Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፮—ሕይወቶችን የለወጡ መልእክቶች፡፡

    አንድ ወንጌላዊ በቡሽነል፤ በሚችጋን አከታትሎ የጸሎት ስብሰባዎች አድርጎ ነበር፤ ከጥምቀት በኋላ፤ በመልእክቱ ምዕመናንን የጸኑ ሳያደርጋቸው (ሳይመሠርታቸው) ሰዎቹን ትቶ ሔደ፡፡ ሰዎቹም ቀስ በቀስ ተስፋ ቆረጡ፤ አንዳንዶቹም ክፉ ልማዳቸውን እንደገና ጀመሩ፡፡ በመጨረሻ ቤተ ክርስቲያኒቱ እያነሰች ሔደች የቀሩትም አሥር ወይም አሥራ ሁለት የሆኑ ከእንግዲህ በእንዲህ መቀጠል ጠቀሜታ እንደ ሌለው ቁርጥ ሐሳብ አደረጉ፡፡ ይህ የመጨረሻ የጸሎት ስብሰባቸው ነው ብለው አስበው ከተበታተኑ በኋላ ፖስታ ደረሳቸው፡፡ በደብዳቤዎቹም መኻኸል ዘ ሬቪው አንድ ሔራልድ የተባለ መጽሔት ነበር፡፡ ስለ ጉዞ በሚያወሳው ሐተታ ውስጥ ኤልደርና ሚስስ ኋይት እ.ኤ.አ በሐምሌ ፳ ቀን ፲፰፻፷፯ ዓ.ም ለጸሎት ስብሰባ በቡሽኔል ይሆናሉ የሚል ማስታወቂያ ነበር፡፡ ይህም አንድ ሳምንት ብቻ ቆይቶ የሚሆን ነበር፡፡ ወደ ቤታቸው ለመመለስ ከመንገድ የነበሩትን ሰዎች ይጠሩዋቸው ዘንድ ልጆች ተላኩ፡፡ አንዱ ዛፎች ውስጥ ስፍራ እንዲያዘጋጅና ሁላቸውም ጐረቤቶቻቸውን በተለይም ወደ ኋላ ያፈገፈጉትን አባሎች ያድሙ ዘንድ ቁርጥ ሐሳብ ተደረገ፡፡CCh 21.1

    በሰንበት ጧት ሐምሌ ፳ ቀን ኤልደርና ሚስስ ኋይት ስልሣ ሰዎች ከተሰበሰቡበት ዛፎች (ደን) ውስጥ ደረሱ፡፡ ኤልደር ኋይት በጧት ንግግር አደረጉ፡፡ ከቀትርም በላይ ሚስስ ኋይት ልትናገር ተነሳች ግን ጥቅስዋን ካነበበች በኋላ ጭንቅ ብሏት ተመለከተች፡፡ ሐተታዋን ስትቀጥል መጽሐፍ ቅዱስዋን ዘግታ የግል ንግግር በማድረግ ጐዳና እንዲህ ልትነጋገራቸው ጀመረች ፤CCh 21.2

    «በዚህ ቀትር በላይ እፊታችሁ ስቆም ከሁለት ዓመት በፊት በራእይ ታይተውኝ የነበሩትን ፊታቸውን እየተመለከትሁ ነው፡፡ ፊቶቻችሁን ስመለከት ፤ ሁኔታችሁ በእእምሮዬ በግልጽ እንደገና ትዝ ይለኛል ፤ እኔም ከጌታ ለእናንተ መልእክት አለኝ፡፡CCh 21.3

    «ይህ ወንድም በጥዱ ዛፍ አጠገብ ይኸውና፡፡ ስምህን ልጠራ አልችልም አልተዋወቅሁህምና ፤ ፊትህ ግን ይታወቀኛል ፤ ሁኔታህም በፊቴ በግልጽ ይታየኛል»፡፡ ከዚያ በኋላ ለዚህ ወንድም ወደ ኋላ ስለ ማፈግፈጉ ነገረችው፡፡ እንዲመለስና ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋራ እንዲሔድ አደፋፈረችው፡፡CCh 21.4

    ከዚያ በኋላ በሌላው ክፍል ካሉት አድማጮች ውስጥ ወዳለችው እህት ዙራ እንዲህ አለች ፤ «ይህች እህት ከግሪንቪል ቤተ ክርስቲያን ከሆነችው ሲስተር ሜይናርድ አጠገብ የተቀመጠችው ስምሽን ልናገር አልችልም ፤ ምን እንደሆነ አልተነገረኝምና ፤ ግን ከሁለት ዓመት በፊት ስላንቺ ጉዳይ በራእይ ታይቶኝ ነበር ፤ ሁኔታሽም በኔ ዘንድ ዕውቅ ነው»፡፡ ከዚያ በኋላ ሲስተር ኋይት ለዚች እህት ማደፋፈሪያ ሰጠች፡፡CCh 21.5

