Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    «ኑ እንስገድ በእግዚአብሔር ፊት» ፡፡

    ክርስቶስ «ሁለት ሁነው ወይም ሶስት ሁነው በስሜ ወደ ተከማቹበት ከዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና» አለ፡፡ ማቴዎስ ፲፰ ፡፳፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ምዕመናን ባሉበት የጌታን ተስፋ ይለምኑ ዘንድ በሰንበት ባንድነት ይሰብሰቡ ፤CCh 47.3

    ጥቂቶች ሰዎች (ጓደኞች) በተቀደሰው ቀኑ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ የተሰበሰቡት የበለጸገውን ያምላክን በረከቶች ለመለመን መብት አላቸው፡፡ ጌታ የሱስ በጉባዔያቸው የተከበረ እንግዳ መሆኑን ማመን አለባቸው፡፡ የተቀደሰውን ሰንበት የሚጠብቅ እውነተኛ ሰጋጅ ሁሉ «እኔ እግዚአብሔር የምቀድሳችሁ እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ” ያለውን ተስፋ መለመን አለበት፡፡ ዘፀዓት ፴፩፡፲፫፡፡ ፯76T360,361;፡፡CCh 47.4

    ከተለመደው ሥራ አእምሮውን አዙሮ ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ክብር በማሰብ በረከት እንዲሆንለት ሰንበት ለሰው ተፈጠረ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለርሱ ለመነጋገር ፤ በቃሉ ውስጥ ስላለው እውነት ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጥና ለግል ጸሎትም ጊዜ ወስደው መሰብሰብ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ግን እነዚህ ጊዜያት በሰንበት ዕለት እንኳ ቢሆን ጊዜውን በዚሁ ማስረዘምና ደስታ የጐደለበት ሆኖ የሚያሰለች መሆን የለበትም፡፡ ፰82T583CCh 48.1

    ቤተ ክርስቲያኒቱ ሰባኪ የሌላት የሆነ እንደሆን አንዱ የስብሰባው መሪ ሁኖ ሊሾም ይገባል፡፡ ግን ስብከት መስበክ፤ ወይም ከአገልግሎቱ ጊዜ ብዙውን መውሰድ የሚያስፈልገው አይደለም፡፡ አጠር ያለ አስደሳች የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን ንባብ ማንበብ ብዙ ጊዜ ከስብከቱ ይልቅ ትልቅ ጥቅም የሚሰጥ ነው፡፡ ይህንንም የጸሎት ስብሰባና የምስክርነት ንግግር ሊከተለው ይቻላል፡፡CCh 48.2

    ሁሉም የሰንበትን የጸሎት ስብሰባዎች የሚደሰትበት በማድረግ ረገድ ተካፋይነት እንዳለው ሊስማው ይገባል፡፡ ለታይታ (ለዘልማድ) ጉዳይ ባንድነት መሰብሰብ የለባችሁም ፤ ዳሩ ግን ሐሳብ ለሐሳብ ለመለዋወጥ ከዕለታዊ ሁኔታዎቻችሁ ጋር ስላላችሁ ግንኙነት ምስጋና ለማቅረብ እግዚአብሔርንና የላከውን የሱስ ክርስቶስን ታውቁ ዘንድ ስለ ተብራራላችሁ መለኮታዊ ብርሃን ከልብ ያላችሁን ፍላጎታችሁን አንድትነጋገሩ ነው፡፡ ባንድነት ሁኖ ስለ ክርስቶስ መነጋገር ነፍስን በሕይወት ፈተናዎችና ተጋድሎች ላይ ያበረታታል፡፡ ራሳችሁን በራሳችሁ ውስጥ ሸጉጣችሁ ክርስቲያኖች ለመሆን እንችላለን ብላችሁ አታስቡ፡፡ እያንዳንዳችሁ ታላቁ የሰብዓዊ ጉንጉን ክፊያ ናችሁ የእያንዳንዳችሁም ሁኔታ አብዛኛውን በጓደኞቻችሁ ሁኔታ የሚወሰን ነው፡፡ ፱96 T 3 6 1,362; CCh 48.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents