Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ኅብረት የመንፈስ ቅዱስን መፍሰስ መቅደም አለበት፡፡

    ደቀ መዛሙርት ፍጹም በሆነው ኅብረት ከሆኑ በኋላ እጅግ ከፍ ላለው ስፍራ እንግዲህ በማይጣጣሩበት (በማይታገሉበት) ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የፈሰሰላቸው መሆኑን ልብ በለው፡፡ ባንድነት ነበሩ መለያየትም ሁሉ ተወግዶ ነበር፡፡ መንፈስ ከተሰጣቸው በኋላ ስለነሱ የተመሰከረው ምስክርነት ያው ነው የተነገረውን ቃል ተመልክተው ‹‹ላመኑትም ሁሉ አንድ ልብ አንዲት ነፍስም ነበራቸው›› (የሐዋ ( (()፡፡ ኃጢአተኞች ይኖሩ ዘንድ የሞተው መንፈሱ መላውን የምዕመናን ጉባዔ አነቃቃ፡፡CCh 160.4

    ደቀ መዛሙርት ለራሳቸው ሲሉ በረከትን አለመኑም፡፡ የነፍሳት ሸክም ከብዶባቸው ነበር፡፡ ወንጌል ወደ ምድር ዳርቻዎች መወሰድ አለበት ስለዚህ ክርስቶ ተስፋ የሰጣቸውን የኃይል ስጦታ ለመኑ፡፡ በዚያን ጊዜ ነው መንፈስ ቅዱስ የፈሰሰላቸውና በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ባንድ ቀን የተመለሱት፡፡CCh 160.5

    አሁንም እንደዚሁ ይሆናል፡፡ ክርስቲያኖች ፀብን (መለያየትን) አስወግደው የጠፋትን ለማዳን ራሳቸውን ለእግዚብሔር ይስጡ፡፡ ተስፋ ለተሰጣቸው በረከት በሃይማኖት ለምኑ ይመጣላቸዋልም፡፡ በሐዋርያት ጊዜያት የመንፈስ ቅዱ መፍሰስ ‹‹የፊተኛው ዝናብ›› ነበር ውጤቱም የተከበረ (ተመሰገነ) ነበር፡፡ የኋለኛው ዝናብ ግን በጣም በብዙ ይሆናል፡፡ በእነዚህ መጨረሻ ቀናት ለሚኖሩት ተስፋው ምንድን ነው( ‹‹እላንት በተስፋ የታሠረችሁ ወደ ጽኑ አምባ ተመለሱ፡፡ በዚህም ቀን ደግሞ ሁለት ዕጽፍ እንድመልስልሽ እነግርሻለሁ›› ‹‹በኋለኛው ዝናም ወራት ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናም እሹ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል አርሱመ የጎርፍ ዝናም ይሰጣችኋል ለሣሩ ሁሉ ለእያንዳንዱ›› (ዘካርያስ ( (( ምዕ ( ()፡፡CCh 161.1