Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents

የቤተ ፡ ክርስቲያን፡ ምክሮች፡፡

 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ‹‹ከሰው ሁሉ በገዛጁ ሊሰጠን ከሚያምረው ውሰዱ››

    እግዚአብሔር ጉዳዩን ለማስፋፋት ያዘዘው ሰዎችን በንብረት መባረኩ ነው፡፡ እርሱ የጸሐይ ብርሃንና ዝናምን ይሰጣቸዋል ዕፅዋትን እንዳያብብ ያደርጋል ገንዘብን ያገኙ ዘንድ ጤናና ችሎታ ይሰጣቸዋል፡፡ የምናገኛቸው በረከቶች ሁሉ ከለጋስ እጁ የሚመጡልን ናቸው፡፡ ስለዚህ መልሶ በአሥራትና በሥጦታዎች ማለት በምሥጋና ሥጦታዎች በነፃ ፈቃድ ሥጦታዎች በሕግ መተላለፊያ ሥጦታዎች ወንዶችም ሴቶችም ለርሱ በመመለስ ምሥጋናቸውን እንዲያሳዩ ይፈልጋቸዋል፡፡ ፬45T150; CCh 74.1

    አይሁዶች የማኀበሩን ድንኳን በመሥራትና ቤተ መቅደሱን በማቋቋም ረገድ ያደረጉት ልግሥና የደግነትን መንፈስ ይገልጣን ያውም ከዚያ በኋላ የነበሩት ማናቸውም ክርስቲያኖች የሚተካከሏቸው አልነበሩም፡፡ በምሥር ለረዥም ጊዜ ተገዝተው ከነበሩበት ባርነት በቅርቡ ነበር ነፃ የወጡት፡፡ በምድረ በዳም ተቅበዝባዦች ነበሩ ሆኖም “ለእሥራኤል ልጆች ንገር የስለት ሥጦታ ይሰጡኝ ዘንድ፡፡ ከሰው ሁሉ በገዛጁ ሊሰጠኝ ከሚያመረው ውሰዱ” ሲል የአምላክ ቃል ለሙሴ በመጣለት ጊዜ በተፋጠነው ጉዞዋቸው ላይ ሆነው ከተከተሏቸው የምሥራውያን ሠራዊቶች ገናም አልዳኑም ነበር፡፡ ዘፀዓት ፳፭፣፫፡፡54T 77-79;CCh 74.2

    ሕዝቡ ትንሽ ንብረት ነበራቸው ስለነሱ የመደለል ሐሳብ ጨምሮ ለማቅረብ አይደለም ግን አንድ ዓላማ በፊታቸው ነበር ይኸውም ለአምላክ መቅደስ ለመሥራት ነው፡፡ አምላክ ነግሮአቸዋል እነሱም ለድምፁ መታዘዝ የሚገባቸው ነው፡፡ ምንም ነገር አላስቀሩም፡፡ ሁላቸውም በፈቃደኛ እጅ ሰጡ ያውም ከገቢያቸው የተለየው ያህል አይደለም ከንብረታቸው አብዛኛውን ክፍል ነው፡፡ በደስታና ከለልባቸው ላምላክ ሰጡ ይህነንም በማድረጋቸው አስደሰቱት፡፡ ሁሉስ የርሱ አልነበረምን? የነበራቸውን ሁሉ የሰጣቸው እርሱ አይደለምን? ከጠየቃቸው ለአበዳሪው የራሱን መልሰው መስጠት ተግባራቸው አልነበረምን?CCh 74.3

    ማስገደድ አያስፈልግም ነበር፡፡ ሕዝቡ ከሚያስፈልገው በላይ አመጡ ከሚያስፈልገው (ከሚገባ) በላይ ነበርና እንዲያቋርጡም ተነገሩ እንደገና ቤተ መቅደሱን ሲሰሩ ገንዘብ በማዋጣት ረገድ ጥሪው ከልብ በሆነው አቀባበል ተሳካ፡፡ ሕዝቡ ያለ ወዴታ አልሰጡም፡፡ ለአምላክ መስገጃ የሚሆን ቤት ለማቋቋም በታሰበው ሐሳብ ተደሰቱ ስለዚሁ ሐሳብ ከሚበቃ በላይ ሰጡ፡፡CCh 74.4

    እንግዲያውስ ዕብራውያን ከነበራቸው ይልስ ሰፋ ያለ ብርሃን እንዳላቸው የሚፎክሩ ክርስቲያኖች ከነሱ ያነሰ መስጠት ይችላሉን? በየጊዜው ፍጻሜ የሚኖሩ ክርስቲያኖች የእነዚያ የአይሁዶቹን ግማሽ ያህል ባልሆነው ሥጦታቸው ሊደሰቱ ይችላሉን? ፭፡፡CCh 74.5

    የሰማያዊ ሥጦታዎች ተካፋዮች የሆኑት በፈቃዳቸው ባደረጉት ጥረቶችና በሰጡት ሥጦታዎች እግዚአብሔር ብርሃኑና እውነቱ በምድር እንዲሰራጭ አድርጎአል ስንገምተው ሰባኮች ወይም ወንጌላውያን ሆነው ይጓዙ ዘንድ ተጠርተዋል ግን በገንዘባቸው እውነትን በመዘርጋት ብዙዎች ተባብረው መሥራት አለባቸው፡፡CCh 74.6

    ደኀና ነው ይላል አንዱ ለጉዳዩ እንድንሰጥ ጥሪው እየቀጠለ ነው፡፡ ለመስጠት ሰልችቶኛል ስልችቶሃልን እስቲ ልጠይቅህ ከለጋሱ ያምላክ እጅ መቀበል ሰልችቶሃልን እርሱ አንተን መባረክን እስኪተው ድረስ የሚፈልግብህን ድርሻ ትመልስለት ዘንድ ግዳጅነትህን መተው የለብህም በተቻለህ ኃይል ሌሎችን ትባርክ ዘንድ እርሱ ይባርክሃል፡፡ መቀበል ሲሰለችህ በዚያን ጊዜ ለመስጠት ለቀረቡት ጥሪዎች ሰልችቶኛል ለማለት ትችላለህ እግዚአብሔር ከምንቀበለው ሁሉ ለራሱ ድርሻውን ያስቀራል፡፡ ይህ ሲመለስለት የቀረው ድርሻ ይባረካል ግን ሲቀርበት መላው ወዲያው ወይም ቆይቶ የተረገመ ይሆናል፡፡ ያምላክን ፍላጎት መጀመሪያ ማስቀደም ነው ሌላውን ሁሉ ሁለተኛ ማድረግ ነው፡፡ ፮65T148, 150;CCh 75.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents