Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ምዕራፍ፪—በክርስቶስና በሰይጣን መኻከል ስላለው ታላቅ ተጋድሎ የታያት ራእይ፡፡

    በምስራቃዊ አሜሪካ ክፍል በአንዲት መንደር ውስጥ በነበረችው ትንሽ ትምህርት ቤት በመጋቢት ወር አጋማሽ ላይ ፲፰፻፶፰ ዓ.ም እ.ኤ.አ እሑድ ዕለት ወንዶችም ሴቶችም ተሰብስበው ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ አንድ ወጣት ሰው ስለሞተ ኤልደር ጀምስ ኋይት የቀብሩን ሥነ ሥርዓት ለማካሔድ ይሰብኩ ነበር፡፡ ንግግሩን እንዳበቁ፤ ሚስስ ኢ ጂ ኋይት ለአዘንተኞቹ ጥቂት ቃላት እንድትናገር ተሰማት፡፡ ብድግ አለችና ለአንድ ሁለት ደቂቃዎች ተናግራ ላንድ አፍታ ዝማ አለች፡፡ ሰዎቹ ቀጥሎ የምትናገረውን ለመስማት አተኩረው ይመለከትዋት ነበር፡፡ ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር!››፡፡ ‹‹ክብር ለእግዚአብሔር!›› እያለች ሦስት ጊዜ ደጋግማ ድምጽዋን ከፍ አድርጋ በተናገረችው ንግግር ሰዎቹ ትንሽ ነቃ አሉ፡፡ በዚህን ጊዜ ሚስስ ኋይት ራእይ ታይ ነበረች፡፡CCh 3.1

    ኤልደር ኋይት ለሚስስ ኋይት ስለ ተገለጹላት ራእዮች ለሕዝቡ ነገሩ፡፡ ያሥራ ሰባት ዓመት ልጅ ሳለች ጀምራ ራእይ ይገለጥላት እንደነበር ጨምረው ነገሯቸው፡፡CCh 3.2

    ዓይኖችዋን ገልጣ እሩቅ የምትመለከት መስላ ብትታይም በአካባቢያዋ ያለውንና ስለሚሆነውም ነገር ሁሉ የማታውቅ እንደ ነበረች ነገሯቸው፡፡ በዘኁልቁ ፳፬ ፬ና ፲፮ ቁጥር፤ ‹‹የእግዚአብሔርን ነገር የሚሰማ፡፡ የልዑልን እውቀት የሚያውቅ፡፡ ሁሉ የሚቻለውን ራዕይ ያየው፡፡ የወደቀ ዓይኖቹም የተገለጡ›› እያልን የምናነበውን ጠቀሱ፡፡CCh 3.3

    ራዕይ ስታይ ሳለች ያለ ትንፋሽ እንደ ነበረችና በዳንኤል ምዕ ፲ ቁጥር ፲፯ ዳንኤል ራእይ ሲያይ የነበረበትንም ሁኔታ ገለጹላቸው፡፡ ‹‹ከኃይል አንዳች የለኝምና ትንፋሽም አልቀረልኝም›› አለ፡፡ ከዚያ በኋላ ኤልደር ኋይት ሚስስ ኋይት ራእይ ስታይ ሳለች፤ የፈለጉት ሁሉ ወደርስዋ ቀርበው እንዲመረምሩዋት ጋበዟቸው፡፡ እርሳቸው ለእንዲህ ያለ ምርመራ ሁልጊዜ ነጻነት ይሰጧቸው ነበር፤ በራእይም ሳለች፤ የሚመረምራት ሐኪም ቢገኝ ይደሰቱ ነበር፡፡CCh 3.4

    ሰዎቹ ሲቀርቧት፤ ሚስስ ኋይት የማትተነፍስ መሆንዋን አዩ፤ ሆኖም ልብዋ በደንበኛው ይንር ነበር፤ የጉንጭዋመው ደም ግባት እንደ ተለመደው ነበር፤ መስተዋት ወደ ፊትዋ ቢያቀርቡላት፤ በመስተዋቱ ላይ ምንም እርጥበት አልታየም፡፡ ከዚህ በኋላ ሻማ አመጡና አብርተው ወደ አፍንጫዋና አፍዋ ቀረብ አድርገው ያዙ፡፡ ነበልባሉ ግን ሳይዛባ ቀጥ ብሎ ቆመ፡፡ ሰዎቹ የማትተነፍስ መሆንዋን አወቁ፡፡ በክፍሉ ውስጥ መዛወር ጀመረች፤ ስለተገለጸላትም ባጭሩ ስትናገር ክንዶችዋን ታዝናና ነበር፡፡ እንደ ዳንኤል በመጀመሪያ አቅም አልነበራትም፤ ከዚያ በኋላ ከተፈጥሮ በላይ በሆነ (ሱፐርናቹራል) ኃይል ተሰጣት፡፡ ዳን ፲፣ ፯፣ ፰፣ ፲፰፣ ፲፱ን ተመልከት፡፡ ሚስስ ኋይት ለሁለት ሰዓታት ራእይ ስታይ ነበረች፡፡ ለሁለት ሰዓታት አንድ ጊዜ እንኳ አልተነፈሰችም፡፡ ከዚያ በኋላ ራእዩ ሲያበቃ፤ በኃይል ትንፋሽ ዋጠች፤ ለአንድ ደቂቃ ያህል ቆም ብላ ከዚያ በኋላ እንደገና ተነፈሰች፤ ወዲያውም እንደ ተፈጥሮው መተንፈስ ጀመረች፡፡ በዚያኑ ጊዜ በአካባቢዎችዋ ያሉትንና በዙርያዋ ስለሆነውም ሁሉ ታውቅ ነበር፡፡CCh 3.5

    ሚስስ ማርታ አማዶን ብዙ ጊዜ ሚስስ ኋይትን ራእይ ስታይ ያዩዋት ከዚህ የሚከተለውን ማስረጃ ይሰጣሉ፣CCh 4.1

    ‹‹ራእይ ስታይ ዓይኖችዋ የተገለጡ ነበሩ፡፡ አትተነፍስም ግን ትከሻዎችዋን፣ ክንዶችዋን፣ እጆችዋንም ደህና አድርጋ ታዝናና ነበር፤ ያየችውንም ትገልጽ ነበር፡፡ ማንም እጆችዋን ወይም ክንዶችዋን ለማንቀሳቀስ አይቻለውም ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ ብቻዋን ሆና አንዳንድ ቃላት ስለ ሰማይም ሆነ ስለ ምድር የታያትን ነገር ለመግለጽ ትናገር ነበር፡፡CCh 4.2

    ‹‹ራእይ ስታይ የምትናገረው መጀመሪያ በቅርብ ይመስልና እየቀደም እየራቀ የሚሔድ የሚመስል ‹‹ተመስገን› የሚል ቃል ነበር ይህም አንዳንድ ጊዜ ይደጋገም ነበር፡፡CCh 4.3

    ‹‹በራእይ ጊዜ ባሉት መኻከል ውካታም ሆነ የሚያስፈራ ነገር አልነበረም፡፡ የረጋና ጸጥ ያለ ትርዕይት ነበር፡፡CCh 4.4

    ‹‹ራእዩ ሲያበቃ፤ የሰማያዊንም ብርሃን ማየትን ስታቋርጥ፤ እንደገና ወደ ምድር ስትመለስ፤ እንደ ተፈጥሮዋም በኃይል ስትተነፍስ፣ ‹‹ጨ--ለ---ማ›› (‹‹D—A—R—K››) እያለች ትናገር ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ድኩምና አቅመቢስ ነበረች››፡፡CCh 4.5

    እንዲህ በትምህርት ቤት ውስጥ ወደ ታያት የሁለት ሰዓታት ራእይ ታሪክ እንመለስ፡፡ ስለዚሁ ራእይ ሚስስ ኋይት ቆይታ እንዲህ ስትል ጻፈች፤CCh 4.6

    ‹‹በዘመኑ ሁሉ በክርስቶስና በሰይጣን መኻከል ስላለው ታላቅ ታጋድሎ ከአሥር ዓመት በፊት ያየሁት አብዛኛው ነገር ተደጋግሞ ተነገረኝ፤ ይህንንም እንድጽፍ ተመከርሁ››፡፡CCh 4.7

    በራእይ የምታየውን ነገር ሁሉ እዚያ ሁና የምታየው ይመስላት ነበር፡፡ በመጀመሪያ በሰማይ እንደ ነበረች ሆና፣ የሉሲፈርን (የሚያበራ ኮከብ) ኃጢአትና ውድቀት አየች፡፡ ከዚያ በኋላ ስለ ዓለም ፍጥረትና መጀመሪያዎቹን ወላጆቻችንን በዔድን ቤታቸው ሁነው አየቻቸው፡፡ እባብዋ በፈተነቻቸው ፈተናዎች ወድቀው ከገነት ቤታቸውም ተባርረው አየቻቸው፡፡ በተፋጠነ ተከታታይነት የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እፊትዋ ተገለጸላት፡፡ ስለ እሥራኤልም አበዎችና ነቢያቶች ሁኔታ አየች፡፡ ከዚያ በኋላ ስለ መድኃኒታችን የሱስ ክርስቶስ ሕይወትና ሞት፤ ወደ ሰማይም ስላረገው እርገቱ፤ እዚያም የካሕናት አለቃችን ሁኖ ከዚያ ወዲህ ሲያገለግል የኖረ መሆኑን ጭምር አየች፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ደቀመዛሙርት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ የወንጌልን መልእክት ያደርሱ ዘንድ ሲወጡ አየች፡፡ ይህንንም ወዲያውኑ ክሕደትና የጨለማ ዘመን የተከለው መሆኑ የሚያስገርም ነው፤ ቀጥሎም የፊፎርሜሺንን (የመታደሻ ጊዜ) ጊዜ፤ የከበሩ ወንዶችም ሴቶችም ሕይወታቸውን አጋፍጠው ለእውነት ቁመው፤ በራእይ አየቻቸው፡፡ እ.አ.አ በ((((( ዓ.ም በሰማይ ስለ ተጀመረውና እስከ ጊዜያችን ስላለው የፍርድ ሥራ ከዚያም በኋላ ስለ የወደፊት ሁኔታ፤ በሰማይም ደመናዎች የክርስቶስን መምጣት አየች፡፡ ስለ ሺሁ ዓመትና ስለ አዲሲቱ ምድርም ተገለጸላት፡፡CCh 4.8

    እፊቷ ይህ ሁሉ በአእምሮዋ እንዳለ ሚስስ ኋይት ወደ ቤትዋ ከተመለሰች በኋላ በራእይ ያየችውንና የሰማችውን መጻፍ ጀመረች፡፡ ስድስት ወራት ያህል ቆይታ፤ ክርስቶስና መላእክቱ በሰይጣንና መላእክቱ ላይ የሚያደርጉት ታላቅ ተጋድሎ» የተባለውን አርዕስት የያዘ ከማተሚያ ቤት ፪፻፲፱ ገጽ ያለው ትንሽ ቮሊዩም የሆነ መጽሐፍ ወጣ፡፡ (The Great Controversy Between Christ and His Angels and Satan and His Angels)CCh 5.1

    ይህ መጽሐፍ በቤተ ክርስቲያኒቱ ፊት ስላለው ሁኔታ አጉልቶ ስለሚያመለክትና በምድሩ የመጨረሻ ተጋድሎ ቤተ ክርስቲያኒቱንና ዓለምን ከመንገድ ያሳስት ዘንድ የሚሞክርበትን የሰይጣንን እቅድ (ፕላን) የገለጸ በመሆኑ በደስታ ተቀበሉት፡፡ እንግዲህ አድቬንቲስቶች እግዚአብሔር በሰጣቸው ተስፋ በመጨረሻ ቀናት በትንቢት መንፈስ አማካይነት ስለ ተናገራቸው እንዴት አመስግነው ይሆን፡፡ ስፕሪቹያል ጊፍትስ በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ስለ ታላቁ ተጋድሎ ባጭሩ የተነገረው ቆይቶ ኤርሊ ራይትንግስ በተባለው መጽሐፍ ውስጥ ከግማሹ ይዞ ወደ መጨረሻው ውስጥ እንደገና ታትሞ ዛሬም እዚያው ውስጥ ይገኛል፡፡CCh 5.2

    ግን ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳደገችና ጊዜው እንደ ሔደ መጠን ጌታ በተከታታዮቹ ራእዮች በብዙ ዘርዝሮ ስለ ታላቁ ተጋድሎ ታሪኩን ገለጠ፤ ሚስስ ኋይትም እንደገና በ፲፷፻፸ እና በ፲፷፻፹፬ ዓ.ም. መኻከል (እ.ኤ.አ) በአራት ቮሊዩም የትንቢት መንፈስ (ስቶሪ ኦፍ ፕሮፈሲ) የተባለውን መጽሐፍ ጻፈች፡፡ የደህንነት ታሪክ (ስቶሪ ኦፍ ርደምፕሺን) የተባለ መጽሐፍ ስለ ታላቅ ተጋድሎ ዋና ዋናውን ክፍል የሚገልጸው ከነዚህ መጽሐፎች የተቀዳ ነው፡፡ ይህ ቮሊዩም በብዙ ቋንቋዎች የታተመው ስለ ታላቁ ተጋድሎ በነዚህ ራእዮች የታዩትን ለብዙ ሰዎች የሚያስተምር ነው፡፡ ቆይታ ሚስስ ኋይት ደግሞ በአምስት ቮሊዩም፤ «ኮንፍሊክት ኦፍ ዘ ኤጅስ ሲሪስ” በተባሉት መጻሕፍት ውስጥ ማለት አበውና ነቢያት፤ ነቢያትና ነገሥታት፤ የዘመናት ምኞት (ዘ ዲዛየር ኦፍ ኤጅስ) የሐዋርያት ሥራ (አክትስ ኦፍ ዘ አፖስትልስ) እና ታላቁ ተጋድሎ (ዘ ግሬት ኮንትሮቨርሲ) በተባሉት ውስጥ ዘርዝራ መላውን ተጋድሎ ገልጻለች፡፡CCh 5.3

    እነዚህ መጻሕፍት ከፍጥረት አንስቶ እስከ ክርስቲያናዊ ዘመን ድረስ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እየገለጹ እስከ ፍፃሜ ጊዜ ድረስ ያለውን ታሪክ የሚናገሩ ታላቅ ብርሃንና መደፋፈሪያ ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ መጻሕፍት ሰባተኛዋ ቀን አድቬንቲስቶችን «የብርሃን ልጆች” እና «የቀን ልጆች” ያደርጓቸው ዘንድ የሚፈረዱ ናቸው፡፡ በዚሁ ሁኔታ ነገሩ በእንዲህ ያለ እርግጠኛ ነገር እንደ ተፈጸመ እናያለን፡፡CCh 5.4

    «እግዚአብሔር ነገር አያደርግምና ምሥጢሩን ለባሮቹ ለነቢያት ካልነገረ (አሞጽ ፫፡፯)፡፡ በነዚህ መጻሕፍት ውስጥ ስለ ታላቁ ተጋድሎ ታሪኩን በማውሳት ብርሃን እንደምን እንደመጣላት ስትጽፍ ሚስስ ኋይት እንዲህ አለችን፤CCh 5.5

    «በመልካምና በክፉ መኻኸል ለብዙ ጊዜ የቀጠለው የተጋድሎ ሁኔታ ለእነዚህ መጻሕፍት ጸሐፊ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን ተገለጡላት፡፡ በልዩ ልዩ ዘመናት የሕይወት አለቃና የደህንነት ዋና በሆነው በክርስቶስ መኻከልና በሰይጣን እሱም የክፉው አለቃ የኃጢአትም ዋና መጀመሪያ የእግዚአብሔርን ሕግ ተላላፊ ከሆነው መኻኸል ሲደረግ የነበረውን ታላቅ ተጋድሎ እንድመለከት በየጊዜው ተፈቀደልኝ፡፡ …CCh 5.6

    «የቃሉን እውነት ያለፉትንና የወደፊቱን ሁኔታዎች የእግዚአብሔር መንፈስ በገለጠልኝ ጊዜ የተገለጠልኝን ለሌሎች አስታውቅ ዘንድ፤ ማለት ባለፉት ዘመናትም የሆነውን የተጋድሎውን ታሪክ እንዳመለክት፤ ደግሞ በተለይ እየተፋጠነ በቅርቡ በሚሆነው የወደፊቱ ተጋድሎ ላይ ብርሃንን ለማብራት እንዳስታውቅ ታዝዣለሁ” ፡፡CCh 6.1