Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምሥክሮችን በስህተት ሁኔታ መጠቀም፡፡

    መጀመሪያ የወጣው የምሥክሮች ቁጥር ለአመላክ ሕዝብ እንዲህ የተሰጠውን ብርሃን ባለመጠንቀቅ ስለ መጠቀም የተሰጠ ማስጠንቀቂያ አለበት አንዳንዶች ስለ ኃይማኖታቸው ለማያምኑ ሲናገሩና ለዚሁ ማስረጃ በተጠየቁ ጊዜ፤ ለማስረጃ ወደ መጽሐፍ ቅዱስ በመሔድ ፈንታ ከጽሑፎቼ ሲያነቡላቸው፤ የማይገባ (የሞኝነት) እርምጃ መውሱዳቸውን ተናግሬአለሁ፡፡ ይህ እርምጃ የማይ ገባ እንደሆነና የማያምኑ እውነትን እንዲቃወሙ እልክ የሚፈጥርባቸው መሆኑ ታይቶኝ ነበር፡፡ ምሥክሮች ስለ መንፈሳቸው ምንም በማያውቁ ዘንድ ምንም ክብደት /ግምት/ ሊኖራቸው አይችሉም፡፡ በእንዲህ ያለ ነገር ሊጠቀሱ አይገባም፡፡CCh 147.5

    ምስክሮችን ስለ መጠቀም የተሰጡት ሌሎች ማስጠንቀቂያዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደሚከተለው ተሰጥተዋል፤CCh 148.1

    ‹አንዳንዶች ሰባኮች በጣም በስተኋላ ናቸው፡፡ የቀረበላቸውን ምሥክር እናምናለን ይላሉ፤ ስለነሱ አወላስ ምንም ልምምድ ላልነበራቸው የብረት ደንብ በማድረጋቸው አንዳንዶች ጉዳት ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ራሳቸው ሊመሩባቸው ያቅታቸዋል፡፡ እነሱ ፈጽመው ችላ ያሏቸውን ምስክሮች ደጋግመው አንብበው ነበር፡፡ እንዲህ ያሉት እርምጃቸው ጽኑ አይደለም›፡፡CCh 148.2

    ‹እግዚአብሔር ስለ ሌሎች ኀጢአቶችና ስህተቶች ስላሳየው ብዙዎች ከልክ በላይ ሲጠሙበት አየሁ በራእይ ስለ ታየው ከልክ በላይ ትርጓሜውን ይዘውታል፤ እንግዲህ እግዚአብሐር ባሳየው የብዙዎችን ኃይማኖት ለማዳከምና ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱን ተስፋ ለማስቆረጥና ለማስፈራራት ዝንባለ እስኪኖረው ድረስ ገፍተውበታል›፡፡ ፱95T669, 670; CCh 148.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents