Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወደ አዳዲስ ስፍራዎች በመዛወር መመስከር፡፡

    ሕዝቡ ተከማችው (ታፍገው) ወይም ትላልቅ ጉባዔዎች ሆነው ባንድነት ይቀመጡ ዘንድ የእግዚአብሔር ሐሳብ አይደለም፡፡ በክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በምድር ላይ የርሱ እንደራሴዎች ናቸው ፤ እግዚአብሔርም ባገር ሁሉ በመናገሻ ከተማዎች በከተሞችና በመንደሮች ውስጥ ፤ በዓለም ጨለማ ውስጥ ብርሃናት ሆነው ይበታተኑ ዘንድ ያስባል፡፡ የሚመጣው መድኅን መምጫው በጣም ቅርብ መሆኑን በኃይማኖታቸውና በሥራቸው እየመሰከሩ ለአምላክ ወንጌላውያን መሆን አለባቸው፡፡CCh 58.4

    ፈቃደኞች ሰራተኞች የቤተ ክርስቲያናችን አባሎች ገና በትንሹ የጀመሩትን ሥራ ሊፈጽሙ ይችላሉ፡፡ ማንም ዓለማዊ ጥቅም ለማግኘት ብሎ ወደ አዳዲስ ሥፍራዎች መዛወር አይገባውም፤ ግን ለኑሮ የሚሆነውን ለማግኘት ክፍት በሆነ ሥፍራ ቤተሰቦች በእውነት ደህና ሆነው የተመሠቱ አንድ ወይም ሁለት ቤተሰቦች ወንጌላውያን ሆነው እንዲሠሩ ባንድ ሠፍራ ይግቡ፡፡ እነሱም ለነፍሳት ፍቅር ያላቸው ፤ ለነሱም የሥራ ሸክም እንዳለባቸው ሊሰማቸው ይገባል፤ ወደ እውነትም እንዴት እንደሚያመጧቸው ማጥናት አለባቸው፡፡ ጽሑፎቻችንን ሊያድሉ፤ በቤቶቻቸውም የጸሎት ስብሰባዎች ሊያደርጉ ከጐበቤቶቻቸውም ጋር መተዋወቅና ወደነዚሁ ስብሰባዎች ይመጡ ዘንድ ሊያድሟቸው ይችላል፡፡ በእንዲህ ብርሃናቸው በመልካም ሥራዎች እንዲያበራ ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡CCh 59.1

    ሰራተኞች እያለቀሱ እየጸለዩም ፤ ለባልንጀሮቻቸውም ደህንነት እየሰሩ በእግዚአብሔር ብቻ ጸንተው ይቁሙ፡፡ እሽቅድምድም የምትሮጥ ለማይጠፋውም አክሊሊ የምትጣጣር መሆንህን አስብ፡፡ ብዙዎች ከአምላክ ሞገሥ ይልቅ ፤ የሰዎችን ምሥጋና ሊቀበሉ ሳለ፤ በትህትና ትሰራ ዘንድ ያንተው ይሁንልህ፡፡ በጸጋው ዙፋን ፊት ባልንጀሮችህን እንድታቀርብና ልባቸውንም እንዲነካ በአምላክ ታማጽን ዘንድ ኃይማኖት እንዲኖርህ ተማር፡፡ በዚህ ጐዳና ፍሬ ያለው ወንጌላዊ ሥራ ይሰራል፡፡ አንዳንዶች ሰባኪውን ወይም መጽሐፍ ሻጩን የማይሰሙ በዚህ ይደረስባቸው ይሆናል፡፡ በአዳዲስም ስፍራዎች እንዲሁ የሚሠሩ ወደ ሰዎች የሚቀርቡበትን የተሻለ መንገድ አውቀው ለሌሎችም ሰራተኞች መንገዱን ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡ ፲፮168T244, 245CCh 59.2

    ጐረቤቶችህን ጐብኝና ለነፍሳቸው ደህንነት ማሰብህን (መደሰትህን) አሳያቸው፡፡ መንፈሳዊ ኃይልህን ሁሉ ለሥራ አነቃቃው፡፡ የሁሉ ነገሮች ፍጻሜ ቅርብ እንደሆነ የምትጐበኛቸው ንገራቸው፡፡ ጌታ የሱስ ክርስቶስ የልባቸውን በር ይከፍትና የጸና ሐሳብ በልባቸው ያሳትፍላቸዋል፡፡CCh 59.3

    በዕለት ሥራቸው ላይ ሳሉ እንኳ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሌሎችን ወደ ክርስቶስ ሊመሩ ይችላሉ፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ ሳለ ፤ መድኃኒታችን ባጠገባቸው ቀርቦአቸው እንዳለው የተከበረ ማረጋገጫ ይኖራቸዋል፡፡ በደካማ ጥረታቸው ላይ ይታመኑ ዘንድ የተተው እንደሆኑ ማሰብ አያስፈልጋቸውም፡፡ ክርስቶስ በጨለማ ውስጥ ያሉትን የሚታገሉትን ድሆች ነፍሳት የሚያለመልሙና የሚያደፋፍሩ፤ የሚያበረታቱትንም ቃላት እንዲናገሩ ይሰጣቸዋል፡፡ የመድኅን ተስፋ መፈጸሙን ሲገነዘቡ፤ የገዛ ራሳቸው ኃይማኖት ይበረታል፡፡ ለሌሎችም በረከት መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ግን ለክርስቶስም የሚያደርጉት ሥራ ለራሳቸው በረከትን ያመጣላቸዋል፡፡ ፲፯፤179T3S, 39; CCh 59.4

    መጽሐፍ ቅዱስን እንደሚነበበው አድርጎ ለሕዝብ በማቅረብ ታላቅ ሥራ ሊሰራ ይቻላል፡፡ ያምላክን ቃል ወደየሰው በር ውሰድ ፤ በየሰው ሕሊና ግልጽ የሆነውን ንግግሮቹን አሳትፍለት፤ «መጻሕፍትን እሹ» (ዮሐንስ ፭፡፴፱) ሲል ጌታችን የተናገረውን ትእዛዙን ሁሉ ደጋግምላቸው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዳለ እንዲቀበሉት፤ መለኮታዊ ብርሃንም እንዲለምኑ ፤ ከዚያ በኋላ ብርሃኑ ሲበራ ክቡር የሆነውን እያንዳንዱን ጮራ በደስታ ተቀብለው ሳይፈሩ ለውጤቱ እንዲጠባበቁ ምከራቸው፡፡ ፲፰ ፤185T388;CCh 59.5

    በቤተ ክርስቲያኖቻችን አባሎች መኻከል የመጽሐፍ ቅዱስን ንባቦች በመስጠትና ጽሑፎችን በማደል ረገድ በበለጠው የቤት ለቤት ሥራ ሊሆን ይገባል፡፡ ክርስቲያናዊ ጠባይ ያማረና ፍጹም ሁኖ ሊቀረጽ የሚቻለው ሰብዓዊ ወኪል (ሠራተኛ) ራስን ባለመውደድ እውነትን በማወጅና ያምላክን ጉዳይ በገንዘብ በመደገፍ ይሰራ ዘንድ እንደ እድል አድርጎ ሲቆጥረው ብዠ ነው፡፡ ነፍሳችንን በአምላክ ፍቅር እየጠበቅን ቀንም ሳለ እየሰራንና ማናቸውንም እየተከታተለ የሚመጣብንን ተግባር እናደርግ ዘንድ ጌታ የሰጠንን ችሎታ (ገንዘብ) እየተጠቀምንበት በውኃዎች አጠገብ ሁሉ መዝራት አለብን፡፡ እጃችን ያደርግ ዘንድ የሚያገኘውን ሁሉ በታማኝነት መሥራት አለብን፤ መሥዋዕት ለማድረግ የተጠራንበትን ሁሉ በደስታ ማድረግ አለበን፡፡ በውኃዎች አጠገብ ሁሉ ስንዘራ ፤ «በበረከትም የዘራ በበረከትም የሚያጭድ” መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ፪ ቆሮንቶስ ፱፡ ፮ ፡፡ ፲፱ ፤199T127;CCh 60.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents