Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የክርስቶስን መሳይ ጠባይ ማበጀት፡፡

    የክርስቶስ ሃይማኖት ተቀባዩን አያዋርድም ፤ ጨምጋጋ ወይም ጠማማ ባለጌ ወይም ጅንን ፤ ቁጡ ወይም ልበ ደንዳና ከቶ አያደርገውም፡፡ አልፎ ተርፎ ፤ ጠባይን ያሳምራል ፤ ሐሳብን (ፍርድን) ይቀድሳል፤ ሐሳቦችንም ወደ ክርስቶስ እየማረከ ያነጻል ፤ ያስከብራልም፡፡ ለልጆቹ ያምላክ ሐሳብ እጅግ ከፍ ያለው ሰብዓዊ ሐሳብ ሊደርስበት ከሚችለው በላይ ከፍ ያለ ነው፡፡ በተቀደሰው ሕጉ ውስጥ የጠባዩን ቅጅ ሰጥቶናል፡፡CCh 138.5

    የክርስቲያናዊ ጠባይ ሐሳብ (ዓላማ) ክርስቶስን መምሰል ነው፡፡ የዘወትር ግሥጋሤ ጐዳና በፊታችን ተከፍቷል፡ መልካምና ንጹህ የተከበረና ከፍ ያለ ነገር ሁሉ ያለበትን የምናገኝ ነገር ፤ የምንደርስበትም ደረጃ (አቋም) አለን፡፡ ወደ ጠባይ ፍጹምነት እንደርስ ዘንድ ወደፊት እየቀጠልንና እየገፋን ዘወትር መጣጣርና መገስገስ አለብን፡፡ ፪28T65; 64;CCh 138.6

    ዓመሎቻችን እንደሚያደርጉን ሁነን በየራሳችን ለጊዜውና ለዘልዓለማዊነት አንሆናለን፡፡ ቅን ዓመሎችን የሚያበጁና ተግባርን ሁሉ በመፈጸም ታማኞች የሆኑ ሕይወታቸውን በሌሎቹ ጐዳና ላይ የሚያበሩ ጮራዎችን እያሰራጩ የሚያበሩ ብርሃናት (መብራቶች) ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ያለመታመን ዓመሎች የተወደዱ እንደሆነና ቧልፈሰስ፤ ታካቾች ችላ ባዮች ዓመሎች እንዲጠነክሩ የተፈቀዱ እንደሆነ ፤ ከእኩለ ሌሊት የጨለመ ደመና በዚህ ሕይወት አለኝታዎች ላይ ይወርና ሰውንም የወደፊት ሕይወት ከማግኘት ለዘላለም ያግደዋል፡፡ ፫34T452;CCh 139.1

    የዘልዓለምን ሕይወት ቃላት የሚቀበል ብሩክ ነው፡፡ «በመንፈስ እውነት» ተመርቶ ወደ እውነት ሁሉ ይመራል፡፡ በዓለም ዘንድ የሚወደድ የሚከበርና የሚመሰገን አይደለም፤ ነገር ግን በሰማይ ፊት የከበረ ነው፡፡ «እዩ እንዴት ያለውን ፍቅር ሰጠን አብ የእግዚአብሔር ልጆች እንባል ዘንድ፡፡ ስለዚህ ዓለም አያውቀንም እርሱን አላወቀምና» ፩ ዮሐ መል ፫ ፡፡ ፬45T439;CCh 139.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents