Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    መክሊቶችህ ለፍላጎቱ የሚስማማ ነው፡፡

    ጌታ በታላቅ ሐሳቡ ለሁሉም ሥፍራ አለው፡ የማያስፈልጉ መክሊቶች አይሰጡም፡፡ መክሊቱ ትንሽም ቢሆን፤ እግዚአብሔር ለርሱ ሥፍራ አለው፤ ያው አንዱ መክሊት በታማኝነት ቢጠቀሙበት፤ ሊየደርግ የሚገባውን አምላክ የሚያስበውን ያንኑ ሥራ ይሠራል፡፡ የዝቅተኛው (የትሁቱ) ባለጎጆ መክሊቶች በቤት ለቤት ሥራ የሚያስፈልጉ ናቸው፤ ከብሩሆቹ ሥጦታዎች ይበልጥ በዚህ ሥራ ሊፈጽም ይችላል፡፡ ፬49T37,38;CCh 63.1

    እግዚአብሔር እንደሚያመለክታቸው ሰዎች ኃይሎቻቸውን ሲጠቀሙበት መክሊቶቻቸው ይጨመራሉ፤ ችሎታቸው ይስፋፋል፤ የጠፋውንም ለማዳን ሰማያዊ ጥበብ ይኖራቸዋል፡፡ ግን የቤተ ክርስቲያን አባሎች ለሌሎች ያካፍሉ ዘንድ እግዚአብሔር በሰጣቸው ኃላፊነት ችላ ባዮችና ግድየለሾች ሲሆኑ ሳለ የሰማይን በረከቶች ለመቀበል እንደምን ተስፋ ሊያደርጉ ይችላሉ ክርስቲያኖች ነን የሚሉ በጨለማ ውስጥ ላሉት ሊያብራሩላቸው ምንም ሸክም የማይሰማቸው ሲሆኑ ጸጋንና ዕውቀትን ማካፈል ሲተው ማስተልላቸው ይቀነሳል የሰማያዊን ሥጦታ ብልጽግና ከቁም ነገር አይቆጥሩትም፤ ራሳቸው ከዋጋ ሳይቆጥሩት ቀርተው ለሌሎች መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ሳይገነዘቡ የቀራሉ፡፡CCh 63.2

    ትላልቅ ቤተ ክርስቲያናት በልዩ ልዩ ሥፍራዎች ተሰብስበው እናያለን፡፡ አባሎቻቸው የእውነትን ዕውቀት አግኝተዋል፤ ብዙዎችም ብርሃንን ለማካፈል ሳይሹ የሕይወትን ቃል ለመስማት ደስ ይላቸዋል፡፡ ለሥራው ግሥጋሤ ትንሽ ኃላፊነት ነፍሳትንም በማዳን ረገድ ትንሽ ሐሳብ ይሰማቸዋል በዓለማዊ ነገሮች በቅናት ተመልተዋል፤ ኃይማኖታቸውን ግን በሥራቸው ውስጥ አያገቡም፡፡ ‹‹ኃይማኖት ፤ኃይማኖት ነው፤ ሥራው ሥራ ነው›› ይላሉ፡፡ እያንዳንዳቸው ትክክለኛ (የተገባ) ቦታ እንዳላቸው ይናገራሉ ግን ‹‹ይለያዩ›› ይላሉ፡፡CCh 63.3

    ምቹ ጊዜያቸውን ችላ ስላሉና መብቶቻቸውን ስለ ነቀፉ፤ የእነዚህ ቤተ ክርስያናት አባሎች ‹በጸጋ ብዚ በጌታችንም በመድኃኒታችንም በየሱስ ክርስቶስ እውቀት› እንዳለው የሚያደጉ አይደሉም፡ ፪ ጴጥሮስ ፫፡፲፰፡፡ ስለዚህ በሃይማኖት ደካሞች በዕውቀትም ጐደሎዎች፤ በልምምድም /በአክስፒሪየንስ/ ልጆች ናቸው፡ በእውነት ሥር የሰደዱና የተመሠረቱ አይደለም፡፡ በዙሁ የቀሩ እንደሆን ብዙዎቹ የመጨረሻዎች ቀናት ማታለያዎች በእርግጥ ያታልላቸዋል፤ እውነትን ከአሰት ይለዩ ዘንድ መንፈሳዊ ዓይን የላቸውም፡፭56T424,425;CCh 63.4