    «ከዚያም በኋላ ፤ ይህ ወንድም በወርካ ዛፍ አጠገብ በስተኋላ ይኸውና በስምህ ልጠራህ አልችልም ገና አልተገናኘሁህምና ግን ያንተ ጉዳይ ለኔ ግልጽ ነው»፡፡ ከዚያ በኋላ ስለዚህ ወንድም በሐሳቡ ውስጥ ያለውን እዚያ ላለው ሁሉ እየገለጠችና ስለ ሁኔታው እያወሳች ተናገረች፡፡CCh 21.6

    ካንዱ ወደ ሌላይኛው ወደዚያ ጉባዔ ዘወር ብላ ሁለት ዓመት በፊት በራእይ ታይቶአት የነበረውን ነገረቻቸው፡፡CCh 22.1

    ሚስስ ኋይት የግሣጼ ቃላት ብቻ ሳይሆን የማደፋፈሪያም ቃላት ተናግራ ፤ ስብከትዋን ከፈጸመች በኋላ ተቀመጠች፡፡ ከጉባዔው አንዱ ቆመና አለ፤ «ሲስተር ኋይት ካሁን ቀደም ከዚህ ቀትር በላይ የነገረችን እውነት እንደሆነ ላውቅ እፈልጋለሁ፡፡ ኤልደርና ሚስስ ኋይት ካሁን ቀደም እዚህ አልነበሩም ፤ በፍጹምም አያውቁንም፡፡ ሲስተር ኋይት የብዙዎቻችንን ስሞች እንኳ አታውቅም ግን በዚህ ቀትር በላይ የኛ ጉዳዮች ለርሷ የታዩበት ራእይ ከሁለት ዓመት በፊት እንደ ተሰጧት ትነግረናለች ፤ ከዚያ በኋላም ለእያንዳንዳችን መናገርን ትቀጥላለች ፤ ስለ አኗኗራችን ሁኔታ ፤ በውስጣችንም ስላለው ሐሳብ ለሁላችንም ትገልጥልናለች፡፡ በማንኛውም እነዚህ ሁሉ እውነት ናቸውን ወይንስ ሲስተር ኋይት አንዳች ስህተት አድርጋለች? እኔ ላውቅ እፈልጋለሁ»፡፡CCh 22.2

    አንድ በአንድ ሰዎቹ ብድግ ብለው ቆሙ በጥዱ ዛፍ አጠገብ ያለው ሰው ብድግ አለና ፤ ሊነግር ከሚቻለው የበለጠ ሲስተር ኋይት ስለርሱ ጉዳይ እንዳስታወቀች ተናገረ፡፡ ወደ ኋላ የማፈግፈግ እርምጃውንም ተናዘዘ፡፡ ተመልሶ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ይሔድ ዘንድ ቁርጥ ሐሳብ ማድረጉንም ገለጸ፡፡ ከግሪንቪል ቤተ ክርስቲያን የሆነችው በሲስተር ሜይናርድ አጠገብ የተቀመጠችው እህት ደግሞ እንደዚሁ መሰከረች፡፡ ሲስተር ኋይት ሁኔታዋን እርሷ ለመናገር ከምትችለው የበለጠ ተናግራለች አለች፡፡ በወርካው አጠገብ የነበረው ሰው ሲስተር ኋይት ከግሣጼና የማደፋፈሪያ ቃላት የነገረችው ፤ እርሱ ሊገልጸው ከሚችለው የበለጠ ጉዳዩን እንደተናገረች ነገራቸው፡፡ ኑዛዜም ተደረገ፤ ኃጢአትም ተወገደ፡፡ የእግዚአብሔርም መንፈስ ገባ፤ በቡሽኔልም መነቃቃት (ሪቫይቫል) ሆነ፡፡CCh 22.3

    ኤልደርና ሚስስ ኋይት ቀጥሎ ባለው ሰንበት ተመልሰው መጡ፤ ጥምቀትም ተደረገ ፤ በቡሽኔል ያለችውም ቤተ ክርስቲያን ደኅና ሁና ተቋቋመች ፤ የነቃችም ሆነች፡፡CCh 22.4

