Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ፲፰—አካል ባለው መለኮት ማመን፡፡

    እግዚአብሔር ሁሉን በስሙ እንደሚያውቀው በመጨረሻው የውሳኔ ቀን ላይ ይገኛል፡፡ ለሕይወት አድርጎት ሁሉ የማይታይ መስካሪ አለ፡፡ ‹‹ስራህን አወቅሁ›› ይላል ‹‹በሰባቱ በወርቅ መቅረዞች መካከል የሚሔድ›› (ራእይ (፣():: ምን ምቹ ጊዜያት ችላ እንደ ተባሉ መልካሙም እረኛ በጠማሞቹ መንገዶች ሲቅበዘበዙ የነበሩትን ለመፈለግና ወደ ደህንነትና ወደ ሰላም ጎዳና መልሶ ሊያመጣቸው ያደረጋቸው ጥረቶቹ እንደምን ያልተቋረጡ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ እየደጋገመ እግዚአብሔር ተድላ አፍቃሪዎችን ጠርቶአቸዋል የሚያሰጋቸውንም አይተው ያመልጡ ዘንድ የቃሉን ብርሃን በመንገዳቸው ላይ እየደጋገመ አብርቶአል፡፡ ነገር ግን እነሱ በሰፊ መንገድ ላይ ሲጓዙ እየቀለዱና እያፌዙ መንገዳቸውን ቀጠሉ በመጨረሻ የምሕረት ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ፡፡ ያምላክ መንገዶች የቀኑና የተስተካከሉ ናቸው ጎደሎች ሆነው በተገኙት ላይ ፍርድ ሲነገር አፍ ሁሉ ዝም ይላል፡፡ 15T435; 8T263—273.CCh 134.1

    በተፈጥሮ ሁሉ ውስጥ የሚሠራና ሁሉን ነገሮች የሚደግፍ ኃይሉ ኃይል አንዳንዶች የሳይንስ ሰዎች እንደሚያመለክቱት በሁሉ ውስጥ የሚዋኻድ ፕርሲፕል የሚቀሰቅስ (የሚያነቃቃ) ኃይል ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር መንፈስ ነው ሆኖም እርሱ አካል ያለው አምላክ ነው ሰው የተፈጠረው በአምሳሉ ነውና፡፡CCh 134.2

    በተፈጥሮ ውስጥ ያምላክ የእጅ ሥራው በተፈጥሮ ራሱ እግዚአብሔር አይደለም፡፡ የተፈጥሮ ነገሮች ያምላክ ባሕርይ ገለፃ ናቸው በነሱ ፍቅሩን ኃይሉንና ክብሩን እናስተውላለን፡፡ የሰብዓዊ ፍጥረቶች ኪነጥበብ ብልሃት እጅግ ያማረ የሰው ሥራ ዓይንን የሚያስደስቱ ነገሮችን ይሠራል እነዚህም ነገሮች ስለ ሰሪው ሐሳብ አንዳች ነገር ይሠጡናል ዳሩ ግን የተሠራው ነገር ሰውየው መሆኑ አይደለም፡፡ ክብር የሚገባው ሆኖ የሚቆጠርለት ሥራው አይደለም ሰሪው የሆነው ሰው ነው እንጂ፡፡ እንደዚሁም ተፈጥሮ ያምላክ ሐሳብ ገለጻ ሁኖ ሳለ ከፍ ለማለት ያለበት የተፈጥሮ አምላክ ነው እንጂ ተፈጥሮው አይደለም፡፡CCh 134.3

    ሰው በመፈጠሩ ያምላክ አምሳለ አማካይ ተገለጸ፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ በፈጠረ ጊዜ ሰብዓዊ መልክ በድልድሉ ሁሉ ፍጹም ነበር ነገር ግን ሕይወት የሌለበት ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ አካል ያለው በራሱ የሚኖር አምላክ በዚያ መልክ ውስጥ የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት ሰውም ሕያው የሚተነፍስ አስተዋይ ፍጥረት ሆነ፡፡ ሰብዓዊ ሰውነት ክፍሎች ሁሉ መሥራት ጀመሩ፡፡ ልብ ትላልቅ የደም ሥሮች (አርቴሪስ) ትናንሽም የደም ሥሮች፣ ምላስ፣ እጆች፣ እግሮችም፣ ሕዋሳቶችም፣ የሐሳብም ማስተዋል ሁላቸውም ሥራቸውን ጀመሩ ሁላቸውም በሕግ በታች ተደረጉ፡፡ ሰውም ሕይወት ያለበት ነፍስ ሆነ፡፡ በየሱስ ክርስቶስ አማካይነት እግዚአብሔር ሰውን ፈጠረና አእምሮንና ኃይልን ሰጠው፡፡CCh 134.4

    በምሥጢር በተፈጠርን ጊዜ አፈጣጠራችን ከርሱ አልተሰወረም፡፡ ዓይኖቹ አፈጣጠራችንን ተመለከቱ ፍጹምነት የሌለው መሆኑንም በመጽሐፉም ገና ሳኖሩ ብልቶቻችን ሁሉ ተጽፈዋል፡፡CCh 135.1

    ከዝቅተኞቹ የፍጥረት ሥነ ሥርዓቶች በላይ እግዚአብሔር ሰው የተቀዳጀው የፍጥረቱ ሥራ የሆነው ሐሳቡንና ክብሩን እንዲገልጽ አሰበ፡፡ ሰው ግን ራሱን ከአምላክ በላይ እንዲያልቅ አይደለም፡፡CCh 135.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents