Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ንብረታችን የእግዚአብሔርንም ሥራ መደገፍ፡፡

    አምላክን ከልብ ለሚወዱና ገንዘብ (ችሎታ) ላላቸው እንዲህ እንድላቸው ታዝዤአለሁ የጌታን ሥራ በመደገፍ ገንዘባችሁን ትሰጡ ዘንድ ለእናንተ ጊዜው አሁን ነው፡፡ የሚጠፉትን ነፍሳት ለማዳን ራሳችሁን በመካድ በምታደርጉት ጥረቶች የሰባኮችን እጆች ለመደገፍ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ለማዳን የረዳችኋቸውን ነፍሳት በሰማይ ግቢዎች ስትገናኙዋቸው የተከበረ ዋጋ የምታደገኙ አይደላችሁምን?CCh 82.4

    ማንም የራሳቸውን ድሪም አያስቀሩ ብዙ ያላቸው የማያልፈውን መዝገብ በሰማይ ሊያከማቹ የሚችሉ በመሆናቸው ደስ ይበላችሁ፡፡ በጌታ ሥራ እናከማች ዘንድ የማንፈቅደው ገንዘብ ይጠፋል፡፡ በርሱ በሰማይ ባንክ ምንም ወለድ አይከማችም፡፡CCh 83.1

    ጌታ ራሳቸውን ለርሱ ቀድሰው እንዲሰጡና የተቻላቸውን ያህል ያደርጉ ዘንድ እንደየባሕላቸው በሥራውም እንዲረዱ በየሥፍራው ያሉትን ሰባተኛው ቀን አክባሪዎችን አሁን ይጠራቸዋል፡፡ ስጦታዎችንና መሥዋዕቶችን በመስጠት በሚያሳዩት ልግሥና ስለ በረከቶቹ ማመስገናቸውንና ስለ ምህረቱም ምሥጋና ማቅረባቸውን ይገልጹ ዘንድ ይፈልጋቸዋል፡፡ ፳፬249T131, 132;CCh 83.2

    በመከራ ጊዜ ለሥጋዊ ፍላጎታችን ማናቸውንም ስንቅ ማሰናዳት ለመጽሐፍ ቅዱስ ተቃራኒ መሆኑን ጌታ ደጋግሞ አሳይቶኛል፡፡ ጻድቃን በነሱ የተከማቸ (የተጠራቀመ) ምግብ ወይም በመከራ ጊዜ በእርሻ ውስጥ ቢኖራቸውም ቅሉ ሰይፍ ረሐብና ቸነፈር ባገር ውስጥ ሲሆኑ በብርቱ እጆች ከነሱ ይወሰድባቸዋል እንግዶዡም እርረዎቻቸውን ያጭዳሉ፡፡ በዚያን ጊዜ ነው በፍጹም በአምላክ መታመን ያለብን እርሱም ይደግፈናል፡፡ በዚያን ጊዜ ነው በፍጹም በአምላክ መታመን ያለብን እርሱም ይደግፈናል፡፡ በዚያን ጊዜ እንጀራችንና ውኃችን የተረጋገጠ ይሆንልናል ምንም የሚጐድለን የለም ወይም በረሐብ የምንሠቃይ አይደለንም አምላክ በምድረ በዳ ማዕድ (ጠረጴዛ) ሊዘረጋልን ይችላልና፡፡ ካስፈለገም ኤልያስን ሊመግብ እንዳደረገ ይመግበን ዘንድ ቁራዎችን ይልክልናል ወይም ለእሥራኤላውያን እንዳደረገ ከሰማይ መናን ያዘንብልናል፡፡CCh 83.3

    በመከራ ጊዜ ቤቶችና መሬቶች ለጻድቃን ምንም የማይረቡ ይሆናሉ፡፡ በዚያን ጊዜ እነሱ ከቁጠኞቹ ሰዎች ፊት መሸሽ አለባቸውና በዚያን ጊዜም ያሁኑን የእውነት ጉዳይ ለማስፋፋት ንብረቶቻቸውን ማበርከት የማይቻል ነው፡፡ የመከራ ጊዜ ከመምጣቱ በፊት ጻድቃን ከሸክም ሁሉ ተላቅቀው በመሥዋዕት ከእግዚአብሔር ጋር ቃል ኪዳን ይገቡ ዘንድ ያምላክ ፈቃድ መሆኑ ታየኝ፡፡ ንብረታቸውን በመሠውያ ላይ አኑረው ለሚያደርጉት ተግባር አምላክን ቢለምኑ (ቢጠይቁ) እነዚህን ነገሮች መቼ እንደሚያበረክቱ ያስተምራቸዋል በዚያን ጊዜ በመከራ ጊዜ ነጻ ይሆናሉ ወደ ታችም የሚመዝኑዋቸው ምንም እክሎች የለባቸውም፡፡CCh 83.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents