Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሰንበት ትምህርት፡፡

    የሰንበት ትምህርት የሥራው ዓላማ የነፍሳት መሰብሰብ ሊሆን ይገባል፡፡ የሥራው ሥርዓት የሚፈለጉት ችሎታዎች ሁሉ ምንም ስህተት የሌለበት ይሆን ይሆናል፤ ዳሩ ግን ልጆችና ወጣቶች ወደ ክርስቶስ ባይመጡ ፤ የሚሰጣቸው ትምህርት ውድቅ ነው ፤ ነፍሳት ወደ ክርስቶስ ባይሳቡ በዘልማድ ሃይማኖት ተመርተው የበለጠውን የማይሳተፉት ይሆናሉ፡፡ ስለዚህ አስተማሪ የሆነ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን የልባቸውን በር ሲመታ ሳለ፤ አብሮዋቸው ሊሠራ ይገባዋል፡፡ ተማሪዎቹ የመንፈስ ቅዱስን ተማኅጽኖ ቢቀበሉና የሱስ ወደ ውስጥ እንዲገባ የልባቸውር በር ቢከፍቱ ፤ የእግዚአብሔርን ነገሮች ያስተውሉ ዘንድ እርሱ ልቦናቸውን ይከፍታል፡፡ የአስተማሪ ሥራ ቀላል ሥራ ነው ፤ ግን በየሱስ መንፈስ ቢሠራ በእግዚአብሔር መንፈስ ሥራው ጥልቀትና ችሎታ ይጨምርለታል፡፡CCh 48.4

    ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር ትማሩ ዘንድ ለሰንበት ትምህርት ጥናት በየቀኑ ትንሽ ጊዜ ለይታችሁ ወስኑ፡፡ ለተከበሩት የተቀደሰው የታሪክ ትምህርቶች የተወሰነውን ሰዓት ከመሠዋት ካስፈለገ ማኅበራዊ (ሶሺያል) ጉብኝትን ተው፡፡ ወላጆችም ሆነ ልጆች ከዚህ ጥናት ጥቅም ይቀበላሉ፡፡ ከትምህርቱ ጋር የተያያዙት ዋና ዋናዎቹ የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላት በቃል ይጠኑ ፤ ይኸውም እንደ ተግባር ሁኖ አይደለም፤ መታደል ነው እንጂ፡፡ በመጀመሪያ መታሰቢያው ቃል በትክክል ባይነገርም ፤ ልምምድ በማድረግ ብርታት ይገኛል ፤ እንዲሁም ከጊዜ በኋላ የተከበሩትን የእውነት ቃላት በመሳተፋችሁ ትደሰቱበታላችሁ፡፡ ይህ ልምድ ለሃይማኖታዊ እድገት እጅግ ዋጋ ያለው እርዳታ መሆኑን ያስረዳል፡፡CCh 48.5

    በቤተሰቦቻችሁ ውስጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማጥናት ረገድ ሥርዓቱን ተጠባበቁ፡፡ ስለ ማናቸውም ሥጋዊ ጉዳይ ችላ በሉት፡፡ የማያስፈልገውን ስፌት ፤ በማዕድ የሚቀርበውንም የማያሻ ጉዳይ ሁሉ ተውት ፤ ግን ነፍስ በሕይወት እንጀራ መመገቡን እርግጠኞች ሁኑ፡፡ በየቀኑ በሚያስደስት ሶሺያዊ (ማኅበራዊ) ሁናኔ አንዲት ሰዓት እንኳ ወይም ግማሽ ሰዓት ቢሆን ለእግዚአብሔር ቃል ማጥኛ ቀድሶ የመስጠትን መልካም ውጤት ለመገመት የማይቻል ነው፡፡ በልዩ ልዩ ጊዜያትና ሁኔታዎች ስለ ተሰጠው አርእስት የተነገረውን ሁሉ ባንድነት አቀናብራችሁ መጽሐፍ ቅዱስን የራሱ ገላጭ (ተርጓሚ) አድርጉት ለጠሪዎች ወይም ለጐብኚዎች ብላችሁ የቤታችሁን የማጥኛ ክፍል አታቋርጡ፡፡ በትምህርት ጊዜ ቢገቡ፤ በዚሁ ተካፋይ እንዲሆኑ አድሟቸው፡፡ የዓለምን ትርፍ ወይም ተድላዎች ከማግኘት ይልቅ የእገዚአብሔርን ቃል ዕውቀት ማግኘት የበለጠውን ጠቃሚ መሆኑን የምታስቡ መሆናችሁ ይታይ፡፡CCh 49.1

    በአንዳንድ (የሰንበት) ትምህርቶች ፤ ትምህርቱን ከትምህርቱ ጽሁፍ ውስጥ የማንበብ ልምድ የሚያይል ነው በማለቴ አዝናለሁ፡፡ ይህ ሊሆን አይገባም፡፡ ብዙ ጊዜ በማያስፈልግና እንዲያውም በኃጢአት የሚጠቀሙበት ጊዜ ቅዱሣት መጻሕፍትን ለማጥናት ተሰጥቶ ቢሆን ኑሮ እንዲህ ሊሆን አያሻውም ነበር፡፡ አስተማሮቹ ወይም ተማሮቹ ከቀኑ ትምህርት ቤት ባነሰው ፍጹምነት የለም፡፡ እጅግ ጠቃሚዎች ስለ ሆኑት አርዕስቶች የሚያወሱ ስለሆነ፤ እንዲያውም በበለጠው ሊማሩዋቸው የተገኘ ነው፡፡ በዚህ ላይ ችላ ማለት እግዚአብሔርን ማሳዘን ነው፡፡CCh 49.2

    የሰንበት ትምህርትን የሚያስተምሩ ሰሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የቃል አድራጊዎች ደግሞ እንዲሆኑ ልባቸው በእግዚአብሔር እውነት የጋለና የጠነከረ መሆን አለበት፡፡ ቅርንጫፎች ከወይኑ ጉንድ እንደሚመገቡ ከክርስቶስ መመገብ አለባቸው፡፡ ልባቸው እንደ ክቡር አትክልቶች ቆባዎቸቸው እንደሚከፈቱና ተንሰራፍተው በእግዚአብሔር አትክልት ቦታ ውስጥ አስደሳች ሽታ እንዳላቸው አበቦች ይሆን ዘንድ የሰማያዊ ጸጋ ጤዛዎች በነሱ ላይ ማረፍ አለባቸው፡፡ አስተማሮች የእግዚአብሔርን ቃል በትጋት የሚማሩ ትጉዎች ተማሮች መሆን ፤ ዘወትርም በክርስቶስ ትምህርት ቤት ዕለታዊ ትምህርቶችን በውነት የሚማሩ መሆናቸውንና ታላቅ አባት የዓለምም ብርሃን ከሆነው አምላክ የተቀበሉትን ብርሃን ለሌሎች ለመናገር የሚችሉ መሆናቸውን መግለጽ አለባቸው፡፡CCh 49.3

    በየጊዜው አለቆችን በመምረጥ ረገድ የግል ምርጫዎች የማይገቡ መሆናቸውን እርግጠኞች ሁኑ፤ ዳሩ ግን እግዚአብሔርን የሚያፈቅሩና የሚፈሩ መሆ ናቸውን የምታምኑዋቸውን እግዚአብሔርን መካሪያቸው የሚያደርጉትን በመተማመኛ ሥራ (ማዕረግ) ላይ አድርጓቸዋል፡፡ ፲102TT557—566;CCh 49.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents