Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ስምምነትና ኅብረት ብርቱ የሆነ ምሥክራችን ነው፡፡

    አብዛኛውን የሚያሠጋን የዓለም መቃወም አይደለም እጅግ የሚያሳዝን መዓት የሚያመጣብንና ያምላክን ጉዳይ ከመገስገስ አብዛኛውን የሚያዘገየው በአፍአውያን ምዕመናን ልቦች ውስጥ የተወደደው ክፋት ነው፡፡ ቀናተኞች እርስበርሳችንን መጠራጠር አንዱ ባንዱ ላይ ስህተት በመፈላለግና በክፉ ሐሳብ የተመላን ከመሆናችን በቀር መንፈሳዊነታችንን የሚያደክም የተረጋገጠ መንገድ የለም፡፡ ‹‹ይህች ጥበብ ከላይ የወረደች አይደለችም ነገር ግን የምድር ናት የሥጋም ናት የሰይጣንም ናት፡፡ ቅንዓትና መተማማት ባለበት ሥፍራ ከዚያ አንድነት የለምና ክፉም ሥራ ሁሉ አለበት፡፡ ከሰማይ ግን የወረደች ጥበብ ታራቂ አስቀድሞ ንጹሕ ነው ደግሞም የዕርቅ ወዳጅ ገርም እሺ ባይም ምሕረትና መልካም ፍሬ የመላበት ያለ ማድላትና ያለ ግብዝነት፡፡ የጽድቅ ፍሬ ግን በሰላም ትዘራለች ሰላም ለሚያደርጉ››፡፡ ያዕቆብ ፫፣፲፭-፲፰፡፡CCh 86.4

    ልዩ ልዩ ጠባያት (ባሕሎች) ባላቸው ሰዎች መኻከል ያለው ስምምነትና ኅብረት እግዚአብሔር ኃጢአተኛችን ያድን ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም መላኩን ሊመሰከር የሚቻልበት ብርቱ ምሥክር ነው፡፡ ይህን ምስክር እንመሰክር ዘንድ መብታችን ነው፡፡ ነግር ግን ይህን ለማድረግ በክርስቶስ ትእዛዝ በታች ራሳችንን ማስቀመጥ ነው፡፡ ጠባያችንን ከጠባዩ ጋር በማስማማት የታነፀ መሆን ይገባዋል ፈቃዳችን ለፈቃዱ ሊገዛ ይገባዋል፡፡ በዚያን ጊዜ ያለ ግጭት ሐሳብ ባንድነት ልንሰራ እንችላለን፡፡CCh 87.1

    የጸኑበት ትንሽ መለያየት ክርስቲያናዊ ኅብረትን ወደሚያጠፋ ሥራ መርቶአል፡፡ እንግዲህ ጠላት እንዲያይልብን አንፍቀድለት፡፡ ወደ እግዚአብሔርና ወደ እርስበርሳችን እንቃረብ፡፡ በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር እንደ ተከለውና በሕይወት ውኃ እንደ ተጠጣው ጽድቅ ዛፍ እንሆናለን፡፡ ምንኛ ፍሬያማዎች እንሆናለን! ክርስቶስ ‹‹በዚህ አባቴ ይመሠገናል እጅግ ፍሬ ታፈሩ ዘንድ›› አላለምን? ዮሐንስ ፲፭፣፰፡፡CCh 87.2

    የክርስቶስን ጸሎት ፈጽመን ስናምን ምክሩ (ትምህርቱ) ለእግዚአብሔር ሕዝብ ዕለታዊ ሕይወት ሲሰተፍ በረድፎቻችን ውስጥ የምግባር ኅብረት ይታያል፡፡ ወንድም ከወንድም ጋር በወርቃዊው የክርስቶስ ፍቅር ማሠሪያዎች ይተሳሰራል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ይህን አንድነት ሊያመጣ ይችላል፡፡ ራሱን የቀደሰ ደቀ መዛሙርቱን ሊቀድስ ይችላል፡፡ ከርሱ ጋር ተባብረው እጅግ በተቀደሰው ኃይማኖት እርስበርሳቸው ይተባበራሉ፡፡ እንጣጣርበት ዘንድ እግዚአብሔር እንደሚፈልግብን አድርገን ለዚህ አንድነት ስንጣጣር ይመጣልና፡፡ ፫38T242,243;CCh 87.3

    እግዚአብሔር የሚፈልገው ብዙ ድርጅቶች ታላላቅ ቤቶችና ውጫዊ ታይታ አይደለም ግን ስምሙ የሆነውን የተለየ ሕዝብ ምግባር በእግዚአብሔር የተመረጠውን ሕዝብ የተወደደና እርስ በርስ የተባበረ ሕይወቱ በእግዚአብሔር በክርስቶስ የተመሠረተውን ነው፡፡ ሰው ሁሉ በአሳቡ በቃሉና በምግባሩ የቀና አርአያ በማሳየት በእድሉና በሥፍራው መቆም አለበት ያምላክ ሠራተኞች ሁሉ ይህነን ሲያደርጉ ነው እንጂ እስከዚያ ግን ሥራው ፍጹምና የተሟላ ፍጹምነት ያለው የሚሆን አይደለም፡፡ ፬48T183;CCh 87.4

    ጌታ ዓይነተና ኃይማኖት ደህና ሐሳብ ያላቸውን ሰዎች በእውነተኛውና በአሰተኛው መኻከል ያለውን ልዩነት የሚያውቁትን ይፈልጋል፡፡ እያንዳንዳቸው በአስራ ሰባተኛው የዮሐንስ ምዕራፍ የተሰጡትን ትምህርቶች እያጠኑና ከምግባር ላይ እያዋሉ ለዚህ ጊዜ በሚሆነው እውነት ውስጥ ያለውንም ሕያው ኃይማኖት እየጠበቁ ጥንቁቆች መሆ ን አለባቸው፡፡ ልማዶቻችንን (ዓመላችንን) ከክርስቶስ ጸሎት ጋር እንድናስማማ የሚያስችለን ራስን መግታት ያስፈልገናል፡፡ ፭58T239;CCh 87.5

    የመድኃኒታችን ልብ ያምላክን ሐሳብ በከፍታውና በጥልቀቱ ሁሉ ወደ ሚፈጽሙት ተከታዮቹ የሚያመራ ነው፡፡ ምንም እንኳ በዓለም ሁሉ የተበታ ተኑ ቢሆኑ እነሱ ከርሱ ጋር አንድ መሆን አለባቸው፡፡ ዳሩ ግን የራሳቸውን መንገድ ለርሱ መንገድ ለመተው ካልፈቀዱ እግዚአብሔር አንድ ሊያደርጋቸው አይችልም፡፡ ፮68T243;CCh 87.6

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents