለሰብዓዊ አእምሮ እጅግ የጠለቁ ምሥጢሮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ግን ስለ መለኮታዊ ባሕርያቸው በቅድሣት መጽሐፍት ውስጥ በቂ ማስረጃ ሰጥቶናልና የቸርነቱን ምሥጢሮች ሁሉ ለማስተዋል ስለማንችል ስለ ቃሉ መጠራጠር የለብንም፡፡CCh 153.4

    ፍጡራን ስለ እግዚአብሔርና ስለ ሥራዎቹ በምሉ በማስተዋል ረገድ ሊደርሱበት የሚቻል ቢሆን ኑሮ እንግዲህ ወደዚህ ዓላማ በመድረሳቸው እውነትን የማግኘት ጉዳይ በዕውቀትም ማደግ የአእምሮና የልብ እድገትም ደግሞ ማግኘት አይኖርባቸውም፡፡ እግዚአብሔርም እንግዲህ ከፍ ያለ አይሆንም ነበር ሰዎችም የእውቀትና የግባቸውን ወሰን ስለ ደረሱበት ቅድሚያ /ግሥገሤ/ ማድረግን ያቋርጡ ነበር፡ እንዲህ ባለመሆኑ አምላክን እናመሰግን፡፡ አግዚአብሔር ወሰን የሌለው ነው በርሱ ‹የጥበብና የእውቀት መዝገብ ሁሉ› አለ፡፡ ለዘለዓለም ሁሉ ሰዎች ዘወትር ይመረምሩ ይማሩ ይሆናል፤ ሆኖም የጥበቡን የቸርነቱንና የኃይሉን መዝገቦች ከቶ ሊደርሱበት አይችሉም፡፡CCh 153.5

    ያለ መንፈስ ቅዱስ መሪነት ቅዱሣት መጽሕፍትን ለማጣመም ወይም ያለ አግባብ ልንተረጉማቸው ዘወትር እንቃጣለን፡፡ ያለ ጠቀሜታ መጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ይነበባል ብዙ ጊዜያትም ትልቅ ጉዳት የሚያመጣ ነው፡፡ ያምላክ ቃል ያለ ከበሬታና ያለ ጸሎት ሲገለጥ ሐሳቦችና ፍቅር ከፈቃዱ ስምሙ ሆነው በአምላክ ላይ ያልተመሠረቱ ሲሆን ሐሳብ በጥርጣሬ ይጨልምበታል መጽሐፍ ቅዱስንም በማጥናት ረገድ ክህደት ይጠነክርበታል ጠላት ሐሳቦችን ይማርካል ልክ ያልሆኑትንም ትርጓሜዎች ያሳስባል፡፡ ፱95T699—705;CCh 153.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents