Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    በክርስቶስ የተገለጸው እግዚአብሔር አብ፡፡

    አካል ያለው አምላክ መሆኑን እግዚአብሔር እራሱን በልጁ ገለጸ፡፡ የሱስ የአብ የክብሩ ብርሃን ‹‹የአካሉም ምሳሌ›› (ዕብ (፣() የሰውን አካል ለብሶ በምድር ነበር፡፡ የግል አዳኛችን ወደ ዓለም መጣ፡፡ የግል አዳናችንም ሁኖ ወደ ላይም አረገ፡፡ የግል አዳኛችንም ሁኖ በሰማያዊ ግቢዎች ውስጥ ያማልደናል (ይጸልይልናል)፡፡ ‹‹አንድ የሰው ልጅ የሚመስል›› (ራእይ (፣(() ለኛ ሲል በአምላክ ዙፋን ፊት ያገለግላል፡፡CCh 135.3

    ክርስቶስ የዓለም ብርሃን የሚያብረቀርቀውን የመለኮትነቱን ብርሃን ጋርዶ በሰዎች መኻከል ሰው ሁኖ ለመኖር መጣ ሳይጠፉ ከፈጣሪ ጋር ይተዋወቁ ዘንድ፡፡ እርሱ በክርስቶስ አማካይነት ከሚገጸለው በቀር ማነም ሰው በማንኛውም ጊዜ አምላክን አላየውም፡፡CCh 135.4

    ክርስቶስ እግዚአብሔር እንዲያውቁ የሚፈልግባቸውን ለሰብዓዊ ፍጥረቶች ሊያስተምር መጣ፡፡ በላይ በሰማዮች በምድር በሰፊው የውቂያኖስ ውኃዎች ውስጥ ያምላክን የእጁን ሥራ እናያለን፡፡ የተፈጠሩት ነገሮች ሁሉ ለኃይሉ፣ ለጥበቡ፣ ለፍቅሩ ይመሰክራሉ፡፡ ነገር ግን በክርስቶስ እንደሚገለጸው አድርገን ያምላክን መልክ ከከዋክብት ወይም ከውቂያኖስ ወይንም ከፍዋፍዋቴ ልንማር (ልናውቅ) አንችልም፡፡CCh 135.5

    እግዚአብሔር መልኩንና ባሕርዩን ያመለክት ዘንድ ከተፈጥሮ በጣም ግልጽ የሆነው ገለጻ አስፈላጊ መሆኑን አየ፡፡ የማይታየው ያምላክ ባሕርይና ጠባ በሰብዓዊ አተያየት ሊታይ በተቻለው መጠን ይገልጽ ዘንድ ልጁን ወደ ዓለም ላከው፡፡CCh 135.6

    እግዚአብሔር በተፈጥሮ ነገሮች ውስጥ ማለት በአበባ፣ በዛፍ፣ በሣር ቅንጣት ውስጥ አካል ያለው ሆኖ የሚኖር በመሆን የተመሰለ (የተመለከተ) እንዲሆን ፈልጓዋልን( የሱስ በምድር በነበረ ጊዜ ስለዚሁ ለደቀ መዛሙርቱ ይናገር አልነበረምን( በክርስቶስ ትምህርት ውስጥ እግዚአብሔር እንደዚህ ከቶ አልተነገረም፡፡ ክርስቶስና ሐዋርያት አካል ያለው አምላክ መኖሩን ገልጸው እውነቱን አስተምረዋል፡፡CCh 135.7

    ክርስቶስ በሰብዓዊ ፍጥረቶች ሳይጠፉ ለመቀበል በሚችሉበት ሁናቴ ስለ እግዚአብሔር ሁሉንም ገለጻ፡፡ እርሱ መለኮታዊ መምሕር የሚያብራራው ነው፡፡ እግዚአብሔር በክርስቶስና በተጻፈው ቃሉ አማካይነት ከተደረጉት ገለጻዎች ሌላ ሌላዎች ገለጻዎች ሊያደርግልን የሚያስፈልገን መሆኑን አስቦ ቢሆን ኑሮ በሰጣቸው ነበር፡፡CCh 135.8