    ጌታ ወደርሱ ለሚመለከቱት እንደሚያደርገው በቡሽኔልም ያሉትን ሕዝቡን ወደደ፡፡ «እኔ የምወደውን ሁሉ እዘልፈዋለሁ እገስጸውማለሁ፡፡ አሁንም ቅና ንስሐም ግባ» ፤ (ራእይ ፫ ፡ ፲፱)፡፡ ያለው ቃል እዚያ ለነበሩት በአእምሮዋቸው ትዝ አላቸው፡፡ ሰዎቹ ጌታ እንዳያቸው ፤ እነሱም የገዛ ልባቸውን ባዩ ጊዜ እውነተኛ ሁኔታቸውን አስተዋሉና በሕይወታቸው መለወጥ እንዲሆንባቸው ፈለጉ፡፡ ይህ ለሚስስ ኋይት ከተሰጡት ብዙዎች ራእዮች ውስጥ እውነተኛ ሐሳብ ነው፡፡CCh 22.5

    ኤልደር ኋይት ከሞቱ በኋላ ሚስስ ኋይት በሔልድስቡርግ ኮሌጅ አቅራቢያ ኖረች፡፡ ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ አያሌዎች ወጣቶች ወይዛዝርት እቤቷ ይቆዩ ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ በጸጉራቸው ላይ ቀለል ያለ ሻሽ ጣል ማድረግ ልማድ ነበር፤ ቀኑን በንጽሕናና በሥርዓት ይጠብቁት ዘንድ ፡፡ አንድ ቀን በሚስስ ኋይት ክፍል ውስጥ ሲያልፉ ከልጃገረዶች አንድዋ ሥራው ጥሩ የሆነውን ሻሽ አየችና ፈለገችው፡፡ እንዳያመልጣት አስባ ፤ ወሰደችውና በሻንጣዋ ውስጥ ከላይ አደረገች፡፡ ትንሽ ቆይታ ወደ ውጭ ለመሔድ ስትለብስ ሚስስ ኅይት ሻሽዋን አጥታ ፤ ሳታደርገው መሔድ ሆነባት፡፡ ማታውኑ ቤተሰብዋ ባንድ ላይ በሆኑ ጊዜ ሚስስ ኋይት ስለ አጣችው ሻሽዋ ጠየቀቻቸው ፤ ግን ማንም የት እንደሆነ ማናቸውም የማወቅ ምልክት የሰጠ የለም ፡፡CCh 22.6

    አንድ ቀን ያህል ቆይታ ፤ ሚስስ ኋይት በልጃገረድዋ ክፍል ስታልፍ አንድ ድምፅ «ያነን ሻንጣ ክፈቺ” የሚል ተናገራት ፡፡ ሻንጣው የርሷ ስላልነበረ እንዲህ ልታደርግ አልፈለገችም፡፡ በሁለተኛውም ትእዛዝ የዚያ የመልአኩ ድምፅ መሆኑን አወቀች፡፡ መክደኛውን ብድግ ባደረገችው ጊዜ መልአኩ ለምን እንደ ነገራት አየች ፤ የርሷ ሻሽ እዚያ ውስጥ ነበርና፡፡ ቤተሰብዋ እንደገና ባንድ ላይ በሆኑ ጊዜ ሚስስ ኋይት እንደገና ስለ ሻሹ ጠየቀቻቸው በራሱ ሊጠፋ አይቻለውም ስትልም ነገረቻቸው ፡፡ ማንም ስለዚህ የተናገረ የለም ፤ ስለዚህ ሚስስ ኋይት ነገሩን ተወች፡፡CCh 23.1

    ጥቂት ቀናት ቆይታ ሚስስ ኋይት ከጽሕፈት ስራዋ ስታርፍ ሳለች አጠር ያለ ራእይ አየች፤ ያንዲት ልጃገረድ እጅ የጸጉርን ሻሽ ወደ አንድ የጋዝ ፋኖስ ሲያስጠጋ አየች፡፡ ሻሹ ነበልባሉን በነካ ጊዜ እሳቱ ቦግ ብሎ ቦነነ የራእዩ ፍጻሜ ይህ ነበር፡፡CCh 23.2

    ቤተሰቡ ቀጥሎ ባንድ ላይ በሆኑ ጊዜ ሚስስ ኋይት እንደገና ስለ የጸጉሩ ሻሽ መጥፋት ነገሩን አከረረች፤ ግን አሁንም ምንም ኑዛዜ አልተደረገም የትም እንዳለ የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ከዚያ በኋላ ትንሽ ጊዜ ቆይታ ሚስስ ኋይት ይህችን ወጣት ሴት ለብቻዋ ጠርታ ስለ ድምፁና በሻንጣዋ ውስጥ ያየችውን ነገረቻት ፤ ስለዚሁ አጠር ያለ ራእይ የጸጉሩ ሻሽ በፋኖሱ እላይ ሲነድ (ሲቃጠል) ያየችውንመ ነገረቻት ፡፡ እፊቷ በቀረው እንፎርሜሺን ልጃገረድዋ ሻሹን መውሰድዋንና እንዳይገለጽባት ማቃጠልዋን ተናዘዘች፡፡ ከሚስስ ኋይትና ከእግዚአብሔር ጋር ነገሩ የተቃና እንዲሆን አደረገች፡፡CCh 23.3

