Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    በትጋትና በደንብ አጥና

    ወላጆች አምላክን እንዲያገለግሉና በዓለም መልካም እንዲያደርጉ ልጆቻችሁን ልታስለጥኗቸው ብትፈልጉ መጽሐፍ ቅዱስን የጥቅጽ መጽሐፋችሁ አድርጉ የሰይጣንን ተንኮሎች ያጋልጥበታል፡፡ የዘር ታላቁ ከፍ አድራጊ ስለ ግብረገብ /የሞራል/ ክፋቶች ገሣጺና አራሚ አራሚ በእውነትና በአሰት መኻከል ለይቶ ለማወቅ የሚያስችለን አመልካች /ገላጭ/ ነው፡፡ በቤት ወይም በትምህርት ቤት ሌላውን ሁሉ ሲያስተምሩ መጽሐፍ ቅዱስ ታላቁ አሠልጣኝ ሁኖ መጀመሪያ መቆም አለበት፡፡ በዚህ ስፍራ የተሰጠው እንደሆን አምላክ ይከበራል፤ ልጆቻችሁንም በመመለስ ረገድ ይሰራላችኋል፡፡ በዚህ ቅዱስ መፍሐፍ ውስጥ የእውነትና የውበት ማዕድን አለ ወላጆችም በጣም የሚደሰቱበት የማያደርጉት እንደሆነ ራሳቸውን መንቀፍ አለባቸው፡፡ ፮65T322CCh 152.2

    ፈታኙ ለማሳት በመጣበት ጊዜ ክርስቶስ የተጠቀመበት መሣሪያ ‹ተጽፎዋል› የሚል ብቻ ነበር፡፡ የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ትምህርት ወላጅ ሁሉ ሊያደርግ የሚገባው ታላቅና ሰፊ ሥራ ነው፡፡ በሚያስደስት ተደሳች በሆነው የሐሳብ መልክ በአምላክ እንደተነገረው በልደች ፊት እውነትን አቅርብላቸው እንደ አባቶችና እናቶች ትዕግሥትን ቸረነትንና ፍቅርን በማሳየት ወደ ራስህም እንሱን በማስጠጋት ለልጆች ሥነ ትምህርቶች ልትሆን ትችላለህ፡፡ እንደ ፈቀዱት እንዲያደርጉ አተተዋቸው ነገር ግን ሥራህ ያምላክን ቃል በምግባር የሚገልጽ መሆኑንና በጌታ አሳዳጊነትና (አልሠልጣኝነትና) ምክር የሚያሳድጋቸው መሆኑን አሳያቸው፡፡CCh 152.3

    በቤተ ሰቦችህ ውስጥ ቅዱሣት መጽሕፍትን በማጥናት ረገድ ሥርዓት አድርገላቸው፡፡ ማናቸውንማ ጊዜያዊ የሆነውን የተፈሮ ነገር ችላ በል፡፡ ነገር ግን ነፍስ በሕይወት እንጀራ መመገቡን አረጋግጥ ተደሳች በመሆን በማህበራዊ (በሶሺያል) ሁናቴ ያምላክን ቃል በመሳተፍ አንድ ሰዓት ወይም ግማሽ ሰዓት እንኳ ቡሆን ራስን ቀድሶ የመስጠትን መልካም ውጤቶች ለመገመት የማይቻል ነው፡፡ በልዩ ልዩ ጊዜያትና በልዩ ልዩ ሁኔታዎች ስለ ተሰጠው ጉዳይ (አርእስት) የተነገረውን ሁሉ ባንድነት እያጣመርህ መጽሐፍ ቅዱስን የራሱ ገላጭ አድርገው፡፡ ለጠሪዎች ወይም ለጐብኚዎች ብለህ የቤት ጥናት ክፍልህን አታቋርጥ፡፡ በትምህርት ጊዜ ቢመጡ እንዲካፈሉት አድማቸው፡፡ የዓለምን ትርፎች ወይም የዓለምን ተድላዎች ከማግኘት ይልቅ ያምላክን ቃል ዕውቀት ማግኘት በጣም ጠቃሚ መሆኑን አሰብ፡፡CCh 152.4

    በየቀኑ በመትጋትና በጸሎት መጽሐፍ ቅዱስን ብናጠና አዲስ ግልጽ በሆነውና ኃይለኛ ብርሃን አንዳች ውብ የሆነውን እውነት በየቀኑ እናያለን፡፡ ፯7CG510,511; CCh 153.1

    ልጆችህን በአምላክ አሳዳጊነትና (አሠልጣኝነትና) ምክር ልታሳድጋቸው ብትፈልግ፤ መጽሐፍ ቅዱስን መሪህ ማድረግ አለብህ የክርስቶስ ሕይወትና ጠባይ የሚቀዱት አርአያ ሁኖ ይቅረብላቸው ቢሳሳቱም ተሳሳይ ስለሆኑት ኃጢአቶች ጌታ ያለውን እንብብላቸው፡፡ በዚህ ሥራ ዘወትር መጠንቀቅና መትጋት የስፈልጋል፡፡ ወላጆች የተገሡት በአስተማሮችም ያልታረመው አንድ የስህተት ጠባይ መላውን ጠባይ የተበላሸና ከሚዛን ውጭ ያደርገዋል፡፡ ልጆች አዲስ ልብ ሊኖራቸው አዳዲስም ስሜቶች ሊፈጠሩባቸው አዳዲስም ሐሳቦች ሊነቃቁባቸው እንዳለባቸው አስተምራቸው ከክርስቶስ እርዳታ ሊያገኙ አለባቸው በቃሉ ውስጥ እንደ ተገለጸው የአምላክን ጠባይ ማወቅ አለባቸው፡፡፰8CG5I5;CCh 153.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents