Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዳንኤል የተቀደሰ ሕይወት በመኖር ያሳየው አርአያ፡፡

    የዳንኤል ሕይወት ስለ ተቀደሰው ጠባይ በሚመለከተው ረገድ በመንፈስ የተጻፈለት መግለጫ ነው፡፡ ለሁሉ በተለይም ለወጣቶች ትምህርትን የሚሰጣቸው ነው፡፡ ከአምላክ ፍላጎቶች ጋር በጥብቅ መስማማት ለአካልና ለአእምሮ ጤንነት ጠቃሚ ነው፡፡ እጅግ ከፍ ያለ የሞራልና (የግብርገብነት) የአእምሮ ግቦች ለመድረስ ከአምላክ ጥበብንና ኃይልን መሻትና በሕይወት ልምዶች ሁሉ ላይ ጥብቅ የሆነ መሻትን መግዛት (መመጠኛ ኑሮ) ለማድረግ ያስፈልጋል፡፡8SL23;CCh 96.1

    የዳንኤል ጠባይ እጅግ ነውር የሌለው እንደ መሆኑ መጠን በጠላቶቹ የተሰነዘረበት ጥላቻ እጅግ ታላቅ ነበር፡፡ በግብረገብ ጠባዩ ላይ ምንም ነገር ሊያገኙ ባለመቻላቸው ወይም ከሥራው ያሰናብቱት ዘንድ ለወቀሳ የሚሆን ነገር ለማግኘት ባለመቻላቸው በዕብደት ተመሉ፡፡ ‹‹የዚያን ጊዜ እሊያ ሰዎች በዚህ በዳንኤል ላይ ከአምላኩ ሕግ በቀር ሌላ ምክንያት አናገኝበትም አሉ››፡፡ (ዳንኤል፮፣፭)CCh 96.2

    እዚህ ለክረስቲያኖች ሁሉ እንዴት ያለ ትምህርት ቀርቧል፡፡ ዕለት ዕለት በዳንኤል ላይ ብርቱ የሆኑ የቅናት ዓይኖቻቸውን አተኩሩበት፡፡ የነሱ መተባበቅ በጥላቻ ተመላ ሆኖም ከቃሉ ወይም ከሕይወቱ አድራጎት ስህተት ሊገልጹበት አልቻሉም፡፡ ቢሆንም የቅድስና ኑሮ እንደሚኖር አልተናገረም ነገር ግን እጅግ የተሻለውን አደረገ ይኸውም የታማንነትና የቅድስና ኑሮ ኖረ፡፡CCh 96.3

    አዋጁ ከንጉሡ ይወጣል፡፡ ዳንኤልም ያጠፋል ዘንድ የጠላቶቹን ሐሳብ ያውቃል፡፡ ነገር ግን እርሱ በአንድም ነገር እርምጃውን ኤለውጥም፡፡ በጸጥታ (በርጋታ) የተለመዱትን ተግባሮቹን ያደርጋል፣ በጸሎትም ሰዓት ወደ ክፍሉ ይገባና መስኮቶቹን ወደ የሩሳሌም ተከፍተው ለሰማይ አምላክ ልመናዎቹን ያቀርባል፡፡ ምድራዊ ባለሥልጣን በርሱና በአምላኩ መኻከል ጣልቃ ገብቶ ለማን ያቀርባል፡፡ ምድራዊ ባለሥልጣን በርሱና በአምላኩ መኻከል ጣልቃ ገብቶ ለማን መጸለይ የሚገባው ወይንም የማገባው መሆኑን ሊናገረው መብት እንደሌለው ሳፈራ በሥራው እርምጃ ይናገራል፡፡ የተከበረው የፕሪንሲፕል ሰው! እርሱ ዛሬ ለክርስቲያን ድፍረትና ታማኝነት የተመሰገነ ምሳሌ ሆኖ ይቆማል፡፡ ለቅድስና ኑሮው ሞት መቀጮው መሆኑን ቢያውቅም እንኳ ከነልቡ ወደ አምላኩ ይዞራል፡፡CCh 96.4

    ‹‹የዚያን ጊዜ ንጉሡ አዘዘ ዳነኤልንም አመጡት በአናብስት ጉድጓድም ጣሉት፡፡ ንጉሰሡም ዳንኤልን ተናገረው አለውም፡፡ አምላክህ ሁልጊዜ የምታመልከው እርሱ ያድንህ›› (ቁ፲፯)፡፡ በማለዳ ጥዋት ንጉሡ ወደ አናብስት ዋሻ ፈጥኖ ሔዶ ‹‹ዳንኤል ሆይ የሕያው የእግዚአብሔር ባሪያ አምላክህ አንተ ሁልጊዜ የምታመልከው ከአናብስት ያድንህ ዘንድ ቻለ›› (ቁ 20) ሲል ጮሆ ተናገረ፡፡ ሲመልስለት የነቢዩም ድምፅ ‹‹ንጉሥ ሆይ ለዘላለም ሕያው ሁን አምላኬ መልእክተኛውን ልኮ ያናብስት አፍ ዘጋ አልጎዱኝምም በፊቴ እውነት ተገኝቶብኛልና ደግሞም ንጉሥ ሆይ በፊትህ አልበደልሁም›› የሚል ተሰማ፡፡CCh 96.5

    የዚያን ጊዜ ንጉሡ ስለርሱ ታላቅ ደስታ ደስ አለው ዳንኤልንም ከጉድጓዱ እንዲያወጡት አዘዘ፡፡ ዳንኤልም ከጉድጓዱ ወጣ አንዳችም አልተጎዳም በአምላኩ ታምንዋልና›› (ቁጥር ፳፪፣፳፫)፡፡ በእንዲህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ዳነ፡፡ ጠላቶቹ እርሱን ለማጥፋት ጠመዱት ወጥመድ ለገዛ ራሳቸው ማጥፊያ መሆኑን አስዳቸው፡፡ በንጉሡ ትእዛዝ ወደ ጉድጓዱ ተጣሉ በዱር አውሬዎችም ወዲያው ተዋጡ፡፡CCh 96.6

    የሰብዓ ዓመታት ምርኮ ዘመን ማለቂያው ጊዜ ሲቃረብ የዳንኤል ሐሳብ ወደ ኤርምያ ትንቢቶች በጣም አዘነበለ፡፡CCh 97.1

    ዳንኤል በጌታ ፊት ስለ ታማኝነቱ የሚናገር አይደለም፡፡ ንጹህና ቅዱስ እንደሆነ በመናገር ፈንታ ይህ የተከበረው ነቢይ በርግጥ ኃጢአተና ከሆነው እሥራኤል ጋር በትህትና ራሱነ አንድ ያደርጋል፡፡ በቀትር ጊዜ በሰማዮች ላይ የሚያበራው ጸሐይ ብርሃኑ ከደካማዋ (ከዝቅተኛዋ) ኮከብ ይበልጥ የሚያበራ እንደሆነ እግዚአብሔርም የሰጠው ጥበብ ከታላላቆቹ የዓለም ሰዎች እጅግ የሚበልጥ ነበር፡፡ ሆኖም ከዚህ ሰው ከናፍር የቀረበው ጸሎት በሰማይ አምላክ ዘንድ እጅግ የተከበረ መሆኑን አስብ፡፡ በጠለቀ ትህትና በእንባና ልብን በመስበር ለራሱና ለሕዝቡ ይለምናል፡፡ ያልተገባ መሆኑን እየተናዘዘና የአምላክን ታላቅነትና ግርማነት እያስታወቀ ነፍሱን በአምላክ ፊት ይገልጣል፡፡CCh 97.2

    ‹‹ዳንኤል ጸሎቱ ወደ ላይ ሲቀርብለት ሳለ መልአኩ ገብርኤል ጸሎቱ እንደተሰማለትና መልስ እንደመጣለት ይነግረው ዘንድ ፈጥኖ ከሰማያዊ ግቢዎች መጣ፡፡ ኃያሉ መልአክ ብልሃትና ማስተዋል ሊሰጠው የወደፊቱንም ዘመኖች ምሥጢሮች እፊቱ ይገልጥለት ዘንድ ተልኮ ነበር፡፡ እንዲሁም እውነቱን ለማወቅና ለማስተዋል አጥብቆ ሲሻ ዳንኤል ከተላከው የሰማይ መልእክተና ጋር ንግግር አደረገ፡፡CCh 97.3

    ለጸሎቱ መልስ የሚሆን ዳንኤለ ለርሱና ለሕዝቡ በብዙ ያስፈልጋቸው የነበረውን ብርሃንና እውነት ብቻ የተቀበለ ሳይሆን ግን ስለ ወዲት ታላላቅ ሁኔታዎች እስከ ዓለም መድኅን ዳግመና ምጽዓት እንኳ ድረስ ያለውንም ትርዕት (ሁኔታ ነው፡፡ ቅዱሳን መጻሕፍትን ለመመርመር ወይም የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት አጣርተው ለማስተዋል ከአምላክ ጋር በጸሎት ለመታገል ምንም ምኞች ሳይኖራቸው ለመቀደስ የሚፈልጉ እውነተና ቅድስና ምን ማለት እንደሆነ አያውቁም፡፡CCh 97.4

    ዳንኤል ከአምላክ ጋር ተነጋገረ፡፡ ሰማ በፊቱ ተከፈተለት፡፡ ነገር ግን ከፍ ያለ ክብር የተሰጠው የትህትናውና ከልብ የመሻት ውጤት ነበር፡፡ ያምላክን ቃል በሙሉ ልብ የሚያምኑ ፈቃዱን ለማወቅ የሚራቡና የሚጾሙ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር የእውነት እንዲጨብጥና እንዲያስተውል ለሰው አእምሮ ኃይል ይሰጣል፡፡CCh 97.5

    በዓለም መድኅን የተገለጹት እውነቶች እንደተሰወሩት መዝገቦች እውነትን ለሚፈልጉ የሚሆኑ ናቸው፡፡ ዳንኤል ሽማግሌ ሰው ነበር፡፡ ሕይወቱነ በአረማዊ ግቢ ማባበያዎቸ መኻከል ያሳለፈ ነበር ሐሳቡንም የታላቁ መንግሥት ጉዳዮች ተጫጭኖበት ነበር፡፡ ሆኖም ነፍሱን በአምላክ ፊት ለማቅረብና የልኡል አምላክ ሐሳብ ዕውቀት ይሻ ዘንድ ከነዚህ ሁሉ ዘወር ይላል፡፡ ለልመናዎቹም መልስ ተገ ኝቶለት በመጨረሻ ቀናት ለሚኖሩ ከሰማያዊ ግቢዎች ብርሃን ተነገረው፡፡ እንግዲህ ከሰማይ የመጣልንን እውነት እንድናስተውል ማስተዋላችንን ይከፍትልን ዘንድ እንደምን አምላክን ከልብ መሻት ይገባናል፡፡CCh 97.6

    ዳንኤል የተቀደሰ የልዑል አምላክ አገልጋ ነበር፡፡ ረዘም ያለ ሕይወቱ ለጌታው በተከበሩት የአገልግሎት አድራጎቶቸ የተመላ ነበር፡፡ የጠባይ ንጽሕናና ውልውል የሌለበት ታማኝነት ከልቡ ትህትናና በአምላክ ፊት ከመጠጠቱ ጋር እኩል ለእኩል ነው፡፡ ስለዚህ የዳንኤል ሕይወት ስለ እውነተኛ ቅድስና በመንፈስ የተጻፈ መግለጫ መሆኑን ደጋግመን እንናገራለን፡፡፱9SL42— 52;CCh 98.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents