Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በነቢያት የተቋቋሙ ቤተ ክርስቲያናት፡፡

    በየሩሳሌም የቤተ ክርስቲያን ድርጅት የእውነት መልእክተኞች ለወንጌል አማኞችን በሚመልሱበት ሌላ ሥፍራ ሁሉ ቤተ ክርስቲያናትን ለማቋቋም አርአያ ሁኖ እንዲያገለግል ነው፡፡ በጠቅላላ የቤተ ክርስቲያን ተጠባባቂዎች ለመሆን ኃላፊነት ተሰጥቶአቸው የነበሩት በአምላክ ርስት ላይ ጌትነት እንዲኖራቸው አልነበረም፣ ነገር ግን ጠቢባን እረኞች ሆነው፣ ‹‹የእግዚአብሔርን መንጋ መጠበቅ … ለመንጎች ምሳሌ እንደሚሆኑ›› እንጂ፡፡ … ዲያቆናትም፣ ‹‹በመልካም የተመሰከረላቸው መንፈስ ቅዱስ ጥበብም የመላባቸው›› እንዲሆኑ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በቀና ጎዳና ላይ ተባብረው ሥራቸውን መሥራትና በጽናትና በቁርጥ ሐሳብ ማካሔድ ነበረባቸው፡፡ በእንዲህ በመላው መንጋ ዘንድ የተባበረ ኃይል (አነቃቂነት) ነበራቸው፡፡4AA91;CCh 108.2

    ለአዲሶቹ ምዕመናን የመንፈሳዊ እድገት ጠቃሚ ድጋፍ በመሆኑ ሐዋርያት በወንጌል ሥርዓት ያከባክቧቸው ዘንድ ጥንቁቆች ነበሩ፡፡ አለቆች በእያንዳንድዋ ቤተ ክርስቲያን ተሸሙ፣ ለምእመናንና የመንፈሳዊ በጎ አድርጎት ለሆኑት ጉዳዮች ማካሔጃ ሁሉ የሚገባ ሥርዓትና ሲስተም ተቋቋመላቸው፡፡CCh 108.3

    ይኸውም ምዕመናንን ሁሉ በክርስቶስ በአንድ አካል ለማስተባበር ከወንጌል ፕላን (እቅድ) በመስማማት ነበር ይህነንም ዕቅድ ጳውሎስ በአገልግሎቱ ሁሉ ይከተለው ዘንድ ጥንቁቅ ነበር፡፡ በማናቸውም ሥፍራ በርሱ ሥራ ክርስቶስን መድኃኒታቸው አድርገው ለመቀበል የተመሩ በሚገባ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ሆነው ተቋቁመው ነበር፡፡ ምዕመናን በቁጥር ዋቂቆች ቢሆኑም እንኳ ይህ ይደረግ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ‹‹ሁለት ሁነው ወይም ሶስት ሁነው በስሜ ወደ ተከማቹበት ከዚያ በመኻከላቸው እሆናለሁና›› የተባለውን ተስፋ እያስታወሱ እርስበርሳቸው እንዲረዳዱ ተምረው ነበር፡፡ 5AA185.186; CCh 108.4