    ጌታ ስለዚሁ ማለት ስለ ጠጉር ሻሽ ይህን ያህል ሊቸገርበት ትንሽ ነገር ነው ብለን እናስብ ይሆናል ፤ ግን የተሰረቀው ዕቃ ከሚያወጣው ዋጋ የበለጠ ሁኖ ዋና ነገር ነው፡፡ እዚህ ወጣትዋ ሴት የሰባተኛዋ ቀን አድቬንቶስት ቤተክርስቲያን አባል ነበረች፡፡ ሐቀኛ (እውነተኛ) እንደሆነች ተሰማት ፤ ግን በጠባይዋ ውስጥ ያለውን ጉድለት አልተመለከችም ፡፡ ለመስረቅና ለማታለል የመራትን ራስን ወዳድነት አልተመለከተችም፡፡ አሁን ግን ትንንሾቹ ነገሮች እንደምን ዋናዎች እንደሆኑ በዚህ ምድር ላለችው ትጉ መልእክተኛው ስለ የጸጉር ሻሽ ራእይ የሚሰጣት መሆኑን በተገነዘበች ጊዜ ይህች ወጣት ልጅ ነገሩን በእውነተኛ አስተያየት ልታይ ጀመረች፡፡ ይህ ሁኔታ በሕይወቷ የመመለስ ሐሳብ ፈጠረባት ፤ እርሷም ጥሩ የሆነ ጽኑ ክርስቲያናዊ ሕይወት ኖረች፡፡CCh 23.4

    ራእዮቹ ለሚስስ ኋይት የተሰጡት ስለዚህ ነው፡፡ በሚስስ ኋይት የተጻፉት ብዙዎች ምሥክሮች የተለዩ ትርጓሜዎች ቢኖራቸውም ፤ ሆኖም በዓለም አህጉር ሁሉ ውስጥ ያለውን የቤተ ክርስቲያን ፍላጎት የሚሞሉትን ፕርንስ ፕል (ዓላማ) ይሰጣሉ፡፡ ሚስስ ኋይት እነዚህን ቃላት በመናገር የምሥክሮቹን ሐሳብና ሥፍራ ገልጻለች፡፡CCh 23.5

    «የተጻፉት ምስክሮች አዲስ ብርሃን ለመስጠት አይደሉም ፤ ግን ካሁን በፊት የተገለጸውን በመንፈስ የተጻፈውን እውነት በልብ ውስጥ አጥብቆ ለማሳተፍ ነው፡፡ ሰው ለእግዚአብሔርና ለባልንጀሮቹ ተግባሩ ምን እንደሆነ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ በግልጽ ተነግሮአል ፤ ግን ጥቂቶቻችሁ ለተሰጣችሁ ብርሃን ታዛዦች ናችሁ ተጨማሪ እውነት የመጣ አይደለም ፤ ግን እግዚአብሔር በምሥክሮቹ አማካይነት ካሁን ቀደም የተሰጠውን እውነት ማጉላቱ ነው፡፡ … ምሥክሮቹ የእግዚአብሔርን ቃል ዝቅ ለማድረግ አይደለም ከፍ ለማድረግና ሐሳቦችን ወደርሱ ለመሳብ ነው፤ ውብ የሆነውን የእውነት ጉልህነት ሁሉ እንዲሳተፉት ነው፡፡CCh 24.1

    በሕይወቷ ሙሉ ሚስስ ኋይት የእግዚአብሔርን ቃል በሕዝብ ፊት አቅርባለች፡፡ የመጀመሪያ መጽሐፍዋን በዚህ ሐሳብ ዘጋችው ፤ እንዲህ ተናገረች ፤CCh 24.2

    «የተወደድህ አንባቢ ሆይ የእግዚአብሔር ቃል የሃይማኖትህና የልምምድህ ደንብ መሆኑን አደራ እለሃለሁ፡፡ በዚያ ቃል የምንፈረድ ነን፡፡ እግዚአብሔር በዚያ ቃል፤ «በኋለኛዩቱ ቀን» ራእዮችን ይሰጥ ዘንድ ተስፋ ሰጥቶአል፤ አዲስ የኃይማኖት ሕግ ለማውጣት አይደለም ግን ሕዝቡን ለማጽናናትና ከመጽሐፍ ቅዱስ የሚሳሳቱትን ለማረም ነው»፡፡CCh 24.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents